የጎሳን እድል በጎሳ መወሰን – ሰመረ አለሙ

 ሰመረ አለሙ s
emere.alemu@yahoo.com                               woyane satenaw 9

እንኳን ለታላቁ የአድዋ በአል አደረሳችሁ የአርበኛ ልጆች

ሰላም ዉድ ኢትዮጵያዉያን እንኳን ለታላቁ የአድዋ በአል አደረሳችሁ።ከዚህ በላይ እንደ ጸሐይ ደምቀዉ እንደ ክዋክብት አብርተዉ የሚታዩት ትግሬዎች በዘመነ ትህነግ የበላይነታቸዉን፤ ደስታቸዉን፤ ያሳዩበት ሁኖ ነገር ቢለወጥ ብለን ለታሪክ ያስቀመጥነዉ ፎቶ ነበር። እንደዉ ለምልክት አደዋ ላይ የተዉለበለበዉ  አንድ የኢትዮጵያ ሰንደቃ አላማ እንኳን አልተያዘም አደዋ  ላይ የወቀደቁት ያባቶቻችን ዉለታ በዛ አካባቢ እንዲህ ሁኖ ቀርቷል።

ከማርገሬት ታቸር በፊት የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስተር የነበሩት ኤድዋርድ ሂዝ “ጠንካራ መንግስት ህዝብ የማይፈልገዉንም ማሰማት የሚችል ነዉ” በማለት ስለ ህይወት ታሪካቸዉ በደጎሱት ድርሳን ላይ አስፍረዉት ነበር።

የትግሬ መሳፍንት የዘረጉት የአገዛዝ ስልት  እነሱ ከማእከላዊ መንግስት በሚባረሩበት ጊዜ ተጠቃሚ እንደማያደርጋቸዉ በቅጡ ሳይገነዘቡ መለስ ዜናዊ የሰጣቸዉን ከተታ ኮተት የመንግስትና የህዝብ መተዳደሪያ ደምብ አድርገዉ ካወጡ በሁዋላ ከማእከላዊ መንግስት ተገፍትረዉ በክልላቸዉ ብቻ ሲወሰኑ ሿሚ ሻሪ ፤ ሰጭ ነሺ፤ ገዳይ አስገዳይ መሆናቸዉ ሲያበቃ በወንጀልና በስርቆት መጠየቃቸዉ የማይቀር መሆኑን ሲረዱት  ወደ ክልላቸዉ በማፈግፈግ ህዝባችን የሚሉትን በማደራጀት፤ ሰላዮቻቸዉንና የዘረፉትን ገንዘብ በመጠቀም፤ ወደ መሀል አገር የጥፋት ወኪሎቻቸዉን በማሰረግ ኢትዮጵያ ላይ ዘመቱ።  ይህንን የጥፋት ሴራ ከዶለቱ በሗላም  ከሻቢያ ወራሪ ሀይል ለመጠበቅ በክልላቸዉ የሰፈረዉን የኢትዮጵያ የመከላከያ  ጦር ባሳፋሪ ሁኔታ በማዋረድ፤ በማረድ፤በመክዳት  ያጡትን ስልጣን እንደገና ለመጨበጥ የማይሆን ሙከራ አድርገዉ ሙከራዉ ሲከሺፍ ብዙ ያልተባለለትን የወልቃይትና ጠገዴን ግፍ በዜጎች ፈጽመዉ ግማሹ ወደ ሱዳንና ትግራይ ሲያቀና ቀሪዉ ማንነቱን ለዉጦ ህዝብ ዉስጥ ተሰግስጎ ቀረ።

ይህ በበረራ የተዳሰሰ ሁኖ ለዛሬዉ ትኩረት የተሰጠበት  የትግሬ ፋሺስቶች ከተነቀሉ በሁዋላ  በዉጭ ሀገር የሚገኙ ትግሬዎች (ከሁለት ሰዉ በስተቀር) ቀደም ያሉ የፈረንጂ ወዳጆቻቸዉን በመጠቀም ለዋሹበትም አበል በመክፈል አለሙን ከማመሳቸዉም አልፈዉ  ከእስር ተፈትተዉ ተልኮ የተሰጣቸዉ የትግሬ ወንጀለኞች የሚሰሩትን ወንጀል የኢትዮጵያ ሰራዊት አደረሰብን በማለት ስለ ሁኔታዉ ግንዛቤ የሌላቸዉን ፈረንጆች በማሳሳት ላይ ተጠምደዋል። በተለያየ ምክንያት ኢትዮጵያ እድሉን ሰጥታ በዉጭ ሀገር የሚኖሩ የትግሬ ዲፕሎማቶችና  በአለም አቀፍ ተቋም የሚሰሩ ትግሬዎች ያላቸዉን ንክኪ በመጠቀም ሙሉ ስራቸዉ ኢትዮጵያን በማጠልሸትና ለዉጭ  ሐይሎች መጠቀሚያ በመሆን አገዛዙን በመፈታተን ላይ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያዊነታቸዉ ምለን የተገዘትንላቸዉ የሚዲያ ተቋማትና ሰራተኞቻቸዉ ለምሳሌ ርእዮት ሚዲያ፤ ኢትዮ ሚዲያ ሰልፋቸዉን በቀጥታ ከነዚህ ወንጀለኞች ጋር ማድረጋቸዉ በዛ በኩል ባለዉ ሁኔታ ተስፋ እንድንቆርጥ ከማድረጉም በላይ የቀደመ አካሄዳቸዉንም መልሰን ለማጤን ተገደናል። በቢቢሲ፤በቪኦኤ፤በአምነስቲ  በመሳሰሉት ተቋማት የሚሰሩት ትግሬዎችም የሙያዉን  ኤቲኪስ ጥለዉ ሰልፋቸዉን ከህወአት ብሶተኞች ጋር በማድረግ ደካሞችን የተሳሳት ግንዛቤ በማስጨበጥ ላይ ይገኛሉ። ሰሞኑን የባይቶና ይሁን የባይተዋር ሹም ባደረገዉ ቃለ መጠይቅ እዉነትም ትህነግና ትግሬዎች የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸዉን በግልጽ አሳይቷል። በማያሻማ ቋንቋ ከመሀል መዲናችን ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኛዉ ሚዲያ በኛዉ ጋዜጠኛ ገልጾልናል። በዛ ወምበር ላይ ለቃለ መጥይቁ የቀረበዉ  አብን ወይ ባልደራስ ቢሆን ምርመራዉ ከፖሊስ ያልተናነሰ ይሆን ነበር። በተመሳሳይ ሁኔታ ጠያቂዉ ባገር መዉደድ ስሜት ልባቸዉ የተቃጠለ ትንታግ ጋዜጠኞች ላይ ቢወድቅ ይህ የባንዳ ተላላኪ የተጠየቀዉን ሳይሆን የሚፈልገዉን መርዝ ረጭቶ ባልሄደ ነበር ታዲያ ምን ያደርጋል ትህነግ ትዉልድ እንዳይወጣ አድርጎ ሄዷል።

ትግሬዎች ወደ ትግራይ ለእርቅ የሚላኩ ሺማግለዎችን፤ ወደ ትግራይ የሚላከዉን እርዳታም ሆነ የሰላም ጥሪ አንፈልግም ከማለታቸዉም በስተቀር ወያኔ በሺፋን ስም አስሮት የነበረዉ አብረሀ ደስታም ወያኔ ከወደቀ በሗላ አቅሉን እንደመንሳት አድርጎት በየሚየዲያዉ ሲቅበዘበዝ ታይቷል። ትግራይ ዉስጥ ህወአት 100% በተመረጠበት ጊዜም እንኳን ደስ አላችሁ ብሎ የላከዉ ከግምት ይወሰድ።

እንግዲህ ”አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዲሉ እነዚህ ሰዎች ምን ቢባበሉ አንድም ዉርደቱ፤አንድም የሰሩት ግፍ በትግሬነታቸዉ ያገኙት  ጥቅም ዳግም እንደማይገኝ  በተገነዘቡ ጊዜ  ኢትዮጵያ የሚለዉን ነገር በእጅጉ ስለጠሉ የጠሉትን ደግሞ በግድ ሁኑ ማለት ስለማይቻል እነሱን ማባበሉና የሚያቀረሹትን እንዳለ መቀበል ልባቸዉ ያሰበዉን  ነገር  ስለማያስቀረዉ በእርግጥ የትግራይ ህዝብ የመገንጠል ፍላጎት ካለዉ ህዝቡ ተማክሮ የሚበጀዉን እንዲመረጥ ቢደረግ ዘወትር እንደ አልቂጥ ተጣብቀዉ ህልዉናቸዉን ከሚፈታተኑት በማያዳግም ሁኔታ ወይ ትግሬ ወይ ኢትዮጵያዊ የሚሆኑበት ሁኔታ በአስቸኳይ ቢመቻች እነሱንም በየቦታዉ ተንከባልለዉ ከመላላጥ እኛም በአንድ ልብ ወደ ሀገር ግምባታ ለማተኮር ይረዳናል።

የሻቢያም ሆነ የህወአት ትግሬዎች ንቅናቂያቸዉ ሲጀመር ህዝቡ እኛን ነጻ አዉጡን ብሎ አልጠየቀም ወይም ዉክልና አልሰጠም። ህዝቡ በቀደመዉ ስርአት በደስታ የእለት እለት ስራዉን ሲሰራ ጥቂት አማጽያን ትርክት ፈጠረዉ  አልቀበል ያላቸዉን ያካባቢ ህዝብ በጥይት እየደበደቡ በፍርሀትና በትርክት የማለለዉን  የአካባቢዉ ህዝብ በማእከላዊ መንግስት እንዲያምጽ አድርገዉ  የጥቂት ሰዎች ሃሳብ  በግድ ነዋሪዉ እንዲቀበለዉ ተደረጎ ትርክቱም ህዝባዊ መልክ ያዘ ትግሬም ኢትዮጵያን ሻቢያም ኤርትራን ተከፋፈሉ።

በወቅቱ መንግስቱ ሐይለ ማርያም የኤርትራን ህዝብ ሰብስቦ ከኢትዮጵያዊነታችሁ ወይም ከሻቢያነታችሁ ምረጡ ቢል ያ ሁሉ ወጣት ከመትረፉም በላይ በዛ የፈሰሰዉ ኢኮኖሚ ሀገርን የላቀ ደረጃ ያደርስ ነበር የኤርትራም ህዝብ ኢትዮጵያዊ ሁኖ ሀገሩን በገነባ ነበር።

እንግዲህ ከላይ በመንደርደሪያዬ ለማሳየት እንደሞከርኩት እንዲሁም  በተለያዩ አገሮች ጭምር እንደታየዉ ነገሮች መርቅዘዉ ወደ ችግር ከምንገባ አላስፈላጊም መስዋእትነት ከሚከፈል አሁኑኑ በትኩሱ ትግሬዎች ሪፈረንደም አድርገዉ ከኢትዮጵያዊነት ወይ ከትግሬነት እንዲመርጡ ቢደረግ ወደፊት ሊመጣ የሚችለዉን አደጋ ያስቀረዋል ተብሎ ይታመናል። ትግሬዎቹም ማባባሉ ሲቀርባቸዉ ወደፊት ሊመጣ የሚችለዉን አደጋ ማሰላሰል ይጀምራሉ። እንግዲህ መንግስት መስርተዉ ተገንጥለዉ ራሳቸዉን ችለዉ እንዲኖሩ ሲደረግ እኛን በመጥላት የሚያባክኑት ጊዜ ከመቀነሱም በላይ ባዉሮፓና ባሜሪካ እየተንከባለሉ የጥቁሩን ስም ከማጠልሸት ታቅበዉ  ቀደም ሲል የሚያገኙንት ድጎማ  የሚያሟላ ስራ ላይ ያተኩራሉ።ከእኛ ሲገለሉም የአፍሪካ ጥልያን የመሆን እድላቸዉ የሰፋ ይሆናል እኛም የነሱን ምርት እንገዛለን። ባጠቃላይ ከላይ በምስሉ እንደሚታየዉ  ደስታ በደስታ ሁነዉ ትግሬዎች እንዲኖሩ የመገንጠል እድሉ ተመቻችቶላቸዉ ነጻ ከወጡ እንደ ድሮዉ በሁለት ቢላዋ መብላት ቀርቶ ወደ አዲሲቷ ሀገር በመሄድ ልማቱን ያፋጥናሉ ባጭር ጊዜም ድህነተን ደህና ሰንብት ይላሉ። እዚህ ላይ ማሰብ የሚገባቸዉ ተጎራባቾቻቸዉ ሸሪያ ሱዳን፤ኤርትራ፤ወልቃይትና ጠገዴ፤ራያ  ይሆናሉ  ማለት ነዉ። እነዚህ ሰዎች በነዚህ ቦታዎች የሰሩትን መጥቀስ የአንባቢን ችሎታ ማቃለል ይሆናል ብዬ አልፈዋለሁ።

ዳግም መልካም የድል በአል ክብር ለአሊ በርኬ በካራማራ በአድዋ እንዲሁም  ለሁለተኛ ጊዜ ጥልያንን ለመፋለም በዱር በገደሉ  ለወደቁ ለኢትዮጵያ አርበኞች። በህይወት እስካለን እንዘክራቸዋለን ባንዳን ይጭነቀዉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

 

1 Comment

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.