/

ኢዜማ የተገደለ አባሉን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል

የአባላችን ግርማ ሞገስ ለገሰ ግድያን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)

45433

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሀገራችን በሁሉም አካባቢዎች አባላትን በማደራጀት እና መዋቅሮችን በመዘርጋት በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም የሀገር አንድነት እና ቀጣይነትን የማረጋገጥ ሂደት ውስጥ አወንታዊ አስተዋፅዖ እያደረግን ከመቆየታችን በተጨማሪ አጠቃላይ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ባህል ለመቀየር የበኩላችንን ጥረት ስናደርግ የቆየን መሆኑ ይታወቃል። በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከማኅበረሰቡ ጋር ለመወያየት፣ አባላትን ለመመልመል እና ለማደራጀት በምናደርገው ሙከራ ውስጥ ሥራችንን ለማደናቀፍ እና ተስፋ ለማስቆረጥ የመንግሥትን መዋቅር ጨምሮ የተለያዩ ኢ-መደበኛ አካላት ሙከራ ሲያደርጉ ቆይተዋል። በምናደርገው እንቅስቃሴ ላይ የሚያጋጥሙንን ችግሮች ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመገንባት ረጅም ጊዜ እና ትልቅ ትዕግስት እንደሚያስፈልግ በማመን ችግሮቹን ከማጉላት ይልቅ ችግሩን እና ፈተናውን ተቋቁመን በንግግር እና በውይይት ለመፍታት ጥረት ስናደርግ ቆይተናል።
የሚደርሱብንን ጫናዎች በመቋቋም የዘረጋነውን ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር እና የኢትዮጵያን ሕዝብ የተጠራቀሙ ችግሮችን የሚፈቱ በባለሙያዎች የተዘጋጁ ፖሊሲዎች ይዘን የምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ዝግጅታችንን ባጠናቀቅንበት የመጨረሻ ሰዓት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቢሾፍቱ ከተማ አድአ ምርጫ ወረዳ 1 የኢዜማ መዋቅር ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ እሁድ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በጥይት ተመተው ሕይወታቸው አልፏል።
ከዚህ በፊት በቢሾፍቱ ከተማ የምናደርገው እንቅስቃሴ ላይ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሙን እና አባላቶቻችን ላይ ማዋከብ ሲያጋጥመን ነው የቆየው። በከተማው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ፈልገን በተደጋጋሚ ያደረግነው ሙከራ በከተማው አስተዳደር እምቢተኝነት ምክንያት መሳካት አልቻለም። የምርጫ ወረዳ መዋቅራችን የሚጠቀምበት ጽሕፈት ቤትም ለመክፈት ብዙ ውጣውረድ ብናልፍም ከከተማው አስተዳደር በሚደረግ ጫና መሳካት አልቻለም። በከተማው ኢዜማ ከነዋሪዎች ጋር ሊያደርግ የነበረውን ስብሰባም ሆነ ጽሕፈት ቤት ለመክፈት ይደረግ የነበረውን እንቅስቃሴ በግንባር ቀደምትነት ለማስተባበር ሲሠሩ የነበሩት አቶ ግርማ ነበሩ። ከዚህም የጎላ እንቅስቃሴያቸው ጋር በተያያዘ በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው ነበር።
በቢሾፍቱ የሚገኘው የኢዜማ መዋቅር በየጊዜው የሚያጋጥሙትን ችግሮች በዋናው ጽሕፈት ቤት እገዛ እንዲስተካከል አቤቱታቸውን ቀደም ብለው አስገብተው ነበር። ይህንኑ መሰረት በማድረግ ከከተማው እና ከክልሉ ኃላፊዎች እንዲሁም ከገዢው ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር ሙከራ አድርገን ነበር። ሙከራችን የነበረውን ችግር ማቃለል አልቻለም። እንደውም ችግሩ ተባብሶ የሁለት ልጆች አባት እና የቤተሰብ ኃላፊ እና የኢዜማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ በጥይት ተመተው መተኪያ የሌለው ሕይወታቸውን አጥተዋል።
የኢዜማ የቢሾፍቱ መዋቅር ለኢዜማ ዋናው ጽሕፈት ቤት ካስገባው አቤቱታ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም በከተማው እንቅስቃሴ ለማድረግ ያጋጠማቸውን ችግር እና እየደረሰ ያለውን ወከባ ገልፀው አስፈላጊውን እንዲያደርጉ በደብዳቤ ጠይቀው ነበር።
የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ከዚህ ቀደም የኢዜማ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆነን ሰው መኖሪያ ቤት በፈተሸበት ወቅት የወሰዳቸውን የፓርቲው መገልገያ ሰነዶች እንዲመልስልን ስንጠይቅ ውክልና ያለው ሰው እንድናሳውቅ በጠየቀው መሰረት አባላችን ግርማ ሞገስን ጉዳዩን እንዲከታተሉ እና ንብረቶቻችንን እንዲቀበሉ ወክለን የላክነውን ደብዳቤ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ማሕተም እና ፊርማ አስፍሮ ተቀብሎን ነበር። ይህ በእንዲህ እያለ የአባላችን መገደልን ተከትሎ በፍጥነት ወደድምዳሜ ከመሄድ ይልቅ በጥንቃቄ ዝርዝር መረጃዎችን ለማሰባሰብ ጥረት በምናደርግበት ወቅት የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ጉዳዩን ተከታትሎ በሕግ የተጣለበትን ፍትህን የማስከበር ሥራውን ከመወጣት ይልቅ የአባላችን መገደልን አስመልክቶ የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ ለፋና፣ ኢቲቪ፣ ዋልታ እና ኦቢኤን ቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫ ግርማ የኢዜማ አባል እንደሆነ እንደማያውቁ በመካድ የግድያውን አቅጣጫ ለማስቀየር የሄዱበት ርቀት እና ከዚህ በፊት በከተማው የፓርቲያችን እንቅስቃሴ ላይ እና አባሎቻችን ላይ ይደርስ ከነበረው መዋከብ እና እንግልት ጋር ተደምሮ ግድያው የተቀነባበረ እንደሆነ ያመላክታል።
የሕግ የበላይነት እና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን የሚደረገው ትግል የብዙዎች መራር ትግል እና መስዕዋትነትን የጠየቀ እንደሆነ ይታወቃል። አባላችን ግርማ ሞገስን ጨምሮ ከዚህ ቀደም ስለእኩልነት እና ፍትህ ሲሉ ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያዊያን መስዕዋትነት ቁጭት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመመሥረት ለምናደርገው ትግል ተጨማሪ ብርታት ይሆነናል እንጂ በዚህ ምክንያት በፍፁም ወደኋላ አንልም። እየሞትንም ቢሆን ዴሞክራሲዊት ኢትዮጵያን ከመገንባት የሚያቆመን ምንም ኃይል የለም፡፡ ይህ ለማንም ግልፅ ሊሆን ይገባል።
ቀጣዩ ምርጫ ነፃ እና ፍትሃዊ እንዲሆን መሟላት ከሚገባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች በነፃነት መንቀሳቀስ፣ ለማኅበረሰቡ አማራጫቸውን ማቅረብ መቻል እና ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ በምርጫው ውስጥ ያለምንም ፍርሃት መሳተፍ መቻላቸው እንዲሁም ከምርጫው ጋር በተያያዘ ኃላፊነት ያለባቸው ተቋማት ለማንም ሳይወግኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በገለልተኝነት ማስተናገድ መቻላቸው ይገኝበታል። በምርጫ ቅስቀሳ ዋዜማ አባላችን ላይ የተፈፀመው ግድያ እነዚህ መስፈርቶችን በተመለከተ ብዙ መሠራት ያለባቸው የቤት ሥራዎች እንደሚቀሩ በግልፅ ያሳየ ነው።
ኢዜማ የዓባላትችን ግርማ ግድያ ተከትሎ፣
1. መንግሥት የጓዳችንን ሕይወት የቀጠፉትን ወንጀለኞች አድኖ ሕግ ፊት ባስቸኳይ እንዲቀርብ እንጠያቃለን፣
2. ቀደሚ ሲል አቶ ግርማን ጨምሮ በአባሎቻችን ላይ ወከባን ማስፈራሪያ ያደርጉ የነበሩት የቢሾፍቱ የፓርቲና የመንግስት ሀላፊዎች የምርመራው አካል እንዲድሆኑ እንጠያቃልን፣
3. ጉዳዩን ቀድሞ እንዲያውቁ የተደረጉት የክልሉም ሆኑ የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ግድያውን እንዲያወግዙ እንጠያቃለን፣
በኛ በኩል ይህንን የማጣራት ሥራ በሚመለከት ማገዝ የምንችለውን ሁሉ ለማገዝ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን። የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግሥት ይህን ማድረግ ሲችል ብቻ ነው ለሰላማዊ እና ፍትሀዊ ምርጫ ከልቡ የተዘጋጀ መሆኑን ማወቅ የምንችለው።
ለአባላችን ግርማ ሞገስ ለገሰ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና የትግል አጋሮች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

6 Comments

 1. Abiy Ahmed is so glad about whatever is happening in Ethiopia. In Ethiopia Abiy Ahmed the Masters degree in Business Administration scholar is happy to being the leader of a country where he can can easily sell majority of the working force for cheap labor, as heap as labor is in Ethiopia plus as forgiving as Ethiopia are nomatter what he do or nomatter he don’t do, he knows the best bet for him is to just go with the flow.ABIY AHMED AND ALIKE ARE TRAINED TO GO WITH THE FLOW BEFORE THEY KNEW HOW TO CRAWL . THEY FLOWED WITH TPLF WITH SHABIYA WITH ANY FLOW EVEN THEY ARE FLOLWING WITH SUDAN CURRENTLY.

  Many say there are displacements , violence , genocide , starvation , foreign troops attacking Ethiopians in their own territory , rape , lawlessness , almost all of the evils imaginable took place and are taking place in Ethiopia while under Abiy Ahmed , as long a s none of that are happenrng to him personally and to his flowers he planted or to his immediate family he is happy, what more he can ask for? He got more than he expected when he joined guerilla warfare at the age of 16-19. He doesn’t even know what exact age he was when he joined the guerilla warfare , now he is living unlike the others . He went through civil war and a lot of hardships personally by his choice willingly since he was a teen ager , as long as he don’t repeat volunteer slavery as he did since he was a teen ager he is happy. To escape volunteer slavery his best strategy is to enslave . HE EVALUATES HIS ADMINISTRATION BY STAYING OUT OF JAIL FOR ALL THE CRIMES THEY COMMITTED AND GOT AWAY WITH IT WITHOUT PAYING THE PRICE . THE MORE CRIME THEY COMMIT AND GET AWAY WITHOUT PAYING THE PRICE THE MORE THEYETHINK THEY ARE LIKED .WITHOUT COMMITTING CRIME AND CONSTANTLY GETTING FORGIVEN abiy isnhappy. If they don’t keep making
  times and they don’t keeo forgiven Don’T HAVE ANY OTHER SOURCE OF FEELING SAFE.

 2. ታዲያ ምን ይገርማል ይህ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ብዙ ሲባል ነበር፡፡ የሚያሳዝነው በቅስበተ ተስፋ እዚች አገር ዲሞክራሲያ ያብብ ይሆን ለልጆቻችንስ ተስፋ እናመጣ ይሆን ብለው የሚታገሉ እንደው ደማቸው ከንቱ ሲፈስ እና ለነዛ ተስፋ ናፋቂ ልጆች ሌላ ጠባሳና አሻራ ሲጣል ነው፡፡ ይህን ግድያ የፈፀመ አካል እኔ ነኝ ካላለ በኃላፊነት ላይ ያለ አስተዳደር እኔ ነኝ ተጠያቂ ማለት አለበት፡፡ አለባብሰው ቢያርሱ ሆኖ ነገሩ አሁን ጥይት የሚመዙ ነገ የለየለት መዘዝ እያመጡ እንደሆነ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ የዲሞክራሲ ምርጫ ምና ምን እየተባለ ለሚከፈለው መስዋትነት ምንም ዋስትና የለም መዘዙ ገና እንዲዚህ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ምርጫው የተፈለገበት ምክንያት እንደውም ሌላ ነው እየተባለ ነው፡፡ አረ እስከ መቼ … አለቸ ዘማሪዋ፡፡ ኢዜማም ለስለስ ያለ አቅዋም ነው ያለው፡፡ ምንም ዋስትና እኮ የላችሁም ከመንግስት በኩል ግድያው ሆን ተብሎ ዓላማ ስለሚኖረው ነው፡፡ ትግላችሁን መቀጠሉ ጥሩ ነው ግን ዋስናችሁን ለማስቀጠል ብዙ ከለላ ሊደረግላችሁ ይገባል፡፡ እውነት ከታሰበም መንግስት የጥበቃ ኃይል ሊመድብ ወይም ቢያንሱ ለእጩ ተወዳደሪዎች እና አመራሮች በራሳችሁ ጥበቃ ለመመደብ ግድ ማስፈቀድ አለባችሁ፡፡

  በጣም ይገርማል ይህቺ አገር ግን መቼ ነው የሚያልፍላት? ዲሞክራሲ ተብየውም መሰረት ሊጣልባት የሚችል ሕልም እየሆነ ነው ጊዚያዊ ስልጣ እና የግል ፍላጎት አራመጆች እያሉ ላመለኝ በሰማይ እየሆነ ነው የሚቀጥለው፡፡ ሌሎች ፓርቲዎችስ ምን እያደረጉ ነው? ድርጊቱን እየተቃወሙ ነው እነሱስ ምን ዋስትና አላቸው??? ይህ ዝምታ ገና ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ መዘዙም አስከፊ ነው የሚሆነው፡፡ አለዚያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ምርጫ አንፈልግም ሰለማችን ይቅደም የአስተዳደር ችግሮች ቀድመው ይጥሩ መባል አለበት፡፡ ብልፅግና ፓርቲን ለማስቀጠልም ከሆነ በምርጫ ሰበብ የሚባክን ሃብት፣ ገንዘብ እና ጊዜ ለዚህች ደሃ አገር ለልማት ቢውል ይሻላል እያለ ነው ይህ ህዝብ፡፡

  ዝምታው ምንድን ነው ???

  ሰላም ለአገራችን

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

 3. ታዲያ ምን ይገርማል ይህ ነገር ሊከሰት እንደሚችል ብዙ ሲባል ነበር፡፡ የሚያሳዝነው በቅስበተ ተስፋ እዚች አገር ዲሞክራሲ ያብብ ይሆን ለልጆቻችንስ ተስፋ እናመጣ ይሆን ብለው የሚታገሉ እንደው ደማቸው ከንቱ ሲፈስ እና ለነዛ ተስፋ ናፋቂ ልጆች ሌላ ጠባሳና አሻራ ሲጣል ነው፡፡ ይህን ግድያ የፈፀመ አካል እኔ ነኝ ካላለ በኃላፊነት ላይ ያለ አስተዳደር እኔ ነኝ ተጠያቂ ማለት አለበት፡፡ አለባብሰው ቢያርሱ ሆኖ ነገሩ አሁን ጥይት የሚመዙ ነገ የለየለት መዘዝ እያመጡ እንደሆነ ሊያስቡበት ይገባል፡፡ የዲሞክራሲ ምርጫ ምና ምን እየተባለ ለሚከፈለው መስዋትነት ምንም ዋስትና የለም መዘዙ ገና እንዲዚህ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ምርጫው የተፈለገበት ምክንያት እንደውም ሌላ ነው እየተባለ ነው፡፡ አረ እስከ መቼ … አለቸ ዘማሪዋ፡፡ ኢዜማም ለስለስ ያለ አቅዋም ነው ያለው፡፡ ከመንግስት በኩል እኮ ምንም ዋስት የላችሁም ግድያው ሆን ተብሎ ዓላማ ስለሚኖረው ነው እየተባለ ነው፡፡ ትግላችሁን መቀጠሉ ጥሩ ነው ግን ዋስናችሁን ለማስቀጠል ብዙ ከለላ ሊደረግላችሁ ይገባል፡፡ እውነት ከታሰበም መንግስት የጥበቃ ኃይል ሊመድብ ወይም ቢያንሱ ለእጩ ተወዳደሪዎች እና አመራሮች በራሳችሁ ጥበቃ ለመመደብ ግድ ማስፈቀድ አለባችሁ፡፡

  በጣም ይገርማል ይህቺ አገር ግን መቼ ነው የሚያልፍላት? ዲሞክራሲ ተብየውም መሰረት ሊጣልባት የሚችልበት ጊዜም ሕልም እየሆነ ነው ጊዚያዊ ስልጣን እና የግል ፍላጎት አራመጆች እያሉ ላመለኝ በሰማይ እየሆነ ነው የሚቀጥለው፡፡ ሌሎች ፓርቲዎችስ ምን እያደረጉ ነው? ድርጊቱን እየተቃወሙ ነው እነሱስ ምን ዋስትና አላቸው??? ይህ ዝምታ ገና ብዙ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ መዘዙም አስከፊ ነው የሚሆነው፡፡ አለዚያ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ምርጫ አንፈልግም ሰለማችን ይቅደም የአስተዳደር ችግሮች ቀድመው ይጥሩ መባል አለበት፡፡ ብልፅግና ፓርቲን ለማስቀጠልም ከሆነ በምርጫ ሰበብ የሚባክን ሃብት፣ ገንዘብ እና ጊዜ ለዚህች ደሃ አገር ለልማት ቢውል ይሻላል እያለ ነው ይህ ህዝብ፡፡

  ዝምታው ምንድን ነው ???

  ሰላም ለሀገራችን

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

 4. ዜግነቶች አገር-አቀፍ ከሆናችሁ ክሌሎች የቀደሙ አገር-አቀፍ ፓርቲዎች ጋር ለምን አብራችሁ አትሠሩም?ይህ ካልሆነላችሁ ደግሞ ለምን ከብልጽግና ፓርቲ ጋር አትሠሩም?በእኔ አስተያየት ፓርቲዎች ከሦስት በላይ መሆን የለባቸውም።ከሃምሳ በላይ ተበጣጥሳችሁ ከሕዝብ የመድረስ አቅማችሁ አያወላዳም!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.