የአዲስ አበባ የከተማ ቦታ ጠፍቶ ያልተገኘው መሬቱ ከሀገር ውጭ ሄዶ ይሆን? – አስማማው ዓለሙ

አስማማው ዓለሙ ([email protected]

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በአዲስ አበባ የመሬት ወረራ ቅርምት ውስጥ እጇ እንደሌለችበትና እንደ በይ ተመልካች ወይም እንደ ሪፖርተር ጋዜጠኛ በዝርፊያ ስለጠፋ የከተማ መሬትና እንደ እንጉዳይ ያለ ባለቤት በቅለው ስለተገኙ ኮንዶሚኒይም ህንጻዎች ጉድ የሚያስብል ሰበር መረጃ ነግረውናል፡፡ ይሁን እንጂ ሃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለበት አካል ለጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሄና ሁነኛ መልስ ከመስጠት የተቆጠቡት ወ/ሮ አዳነች መልሰው በአሽሙር “እና ምን ይጠበስ” እንደማለት አላግጠዋል። ከወ/ሮ አዳነች አበቤ ውጪ ስለ አዲስ አበባ የመሬት ወረራና ቅርምት የሚያወራና ማብራሪያ የሚጠይቅ በህወሐት/ ኢህአዴግ ዘመን “ጸረ ልማት” ይባል እንደነበር ሁላ አሁን በተረኛው ኦነግ “ብልጽግና” ደግሞ “ጸረ ብልጽግና” መባል ብቻ ሳይሆን ሽብርተኛ/ወንጀለኛ ተብሎ ዘብጥያ ያስወረውራል፡፡

እንደው ይህን ያክል የከተማ ቦታ ጠፍቶ ያልተገኘው መሬቱ ከሀገር ውጭ ሄዶ ይሆን? ብለን የእብደእት ጥያቄ እራሳችንን እንድንጠይቅ ኮንቪንስም ኮንፊውዝድም አድርገው ወደን ግራ መጋባት የፈለግነውን ግራ አጋብተውናል። ለአዲስ አበቤ ያራዳ ልጆች ግን ዘረፋውና በተረኝነት ስሜት የደፈረሰው ፍትህ እንኳን በህይወት ያለ የሞተ ዳኛ እንደሚቀሰቅስ ስለሚያውቁ ለባልደራሱ እስክንድር ምርጫቸውን ብቻ ሳይሆን ልባቸውን ጭምር ለመስጠት ቆርጠው ተነስተዋል። ወ/ሮ አዳነች አበቤ በወረራ ጠፋ የተባለውን ቦታ ፈልገን እናስመልሳልን ባይሉም የጠፋ እቃ ጠፍቶ የሚቀረው የሰረቀ ሌባ የጠፋውን እቃ እንዲፈልግና እንዲያፈላልግ ሃላፊነት ሲሰጠው እንደሆነ ለሚረዳ ከንቲባዋ ዘራፊዎችን ለህግ ለማቅረብ ፍላጎት እንደሌላቸው ሲያውቅ ምክንያቱ ግልጽ ይሆንለታል። ስለሆነም “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” እንዲሉ አዳነች አበቤ የጠፋውን ፈልጋ ታገኛለች የሚለው የብልጽግና የኮንፊውዝም ጨዋታ ጉም ለመጨበጥ እንደመሞከር ወይም ከእባብ እንቁላል እርግብ እንዲቀፈቀፍ እንደመመኘት ነው።

የባልደራሱ መሪ፣ ጋዜጠኛ፣ የሰባዊ መብት ተክራካሪና ፖለቲከኛ እስክንድር ነጋ ለውጥ መጣ ከተባለ ማግስት ጀምሮ አገንግኖ የመጣውን የተረኝነት ስሜት በጊዜ መስመር መያዝ እንዳለበት ከመጮህም ባሻገር ሁኔታዎችን እየተከታተለ ገዥው አካል (መንግስት) ማረም ያለበትን ስህተቶች ለሚድያ ይፋ በማድረግ ያለእረፍት ሲታገል ቆይቷል። በተለይ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎች ዘርን መሰረት በማድርግ እየተሳሳቡ በገፍ የከተማ መታወቂያና ኮንደሚኒየም ሲታደሉ እንዲሁም ያለ አግባብ በሚደረግ የከተማ ቦታና ታሪካዊ የቤተክርስቲያን ይዞታዎችን በድፍረት በማጠር ሲካግሄድ የነበረውን የመሬት ወረራ ሲያጋልጥ ውሸት ነው እየተባለ ሲስተባበል ነበር። እስክንድር በወሬ ሳይሆን ማስረጃ ይዞ ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰጥበት ቦታ ሁላ በወቅቱ የነበረው ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ድጋፍ ሰጭነት በቄሮ ስም ወሮ በሎችን በማደራጀትና በማሰማራት የስብሰባ ቦታዎችን ሰብሮ በመግባትና በመረበሽ እውነቱ እንዳይሰማ ለማፈን የተሔደበትን ርቀት ሁላችንም ጠንቅቀን የምናውቀው ሃቅ ነው። ሆኖም ተረኞች ሲናገሩት ብቻ ጽድቅ ነውና ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ባንድ ወቅት ሃምሳ አንድ ሺ ኮንዶሚኒየም አድሎ ከጨረሰ በኋላ በጉዳዩ እንደሌለበትና ባደረገው ጥናት ሃምሳ አንድ ሺ ኮንዶሚንየም መጥፋቱን አይኑን በጫው አጥቦ በኩራት ነግሮናል። ሰላማዊው እስክንድር ግን እውነቱን ለአዲስ አበባ ነዋሪ ከማሳወቅ በተጨማሪ በግልም ይሁን በእርዳታ ያገኘውን ገንዘብ በእግሩ እየተጓዘና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ቤታቸው በዶዘር ያለአግባብ ለፈረሰባቸውና ያለመጠለያ ሜዳ የተበተኑ ዜጎችን (የአዲስ አበባ) ነዋሪዎችን በመርዳት በአዲስ አበባ ከሚኖረው ማህበረሰብ ጋር የፈጠረው መልካም ግንኙነት፣ መተማመንና መግባባት ለባለ ተረኞች ትልቅ ስጋት በመሆኑ “የምዬን ወደ አብዬ” ብለው እስር ቤት መወርወራቸው አንሶ ህይወቱን አስይዞ ታግሎ ለዚህ ያበቃቸውን ታላቁን የሰላም ሰው አሸባሪ ብለው ከፍርድ በፊት ፈርደውበታል።

አሁን ደሞ ምርጫ ሳይኖር የይስሙላ ምራጫ ደረሰ ተብሎ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከታከለ ኡማ የተረከቡትን አይን ያወጣ ዘረፋ አጠናክረው ካሳለጡ በኋላ እንደ ኦስካር ተሸላሚ የሆሊውድ አክተር ታጅበው ሸራተን ሆቴል ሽር ብትን እያሉ መፍትሄ የማይሰጥበትን ያገጠጠ ሌብነት አርጂ ሆነው ሲቀርቡ ከመቀመጫው ተነስቶ የአዳራሹ ጣሪያ እኪበር የሚያጨበጭውን “ተደጋፊ ተደማሪ” አይተንና ሪፖርቱን ሰምተን ጉድ ብለን ስንገረም ይባስ ሃፍረተ ቢሶቹ “ኢትዮጵያ ወደብልጽግና እየገሰገሰች ነው” እያሉ ጆሯችንን ለማደንቆር ወደ ኋላ አላሉም፡፡ እነዚህ በጭፍን የሚጓዙ የብልጽና ምልምሎች ምክንያታቸው ሶስት ነገሮች ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል። አንደኛው የዘረፋው ተጠቃሚ (“ተደጋፊ ተደማሪ”) ስለሆኑ፣ ሁለተኛው የሚናገሩትን የማያውቁ ከረባት የለበሱ ግን በ “አቡቹ” የጨረባ የብልጽና መንፈስ የተለከፉ (“ውታፍ ነቃዮች”) ስለሆኑ ወይም “ኢትዮጵያ ሱሴ” (ኦነግ) የሚያቀርብላቸውን አሺሽ እየሳቡ ኑሯቸውን በጡዘት አየር ላይ ያደረጉ ብቻ ናቸው።

በሁሉም አቅጣጫ ያለው አብዛኛው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ግን በአቡቹ/የጨረባ ብልጽግና ተስፋ ቆርጦ ሀገሩን ነጻ ለማውጣት ሳይዘገይ ወደ ትግሉ ዓለም ተመልሶ ከገባ አያሌ ወራቶች ተቆጥረዋል። የሃገሪቱ እጣ ፈንታም “በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ” በሚሉ የጨረባ ብልጽግና (የኮንፊውዝም ቁማርተኞች) እጅ በመውደቋ የዜግነትና የሉዓላዊንት ጉዳይ ክፉኛ አደጋ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት ባልታዬ መልኩ መጪው ጊዜ በእጅጉ አስፈሪ እንዲሆን አድርጎታል።

ለማንኛውም ወደ ዋናው የተነሳንበት ጉዳይ እንመለስና ለግንዛቤ እንዲረዳ ጠፋ የተባለው መሬት ምን ያክል ነው የሚለውን በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ከተገለጸው አወጫባሪ ቁጥር ባሻገር በንጽጽርና በይዘት ገምግመን ለመታዘብ ከታች ያለውን እንመልከት። ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቅም ሳይላቸው 1,338 ሄክታር መሬት ከዲስ አበባ ተዘርፎ ጠፍቷል ብለዋል፡፡ እንግዲህ 1,338 ሄክታር መሬት ወደ ካሬ ሜትር ሲቀየር በ10 ሺ ይባዛል ምክንያቱም አንድ ሄክታር 10 ሺ ካሬ ሜትር ነውና።

በዚህ ቀመር 13,380,000 ካሬ ሜትር (አስራ ሶስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ ሺ ካሬ ሜትር) ማለት ነው፡፡ የህን እዚህ ላይ አስምረን እናቆየውና አቶ ታከለ ኡማ በነሃሴ 27 2012 ያወጣውን ሪፖርት እናስታውስ። እንዲህም ብሎ አሳውቆን ነበር በአዲስ አበባ ከ213ሺ ካሬ ሜትር በላይ የከተማ ቦታ ጠፍቷል ብሎናል። እነዚህን ሁለት ሪፖርቶች የታኬውንና የአዳነችን አንድ ላይ ስናደርግ በጠቅላላው ተረኛው ገዢ አካል ያመነበት 13,593,000 (አስራ ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ) ካሬ ሜትር የከተማ ቦታ እንደ ትኩስ ቡና ፉት ተብሎ ሶስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተዘረፎ ጠፍቷል።

rrr

ለምሳሌ አራዳ ክፍለ ከተማን ብንወስድ ከጎን ባለው ምስል በቀይ እንደሚታዬው ጠቅላላ ስፋቱ 991 ሄክታር ወይም 9,910,000 (ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስር ሺ ካሬ ሜትር) ነው። ከዚህ ጋር ስናወዳድረው ጠፋ የተባለው ቦታ የአራዳ ክፍለከተማን ወደ 1.37 እጥፍ ይሆናል ማለት ነው ። እንደገና በሌላ መልኩ ለመረዳት በሀገራችን የኮንዶሚኒየም አሰራርና ለአመታት ገንዘቡን ቆጥቦ በመጨረሻ አፍንጫችሁን ላሱ ለተባሉ ወገኖቻችን ሊሰጥ የሚችለው አስተዋጾ እንዲሁም ባጠቃላይ በከተማዋ ያለውን የቤት እጥረት በምን ያክል ደረጃ ሊቀርፍ እንደሚችል እንመልከት፡፡

 

  • 2011 እኤአ Condominium Housing In Ethiopia በሚል የ UN ጥናት እንዳወጣው በኢትዮጵያ የቤት እጥረትን ለመቅረፍ ባሰናዳው የኮንዶሚኒየም ዲዛይን መሰረት አንድ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ባለ አራት ፎቅ ያለው ሆኖ የማህበራዊ ስራዎችን መስሪያ ክፍት ቦታ ጨምሮ በአራት መቶ ካሬ ሜትር ላይ ያሳርፈዋል።

 

በግራ ያለውን ምስል ይመልከቱ። እያንዳንዱ ፎቅ ባለ ሁለት መኝታ 1 ፣ ባለ ስቱዲዮ 1 ፣ ባለ አንድ መኝታ 2 ና ባለ ሶስት መኝታ 1 ተደርጎ ይሰራል ስለዚህ በአራት ፎቅ ሁሉንም በአራት በማብዛት አንድ ህንጻ የስንት ሰው መኖሪያ እንደሚሆን ማየት ይቻላል። ሆኖም 13,593,000 (አስራ ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠና ሶስት ሺ ካሬ ሜትር) ለ አራት መቶ ካሬ ሜትር ሲካፈል

13,593,000 /400= 33,983 (ሰላሳ ሶስት ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት) ህንጻዎች ሊያሰራ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ከላይ ያሉትን አሃዞች በመጠቀም ሂሳቡን በማስላት የሚከተለውን ያገኛሉ። ባለ ሁለት መኝታ ቤት ለ135,932 ሰዎች፣ ባለ ስቱዲዮ ለ135,932 ሰዎች ባለ አንድ መኝታ ቤት ለ271,864 ሰዎችና ባለ ሶስት መኝታ ቤት ለ135,932 ሰዎችን ባለ እጣ ወይም ባለቤት ያደርጋል ማለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የአጠቃላይ የቤተሰብ ቁጥር ሳይነሳ በትንሹ 679,660 (ስድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ) ሰዎችን ባለ እጣ ወይም ተጠቃሚ ሊያደርግ ይችል ነበር ማለት ነው፡፡

rrrrwwበመጨረሻም በዘረፋ ጠፋ የተባለው ቦታው በገንዘብ ምን ያክል ሊተመን ይችላል የሚለውን ለማየት በ2016 እ.ኤ.አ በአዲስ ፎርቹን በወጣው ጥናታዊ ዘገባ በአዲስ አበባ በትንሹ ለንግድ የሚሆን ቦታ 12,153 ብር በካሬ ሜትር፣ ለንግና ለመኖሪያ የሚሆን ቦታ 13,165 ብር በካሬ

ሜትር እና ለመኖሪያ የሚሆን ቦታ ደግሞ 16,666 ብር በካሬ ሜትር መሸጣቸውን በወቅቱ የከተማው አስተዳደር አስታውቋል። ዛሬ ስላለው የዋጋ ጭማሪ ከመንግስት ግልጽ የሆነ መረጃ ባናገኝም ከላይ ባዬናቸው አሃዞች አማካይ ውጤት 13,995 ብር በ ካሬ ሜትር ይሸጣል ማለት ነው። ስለዚህ በአዲስ አበባ ጠፋ የተባለው ቦታ በትንሹ በገንዘብ ሲተመን (13,995 x 13,593,000) 190 ቢሊየን ሁለት መቶ ሰላሳ አራት ሚሊዮን ብር ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ግምት የተሰላው የዛሬ አምስት ዓመት የነበረን የሽያጭ ዋጋ መሰረት በማድረግ ሲሆን አሁን የተረኝነት ለውጡን ተከትሎ የታየው የገንዘብ ግሽበት ቢያንስ በከ40-50% ጭማሪ ሊኖረው እንደሚችልና መጠኑ በአስርዮሽ ቢሊዮን እንደሚጨምር ወይም ግምቱ እስከ ከ250 ቢሊዮን ብር ሊሆን እንደሚችል ለጉዳዩ የቀረቡ አዋቂዎችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ችያለሁ። አቶ አህመድ ሽዲ ከስድስት ወር በፊት የኢትዮጵያ ሃገራዊ ባጀት ወደ 386.9 ቢሊሆን ብር ከፍ ማለቱን ነግሮን ነበር በንጽጽር ይሄው ተርኞች የገሪቱን ባጀት ሁልት ሶስተኛ የሚሆነውን በቦታ ቅርምት ስም ከአዲስ አባባ ከተማ ብቻ ሶስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ መዝረፋቸው ተረጋገጠ። ይሰማል ወገኖቼ? ቅጥ ያጣው ተረኝነት ሃገሪቱን ምን እያደረገ ነው? እንግዲህ በሃገራችን እየበለጸገና እየገነገነ ያለው ኦሮሙማ/ፋሺዝም ለመሆኑ ልብ ይበሉ፡፡ “ኢትዮጵያ በብልጽግና እየገሰገሰች ነው” የሚለው የዜሮ ድምር ውጤትም ይህን ይመስላል!። ይህን እያየ ነገሩ ሁሉ ተክድኖ ይብሰል የሚል ዜጋ አለ ብዬ አላምንም!። አዎ “ድል ለዲሞክራሲ ድል ለሰፊው ህዝብ” እውነት ምንጊዜም አሸናፊ ነው!፡፡ አዲስ አበባን በሚመለከት ድምጼን ለባልደራስ ሰጥቻለው!፡፡ እናንተስ?

 

2 Comments

  1. በጠም የሚገርመው ስንት ተዓምር፣ ዘረፋ፣ ቅሚያ ሲፈፀም፣ ስንቱስ የለየለት ሌባ በአንድ ጀንበር ሚሊየነር የሆነበት አረ ስንት ጉድ በመሬት ጉዳይ ሲሰራ ቆይቶ አሁንም ለማድበስበስ ሲሞከር ይገርማል፡፡

    ይልቅስ አሁን ቅጥ ባጣው የአዲስ አበባ ነጋዴ ላይ አፈጣኝ እርምጃ አስተዳደሩ እና መንግስት የማይወስድበት ምክንያት ምንድን ነው፡፡ የምግብ ዘይት በፈለግነው የዋጋ ተመን ካልሆነ አንሸጥም በማለት ከዋና አከፋፋይ እስከ ተራ የመንደር ሱቅ ዘይት ሲደብቁ ምንድን ነው የሚጠበቀው፡፡ ህዝብ እኮ ለሞኖር እንኳን መመገብ የማይችልበት ደረጃ እየደረሰ ነው፡፡ ይህን ስግብግብ ነጋዴ ለምን እሹሩሩ ይባላል፡፡ ከላይ ጀምሮ ንግድ ሚ/ር፣ የክልል ንግድ
    ቢሮ ወዘተ ምን እያደረጉ ነው፡፡ ነጋዴ አገርን የሚመራ ከሆነ አደጋ ነው፡፡ አይ በደርግ ጊዜ አመፀኛ ነጋዴን ልክ ነበር የሚያስገባው፡፡ በበርበሬ መደበቅ ስንቱን ልክ እንዳስገበቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አፋጣኝ እርምጃ ህዝብ ይፈልጋል፡፡ ሰው መኖር አልቻለም፡፡

  2. የአዲስ አበባ መሬት ጉዳይ ከጠቅላዩ ጀምሮ እጃቸውን ያቆሸሸ በመሆኑ ብዙ ጥናትና ጥልቅ ምርምር ይጠይቃል። ኢንጂነር ታከለ ኡማ የሱሉልታ ካንቲባ በነበርበት ጊዜ የጀመራውን የዘር ተኮር መድልዖና ሥር የሰደደ ሙስና ማስቆም ሲገባ፤ በለመደበት አስፋፍቶ እንዲቀጥልበት በጠቅላዩ የትሾመበት ራሱን የቻለ ምክንያት ስላለው ነበር።
    በለቡ አካባቢና በሰበታ ለአማቻችው የትሰጠውን ብዙ ሺህ ካሬ ሜትር ሠፊ ቦታ ምክንያት በማድረግ ታከለ ኡማም መገናኛ አካባቢ እንዲሁ ሠፊ የሐንፃ መገንቢያ ቦታ ለራሱ አድርጎ በነሐሴ ወር አካባቢ በቅጥታ ለሌላ ሰው ለመሸጥ በደላላ ሲሸማገውል እንደነበር ይታወቃል። የዓሣ ግማቱ ከአናቱ እንዲሉ ጠቅላዩ የሚናገሩትና የሚሠሩት ስለማይገጣጠም ተሰሚነታቸውንና ክብራቸውን በየጊዜው እያጡ ናቸው። ወ/ሮ አዳነች አቤቤም የናዝሬት ከንቲባ በነበሩበት ጊዜ በቂ ልምድ አላቸው ተብለው እንደተመደቡ ቢታወቅም የሙስናውን መንገድ አጠናክሮ ለመቀጠል ካልሆነ በስተቀር የተለየ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን የሐዝብን ትኩረት ለመሳብና ምርጫዋን ለማሸነፍ ሲባል ሐቀኛ መስሎ ለመታየት የቀረበ ሪፖርት እንጂ በተግባር ላይ የተመሠረተና ፍትሐዊ እርምጃ የተወሰደበት ውጤት እንዳልሆነ ይታወቃል። የሆነው ሆኖ ግን የአዲስ አበባን ሕዝብ ለመሸወድ አይቻልም። “የአህያ ብልት በሆዱ ነው!” እንደሚባለው ምርጫው እውን ከሆነ በካርዱ እየመነጠረ እንደሚያስወጣቸው የሚያጠራጥር አይደለም። ዶ/ር ዓቢይን ብልጥና አስተዋይ መሪ እያሉ የሚክቡ የጴንጤ ስብስቦች በጣም ይገርሙኛል። የፈለገውን ብልጥ ቢሆኑ የአዲስ አብባን የአራዳ ልጅ በምንም መልኩ ማታለል እንደማይችሉ የተረዱት አይመስልም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ የተሰወረ አንዳችም ነገር እንደሌለ ማወቅ ተስኗቸዋል፡ የዚህ ድምር ውጤት ውድቅት እንጂ ድል ሊሆን አይችልም። ግለስቦችን በትምህርታቸው፤ በሚያሳዩት ሥነምግባርና በሥራ ውጤታቸው ተመስርቶ አሳንሶ ማየት ይቻል ይሆናል። ነገር ግን ሕዝብን አሳንሶና ንቆ መመልከት ከቂልነት በምን ይለያል። ተደብቆ የተሠራው ሥራ ሁሉ ከሐዝብ የተሰወረ አይደለም። አባቶች በከፍተኛ ምስጢር የተፈጽመን ወንጀል የሚመረምሩበት እውስ (አፈርሳታ) የሚባል ጥበብ ነበራቸው። በመጨረሻም ወንጀሉን በስውር የፈጸመውን ሰው ነቅሰው ያወጡታል። እንዴት አወቃችሁ ሲባሉ ግን ጠቋሚውን ሰው ላለማጋለጥ ሲሉ፤ “ተጠርጣሪው ሰው ወንጀሉን ሲፈጽም ወፍና ድንጋይ አይተውታል፤” በማለት ይደመድሙታል። ዶ/ር ዓቢይ ምንም ነገር በስውር አንሠራም በማለት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም እጅግ በጣም ድብቅ አጀንዳዎችን ሲያራምዱ በመቆየታቸው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ታዝቧቸዋል። ከዚህም በላይ ደግሞ ጣዖት አምላኪ ናቸው። ኢትዮጵያን ለማፍረስና ሕዝብን በጎሣና በቋንቋ የሚከፋፍል፤ የግለሰቦችን ሰብአዊ መብት ለምደፍጠጥ የተዘጋጀን ሕገመንግሥት ሙጥኝ ብለው ይዘዋል። እንዲሁም ሕዝብን እርስ በእርስ ለማናከስ የቆመን ሐውልት እያመለኩ ናቸው። ስለዚህ ምርጫ እንደማይኖር ከፍተኛ ጥርጣሬ አለ፤ ነገር ግን ምርጫ ካለ በመሬት አንቀጥቅጥ እንደሚሸነፉ ከአሁኑ መታወቅ አለበት። በምንም ተዓምር የአዲስ አበባን ሕዝብ መሸንገል ከቶ አይቻልም። ከዚህ አኳያ ከላይ የተጠቀሰው ጥናታዊ ሪፖርት የውድቀታቸው ዋነኛ መገለጫ ነው እላለሁ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.