/

ለክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፤ ወልቃይትን፤ ጠገዴን፤ ጠለምትንና ራያን በሚመለከት የአቋም መግለጫ ደብዳቤ

የካቲት 13 ቀን፣ 2013 ዓ ም

ለክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፤ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ጉዳዩ;- ወልቃይትን፤ ጠገዴን፤ ጠለምትንና ራያን በሚመለከት የአቋም መግለጫ ደብዳቤ
ከኢትዮጵያ ውጭ ከምንኖር ተቆርቋሪዎች

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ

እኛ ከአገር ውጭ የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የህወሓት/ትህነግን እጅግ የሚዘገንን ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮጵያዊነት፤ ጸረ-ፍትሃዊነት፤ ጸረ-እኩልነት፤ አጥፊነት፤ ከሃዲነት፤ መዝባሪነት፤ ሕዝብን ከሕዝብ አናካሽነት ወዘተ ስንታገል ቆይተናል። በቅርቡ ዝነኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፤ ፋኖ፤ የአማራ ልዩ ኃይል፤ የአፋር ልዩ ኃይልና ያካሄዱትን በታሪክ ሲጠቀስ የሚኖር ትግልና ድል እናደንቃለን። የፌደራሉ መንግሥት አመራር ከሕዝቡ ጋር በመናበብ ለተጫወተው ሚና ምስጋናችንን እንገልጻለን።

–|[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-


 

 

6 Comments

 1. እንመልስ ካላችሁ

  እንመልስ ካላችሁ
  የእነቶኔን ንብረት ወደ አምናው ሥፍራ
  እሺ ይሰጣቸው ዳንሻና ሁመራ
  ወልቃይት ጠገዴ ልጉዲና ማይካድራ
  ከጸደቅን አይቀር በነካ እጃችን
  እንዲመራርቁን እስከልጅ ልጃችን
  ከወህኒም ከሲዖል ካሉበት ተጠርተው
  ይዘባነኑበት አራት ኪሎም ገብተው።
  ለሥልጣኑ ሲሆን አይያዘን ጉንፋኑ
  መመለስ ከጀመርን ይመለስ ዙፋኑ።
  የሰበሰበውን ሕወሃት በትግሉ
  ጉልበት የሰጠውን አንዷን ሳያጎሉ
  መመለስ ነው ታዲያ እንመልስ ካሉ።

 2. ጉድ በል ጎንደር!
  ክልል ይፍረስ ሲሉን የነበሩ እነዚህ ለምድር ለሰማይ የከበሩ “ምሁራን” [የአማራ] መሬታችንን መልሱና ክልላችንን እናጠናክር ብለውን አረፉት? በቃ ማሰብ የሚችሉት ይቺን ታህል ብቻ ነው? አበስኩ ገበርኩ፤፤ ባይማር ቢቀርስ?

  • Getaye amara bichawun meretun asrekibo achebchibo endiqemet new filagotih ???Ethiopia yehulum nat brother.Amara bichawun waga yikfel yalew manew??? Oromowochunim tigrewochunim endezihu hedeh mikerachew. Enesu ga atmokirewum kkk

 3. ትክክለኛ ትንታኔ ነው። አንድን ህዝብ መልሰህ ከ ገዳይህ ጋር ኑር ማለት የማይታሰብ ነገር ነው። ቢባልም የ አማራ ህዝብ ተመልሶ በ ትግሬዎች ሥር አይኖርም። ለዚህ መብት ማንኛውም አማራ እስከመጨረሻው ይዋደቃል። እርግጠኛ ነኝ። እንደዚህ ያለ የተንሸዋረረ ውሳኔ እንደማይደረግ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።

 4. ለከድር ሰተቴ፣
  አንተና የብልፅግና አጎብጓቢዮች ምን ያህል ከዕውቀት የፀዳችሁ እንደሆናችሁ ገብቶናል። ጉድጓድም አያድንም ፣አይተናል።

  • ሱሬው፡
   ረጋ በላ! “በምርጫ ብቻ” ብላለች ጀግኒት ብርቱካን ሚደቅሳ! ጉልበት እስከሌለበት ድረስ ዛቻው ችግር የለውም!
   ብልጽግና ራሱን ይከላከል፤፤ እኔ ከድር ሰተቴ የተናገርኳት እስከዛሬ መሬት ጠብ ያለች ህቅ ግን የለችም፤፤ ስላልገባህ ነው እንጂ “መሬት ከማስመለስ” ከፍ ብሎ ማስብ ይቻል ነበር፡፤ “የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች” የሚባል አዲስ ክልል ሊዋቀር ረፈረንደም እንድሚካሄድ ታውቃለህ? ትርጉሙ ይገባሃል? ለወልቃይት እና ለጠገዴ ራያ ሌሎችም የድንበር ጥያቀዎች እንዴት ሞዴል ሆኖ መልስ ሊሰጥ እንድሚችል አስበህ ታውቃለህ? ያንተ አይነቱ አይገርመኝም፤፤ እነዚህ “የከበሩ” ምሁራን ተመልሰው ክልል ዉስጥ ሲጠቀለሉ ማየት ግን ድፍረት አይሁንብኝ እንጂ ያሳፍራል፤፤ ከዚህ በፊትም እኮ፡”ግልጽ ደብዳቤ” እያሉ ምንም ባልገናቸው ጉዳይ ሲፈተፍቱ ነበር፤፤ በነገራችን ላይ የሃሳባቸውን ማነስ እንጂ የመጻፍ መብታቸውን እንዳልተጋፋሁ ይታውቅልኝ፤ ፤
   መልካም የአድዋ በዓል!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.