ሟፈር ዘመት!!!… ፖለቲካና ፖለቲከኞች!!!…የዶቦ ድርሻ ጥያቄ!!! _ሚሊዮን ዘአማኑኤል

e3333ሚሊዮን ዘአማኑኤል

የስድስተኛው ዙር የምርጫ ውድድር ተሣታፊ ለሆኑ ፖለቲካና ፖለቲከኞች ሃገራችሁን ምን ያህል ታውቃላችሁ ? የህዝቡን  የሥራ አጥነት ችግር በምን ዘዴ ማቃለል ትችላላችሁ ? የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሁኔታ ምንያህል ትገነዘባላችሁ? ፓርቲያችሁ ምርጫውን ቢያሸንፍ ለስንት ወጣቶች የሥራ ዕድል ትከፍታላችሁ? በህዝብና በጋዜጠኞች መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡ በእናት ሃገራችን ኢትዮጵየያ የተመዘገቡ ሠላሳ ሚሊዮን ሥራ አጥ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ  በሽህዎች የሚቆጠሩ የህክምና ዶክተሮች፣ ኢንጂነሮች፣ መምህራን ወዘተ ይገኛሉ፡፡ የብልፅግና ፓርቲ አስር ሚሊየን ካድሬዎች አባላት በማድረግ ደሞዝ ይከፍላል፣ በሃገራችን የተማሩ ሰዎች ሥራ ሳያገኙ ፖለቲከኞች ሥራውን ሁሉ ተቆጣጥረውት ይገኛሉ፡፡ ከዩኒቨርሲቲ የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ማጣት ፖለቲካና ፖለቲከኞች የሆኑ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች አንድ ፣ሁለት ፣ ሦስት ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድል እንፈጥራለን የሚል የፕሮጀክቶች ጥናት ማሳየት በምርጫው ጊዜ ይጠበቅባቸዋል? ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወዳዳሪዎችን እጃችሁ ከምን ብለው መጠየቅ ይገባቸዋል እንላለን፡፡

የብልፅግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድቸ ‹‹የድርሰትና የፖሊሲ ፉክክር ሌላ የሥራ ፈጠራ ሌላ!!! የዶቦ ድርሻ ጥያቄ!!! የሚገነባው ፕሮጀክት ለስንት ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራል!

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን በሃገራችን የሚገኙ የስራ አጥ ቁጥርን ልብ እንድትሉ ይረዳል፡፡ ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ያሉበት የኢኮኖሚ ሁኔታ/ ከ18-34 ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት ወጣቶች ብዛት በክልሎችና በከተማ መስተዳደሮችችና የፈንድ ገንዘብ (ብር 10 ቢሊዩን) ድርሻ እናስተውላለን፡፡

 • በአፋር ክልላዊ መንግሥት 618,827 (ስድስት መቶ አስራ ስምንት ስምንት ሽህ፣ መቶሃያ ሰባት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 206 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በትግራይ ክልላዊ መንግሥት 1,578,463 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ስምንት ሽህ አራት መቶ ስልሳ ሦስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣527   ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በአማራ ክልላዊ መንግሥት 8,024,773 (ስምንት ሚሊዮን ሃያ አራት ሽህ ሰባት መቶ ሰባ ሦስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 2ቢሊዮን 679 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት 1,806,539 (አንድ ሚሊዮን ስምንት ሜ ስድስት ሽህ አምስት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣603 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት 10,314,270 (አስር ሚሊዮን ሥስት መቶ አስራ አራት ሽህ ሁለት መቶ ሰባ ) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 3ቢሊዮን 439 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት 338,433 (ሦስት መቶ ሰላሳ ስምንት ሽህ አራት መቶ ሠላሳ ሶስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 113 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በደቡብ ክልላዊ መንግሥት 5,643,731 (አምስት ሚሊዮን ስድስት መቶ አርባ ሦስት ሰባት መቶ ሠላሳ አንድ) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 1ቢሊዮን 882 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት 150,414 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ አራት መቶ አስራ አራት) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 50 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በሐረሪ ክልላዊ መንግሥት 80,259 (ሰማንያ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) የሥራ  አጥ  ይገኛሉ፣ 27 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በአዲስ አበባ ክልላዊ መንግሥት 1,255,486 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ አራት መቶ ሰማንያ ስድስት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 419 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • በድሬዳዋ ክልላዊ መንግሥት 164,762 (አንድ መቶ ስልሳ አራት ሽህ ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 55 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
 • ጠቅላላ ድምር 29,975,958 (ሃያ ዘጠኝ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ሽህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ ስምንት) የሥራ አጥ  ይገኛሉ፣ 10 ቢሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢጆሌ እታያለሁ ወይ? - አስቻለው ከበደ አበበ

ምንጭ፡- የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ (አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

ከኢትዮጵያ ህዝብ 70 በመቶ ወጣቶች ሲሆኑ፣ መጪውን ህይወታችሁን ለማስተካከል የሥራ እድል ይፈጠርላቸው እንላለን፡፡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመንደፍ ለብዙ ሚሊየን  ወጣቶች የሥራ ዕደል ይፈጥራል የምንለው ለዚህ ነው? የፕሮጀክቱ ጥናት ለሙያተኞች ቀርቦ ሃሳብ ሳይሰጥበት፣ ለህዝብ ቀርቦ ለሚሰራው ሥራ የህዝብ መሆኑን ሳይመክርበት ከላይ ወደ ታች መወርወር ሊታረም ይገባል እንላለን፡፡ ምሁራንም በዚህ ጉዳይ ሃሳባችሁን ለህዝብ እንድታካፍሉ፣ ከሆነ በኃላ እንዲህ ቢደረግ ኖሮ ከሚል ስለ ፕሮጀክቱ በጎና ጎጂ ሁኔታዎችን መግለፅ ሙያዊ ግዴታ አለባችሁ እንላለን፡፡አንድ ፕሮጀክት ስኬታማነት የሚገመገመው በከተማዋ ውስጥ ያሉትን ሥራ አጥ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል ያሰገኘላቸው እንደሆነ ነው፡፡  ለሠላሳ ሚሊዮን ወጣቶች የሥራ እድል ከአሁኑ ጀምሮ ካልተጀመረ የሥራ አጡ ቁጥር ከአመት አመት እየጨመረ መሄዱ ወጣቶችን ለባህር ማዶ ስደት ይዳርጋቸዋል፡፡

ሟፈር ዘመት! የጎጃም ገበሬ በሟፈር ዘመትነት መሬት አርሶ አለስልሶ፣ ዘር ዘርቶ፣ ጦም ያደረውን መሬት ያርሳል፡፡ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ዲግሪ አግኝተው በዕውቀት የተገነቡ ምሁራን  ለአመታት ሥራ አጥተው ይገኛሉ፡፡ በየክልሎቹ ዲግሪ ያላቸው ሥራ ሳይቀጠሩ  ሟፈር ዘመት ኢህአዴግ ካድሬዎች  በሟፈር ዘመትነት ወደ ብልፅግና ፓርቲ አባልነት ተመልምለው ለሠላሳ ዓመታት እንደ ቂጣ ሲገላበጥ ይኖራሉ፡፡ ኢህአዴግ/ብልፅግና  ሟፈር ዘመት ፖለቲካ ያብቃ!!!

በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ለተማሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር አዋቂነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ካድሬዎች ዘመን ሊያበቃ ይገባል፡፡ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ተማሪዎችንና  ህዝቡን ያላሳተፈ ልማት፣ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት አያሻንም፣ በሃገሪቱ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ሁሉ ለወጣቶች የሥራ ዕድል የሚፈጥር መሆን አለበት፣ ማንም ፓርቲ ለእነዚህ ወጣቶች ስራ እስካልፈጠረ ድረስ ህልውናው የወራት እድሜ ነው እንላለን፡፡ የወጣቶች ጥያቄ የዳቦ ድርሻ ጥያቄ መሆኑን አንርሳ፡፡ ካለዛማ ወጣቶች አልወለድም ይሉናል!!!

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ የተሰጠ አስተያየት | አቻምየለህ ታምሩ

አቤ ጎበኛ

e33eeየኢህአዴግ/ብልፅግና  ሟፈር ዘመት ፖለቲካ ያብቃ!!!

ሚዛናዊ ሂስ ያብብ!!

ቸር እንሰንብት!!!

 

1 Comment

 1. ኦ ወገኔ ትዝታ ቀሰቀስክብኝ የአቤን ስራዎች ስታነሳ። ኢትዪጵያ ለገደሏት/ለካዲዎች/ለሚሸጧትና ለአሻጥረኞች የሆነች ሃገር ናት። ለወገንና ለህዝብ ዘርና ቋንቋን ተገን ሳያረጉ የተሟገቱና አሁንም በመፋለም ላይ ያሉ ያለ በደላቸው ሲገድሉና ሲታሰሩ/ሲሰደድ/ሲገደሉ አይናችን እያየ ነው። ለዚህ እውነትነት አልወለድምንና ፓለቲካና ፓለቲከኞችን አንብቦ መረዳት የበለጠ ያጎላዋል። እንደ ከረምት የአሸን ክምር አሁን በየትምህርት ተቋሙ የሚፈለፈሉት ተመራቂ ተማሪዎች የሚጠብቃቸው ሥራ ማጣት፤ የከተማ አውደልዳይነት፤ ከከፋም ለመኖር በዚህና በዚያ መቅበዝበዝ ነው። ያው ያለው እየከፈለም ሆነ እየሰረቀ ልጆቹን ውጭ አስወጥቷል፤ እያስወጣም ይገኛል። ያው ተወቶስ ቢሆን ኑሮ መቼ እንዲህ ቀላል ሆነና። እሱ ራሱ የራሱ ፍልሚያ አለው። ሃገሪቱ እጅግ የተወሳሰብ የችግር ሰንሰለት ውስጥ መሆኗን በየጊዜው ከዓለም ባንክና ከሌሎች የቀጥታና የተዘዋዋሪ ኮሎኒያሊስቶች የምትበደረው ብድር ራሱ አመላካች ነው።
  በትግራይ ወያኔ ለኮሰው በተባለው የጦርነት እሳት ሰዎች እየረገፉ ነው። የሚገርመው ለሃገራቸውና ለወገናቸው በማለት ወደ ሃገር ብቅ ብለው አይዞአችሁ የሚሉትን ሁሉ በሃሳብ ልዪነት ማሸማቀቅ መግደል የተለመደ የፓለቲካ አሻጥር ነው። በእስራኤል አገር የሚኖሩ ስደተኛ ወያኔ አፍቃሪዎች እንዲህ የሚል ቪዲዮ ለቀዋል። “የማነ ንጉሴን ገድለነዋል ቀብረነዋል”። ረጋ ብሎ ላሰበ ሰው ይህ ከጤነኛ ሰው ጭንቅላት የሚመነጭ አይደለም። ባጭሩ ፓለቲካ ሰውን ሁሉ አስክሮታል። እነዚህ ወስላቶች ቆይተውም ባስጠለላቸው ሃገር የጸጥታ ችግር እንደሚሆኑ የታወቀ ነው። ሌላ የቆየ ፊልም ላይ የሻቢያ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች በዚሁ በእስራኤል ሃገር ተከፋፍለው ሲቧቀሱና አንደኛው ድላ በሚመስል ነገር ሌላኛውን ኤርትራዊ ሲዥልጠው ያሳያል። ሌላው በኦሮሞ ጽንፈኞች በውጭ ሃገር እሰጣ ገባ የተፈነከቱ፤ በጩቤ የተወጉ፤ ነፍሴ አውጭኝ ብለው ፓሊስ የጠሩ ብዙ ናቸው። እንዲህ ያለው እይታና በሽታ ራሱ ውጭ እጅ ሃገር ቤት ሆኖ ምድሪቱን እያመሳት እንደሆነ በዚያው በምድሩ የእለት እለት ኑሮውን የሚገፋው ህዝባችን ያውቀዋል። ግን ከየት ተነስተን ወዴት እየሄድን ነው? የምናተርፈው ምን ይሆን? ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን ” በየእለቱ ሞት እንዳልሰንፍ፤ የኪዳኔ ቃል እንዳይነጥፍ” ያኔም እንደ ዛሬ ሆኖበት ይሆን? ሌላው እውቅ ጸሃፊ በዓሉ ግርማ ሀዲስ በተሰኘው መጽሃፉ ላይ ” ባዶ ቅል፤ እንደ ባዶ ነሃስ የሚጮህ፤ የተማረ ደንቆሮ፤ ብር ሃቁ፤ ምቾት ጭንቁ፤ ሆድ አምላኩ” የሚላቸው ፊደል ቆጥረናል አውቀናል፤ እንምራችሁ፤ አለቃ አርጉን የሚሉትን አይደለምን?
  ምርጫ በአፍሪቃ ቀልድ እንደሆነ አይናችን አይቷል፡ አሁን የታለመውን ግን ከመሆኑ በፊት እንዲህና እንዲያ ማለት አይቻልም። በአንድ እጅ ጦር በሌላ እጅ የምርጫ ጎሮጆ ይዞ ምርጫ ለቆጠራ ያስቸራል። ቢሆንም ጠብቆ ማየት ነው። ሌላው የሚያሳዝነው ነገር እልፍ ሰው በከተማና በገጠር እንደ ጉንዳን እየተተርመሰመሰ ሃገሩን በውትድርና ለማገልገል ፈቃደኛ አለመሆኑ ነው። ታዲያ አሁን ባለው የሴራ ፓለቲካ ክልሌ እንጂ ሃገሬ በማይባልበት እይታ እንዴት ተብሎ ነው ሌላ ክልል ሂዶ ህግና ደንበርን የሚያስከበር? ሰው በመግደል፤ በማሰር፤ በማፈናቀል፤ በመዝረፍ፤ ባልተለየ ኢላማ ላይ ተኩስ በመክፈት ተማሪዎችን የሚያፍን፤ የሚጨፈጭፍ የሰው አውሬ በሚተራመስባት ምድር ከተማውን ከነጣቂ፤ ከዘራፊ፤ ከገዳይ፤ የለየለትን የጦር ቀጠና ደግሞ ከጦርነትና ከእልቂት የሚያድን ምን ምድራዊ ሃይል ይኖራል? ቆይቶ ማየት ነው። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.