ስለዋጋ ግሽበትና የገንዘባችን ውድቀት ምን መደረግ ኣለበት? የባለሞያ ያለህ! – ገብረ ኣማኑኤል

birrየባለሞያ ያለህ!

ኣገራችን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ኣንዳለች አረዳለሁ። ሆኖም በየዘርፉ ያለውን ችግር ኣንዳመምጣጡ ካልተጋፈጥነውና ካላቃለልነው በቀር አየተደራረበ ማስቸገሩ የማይቀር ነው።  በመሆኑም አየከበደ ስለመጣው የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ማሳሰብ ወደድኩ።

የኢኮኖሚ ባለሙያ ኣይደለሁም ሆኖም አንደዜጋ ጉዳዩ ይመለከተኛል ብዬ ኣስባለሁ። ከሁሉም በላይ የገንዘባችን ዋጋ ማጣትና ወርዶ ወርዶ ኣንድ ዳቦ ለመግዛት ብሮች መቁጠር ማስፈልጉ ያሳዝነኛል። በዚህ ምክንያት ደግሞ ብዙዎች ለረህብና ለድህነት አንደሚዳረጉ ሳስብ አጅጉን ይቆጨኛል።

የኢኮኖሚ ጽሁፎች አንደሚያሳዩት የዋጋ ግሽበት ማለት የተራዘመ የዋጋ ጭማሪ ማለት ነው። የዋጋ ግሽበት የሚመጣባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች፣ ኣጠቃላይ ፍላጎት ከኣጠቃላይ  ኣቅርቦት ሲበልጥ ወይም ኣቅርቦት ሲያንስ፣ አንደነዳጅ ያሉ ሁለገብ ምርቶች ዋጋቸው ሲንር፣ የምንዛሪ ዋጋ ማሻቀብና የገቢ ምርቶች ዋጋ መናር፣ የጉልበት ዋጋ መናር በምርቶች ዋጋ ላይ ያለው ተጽዕኖና የሰራተኛው የመግዛት ሃይል መጨመርን የመሳሰሉት ናቸው።

አነዚህ ምክናያቶች ቢያንስም ቢያድግም በኣገራችን ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ አንዳመጡ መገመት ይቻላል ሆኖም አኔ ላተኩርበት የምፈልገው ዋና ነጥብ የምንዛሪ ዋጋ መናርን ነው። ኣሁን በማለፍ ላይ ያለው የፖለቲካ ስርዓት ካደረሳቸው ጉዳቶች ዋነኛው የኣገራችንን ገንዘብ ዋጋ ማሳጣቱ ወይም ያለውን ዋጋ በዓለም ላይ በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ አንዲል ማድረጉ መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ነው። ያ መንግስት ስልጣን ላይ በ1983 ከወጣ በኋላ የነበረው የዶላር ዋጋ በ 150% ያሳደገው በጥቂት ዓመታት ውስጥ ነበር።

ዓለም ባንክ የተሰኘው ገንዘብ ኣበዳሪ ድርጅትና ሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት ኢትዮጵያ የገንዘብ ምንዛሪዋን ዋጋ ከፍ አንድታደርግ በጣም ሲታገሉና ሲያስፈራሩ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። በኔ ግምት ዋናው ምክንያታቸው ይቺ ኣንዲት ደሃ ኣገር ገንዘቧ ከዶላርና ከፓውንድ ጋር ኣንዴት ተቀራራቢ ዋጋ ይኖረዋል? የሚል የበላይነት ስሜት ይመስለኛል። በመቀጠልም ብዙ ኣገሮች ያላቸው ዓለም ኣቀፍ ምንዛሪ ዋጋ አጅግ ከፍ ያለ በመሆኑና ሃያላኖቹ ኣገሮች ደሃ ኣገሮችን ገንዘባቸውን ዋጋ በማሳጣት የጥሬ ዕቃና የጉልበት ብዝበዛ ለማድረግ የቻሉ በመሆኑ ኢትዮጵያም ከዚህ ስርዓት ውጪ መሆን የለባትም በሚል ምክንያት ይመስለኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ...የተገፊዋ እናት ደብዳቤ ...! * ያልተመቻቸው የእኛ እናቶችን እንባ ..

ይህም ተሳክቶላቸዋል። ባሁኑ ጊዜ፣ በ 1983 ዓ ም ብር2.07 ይገዛ የነበረው ያንድ የዶላር ዋጋ ዛሬ ወደ 50 ብር ተጠግቷል። በጣም ያሳዝናል። ይህ ያልተገባ ርምጃ የሚወሰደው በብድርና በርዳታ መንግስትን በማባበል፣ ኣንዳንዴም በማስፈራራት አንደሆነ ይታወቃል።

አኔ ለብድርና ለአርዳታ ሲባል የብርን ዋጋ በማሳነስ በፍጹም ኣልስማማም። ብድርም ለጊዜው ይጥቀም አንጂ የሚከፈል ነው፣ በርዳታም ማደግ የሚቻል ቢሆን ኖሮ ኣስከዛሬ የት በደረስን ነበር። ምናልባት ይሄ ሙያዊ ትንተና ላይመስል ይችላል። ነገር ግን ባለም ኣቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች ኣማካኝነት ብዙ ተጽኖ መደረጉን ጥናቶችን መመርመር የሚያሻ ይመስለኛል።

ኣሁን ዋናው ቁም ነገር በግድም በውድም የገንዘባችን ዋጋ ወድቆ ወድቆ ባላፉት 30 ዓመታት 24 ዕጥፍ ወይም

2400% ደርሷል ወይም የኣንድ ዶላር ዋጋ በ24 አጥፍ ኣድጓል። ፍጹም ጤነኛ ኣይደለም። ስለዚህ ይህንን ተሸክመን ነገም ለሌላ ማባበያና ማስፈራሪያ ተጋልጠን ገንዘባችንን በሻንጣና በጆንያ አየያዝን ኣንገበያይ? ኣንደዚምባቡዬ የዓለም መሳቂያ ኣስከምንሆን ይሆን የምንጠብቀው? ህዝባችንስ ላይ ኣስከመቼ ነው የድህነት፣ የስራ ማጣት፣ የረሃብና የቤት ኣልባነት ሸክም ኣንዲሸከም የምንፈቅደው?

በማለፍ ላይ ያለው ስርዓት ያፈረሰውን ኢኮኖሚ ለመገንባት ብዙ ጥረትና ድካም ኣንደሚጠይቅ ይገባኛል። ነገር ግን በከፍተኛ ፍጥነት በመብረር ላይ በሚገኘው ለዚህ የገንዘባችን ውድቀት ልጓም ከዛሬው ካላበጀንለት፣ ሃብታሞቹ ኣገሮች አንደሚፈልጉት ከመሬት ላይ ተዘርረን ካላዩን በስተቀር ኣይትውንምና አንንቃ ዛሬውኑ የመፍትሄውን መንገድ መራመድ አንጀምር አላለሁ።

ኣሁን ዋናው ጥያቄ ይህን የዋጋ ግሽበትና የገንዘባችንን ውድቀት ዝም ብለን ልናየው ይገባል ወይ? ነው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቻችን በዚህ ላይ ምን ይመክሩናል? የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቻችን (Our Economists) የት ኣሉ? ምንስ ይጠብቃሉ? የሚለውን ጥያቄ ኣነሳለሁ። ባለሙያዎቻችን ያሉት ነገር ሊኖር ይችላል። ሆኖም ተፍታቶ ሲነገርና ለተግባር ሲንደረደር ግን ኣልታየም። ስለዚህ ብዙ ጊዜ ቢያመልጠንም አጅና አግራችን ታስሮ ስለነበር ለመፍረድ ኣይቻልም። ዛሬ ግን ኣንጻራዊ መሻሻል ስላለ ሰበብ የለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እስክንድር ነጋ እና ስብሃት ነጋ ብርሃንና ጨለማ!!! - ከቴዎድሮስ ሃይሌ

የባለሙያ አጥረት ኣለን ብዬ ኣላምን በመሆኑም የዋጋ ግሽበትን ለመቋቋም ምን መደረግ ኣለበት? ለሚለው ጥያቄ መልስ መገኘት ኣለበት። ጀግንነት በሁሉም መስክ ሊሰራ ይችላል። ለዓለማቅፍ ተጽዕኖ ስንንበረከክ ከኛ የቀደሙት ኣባቶች ኣስከብረው ያቆዩትን ኢኮኖሚና የገንዘባችንን ዋጋ ባንመልስ አንኳን ማሻሻል አንችላለን ብዬ ኣምናለሁ።

መንግስት ተገቢውን የኢኮኖሚ ስልት አንዲከተልና የኣገራችንን ኢኮኖሚ ኣንዲያስከብር፣ ዜጎችን ከማያባራ ድህነት አንዲታደግና ገንዘባችንን በጆንያ አያጓጓዝን ከምንገበያይበት የግሽበት ጉዞ ኣንዲታብቅ ተገቢውን ሙያዊ ምክርና አገዛ ልናደርግ ይገባል አላለሁ።

ለማጠቃለልም በኔ ቅኝት ያገኘኋቸውን የምፍትሄ ኣቅጣጫዎች የሚያመለክቱ ነጥቦቼን በመጠቆም ኣበቃለሁ።

 1. የወለድ መጠንን ክፍ በማድረግ በኢኮኖሚው ውስጥ ፍላጎትን ይቀንሳል፣ ኣነስተኛ የኢኮኖሚ አድገትንና የዋጋ ግሽበትን ዝቅ ያደርጋል።
 2. የገንዘብ ስርጭት ብዛትና የዋጋ ግሽበት የተያያዙ ናቸው የሚል መከራከሪያ ኣለ። በመሆኑም የገንዘብ ኣቅርቦትን በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር ይቻላል ማለት ነው።
 3. የኢኮኖሚውን ብቃትና ተወዳዳሪነትን የሚያሳግድ ፖሊሲ መኖር ፣ የረጅም ጊዜ ወጪዎች ላይ የመቀነስ ጫና ማድረግ።
 4. የገቢን ታክስ መጨመር ገንዘብ ማጥፋትን ሊቀንስ፣ ፍላጎትንና የዋጋ ግሽበት ጫናን ሊቀንስ ይችላል።

አነዚህ የመፍትሄ ኣቅጣጫ ጠቋሚ ሊሆኑ ይችላሉ ግን ሰፊ ውይይት በማድረግ ተጨማሪ ሃሳቦች ተብላልተው ተግባራዊ መሆን ኣለባቸው። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አባካችሁ ኣንድ በሉ! የገንዘባችን ምንዛሪ መስተካከል ኣለበት። ይሄን ማድረግ የዋጋ ግሽበትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን ክብርንም ማስጠበቅ ነው ብዬ ኣምናለሁ።

ገብረ ኣማኑኤል

 

2 Comments

 1. We need to know that all fields of studies in a country are inter related . Economists can come up.with economic policies to tackle the problem of high cost of living but that will not bring the desired results unless other entities such as the law enforcement do not perform their duties to make sure this economic policies are put into practice. The problem in Ethiopia is not lack of knowledge but it is lack of the willingness to put the knowledge into practice. With the current cost of living it is obvious there is no othet choice for Ethiopians but to engage in criminal activities, in some parts of Ethiopia because the cost of living is too high people are currently literally killing human beings and eating the flesh of human beings.

  Irrigation as much farm lands as possible with all the water resources Ethiopia can reach so people get enough food to eat is the ultimate solution inorder to.bring law and order in Ethiopia. In a country where there is no law order there cannot be any economic policy by itself which will be put into practice . It is just a waste if time and energy of the economists to.even try to come up with a solution if there is no desire to create a descent society to begin with.

  • Thank you,
   I even can see some solutions from your comment such as working together, policy matters, law enforcement, etc. I agree professions are interrelated but I think Economists need to come together, take the lead and seek workable solutions to save our currency. They can forward recommended solutions to the government and do what they can to ensure if steps are taken or not. I think the government need help in what to do to save the economy. Economic associations, Lawyers associations and others do little things unless they intervene at a higher level and influence policies.
   Once the policy directions are in place the law enforcement now rests on the government and the people then can hold the government responsible. I think they now feel that they have to do what World Bank and IMF are telling them to do in order to secure aid and loan. I believe these international institutions need to be challenged.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.