የፈሪሳውያን እርሾ – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“In the mean time, when there were gathered together an innumerable multitude of people, insomuch that they strode one upon another, he began to say unto his disciples first of all, Beware ye of the leaven of the Pharisees, which is hypocrisy.”

— Luke 12፥1

ትላንት ጨካኝ፣ግፈኛ ና ፈሪሃ እግዛብሔር የሌላቸውየአገር መሪዎችና አሥተዳዳሪዎች በዜጎች ላይ የፈፀሙትን እኩይ ፣ ነውረኛ እና አፀያፊ ተግባር የመነጨው ከግብዝነት ነው። ዛሬም ጥላቻን አሥፋፊው ግብዝነት በባሰ መልኩ ተሥፋፍቷል ። ዛሬም በግብዝነት የተሞላው የቆዳ ማዋደድ ፖለቲካና የእበላ ባይ አጨብጫቢዎች አሸሸ ገዳሚ ደምቆል። ”

በማዓት ግብዞች የተሞለው ፖለቲካችን ፣ ብለህ አርቆ አሳቢ ፣አሥተዋይ ፣አገር ወዳድ ወዘተ። ” የሚባለውን መሪ እንኳን ለማጃጃል የሚችል ቡድን እስከመፍጠር ደርሰዋል። እነዚህ ራሳቸው ግብዝ ሆነው፣ እንደጠጅ ቤት አዝማሪ ከውዳሴ በሥተቀር በፊሥ ቡክ ቡድናቸው ገንቢ የሆነ ትችት የማያቀርቡ፣ ብልሁን ሰው ሞኝ ለማድረግ የሚጥሩ ከመሆናቸውም በላይ፣ በየሥርዓቱ ውሥጥ እየተጠናከረ የመጣውን የግብዝነት ትምህርትን የሚሰብኩ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።

ማሥረጃውን ከፈለክ እዛው የግሩፕ የፊሥ ቡክ ገፃቸው ላይ ታገኘዋለህ ። ማድነቅን ሣይሆን ማምለክን እያሥተማሩ እንደሆነ ለመገንዘብ በየጊዜው የሚለጥፎቸውን መልዕክቶች በማንበብ መረዳትም አያዳግትህም ። መሪውን ፈጣሪ ነው ። ለማለት ሲዳዳቸው፣ ቀዳማይት እመቤቷን እምዬማርያም ናት ብለው ለመሥበክ ሲፍጨረጨሩ በቀላሉ ትታዘባለህ። …

ለእኔ እና ለመሰሎቼ የእውነት አቀንቃኞች የእነዚህ ጭፍን ደጋፊዎች ድርጊት በግብዝነት የተሞላ በመሆኑ ፣የለውጡን መሪ የወደፊት ቀና ሃሳብ ና ድርጊት አጨናጋፊ ሆኖ ታይቷናል ። ከዚህም ባሻገር በማመዛዘን ከጠቅላዩ ጎን የቆሙትን የአሥተዋይ ምሁራን ድጋፍ በማሳጣት የጠቅላዩ መሥተዋል ፈፅሞ እንዲጠፋ የሚያደርግ ከንቱ ድራማ ነው።

በእውነቱ ” የፊሥ ቡኮቹ የጠቅላዩ ደጋፊዎች ” ድርጊት ብሥለት የሌሌው የልጆች ጫወታ ነው። እናም መሪው የልጆች ጫወታን የሚፀየፍ ከሆነ ( ይህ ፀሐፊ የሚፀየፍ ነው ፡፡ብሎ ያምናል።) “ግብዝ አይደለሁም ። ግብዝነትንም እጠየፋለሁ።  ” በማለት ከፊሥ ቡክ ገፅ እነዚህን ህፃናት መሪው ገለል ቢያረጋቸው ለለውጡ ጉዞ ይበጃል ብዬ አስባለሁ።

አብዛኞቹ የዚህ የፊሥ ቡክ ቡድን ዓባላት በገፁ የሚለቁት ፁሁፍ ከትላንቱ የወያኔ ፕሮፖጋንዲሥቶች የተኮረጀ ነው ። የቀድሞው እውቁ የአገሬ ጠ/ሚ አቶ መለሥ ዜናዊ እንደ ዶ/ር አብይ ይወደሱ ነበር። ” ሺ የኢህአዴግ ካድሬ ና ሺ የተቃዋሚ ምሁር ከመለሥ ጭንቅላት ጋር ከቶም አይወዳደርም። ” ይባል ነበር። የጠ/ሚሩን የአእምሮ ግዝፈት ለማሳየት።…

በነገራችን ላይ ይህቺን አገር ባለችበት እንድትረግጥ የሚያደርጋት ፣ተጨባጩን እውነት አውቆ እንዳላወቀ የሚያደርገው በየቀበሌው ያለ ካድሬና በትንሽ ጥቅም ለመበጥረቅ ወደ ኋላ የማይለው ተላላ እና ሥሜታዊ ደጋፊ ነው ። ይህ ፈፅሞ ከእውነት ጋር የሚጋጭ ድርጊት በ1997 ዓ/ም በ3 ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ወቀት በወያኔ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተንፀባርቋል። የጨዋውን የኢትዮጵያ ህዝብ ማንነትም መረዳት የሚቻለው መሻገሪያው ድልድይ ላይ ህዝብ በነፃነት ሲደርስ ብቻ ነው። …

ተጨማሪ ያንብቡ:  የወልዲያና ቆቦን ጨምሮ ከተማ ሙሉ በሙሉ ነፃ ውጥተዋል

በዚች አገር ነፃነትን እና ነፃ አሥተሳሰብን ለማጥፋት እውነትን እና ቅንነትን በግብዝነት ለመቀየር የሚደረገው ትግል ዛሬም በመቀጠሉ የዛሬው መንግሥታችን የሚሾፍረው የለውጥ ባቡር ሐዲዱን ለመሣት እየተንገራገጨ መሆኑንን እያሥተዋልኩ ነው። የመንገራገጩ ምልክትም በአንዳንድ የኦሮሚያ ዞኖች እና በትግራይ ክልል ጎልቶ ይታያል። ይህ የመንገራገጭ እና ባቡሩ ከመሥመሩ ወጥቶ የመገልበጡ አደጋ እንዳይከሰት ያለው ብቸኛ አማራጭ ከደርግና ከወያኔ ኢህአዴግ በውሸት ፕሮፖጋንዳ ላይ ከተመሠረተ የካድሬ ፖለቲካ ፈፅሞ መውጣት አማራጭ የሌለው መፍትሄነው። እራሳቸውን መምራት የማይችሉ ግለሰቦችንም ከመሪ ወንበር ላይ ሣይረፍድ ማንሳት ያሥፈልጋል። ከራሳቸው ጥቅም ይልቅ ለደሃ ህዝባቸው በብርቱ የሚጨነቁ። ሰውን በጎሣ ሣይከፋፍሉ ለዜጎች ነፃነት፣ ፍትህ፣ እኩልነት መከበር የሚታገሉ ።በተግባር ደሃውን ለማበልፀግ እንጂ ራሳቸውን ከበርቴ ለማድረግ ህዝብና አገርን የማይበዘብዙ ግለሰቦችን ለሥልጣን ማብቃት፣ ከቃላት በላይ ወደብልፅግና እንደሚያሻግ ርመረዳትም ከመቼውም ጊዜ ይብልጥ ዛሬ አገር እንደምትፈልግ መገንዘብ መልካም ነው። ካለፉት መንግሥታት ካድሪያዊ አደንቆሪ ፖለቲካ አብይ መራሹ ” ወደብልፅግና አሻጋሪ መንግሥት ”  መሠረታዊ ለውጥ በማድረግ እሥካልወጣ ጊዜ ድረሥ የመላውን ህዝብን ልባዊ ድጋፍ ለማግኘት አይችልም።

በነገራችን ላይ ፣በካድሬ ቅሥቀሰ ፣ልክ እንደደርግ ና ኢህአዴግ ገብያና የሱቅ ንግድ ከድጋፍ ሰልፍ በኋላ በማለትም ፣የህዝብን ልብ በማግኘት ለቀጣዩ የህዝብ አገልግሎት ዘመን እበቃለሁ ማለት ያንኑ የወያኔ ፖለቲካ መድገም ይሆናል። ሌሎችም በግብዝነት በማሥመሠል ፣በዱላ፣ በገጀራ ፣ና በጥይት ሥልጣንን ለጊዜው ይዞ መቆየት ቢቻልም ለመሰንበት ግን ፈፅሞ እንደማይቻል ከወዲሁ መገንዘብ አለባቸው።

በፖለቲካው ዓለም ግብዝ መሆን እና ማሥመሰል የኋላ ኋላ አደጋ እንደሚያሥከትል ከታሪክ መገንዘብ ይቻላል። እንደምሳሌም የ1997 ዓ/ም ምርጫን ዞር ብሎ በመመልከት ከትላንት የወያኔ/ኢህአዴግ ውድቀት ለመማር ይቻላል።

ዛሬ ከ18 እሥከ  30 ዓመት የዕድሜ ክልል ውሥጥ የሆናችሁ ወጣቶች የ 3 ኛውን የአገር አቀፍ ምርጫ ሂደትና ፍፃሜውን ካላነበባችሁ አታውቁምና ላላነበባችሁ ታሪኩን ባሥታውሳችሁ ለነገ 6ኛው አገራዊ ምርጫ መነፅራችሁን ቀይራችሁ ሁኔታውን በአንክሮ ለማየት ይበጃችኋል ብዬ አሥባለሁ። …

የ3ኛው ዙር አገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 7 ነበር የተካሄደው። ምርጫው ከመካሄዱ በፊት በተደረገው የምረጡኝ ቅሥቀሣና የመድረክ ፖለቲካዊ ግጥሚያ ቅንጅት የተሰኘ ፖርቲ ኢህአዴጎችን በዝረራ አሸንፎ ነበር። እነፕሮፊሰር መሥፍን ፣ፕሮፊሰር ብርሃኑ፣ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ና ኢንጂነ ርግዛቸው ፣ልደቱ አያሌውን ጨምሮ አያሌ ምሁራን የተቀናጁበት ፖርቲ ኢህአዴግን በምርጫ ቅሥቀሣና በፖለቲካዊ ፣በማህበራዊውና በፖለታካዊ ክርክሩ በዝረራ እንዳሸነፈ ሁሉ በግንቦት 7 ምርጫ ማሸነፍ እንደሚችል ገዢው ፖርቲ በመጠርጠሩ ፣የአዲስ አበባን ህዝብ የድጋፍ ሠልፍ ኢህአዴግ ፣ሚያዚያ 29 ቀን ጠራ። በድጋፍ ሠልፉ የተገኙ በሰልፉ መሀል ውሥጥ ሆነው፣ ” ዛሬ ለእንጀራችን ነገ ለአገራችን ፣ዛሬ ለቲሸርት ነገ ለነፃነት ፣ዛሬ ለሆዳችን ነገ ለክብራችን…” የሚሉ ሰልፈኞችም ነበሩ። በሰልፉም እንደኢቲቪ ዘገባ አንድሚሊዮን ተኩል ይሆናል የተባለ ሰልፈኛ ተገኝቶ ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Sport: የውጭ ተጫቾች በኢትዮጵያ- ተጠቀምን ወይስ ተጠቀሙብን? - ከገነነ መኩሪያ (ሊብሮ)

በማግሥቱ ሚያዚያ 30 ቀን 1997 ዓ/ም ደሞ ቅንጅት በጠራው የድጋፍ ሰልፍ ከሚያዚያ 29 የሚበልጥ ህዝብ (የዋሁ ና በልህ የሆነው በፍቅር እዮነረ ያለው የአዶ ገነት ነዋሪ   ) በመሥቀል አደባባይ ተገኝቶ ለቅንጅት ፖርቲ ያለውን ድጋፍ ገልፆል።

በሚያዚያ 29 ቀኑ የህዝብ ልብ ባልታወቀበት፣ በቀበሌ ካድሬ ቅሥቀሣ በአደባባይ የተገኘ ጨዋ ዜጋ የእሳቸው ደጋፊ መስሎቸው  ” ይህ ማዕበል ኢህአዴግ ምርጫውን ሳያጭበረብር ለማሸነፍ ያሥችለዋል።.. .ምርጫውም እንከን የለሽ ይሆናል።…” በማለት በሥሜት እየተወራጩ መለሥ ዜናዊ ተናግረው ነበር። መለሥ ከግንቦት 7 በኋላ ግን በከፍተኛ አመራሮቻቸው፣ በካድሬዎቻቸውና በድህንነት ኃላፊው ሳያዝኑ እንዳልቀሩ በተከታታይ ያደረጓቸው ለውጦች ያመላክታሉ።

መለሥ ከምርጫ ሽንፈታቸው ማግሥት ጀምሮ፣ የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው “ጣታችሁን የምትቀሰሩ ጣታቸሁ ይቆረጣል። በትግል ያገኘነውን ወንበር በወረቀት አሳልፈን አንሰጥም። አርፋችሁ ቁጭ በሉ። በነውጥ መንግሥት መሆን አትችሉም። በቢላዋ ቀልድ እንደሌለም እወቁ። ” በማለት በጥይት የግንቦት ሰባትን ውጤት የመቀልበሥ የኃይል እርምጃ ወሰዱ። ታላቅ የቅልበሳ የፖለታካ ሥራ ሰሩ። (የተረፈውን አቶ ልደቱ የናገር። ማን ይናገር የነበረ…እንዲሉ። )

የህዝብን እውነተኛ ፍላጎት ከደረሰባቸው ሽንፈት በመገንዘብ ከዚህ ሽንፈት በኋላ አብዛኞቹን የቅንጅት ሃሳቦች ማራመድ ጀመሩ። የተቸከሉት የመሬት ፣የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፣አንቀፅ 39 ና የጎሣ ፖለቲካ እና የጠመንጃ አገዛዝ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አደረጉ።  …የባንዲራ ቀን እና የአባይ ግድብ የመሠረት ዲንጋይ፣ በአቶ መለሥ የአገዛዝ ዘመን እውን ሆነ። የህዝብን ሥነ ልቡናም ተሠረቀ። “አባይን የደፈረ ጀግና መሪ ” መለሥነው። ተብሎ ተጨበጨበ።

ያም ሆነ ይህ ብቸኛው የኢህአዴግ መሪ ድንገት በሞት ሲለዩ ፣ኢህአዴጎች የግል ሀብት በየፊናቸው ለማከማቸት መሯሯጥን አብይ ሥራ አድርገውት አረፉ። የመለሥ ሌጋሲም ተረት፣ተረት፣ ሆኖ ቀረ። በእርግጥ ኢህአዴጎች የመለሥ ሌጋሲ ጉዳያቸው አልነበረም። መለሥ በህይወት እያለ የሚፈሩትና የሚያመልኩት ህልቆ ወመሣፍርት ካድሬዎች ሁሉ፣ ከመለሥ በኋላ መንግሥት እንደሌለ በመቁጠር በዘረፋ ላይ ተሰማሩ። ባጋበሱት ሀብትም በትዕቢት ተወጠሩ። ሲበዛ ግብዝ ሆኑ።ግብዝነታቸውም አጠፋቸው።

በጣም የሚገርመው እነዚህ ሰዎች ግብዝነታቸው እንዳጠፋቸው፣ ዛሬም አይገነዘቡም።_ እነሱ ከሰው ሁሉ በላይ የሆኑ፣ ለመሪነት የተፈጠሩ ሌላው ተገዢ ሆኖ ለመኖር የተፈጠረ ነው።_ብለው የሚመፃደቁ ናቸው። ዛሬም በዳቦ እጦት የሚሰቃየውን ዜጋ ዳቦ እያሳየን እንገዛዋለን። አይቶ የማያውቀውን ብር በመሥጠትም ነፍሰ ገዳይ እናደርገዋለን።ብለው የሚመፃደቁ ናቸው። ዛሬም ከሞት የተረፉት የእናት ጡት ነካሽ የገንጣዩ የህውሃት ቡድን ሥብሥቦች ሥለከንቱነታቸው ነው የሚያወሩት። ሥለጅብነት ነው የሚያወሩት። (ህወሃቶች በጅብነት ቀምተው ሲበሉ የነበሩትን ግጠው ሳይጨርሱ መባረራቸውን አንዘንጋ።)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዳግም ወደ እርድ ቄራ! /ዛሬ ወይም ነገ ታፍነው ሊወሰዱ ነው!

ለሕወሓቶች ፣የህግ የበላይነት ፣እኩልነት ፣ሰብአዊ መብት ወዘተ። ተረት፣ተረት ነው። ዛሬም እነሱ ከጠገቡ ደሃው የትግራይ ህዝብ ለምን አራት እግሩን አይበላም። ” ባዮች ናቸው ። በተግባርም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልን ፡፡

ግብዞቹ ህውሃቶች ደሃው የትግራይ ህዝብ ከጎናቸው ባለመቆሙ ሊበቀሉት ይፈልጋሉ። የኤሌትሪክ አገልግሎትን ጨምሮ መሠረተ ልማትን ማውደም ቀጣይ የበቀል ተግባራቸው ነው። በዚህ እኩይ ተግባራቸው የትግራይ ደሃ ህዝብ የዕለት ምግቡን አብስሎ መመገብ ሲያቅተው ይደሰታሉ። ግብዞች ሁሌም እንዲህ ናቸው። በሰው ቁሥል ውሥጥ የሾለ ብረት መሥደድ ና ማሠቃየትን እንደፅድቅ ሥራ የሚቆጥሩ  ናቸው። ያሳዝናል። መቼ ይሆን ይህቺ አገር ከእነዚህ መሠል ግብዞች የምትፀዳው??? በመላው አገራችን የተዘራው የግብዝነት አረም መቼ ይሆን ተነቅሎና ተቃጥሎ የሚጠፋው ? …

ኮለኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ( ፕሬዝዳንት ) ጠ/ሚ መለሥ ዜናዊ ዛሬ ደግሞ ዶ/ር አብይ አህመድ ግብዝ እንዲሆኑ በየወቅቱ አዳዲስ ከንቱ ውዳሴ የበዛበት መፈክር በሥማቸው የሚያወጡላቸው እበላ ባይ ካዲሬዎች ነበሯቸው። ትላንት ለኢሠፖ ያልተደረተለት በትክክል የማይገልጸው ሥም አልነበረም።

ትላንት ለወያኔ /ኢህአዴግም ጨካኝነቱን መደበቅያ ያልተሰፋለት የወርቅ ካባ አልነበረም። ዛሬ ለመሞት አያጣጣረ እንኳን ፣የጎሣ አቀንቃኝ የኃይማኖት ካድሬዎቹ ቆባቸውን በአደባባይ ረግጠው በውጫ አገር ሲያወድሱት ስናይና ስንሰማ ይህንንኑ የግብዝነት ፖለቲካ ና ቀውሱን እናረጋግጣለን። …

ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ፣ዛሬ ከዚህ ግብዝነት ከሚያስከትለው ቀውሥ እንዴት መውጣት እንደሚችል ዛሬ ቆም ብሎ ማሰብ አለበት። ብዝበዛቸው የተቋረጠባቸው እና የዛሬ አዳዲስ ግብዞች ሊውጦት እያደቡ መሆኑንም የተደበቀውን በመግለጥ የሚችለው ቆም ብሎ ማሰብ ሲችል ብቻ ነው፡፡እነዚህ ያደፈጡ የጎሳ ፖለቲካው የደበቃቸው ህሊና ቢስ ግብዞች   ግንባር ፈጥረው ይህቺን አገር ወደ ከፋ ችግር እንዳይ ወሥዷትም አሥፈላጊውን ጥንቃቄ እና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ ትግራይም እስከምረጫው ድረስ ከወገኑ የፖለቲካ ሰዎች ነጻ መሆን አለባት፡፡ትግራይ በጥብቅ ወታደራዊ ኮማንድ ውስጥ ካልሆነች የተረጋጋ ሰላም ማምጣ የሚከብድ ይመስለኛል፡፡ …

ለማንኛውም.. ይህንን ጥቅስ ጋብዣቸው ፅሁፌን እቋጫለሁ ፡፡

“በዚያን ጊዜ የሕዝብ አእላፍ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ተሰብስበው ሳሉ፥ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፥ እርሱም ግብዝነት ነው።”

— ሉቃስ 12፥1

ይህን ቃል ኢየሱስ የተነገረው ፣እውነትን ለመሥማት ለመጣ ቁጥሩ እጅግ ለበዛ ህዝብ ነው። ከፈሪሳውያን እርሾ አሥቀድሞ መጠበቅ ልብን ድፍን ከማድረግ ይታደጋል። በፈሪሳውያን እርሾ ከተላቆጣችሁ በኋላ ግን ረብ አይኖራችሁም።

 

2 Comments

  1. I doubt the current Ethiopian federal government would let Sudan move out of the Ethiopian territory which Sudan currently invaded in Ethiopia, untill after the upcoming Ethiopian election is over with. Even if Sudan decided to move out of Ethiopia on its own , I doubt Prosperity Party do want the freed Ethiopians to vote at the upcoming election, Prosperity Party/PM Abiy Ahmed might encourage the Sudan government to take every last one of the Ethiopian witnesses residents of the invaded area to Sudan as slaves so they don’t affect the upcoming election by telling their ordeals while were conquered by Sudan.

    The current federal government of Ethiopia and the ruling party Prosperity Party had let Sudan commit despicable crimes against Ethiopians in Ethiopia, If deatailed news comes out of what kind of loss the residents of this invaded area suffered , Prosperity Party will surely loose considerable amount of votes at the upcoming election .

    Currently the Abiy Ahmed’s administration is stalling to drive Sudan out of Ethiopia so the Ethiopian witnesses do not vote at the upcoming election, many Ethiopians suffered first hand by Sudan’s invasion, their families abducted getting enslaved sold in Sudan to Libyans , this brings serious loss of voters to Prosperity Party that is why the witnesses are kept secluded from voting or from even telling their stories even if they escaped from the area Sudan invaded made it to Addis Ababa . Abiy Ahmed’s administration is stalling by holding “talks” after “talks” after “talks” with Sudan so the details of the Sudan invasion doesn’t get told at least until after the next upcoming national election of Ethiopia.

  2. ወገኔ ክዋክብትን በጠራራ ጸሃይ ውስጥ አያለሁ ከሚሉ ፓለቲከኞች ጋር እንዴት ነው ለህዝብና ለሃገር አመርቂ ሥራ የሚሰራው? ጠበንጃ ይዞ አራሽ ገበሬና የከተማ ሰውን እየገደለና እየዘረፈ በሚኖር ህብረተሰብ መካከል እንዴት ባለ ሂሳብ ነው ሰው በሰውነቱ የሚከበረው? በአዲስ አበባ በየጊዜው አንገታቸው ተቀልቶ ተጥለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በዝቷል። ሰው እናቱን፤ አባቱን፤ ወንድሙን፤ እህቱን የሚያታልልበት እንደ አሳማ ለራስ ብቻ ለመኖር የሚደረገው ግብግብ ክራራይሶ አስብሎ ገዳም ያስገባል። በትግራይ ተጀመረ የተባለው “ህግን የማስከበር ዘመቻ” በወያኔ ትራፊዎችና በውጭ ሆነው ሌላው እንዲሞት በሚገፉ አፍቃሪ ወያኔዎች ምድሪቱን እንደገና ለመከራ ለመዳረግ የማይፈነቀል ድንጋይ የለም። ገናም ያተራምሱናል። በመግደልና በመሰወር ብቻ የሚያምነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ በምድሪቱ የመከራ ዝናብ ሲያዘንብ እንደኖረ ንጽህ እይታ ያለው ሁሉ ይረዳዋል። በሴት ብልት እንጨት የሚከት፤ በወንድ ብልት ላይ ውሃ የሚያንጠለጥል፤ ጥፍር የሚነቅል፤ ሆን ብሎ በሚገርፋቸው ሰዎች ላይ ውሃ የሚያርከፈክፍ፤ የሴት ጡት የሚቆርጥ ይህን አረመኔ ነው የትግራይ ህዝብ ታቅፎ የኖረው። የሚገርመው አሁን ወያኔ ሞተ ከተባለ በህዋላ ወያኔን ደግፈው መንገድ የሚመሩ፤ ምግብ የሚያቀብሉ፤ ዘርፈው ተዘረፍን የሚሉ፤ ገድለው ተገደለን በማለት ለዓለም ህዝብ ኡኡታ የሚያሰሙ ስንቶች ናቸው? ልክ የዛሬ 45 ዓመት በረሃ እንዳሉ ያደርጉ እንደነበሩት ባንክ የሚዘርፉ፤ የህዝብ አውቶብሶች አስቁመው ሰው የሚረሽኑ፤ ሃገሩን ሊረዳ የሄደ ወገንን በጥይት መትተው የሚገድሉት የውስጥ ተባባሪዎች በሚሰጧቸው ጥቆማ እየተረድ ነው። እህል የጫኑ የመኪና ሾፌሮችን የሚገድሉ እንስሳዎች ናቸው። የወያኔ ትራፊዎች ወይም መንግስት እንደሚለው ተቆርጠው የቀሩ የሚፈጽሙት ግፍ ልክ የለሽ እንደሆነ ያሳያል። በቴክስት፤ በቀጥታ የስልክ ጥሪ ገና ከስፍራቸው ሰዎች ሲነሱ እየተናገሩ የሚያስገድሏቸው የውስጥ ተላላኪዎቻቸው ናቸው። አዲስ አበባ ላይ እየኖረ እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ትግራዋይ ነኝ እንዳለው የጠባብ ብሄርተኛ በሽተኛ ውስጥ ውስጡን ያኔ የዘረጉት የስለላ መረብ ትራፊዎችና አሁን በጄሌዎቻቸው ያጠናከሩት የስለላ ጥምር የሚፈጽሙት በደል ሰማይ ጠቀስ ነው። ይደረጋል የሚባለው ምርጫን አስመልክቶ እንዳይሳካ ገና ብዙ ጉድ ያደርጋሉ። ኬላ ላይ የተያዘው ፈንጂ የት ነበር የሚሄደው? ወያኔን ያለ ርህራሄ መምታት ካልተቻለ የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን መላው ሃገሪቱ እፎይ ማለት አይችልም። ለዚህም ነው የውሸት ቪዲዮ እየለቀቁ ማረክን፤ ገደልን፤ ደመሰስን የሚሉት። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ተኝቷል። በሚዲያ አፍቃሪ ወያኔዎች የሚለቁትን ቪዲዮና ሌላም መረጃ ማበጠር ለስለላ መረቡ የወርቅ ጉድጓድ ነበር። ግን ማን ስመቶ በዚህም በዚያም ዲስኩር ብቻ። አሰልቺ ዲስኩር። አፍቃሪ ወያኔዎች በሶሻል ሚዲያና በሌላም መልክ የሚለቋቸው ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ምስሎች የሚነግሩን ብዙ ነገር አለ። ጌታቸው ረዳ ተናገረ ደብረ ጽዪን ደገመ ሲባል እንዴት በተራቀቀ መንገድ የእነርሱ ድምጽ መሆንና አለመሆኑን ማጣራት ይከብዳል? የትግራይና የወያኔ ጦስ ገና አላለቀም። ዛሬም ሞት ትላንትም ሞት፤ ዛሬም መኪና ማቃጠል፤ ድልድይ ማፍረስ፤ ሰው መግደል የተለወጠ ነገር የለም። ኢትዪጵያዊ አይደለንም ትግራዋይ ነን ለሚሉት ደግሞ በመኪና አሳፍሮ የትግራይን ህዝብ እንዲረድ በመረጡት መንገድ ወደ ትግራይ መላክ ነው። ሶፋ ላይ ተቀምጦ አካኪ ዘራፍ ቢሉት ዋጋ ይብሉን። ከሁሉ የሚያሳዝነው ግን ዛሬም ትላንትን መምሰሉ ነው። አይበቃም። የትግራይ ህዝብ እፎይ የሚለው መቼ ይሆን? ጠብቀን እንይ! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share