ዓምላክ ሆይ “የሚሰማ’ን” ስጠን? – ማላጂ

Ethiopia 1 ዓምላክ ሆይ “የሚሰማ’ን” ስጠን?  ማላጂአገራችን ብዙ እንደ ንጋት ኮከብ የደመቀ ስብዕና ያላቸዉ እና የነበራቸዉ  ከደቂቅ አስከ ሊቅ ባለቤት ብትሆንም ምን ይዞ መጣ ፤ ምን አሉ የሚል እንጅ ለህዝብ እና ለአገር አንድነት  የሚበጅ ነገር መስማት ሆነ ማሰማት የሚችል ዉግዝ የሆነባት ምድር እና አገር ከሆነች የዓመታት ፖለቲካዊ ባህል ሆኗል፡፡

ምን ይዞ ፣ ምን ተባለ እንጅ ለህዝብ እና አገር ጠቃሚ ነገር ምን ይባላል፣ ምን ይሆናል ቀርቶ ከተረሳ ሰነባብቷል፡፡

እንዲያዉም በአገር አንድነት ስም ልናገር እንጅ ንገሩኝ ባይ ፤ የሚናገር እንጅ የሚናገረዉን የሚኖር መጥፋቱ ነገሩን ከድስት ወጥቶ ለሳት አድርጎታል፡፡

አገራችን የዘመናት አንቱ የሚባሉ ተወዳጅ መሪዎች በደስታም ሆነ በችገር ጊዜ ከህዝብ ፊት የሚገኙ ማንታቸዉ እና መሰረታቸዉ ህዝብ እና አገር እንጅ ሌላ ያልነበረ በህዝብ ተወደዉ እና ተከብረዉ በፍቅር ኑረዉ ፤በፍቅር አልፈዉ ፤በፍቅር በታሪክ እና ትዉልድ  ሲዘከሩ ኖረዋል ፤ይኖራሉ፡፡

ምግባር እና ተግባር የጋራ መገለጫቸዉ ከሆኑት ዉስጥ አፄ ቴወድሮስ፣ ዕምየ ሚኒሊክ፣ ደጃች ተድላ ጓሉ፣ ደጃች/ራስ በላይ ዘለቀ ፣ የቀድሞዉ መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለ ማርያም …….የመሳሉትን እና ዛሬም በህይወት ያሉትን መጥቀስ ይቻላል ፡፡

ከአገር አንድነት  እና ከህዝብ ጥቅም በላይ የምንፈልገዉ  ስልጣንም ሆነ ተድላ የለም ያሉ እና የሚሉ መኖራቸዉን መጥቀስ ይቻላል ፡፡

እዚህ ጋ አንድ ትልቅ አባት ስማቸዉን መጥቀስ የማልፈልግ ግን ሳላመስግን የማላልፋቸዉ እና ኗሪነታቸዉ በጅማ ከተማ የሆኑትን አባ……. ያሉኝን ልጥቀስ፡፡

ቦታዉ ኢሉባቡር ክፍለ ሀገር በ2007 ዓ.ም. ሰኔ ወር ነዉ …..ብዙ ስለ ግል ፣ ስራ እና ዐጠቃላይ ህይተዋቸዉ ብዙ በአንዲት ምሽት ማሻ ዙሪያ አወጉኝ ፡፡

መቸም እኛ ኢትዮጵያዉያን እንጀራ ብቻ አይደለም የሚርበን ፤ ዕዉነትም ከምንም በላይ ተርበናል እና …..እንዲያዉ ስለ ቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም በፊት) እና ሊቀመንበር  ምን ያዉቃሉ አልኳቸዉ ፡፡

በአጋጣሚ አሉኝ  በጋምቤላ የባሮ ድልድይ ምረቃ እና በወለጋ ከተለያዩ የአገሪቷ ክፍል በተፈጥሮ አደጋ ለተፈናቀሉ(በድርቅ) ዜጎች መንደር ምስረታ ተሳትፊያለሁ አሉኝ …..ቀጠሉ እናም የወቅቱ የአገሪቷ ርዕሰ ብሄር ሊ/መንበር መንግስቱ ኃይለማርያም ካስተላለፉት መልዕክት ዉስጥ ፡

 • በጋምቤላ ባሮ ድልድይ ምረቃ ስነ ስርዓት ማብቂያ በጀልባ ወደ ደቡብ ሱዳን (የያኔዋ ሱዳን/ካርቱም) እየቀዘፉ በበትረ ስልጣን ወደ ሱዳን እየጠቆሙ ከእነዚህ ለአፍታም ዓይናችሁን  አታንሱ ፤ድንበራችሁን ጠብቁ ፣በአንድነት እና በህብረት ንቁ ብለዋል አሉኝ ፤
 • በወለጋ የመንደር መስረታ ጉብኝት በነበረ ስነ ስርዓት በመጀመሪያ ዙር ጉብኝት ሊ/መንበር መንግስቱ ሲጎበኙ የምግብ ፣አልባሳት እና መኖሪያ ቤት ችግር በእጅጉ አሳኝ በሚባል ሁኔታ ተመልክተዉ አስቸኳይ ማስተካከያ እንዲደረግ አሳስበዉ እንደነበር እና በዳግም አስቀድሞ በተሰጠ መመሪያ ያለዉን ለዉጥ ለማየት በመንግስት በተያዘ የጊዜ ሠሌዳ ሲጎበኙ የባሰዉን ዕንግዶች የለበሱት ጨርቅ በላያቸዉ አልቆ፣ ጎናቸዉ ተጠብቆ እና አጥንታቸዉ ገጦ ዕርዳታዉ የዉሃ ሽታ ሆኖ ሲያገኙት በሀዘን እና በቁጭት ዕንባቸዉን እያወረዱ ከዚህ ህዝብ ቀምተን የምንበላ ተባዮች የራሳችንን መጥፊያ እያዘጋጀን መሆናችንን እናዉቃለን ወይ ማለታቸዉን በጊዜዉ የነበሩት እኝህ እማኝ አባት ያሉኝ የምረሳዉ አይደለም ፡፡

ይህን ልበል እንጅ ከዚህ በላይ ህዝባዊ እና ብሄራዊ መሪ ብዙ ይጠበቅበታል ነገር ግን በዘመናችን የህዝብን እና የአገርን ሰቆቃ በአካል ማየት እና መረዳት አይደለም መስማት የሚፈልግ ማጣት ዕዉነት በአገራችን የሚሰማ አለ ወይ አስከማለት ያደረሰን ዕጅግ ብዙ ብዙ ፈርጀ ብዙ ክስተቶች እና ሁነቶችን ስናይ  ዓምላክ ሆይ “የሚሰማ ”ስጠን ከማለት ዉጭ ምን እንሁን እንላለን ፡፡

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ”!!
የሚሰማ (“ ሰ” ሲነበብ ጫን፤ ለቀቅ )

3 Comments

 1. መንግስት የሱዳን ጦር ወረራን በማስቆም ረገድ በተግባር መሬት ላይ ባለው እንቅስቃሴው ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲው ረገድም ውጤታማ ስራ እየሰራነው ለማለት እንደሚቸግር ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አማራ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገረው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር አመራር አርበኛ ክፈተው አሰፋ በቅጽል ስሙ ዶክተር ክፈተው የአካባቢው ተወላጅና በቀጠናውም እስከ ኤርትራ በርሃ ድረስ ሲንቀሳቀሳቀሱ ከነበሩት ታጋዮች መካከል አንዱ ነው። አሁን ላይም የሱዳን ጦር ወረራ መፈፀሙን በቅርብ ርቀት ሆኖ ማረጋገጡንና ሱዳን እየሄደችበት ላለው አደገኛ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ በኩል ተመጣጣኝ የሚባል ምላሽ መስጠት አለመቻል አሳሳቢ መሆኑን ይናገራል። የኢትዮጵያ መንግስት የሱዳን ጦር ወረራን ከማስቆም አኳያ መሬት ላይ በሚሰጠው ምላሽ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲው ረገድም ጠንካራ ስራ አለመስራቱን ከሱዳን ጦር የእለት ከእለት የተስፋፊነት እንቅስቃሴ መረዳት እንደሚቻል ነው አርበኛ ክፈተው የተናገረው። ሱዳን ከበፊቱ በተለየ መልኩ የግዛት ጥያቄ አለኝ በሚል ሽፋን ወረራ የፈፀመችው ኢትዮጵያ ተዳክማለች ብላ ከማሰብ እንደሆነ እና ብቻዋን ሳይሆን ከትሕነግ ርዝራዦች እና ከግብፅ ጋር ሆነው እየተንቀሳቀሱ ስለመሆኑ ነው አርበኛ ክፈተው የተናገረው። ከቋራ እስከ ማይካድራ ልጉዲ ድረስ ባለው ቀጠና ውስጥ ወረራ በመፈፀም ባለሀብቶችንና አርሶ አደሮችን በማገት፣በማፈናቀልና በመዝረፍ ላይ ትገኛለች ያለው አርበኛ ክፈተው ከአስር ሽህ ያላነሰ የትሕነግ ኃይልን እያሰለጠነችና እያሰማራች ስለመሆኑ መረጃ አለን ብሏል። ሱዳን በተቆጣጠረችው ሰፊ የኢትዮጵያ መሬት ላይ ካምፕ እየመሰረተችና የመሰረተ ልማት ግንባታ እየጀመረች፣ ድልድይ እየሰራች ነው፤ የሰፈራ ፕሮግራም ለማከናወንም በዝግጅት ላይ መሆኗ ችግሩን የበለጠ ውስብስብ እያደረገው ነው ሲል አክሏል። ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት እየሄደበት ያለው እንቅስቃሴ ደካማ ነው ያለው አርበኛ ክፈተው መንግስት ከዚህ በላይ መዘናጋቱን ትቶ በአስቸኳይ እልባት ለመስጠት ካልቻለ ቀጠናው ሰላማዊ ሆኖ ይቀጥላል ለማለት ይቸግራል ::

  • እግዚአብሄር ለአረመኔ ጉልበት እንጂ ኃይል አይሠጥም ፡፡
   ኢትዮጵያ ሀገራችን ቀደምት ህዝብ ስልጣኔና መንግስት የተመሰረተባት ሀገር ናት ፡፡ዛሬ በየመንደሩ ራሱን ያጠረና አስተሳሰቡና አረዳዱም በዚህ የተገደበ ትውልድ ሳይፈጠር ጠላተ ተበጅቶለት በተለይ አንድ የሕዝብ አካልን እነደጠላት እነዲቆጥርና አሳዶ እነዲያርደው ተኮትኩቶ ብቅ ያለ አደገኛ ትውልድ ህልው ሆኗል እያሰደደም እያረደም ይገኛል መንግስታችንም የዚህ ስራ ውጤት ነውና ነገሬም አላለውም፡፡
   ግጭቶች በተፈለጉ ጊዜ እዚህም እዚያም እየተለኮሱ የተወሰኑና በጠላትንት ተፈርጀው የተነጣጠረባቸው የአማራ ነገድ አባላት በማያውቁት ሁኔታ ግፈኞች በፈጠሩት የሀሰት ትርክት የዘር ማጥፋት /ማጥራት ወንጀል አአተፈጸመበት ይገኛል መንግስት ተብዬውም ችግሩን ከመፍታት ይልቅ ማባባስ ከማስቆም ይልቅ እንዳለየ እንዳልተፈጸመ የማስመሰልና አለም አቀፍ ህብረተሰብ እነዳ|ያውቅ የማድበስበስ ስራ በመከወን ላይ ይገኛል፡፡ ከህበረተሰቡ ዘንደ ጫና የበረታ የመሰለው ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ተከስቶ እኛ እንፈርሳለን እንጂ ኢትዮጵያ አትፈርስም ይለናል በዚህ ወቅት አራጆች ለሌላ ተልዕኮ የሚዘጋጁበትና ተልዕኮ ተቀብለው ለጥፋት የሚሰማሩበት ጊዜነው ቢያንስ ህዝቡን ማዳን ባይቻል በየሰፈሩ ተቧድኖ ራሱን እነዲለከላከል ማብቃት የመንግስት ስራ ነበር ነገር ግን ይህ መንግስተ ከተሰራበት መንገድ ውጭ ለህዝብ ጥቅም እንዲያስብና እንዲቆም መመኘት ጅልነት ነው፡፡ ምክንያቱም መንግስት የተባለው የጥቂት አክራሪ ፕሮቴስታንቶቸና የአክራሪ ሙስሊሞች ስብስብ የተማሩ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታይ ምሁራን ከየትኛውም መንግስታዊ ስልጣን ላይ በዘዴ እየተገለሉ ይገ|ኛሉ፡፡
   ባንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍ ሲሰሰባስቡ በነበረበት ወቅት አድጧቸው ኦረቶዶክስ ሀገር ነች ብለውን ነበር እውነትም ሀገር የሰራች ፤ፊደል ቀርጻ ታሪክ የቀመረች ፤ መንግስት ያሰለጠነች፤ሀገር ነች ለዚህ ውለታዋ እንደ ጠላት ተቆጥራ እየተሳደደች እየተቃጠለች ምዕመኖችዋ በግድ ሀይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ቢገደዱም እየበዙ እየጸኑ ይገኛሉ፡፡
   ምክንያቱም የአክራሪ ፕሮቴስታነትና የአክራሪ ሙስሊም ባለስልጣናት ጉልበት የገለባ እሳትነው ቦግ ብሎ ይጠፋል በየጊዜው የሚቀጠቀጡ ህዝቦች የኋላኋላ አሸናፊዎችና ጠንካሮች ይሆናሉ ጠላቶቻቸውን ያደባያሉ በጀርመን ናዚዎች የተጨፈጨፉ እስራኤሎች ጥንካሬንና እነዲሁም ጠላቶቸ ቻቸውን አሳደው የቀጡበትን መንገድ ያጤኗል፡፡
   ስለዚህ ከሰሩት ቤት እንዲወጡ ካቀኑተ ሀገር እንዲለቁ ካሰለጠኑት መንግስት እንዲገፉ እየተደረጉ ይገኛሉ ይህ ሁሉ ውለታ ቢስ መሆን ነው ፡፡ ዛሬ አንድ የህዝብ አካል በግፈኞችና በአረመኔዎች ተገፍቶ የመጥፋት ጠርዝ ላይ ይገኛል ስለዚህ ህዝብ ለመቆርቆር አማራ መሆን አያስፈልግም ይህ ሰው የመሆን ጥያቄ ነው፡፡
   በዚህ መልክ ወደ ስልጣን የመጡ ኃይሎች ጉልበት እንጂ ልብ አንገት እንጂ የሚያመዛዝን ጭንቅላት የላቸውም በመጨረሻም ይጠፋሉ እግዚአብሄር ለኒህ አረመኔዎች ጉልበት አንጂ ኃይል አይሠጥም በተበደሉ ህዝቦች ክንድ ይደቃሉ ምክንያቱም እውነትና ኃይል ከነዚህ ጋር ነው፡፡ከአለም የግፍ ታሪኮች ፍጻሜ የተማርነው ይህ ነው መፍትሄው በኃይል ገፈኞችን ማስወገድ ነው፡፡
   ለዚህ ለግፈኛና ለበቀለኛ መንግስት ይቀጥልልን ብለን የድጋፍ ሰልፍ መወጣት በግፍ የታረዱ ወንድም እህቶቻችን የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ ተጨማሪ ወንድም እህቶቻችን እነዲጨፈጨፉ መፍቀድ ነው፡፡
   ስለዚህ በምርጫው ብንሳተፍም የዚህን መንግስተ አባላት በካርዳቸን ማስወገድ ይጠበቅብናልሁሉም ግፍን የሚጸየፍ ዜጋ በጋራ ተሠልፎ ግፈኞቸን በድምጹ ሊያንበረክክና ከስልጣነ ማባረር ይጠበቅበታል፡፡
   የተበታተነና በነፍጥ ያልተደገፈ ትግል የትም አይደርስም እራሳችንን በራሳችነ ተደራጅቶና ታጥቆ ግፈኞችን ማዋረድነው ሳያጠፉን እናጥፋቸው ሰይገድሉን እንፋለማቸው የሚታደገን መንግስት የለንምና ለራሳችን እራሳችን እንወቅ፡፡ በመጨረሻም ድል ለተበደሎት ነው ጉልበተኛው ጎልያድ በብላቴናው ዳዊት ጠጠር ወድቋል ፡፡

 2. ለግፈኛና ለበቀለኛ መንግስት ይቀጥልልን ብለን የድጋፍ ሰልፍ መወጣት በግፍ የታረዱ ወንድም እህቶቻችን የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ ተጨማሪ ወንድም እህቶቻችን እነዲጨፈጨፉ መፍቀድ ነው፡፡
  ስለዚህ በምርጫው ብንሳተፍም የዚህን መንግስተ አባላት በካርዳቸን ማስወገድ ይጠበቅብናልሁሉም ግፍን የሚጸየፍ ዜጋ በጋራ ተሠልፎ ግፈኞቸን በድምጹ ሊያንበረክክና ከስልጣነ ማባረር ይጠበቅበታል፡፡
  የተበታተነና በነፍጥ ያልተደገፈ ትግል የትም አይደርስም እራሳችንን በራሳችነ ተደራጅቶና ታጥቆ ግፈኞችን ማዋረድነው ሳያጠፉን እናጥፋቸው ሰይገድሉን እንፋለማቸው የሚታደገን መንግስት የለንምና ለራሳችን እራሳችን እንወቅ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.