የኢዜማ የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው አልፏል

የምርጫው ሂደት በዚህ መልኩ መጀመሩ አሳዛኝም፤ አሳሳቢም ነው። በገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ሲፈጸምበት የነበርው የኢዜማ አባል እና እጩ አቶ ግርማ ሞገስ በቢሸፍቱ ከተማ በጥይት ተመቶ መገደሉ እጅግ አሳዛኝ እና የምርጫውንም ሂደት ከወዲሁ ችግር ውስጥ የሚከት ነው። በቅርቡ በኦሮሚያ ብልጽግና በኩል በተጠራ የድጋፍ ሰልፍ ሌሎች የተቃዋሚ ድርጅቶች ስማቸው እየተጠራ ሲጠለሽ እና ሽብርተኛ ሲባሉ ምርጫ ቦርድ ድርጊቱን ያወገዘ ቢሆንም ሰሚ ያገኘ አልመሰለኝም።
ገዢው ፓርቲ ለዚህ ምርጫ በሰላም መጠናቀቅ ያለውን ቁርጠኝነት ከወሬ በዘለለ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች በቂ ጥበቃ እና ድጋፉን ከወዲሁ ማሳየት ይኖርበታል። ይህ እጅግ መጥፎ ምልክት ነው።
የወንድማችንን አቶ ግርማ ሞገስ ነፍስ ይማር! ለቤተሰቦቹ እና የትግል አጋሮቹ ለሆኑት የኢዜማ አባላት መጽናናትን እመኛለሁ።
Yared hailemariam
151150831 10224935801201321 3859647043802149036 o

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ ትላንት እሑድ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው አልፏል። የኢዜማ አባላት እና አመራሮች ይህን ዜና ስንሰማ ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል።

image 6ኢዜማ በአባሉ ላይ የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል በፅኑ የሚያወግዝ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን ሰብስበን እንደጨረስን ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።

ለግርማ ሞገስ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና የትግል አጋሮች ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን።

የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.