እምበር ተጋዳላይ… እምበር ተንከባላይ… በዲሲ አስፋልት ላይ !! – ወይራው እርገጤ

abiy 1በገሀዱ አለም ውስጥ በማንም መሻት የማይለወጥ አንድ ነገር አለ፡፤ እርሱም “እውነት” ነው፡፡ ወያኔና ኦሮሙማ በየተራ ታላቁዋን ኢትዮጵያን በየራሳቸው ንባብና ምልከታ ሊፈጥሯት ብዙ ሲጥሩ ተመልክተናል፡፤ አንደኛው ከሽፎበት ተወግዷል፡፡ ሁለተኛውም የቁልቁለቱን ጉዞ ተያይዞታል፡፡ እስካሁን ኢትዮጵያ አለች፡፡ወደፊትም ትኖራለች፡: ይህ “ኢትዮጵያ ትኖራለችና አትፈርስም” ወዘተ አባባል በተለይ ተዘውትሮ የሚሰማው ከኦሮሙማው ቁንጮ ከአፈ-ቅቤው ልበ-ጩቤው አብይ አህመድ ነው፡፤ አብይ ኢትዮጵያ የሚላት ኦሮሙማ በራሱ አምሳያ የሚሰራትን አድሲቷን የኦሮሙማ ኢትዮጵያን ማለቱ ነው፡፡ የሁላችን ኢትዮጵያ ግን ተሰርታ ያደረች አገር ነች፡፡ ሽህ አመታትን ያስቆጠረች፡ ረዥም አንጸባራቂ አኩሪ ታሪክ ያላትና መላው አለም የሚያውቃቸው የራሷ የሆኑ እውቅና ዲንቅ መለያዎች ያሏት የአያሌ ጀግኖችና ብሄር ብሄረሰቦች አገር ነች፡፤ እውነቱ ይህ ነው፡፤

እራሳቸው በጫሩት ጦርነት ከሞት ተርፈው አሁን በህይዎት ያሉት ወያኔዎች በመቃብራቸው ላይ የሚጻፈውን ነውረኛ ታሪክ ቁጭ ብለው እያዩት ነው፡፤ ኦሮሙማም ይህንኑ ጽሁፍ እያነበበው ነው፡፡ነገ በራሱ መቃብር ላይ በምጸት እንደሚነበብ ግን አላስተዋለም፡፡ ወያኔ ሞቶ ከተቀበረ በኋላ የወያኔ ርዝራዦች በአለም አቀፍ የተመረጡ ከተሞችና መድረኮች እየጮሁ ይገኛሉ፡፡ ለወያኔ ርዝራዦች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦር አባላት በዘር ተለይተው በወያኔ መታረዳቸው ምናቸውም አይደለም፡፡ በማይካድራ አማራዎች በመሆናቸው በመታወቂያ እየተለዩ ታርደው በአንድ ጉድጓድ መቀበራቸው ለእነርሱ ምናቸውም አይደለም፡፤ ርዝራዦቹ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል በቢቢሲ፡ በራሳቸው ትግራይ ሜዲያ ሀውስና፡በኢትዮ ፎረም በኩል…ወዘተ የውሸት ቁጥሮችን እያጣቀሱ ይህን ያህል ህዝብ ተሰደደ፡ ሴቶች ተደፈሩ ቤቶችና መንደሮች ተቃጠሉ፡ ተደመሰሱ፡ … ወዘተ እያሉ ያላዝናሉ፡፡ ፈረንጆችንም ያስጮሀሉ፡፡ በውጭ አገራት በየአደባባዩ በሰልፍ በየአስፋልቱ በእንክብሎሽ ድራማ እየሰሩ ለቅሶና ሙሾ ያወርዳሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የኖርዌይ ድርጅት፡ የእከሌ የሰብአዊ መብት ድርጅት፡ የኤውሮፓ ምክር ቤት፡ የተባበሩት መንግስትታ የስደተኞችና የምናምን ቢሮ ..ወዘተ እንዲህና እንዲያ ብሎ ኢትዮጵያን አወገዘ፡ ከሰሰ፤ አስጠነቀቀ እያሉ ያናፋሉ፡፤ ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ወደ እነርሱ ቅዠት እንዲቀለበስላቸውም ሀፍረተቢሶቹ የወያኔ ርዝራዦች በአንደበታቸው የአሜሪካ መንግስትና የጸጥታው ምክር ቤት “”እንዲህ እንዲህ”” ማድረግ አለበት ብለው ምኞቶቻቸውን በቅደም ተከተል ዘርዝረው ሲያቀርቡ አይሰቀጥጣቸውም፡፡ እነማን መሆናቸውንና በወንጀልና በዝርፊያ የሚፈለጉ መሆኑን ረስተውታል፡፡ እነርሱ እኮ ወያኔበማንኛውም ሰአት የትም ቦታ ምንም ነገር ማድረግ ሲችል በነበረበት ጊዜ ያዩት እውነታ፡ የለመዱት ነገርና ያደጉበት ባህርይ ስለሆነ ከእውነቱ አለም ተለይተው የሚገኙ ናቸው፡፡ ማወቅ ያለባቸው ግን አንድ ሀቅ አለ፡፡ባንዳነት የእነርሱ ውርስ እንጅ የተቀረው የጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ መገለጫ ስላልሆነ ማንም የውጭ ሀይል ኢትዮጵያን ቢበዛ እርዳታና ብድር ከማስቆም በስተቀር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችል እቅጩን ይወቁት፡፡ ርዝራዦቹ አውቀው የዘለሉት አንድም ሌላ ሀቅ አለ፡፡ የትግራይ ህዝብ ማንነቱን ያውቃል፡፤ ለአያሌ አመታት በሰው በላው ወያኔ የተነዛበትንም ውሸት አይረሳም፡፤ እነማን ሲጠቀሙ እንደነበረና እነማን የበይ ተመልካች ተደርገው እንደቆዩ ያለፈበት ስለሆነ ሊረሳው አይችልም፡፤ በራሱ ህይዎት በልጆቹ ህይዎትና በጎረቤቶቹ ህይዎት ላይ ወያኔ የቱን ያህል የከፋ ቁማር እንደተጫወተ ከህዝቡ ከራሱ ወዲያ የሚያውቀው የለም፡፡ኩሩ ኢትዮጵያዊ ብቻም ሳይሆን የኢትዮጵያ መሰረትም የሆነ ህዝብ ነው፡፤ ይህ ህዝብ ወያኔ በጫረው እሳት ጦርነት በመፈጠሩ ዛሬ ላይ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደገባ ማንም ሰው አይስተውም፡፡ማንም ኢትዮጵያዊ ችግሩን በየአቅሙ መጋራትም አለበት፡፡

ከወያኔ በአምሳያው የተፈጠረውን ኦሮሙማን በሚመለከት አንድ እውነታን ላንሳ፡፡ ኦሮሙማ የወያኔ የእጅ ስራ ውጤት ስለሆነ ኢትዮጵያን ወደጥፋት እያምዘገዘጋት ያለ ነውረኛ ድርጅት ነው፡፤ ከወያኔ የከፋ፡የተዋረደና የዘቀጠ የኬኛዎች መንጋ ነው፡፤ ታላቋን ኢትዮጵያንና ታላቁን ፡ጨዋውንና ደጉን የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ሁሉ የበታችነትና ውርደት ዳርጎታል፡፡ ምሳሌ ለብሄራዊ ጦሩ በወያኔ መታረድና ለሱዳን አሳፋሪ ወረራ ያበቃው አንድም የኦሮሙማው ቀንደኛ መሪ የአብይ አህመድ ስውር አላማ ሲሆን ሁለትም ራሱ አብይ አህመድ በዘር ለተቋቋመ ድርጅት ብቻ እንጅ ኢትዮጵያን ለምታክል ታላቅ አገር መሪነት ብቁ አለመሆን ነው፡፡ አብይ አህመድ የሚጠየቅባቸው ብዙ ወንጀሎች ቢኖሩም ከሁሉም ወንጀሎቹ ልቆ ወደፊት ቀን ሲወጣና ነጻነት ሲመጣ የሚያስጠይቀው ግን የጦሩ ነጻ እንቅስቃሴ በወያኔ ሲታገድ ወድያዉኑ እርምጃ ባለመውሰዱ ምክንያት አሁን ለተፈጠረው ጦርነትና ውድመት መነሻ የሆነው የረቀቀ ምስጢርና እንቆቅልሽ ውናው ወንጀል ነው፡፡ አብይ አህመድ ወደፊት የሚያስጠይቀው ሌላም ሁለተኛ ከባድ ወንጀል ለመስራት በዝግጅት ላይ ነው፡፤ ይህም አማራው በደሙ ያስመለሳቸውን የራያ ወላቃይት ጠለምትና ጠገዴ  የደም መሬቶቹን ለትግራይ ብልጽግና ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆኑ ነው፡፡ ይህ ለአገሪቱም ለህዝቡም ለራሱ ለአብይ አህመድም የመጨረሻው መጨረሻ ይሆናል፡፡ የቤንሻንጉሉ አሰቃቂ ፍጅት እየተንቦገገ እያለና ለአዲስ አበባ ከተማ ስልቀጣ የተቀበረው ሴራና የጊዜ ፈንጅ ሊፈነዳ የተቃረበበት ችግር ሳይፈታ ይህንን ተጨማሪ ወንጀል መፈጸም ለኦሮሙማ የኬኛዎች ስብስብ ግድ ላይሰጥ ይችል ይሆናል፡፡ ኦሮሙማ ለኢትዮጵያ ምንም ስላልሆነ ማለት ነው፡፡ ከህዝቡም ወገን ያለቀው አልቆ የሚተርፈው ይተርፋል፡፡ አገሪቱም ፈራርሳ በዚያው ልትቀር ወይንም እንደገና ልትመለስም ትችል ይሆናል፡፡ ይህ የታሪክ ጠባሳ እንዳለ ሆኖ ለአብይ አህመድ ለራሱ ግን ምንጊዜም የትም ቢሄድ ሊያመልጠው የሚችለው ወንጀል አይደለም፡፡

 

1 Comment

 1. ወይራው፦
  የገለጥከው በሙሉ እውነትን የተላበሰ ነው፡፤ በተለይ ወያኔ በአገሪቱ ወጣቶች ስለ አገር፡ህዝብ፡ ብሄርና ብሄረሰብ ምንነት ትርጉም ላይ የተንሸዋረረ እምነት ይዘውና ኢትዮጵያዊነትን ጠልተው እንዲያድጉ አድርጓቸዋል፡፡ በጥቅሉ በህዝቡ ውስጥ በታሪክና በአገር ፍቅር አረዳድ ላይ አስተሳሰብን በመበረዝ ያደረሰው ጉዳት እጅግ በጣም ከባድ ስለሆነ በቶሎ ሊስተካከል አይችልም፡፤
  ይታያችሁ አብይ አህመድ የደረሰው በእነደዚህ አይነቱ ምስቅልቅል ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ በዚያ ላይ ራሱ የመጣበትም የኦሮሞ ብሄረሰብ የታሪክ አረዳድዱ ፍጹም የተበከለ ስለነበረ በአንዴ ሊቀየር አይችልም፡፤ረዥም ጊዜ ይወስዳል፡፡ እውነቱን እናፍርጠው ካልን እንኳን ብዙ ጸረ ኢትዮጵያነትና ጸረ አንዲነት ፖለቲካው በወያኔና በኦነግ ብዙ የተሰበከው የኦሮሞና የትግራይ ወጣት ቀርቶ ራሱ አብይ አህመድም ከብከላው የጸዳ መሆኑ እጅጉን ያጠራጥራል፡፡
  ይህ እየጠራ ሲሄድ፡ አገሪቱም በትክክለኛው የፌደራሊዚም መሰረት ላይ ተመስርታ ዲሞክራቲክ በሆነ አመራር በወጥነትና ያለአድሎ አንድነቷን አስከብራ በነጻ የህዝብ ምርጫ መተዳደር ስትጀምር ሁሉም ነገር መልክ ይይዛል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ ይህ እውነታ አብይ አህመድን ይጠፋዋል የሚል ብዥታም የለኝም፡፡ አብይ አህመድ በውስጡ በተለይ ከኦሮሞዎቹ ጓዶቹ በኩል ፋታ የማይሰጡና እማያስተነፍሱ ችግሮች ያሉበት ይመስለኛል፡፡ ይህንን ራሱ እንደተነከረበት በዘዴ ራሱ ይፍታው፡፤
  አብይ እድሉን ያኔ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ሆ ብሎ የደገፈው ጊዜ በትኩሱ ሁሉንም ጋሬጣዎችን ማስወገድ ይችል በነበረበረበት ወቅት ሳይጠቀምበት አምልጦታል፡፡ ያ ወቅት በድክመቱ አለፈው፡፡ እድሉ አመለጠውና አሁን ሁሉም ነገር ለውድቀት ተዳረገ፡፡ ራሱ በገባበት የተሳሳተ ምርጫ የእነ ጃዋርና የእነ ዳውድ ኢብሳ መጫወቻም ሆነ፡፤ ወያኔም አብይ ጭንቅላት ላይ ጎጆ ሰራበት፡፤ ያ ሁሉ ግን አለፈ፡፤ በኪሳራ፡፡ ባልተፈለገ መስዋእትነትና በታሪክ ጠባሳነት ወደር ሳይገኝለት ማለት ነው፡፡
  እውነቱን ለመናገር አብይ ብልጥ ሰው ከሆነ ሁሉንም ልክ ማስገባት የምችልበት ጊዜ ላይ አሁን ደርሷል፡፡ ይህ የማይደገም ሁለተኛ እድል ነው፡፡ በተለይ የወያኔ የሰሜኑን ጦር አድብቶ በተኛበት ማረድና ይህንን ያደረገውንም የወያኔ ግብዝ ሀይል አፈር ከድሜ የማስገባቱ የህዝብና የጦሩ ቁጣና እርምጃ የጠቅላላ ህዝቡን ድጋፍ ያስገኘለት ስለሆነ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ለድጋሜ ውድቀት በተለይም ራሱን ለእነዚህ ሁለት ሀይሎች ዳግም መንሰራራት አሳልፎ መስጠት የለበትም፡፤ ምርጫው አሁንም የራሱ ነው፡፤ በተለይ የኦሮሞ ብልጽግና ውስጡም ውጩም በኦነግ ሰርጎገቦችና ከኦነግ ያልተላቀቀ አስተሳሰብና እምነት ያላቸው ሰዎች የተዋጠ መንጋ ስለሆነ አብይ ራሱን ከዚህ መንጋ በስልት እያራቀ ካላጸዳ በስተቀር ይዘዉት ገደል ይገባሉ፡፤አገሪቱንም እንዲሁ፡፡
  ከዚህ የተለየው ሌላው የብዙወች እይታም አለ፡፡ ይህም አብይ እራሱ የዚህ መንጋ የበላይ ነው የሚለው ነው፡፡ ይሀው እውነት ሆኖ ይወጣና ሀቁ በቅርቡ ይታያል፡፡ እስከዚያው ግን በዚህ <> ወቅት ሰውየውን ትንሽ ጊዜ እንስጠው ከሚሉት ወገን ነኝ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.