በምዕራብ ጉጂ ዞን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 የኦነግ ሸኔ አባላት ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደረገ

1613148458 1የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት የነበሩና የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 ግለሰቦች ሥልጠና በመወስድ ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉን የምዕራብ ጉጂ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ደስታ ኢታና እንዳሉት የዞኑ ህዝብ የጥፋት ቡድኑን አባላት አሳልፎ በመስጠቱ የምዕራብ ጉጂ ዞን ወደ ቀደመ ሠላማዊ እንቅስቃሴው ተመልሷል፡፡

የጥፋት ተልዕኮ በመቀበል ሲንቀሳቀሱ የነበረና የቀረበላቸውን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 የኦነግ ሸኔ አባላት በዞኑ ህዝብና በጸጥታ ሀይሉ የጋራ ጥምረት በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ አስረድተዋል፡፡

በይቅርታ ታልፈው በህግ የበላይነትና ሥነ ልቦና ዝግጅት ዙሪያ ሥልጠና ወስደው ከህዝቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል ብለዋል፡፡

ምክርና ተግሳጽ ተቀብለው ወደ ሠላማዊ ህይወት ለመመለስ ፈቃደኛ ባልሆኑት ላይ እርምጃ መወሰዱንና 350 የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የዞኑን መልካም ገጽታ ለማጠልሸት ሠላም እንደሌለ ተደርጎ የሚናፈሰው አሉባልታ ፍጹም ሀሰትና ከእውነት የራቀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከአባላቱ መካከል ገላ ዋቆ እና ፊሮምሳ ዋቆ በሚል በሁለት ስሞች የሚጠቀመው በሰጠው አስተያየት ኦነግ ሸኔ ከጥፋት በቀር ዓላማና ግብ የሌለውና ለህዝብ የማይጨነቅ በመሆኑ እራሱን ከቡድኑ ማግለሉን ተናግሯል፡፡

ሌላው የቡድኑ አባል ሞሮማ አሬሪ እና ኢማና ወባ በሚል ስሞች ይጠቀም የነበረው በበኩሉ ዓላማ ከሌለው የጥፋት ቡድኑ ጋር በመሆን ጊዜ ከማጥፋት ወደ ሠላም ተመልሶ የበደለውን ህዝብ ለመካስ እጅ መስጠቱን ተናግሯል፡፡

ህዝብና መንግስት ይቅር ባይ በመሆኑ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የጥፋት ተልዕኮ ለመፈጸም በጫካ ያሉም ወደ ሠላም እንዲመለሱ መልዕክቱን ማስተላለፉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

3 Comments

 1. እባብ ለመደ ተብሎ በጉያ አይያዝም፡፡
  የኦነግ ሸኔ ቡድን አባላት የነበሩና የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 ግለሰቦች ሥልጠና በመወስድ ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ መደረጉን የምዕራብ ጉጂ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
  ይህን ዜና ስመለከት የመጣልኝ ሃሳብ የመረጥኩት ርዕስነው በብዙ ሚሊዮኝ ብር የሚቆጠር የህዝብ ንብረት የዘረፈ በ20ዎች የሚጠጉ ባንኮች የዘረፈ በሺዎቸ የሚቆጠሩ አማራዎችን ገና ከመነሻው ጀምሮ ሲሰይፍ የኖረ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራና ሌሎች ህዝቦችን በመንግስት ውሰጥ ካሉ አባላት ጋር በመሆን እንደለፈናቀለና እንዳላሰደደ ዛሬ ሰላምን ተቀብሏል ተብሎ በመንግስት ውስጥ ያለው ኦነግ ጫካ ያለውን ኦነግ አሰልጥኖ ወደ ሰላም መለሰስኩኝ የሚባለው ለኛ ፌዝ ነው የታክቲክ ለውጥ ይመስለኛል ለኛ በመንግስት ስል|ጣን ላይ ያለው ኦነግ ነው በስልጣን ላይ ያለውም ኦነግ ነው፡፡
  ኦነግ ለዘረፈው ላፈናቀለውና ላፈሰሰው የሰው ደም ሳይጠየቅ በስልጠና ብቻ ወደ ህብረተሰቡ ገዳዮች እነዲቀላቀሉ ማድረግ ይህንንስ ስልጣን ለአንድ ዞን አስተዳዳሪ ማን ሰጠው ሺዎችን ያረዱ እጆች በፌዝ ስልጠና ወደ ህበረተሰቡ መቀላቀል ማለት ለህዝብ ህይወትና ንብረት የኦንግ ባለስልጣናት ያላቸውን ንቀት ያመላክታል፡፡
  ኦነግ በሰው ደም ያበደ ድርጅትነው ኦነግ የንጹሃንን ደም ባለማቋረጥ ላለፉት 50 ዓመታት ሲጎነጭ የነበረ የከሰረ ድርጅት ነው፡፡ የአንድ ዞን የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በቅርቡ እንኳን በወለጋ ፤ በመተከል ከሰው በላ ጉምዝ ታጣቂዎች ጋር በመሆን ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የአማራና የአገው ነገዶች ደም አልደረቀም ተበዳዮች አሁንም አልተቋቋሙም ይህ በዚህ እንዳለ ኦነግ ኦነግን አሰልጥኖ ወደ ህብረተሰቡ ኦነጎችን መቀላቀል እባብ ለመደ ተብሎ በጉያ መያዝነው፡፡
  የኦነግ አዛውንት መሪዎች በኋላቸው የህጻናት የሴቶች የአዛውንቶች ደም እየጮኸ እያሳደደ መቅኖ እያሳጣቸው ነው፡፡ዳውድ ኢብሳ፤ገላሳ ዲልቦ፤ሌንጮ ለታ፤ ሌንጮ ባቲወዘተ የጊዜ ጉዳይ ነወ እንጂ በሰፈሩት ቁና ይሰፈራሉ ቂም አይበሰብስም፡፡
  ላስታውስ የምፈልገው ከእባብ እንቁላል አርግብ አየፈለፈልም ኦነግና ሰላም አይተዋወቁም ኦነግ እባብ ነው መፍትሄው እባብን እንደ ጥንቱ ጭቅላቱን በዱላ ነው፡፡

 2. እባብ ለመደ ተብሎ በጉያ አይያዝም፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.