ዲያቆናት ሆይ የአብይ አህመድን መንገድ ብትነግሩን፡ለዳንኤል ክብረትና ተረፈ ወርቁ – – ሰርፀ ደስታ

abiy and daniel ዲያቆናት ሆይ የአብይ አህመድን መንገድ ብትነግሩን፡ለዳንኤል ክብረትና ተረፈ ወርቁ  – ሰርፀ ደስታሰሞኑን አንድ ራሱን ዲ/ን ተረፈ ወርቁ ነኝ የሚል ግለሰብ ሰሞኑን ፈተና የበዛበት የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሠላምና እርቅ መንገድ በሚል አንድ ጽሑፍ አቅርቦ አየሁ፡፡ በመጀመሪያ ለዲ/ን ተረፈም ይሁን ሌሎች ብዙ ዶ/ር በርቁዎች የአብይ አህመድን ሥም ለመጥራት በንግግር ከሆነ በየደቂቃው በጽሑፍ ደግሞ በየ አረፍተነገሩ ዶ/ር፣ ዶ/ር ስትሉ ከተነሳችሁበት ሐሳብ ይልቅ የአብይን ዶክተርነት በመናገር ጊዜና ጉልበት ባታባክኑ እንዲሁም ለአንባቢም ሆነ አድማጭ አሰልችና ለአንዳንዶቻችን ደግሞ አሳቃቂ እንደሆነ ብትረዱት ጥሩ ይመስለኛል፡፡ አንድ ሰው በጠ/ሚኒስቴርነት ቦታ ተቀምጦ እነደ አብይ ዶ/ር ዶ/ር እየተባለ የሚጠራ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ይህ በራሱ ትልቅ ማሕበረሰባዊ የስነልቦና ቀውስ እንደሆነ ተረዱ፡፡ ብዙ የዓለማችን መሪዎች ዶ/ር ሲባሉ የማንሰማው ዶ/ር ስላልሆኑ አደለም፡፡ እንደው ምሳሌ እኳን ብንጠቅስ ዛሬ በአገር መሪነት ያሉ የራሺያው ፑቲን፣ የቻይናው ሺ ጂፒንግ፣ ከጀርመኗ መራሄ መንግስት አንጌላ መርክል የዶክትሬት ዲግሪ ያላቸው ናቸው፡፡ በየትኛውም ቦታ ላይ ግን ዶ/ር በሚል ቅፅል ሲጠሩ ሰምቼ አላውቅም፡፡  የአገር መሪ እንደመሆናቸው በመሪነት ስልጣን ማዕረጋቸው ይጠራሉ፡፡ ያ እንኳን ባይኖር በዚህ በመሪነት ደረጃን ያለ ሰው ዶ/ር እያሉ መጥራት ግርታ ፈጣሪ ነው፡፡ ሁሉም የስልጣን ማዕረጋቸው ካልተጠቀሰ የሚጠሩት በመደበኛው ሚስተር ወይም ሚስ በሚል ነው፡፡ ይህ ደረጃውን የጠበቀ አጠራር ነው፡፡  የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ኦባማም ዶክተሬቱ ነበረቸው፡፡ ፕሬዚደንት ኦባማ ወይም ሚስተር ኦባማ እንጂ ዶ/ር አባማ ሲባል የሰማ ካለ እስኪ ይንገረን፡፡  ያሳዝናል፡፡ ፈረንጆቹም ይሄን የእኛን ስነ ልቦታ ስላወቁ ነው አብይን ዶ/ር እያሉ የሚጠሩት ውስጣቸው ግን እየሳቀ ማለት፡፡ ነገሩ ትንሽ ያሳፍራልም፡፡ ፕሮቶኮል የማያሟል ኢመደበኛ መሆኑ፡፡ ስለዚህ ይሄን አይነት የዶ/ር ብርቁ አጠራር ቢያንስ ብትቀንሱት፡፡

ወደተነሳሁበት ስመልሳችሁ ከላይ በርዕሱ የጠቀስኩትን ጽሁፍ ያስነበበው ራሱን ዲ/ን ተረፈ በሚል የሚጠራው ግለሰብ በርዕሱ ያስቀመጠው ነገር ስሁትነት ሳያንሰው ውስጥ ስታነቡት አንድም ይሄ ነው የሚባል ነገር ሳያስቀምጥ ከርሞ በሚቀጥለው ጊዜ ብሎን አልፎታል፡፡ ሲጀምር ፈተና የገጠመው የሚሊለት የአብይን ሴራ የሠላምና እርቅ መንገድ ሲል ይጀምራል፡፡ ዛሬ ለኢትዮጵያ ቀንደኛ ፈተናዋ የአብይና መሰሎቹ ሴራ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ዘግይቶም ቢሆን ሕዝብ እየተረዳው መጥቷል፡፡ ዲያቁኑ የሠላምና እርቅ ያለለት የአብይ መንገድ የቱ እንደሆነ አልነገረንም፡፡ ደግሞ እኮ ምንም ባለማፈር ፈተና በዛበት ይላል፡፡ የሚከተሉትን እንዳደረገ ዛሬ ላይ ግልጽ ነው፡፡

 1. የወያኔ የአማራ ጠል ማኒፌስቶን በልዩ ሁኔታ ማስቀጠል፡- አብይ አህመድ በወያኔ ያደገ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ዛሬ በለውጥ አረማጅ ነን በሚል ሥም አገር እያፈረሱ ያሉት ከወያኔ የተቀዱ እንጂ አዲስ አደሉም፡፡ ከወያኔ ሐሳብም በላይ ማሰብ የማይችሉ እንደሆኑም በተግባር አይተናል፡፡ ባይሆንማ 27 ዓመት ወያኔ በልታበት በመጨረሻ የተወገደችበትን እሱኑ ኮፒ አድርገው ባልቀጠሉ፡፡ ትንሽ መቀየር እንኳን በቻሉ፡፡ የሆነ ሆኖ በአማራ ጠልነት ወያኔ ከሰራቸው በላይ አብይ አህመድ ሥልጣኑን ለማቆየት የሄደባቸው ርቀቶች ገና ዋጋ ያስከፍሉታል፡፡ ወደ ሥልጣን ሲመጣ ደግፎት የነበረው ብዙው ሕዝብ ከዚሁ ማህበረሰብ ነበርና፡፡ ከወያኔ በከፋ ሴራውን ሁሉ አማራ ላይ እየጎነጎነ ብዙ ጥፋት ደርሷል፡፡ ከወያኔ ውድቀት በኋላ ወልቃይት-ሁመራና ራያ ወደ አማራ እጅ መግባቱን አብይ አህመድና ቀሪ የኦሮሞ ነብሰገዳዮች እንዴት እብድ እንዳደረጋቸው አይተናል፡፡ አሁንም ይሄን ሕዝብ ወደ አራጆቹ መልሰው ለመስጠት እየሰሩ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ በግልጽ የትግሬ ተማርኩ የሚል ማንም ይሁን ማን እንኳንስ ለአማራ ለራሱም ሕዝብ አረመኔ እንደሆነ እያየን፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ቦታዎች ወደ ትግራይ ይመለሱ ሲባል ምን ማለት ነው? መሬቶቹ እኮ ባለቤቶቹን እየገደሉና እያሳደዱ የወያኔ ባለስልጣናትና ዘመዶቻቸው ነበሩ የያዟቸው፡፡ ለመሆኑ ትግራይን አስተዳድራለሁ የሚለውስ ቦታውን በምን ሞራል ነው የሚጠይቀው? ለነገሩ እንደነ አገኘሁ ያሉ የአማራ ወኪለ ነን በሚሉበት ማን ስለሕዝቡ ይቆማል፡፡ በተመሳሳይ በመተከል አማራና-አገው (ሲጀምር አገው አማራ አንድ ሕዝብ ነው) እየተመረጠ የሚገደልበት ሴራስ የአብይ አህምድ አደለም፡፡ የሆነው ሁሉ ሕዝብ የሚያውቀው ነው፡፡ ይሄ ነው የሠላሙ መንገድ?
 2. የኦርቶዶክስ ተከታዮች ዒላማ ያደረገ ጥቃት መፈጸም፡- እን ዲያቆናት ለመሆኑ ይሄን አብይ አህመድ ፒፒ ማኒፌስቶው ጽፎት ያለ የፕሮቲስታንቲኒዝም ጎስፔል እምነት ማስፋፋት እቅድ አደለም? ከላይ እንዳነሳሁት አማራው በአማራነቱ ሙስሊም ሳይል ክርስቲያን የሚገደልት ሳይሆን በዚህ ደግሞ በኦርቶዶክስነት አማራውና ሌሎች ሁሉ የሚታረዱበት ሴራ ነው፡፡ ልብ በሉ ሐጫሉ ተገደለ ሲባል ማን ነበር ኢላማ የተደረገው? የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ለመጠየቅ ማን ነበር የታረደው? በሲዳማው የክልልነት ሂደት ውስጥ ማን ነበር ከኋላ የነበረው፡፡ በአብይ፣ አባዱላና ሌንጮ ባቲ አልነበረም? ዛሬ የአማራን መሬቶች ከሕግ ውጭ ወደ አማራ ተጠቃለሉ እያሉ የሚቀሳፍቱት ለመሆኑ ሲዳማን ክልል ለማድረግ ያስቻለው የትኛው የተለየ ሕግ ነው? አማራ ያልተወከለበትን ሕገ-መንግስት ያለመቀበል መብት ሲኖረው ያም ቢሆን የአማራ መሬቶች በየትኛውም ሕግ ሳይሆን በጉልበት ነበር የተወሰዱት፡፡ ቀጥሎም በሕጋዊነት ለማስመለስ ጥያቄ እየቀረበባቸው ነበር፡፡ ለምን እስከዛሬስ ፍትህ አልተሠጠውም? የኦርቶዶክስ ኢላማነት በዚህ አላበቃም፤ ሌላ ቀርቶ ኦርቶዶክስ የሆኑ ጉምዝ ሳይቀር በተከል ከአማራና-አገው ጋር ኢላማ ነበሩ፡፡ አዎ የነፍጠኛ ሐይማኖት በሚል ሲረጭ የኖረ መርዝ አለ፡፡ አብይ አህመድ በማንፌስቶ ያስቀመጠውን በልዩ የሴራ ቡድኑ ኦርቶዶክስን ለማጥቃት ብዙዎችን አሰማርቷል፡፡ የሰሞኑ ዮናታን የተባለው የአማራ ሽብሸባ ስብከት የዚሁ አንዱ አካል ነው፡፡ በለፈው ሶስት ዓመት መረን የወጡ የጴንጤ አጭበርባሪዎችን ታዝበናል፡፡ እንደነ ኢዩ ጩፌ ያሉ አገርን ሲያምሱ ሀይ ያላቸው አልነበረም፡፡ ሌላ ቀርቶ እሱም ከጀርባው ዶ/ር የሚል ታርጋ የለጠፈው ምህረት ደበበ የተባለ ግለሰብ ወጣቶችን ሰብስቦ እዴት ሲያደነዝዝ እንደነበር ታዝበናል፡፡ ዶ/ር ነኝ ሲል ስለሚናገረው ነገር እኳን በቂ መረጃ ይዞ አደለም፡፡ ጅብ የማያውቁት አገር ሄዴ እንደተባለው …. ወጣቶችን ሰብስቦ ሲያጃጅል ተመልክተናል፡፡ በፕሮቲስታንት ስም ያሉ የትኞቹ አይነት እንደሆኑ ባላውቅም አንዳንዶች እንደ እምነት ሰከን ያለ ነገር ሲናገሩ ብሰማም ብዙ ወጣቱን ወደ አላስፈላጊ ነገር እየመራ ያለው ግን ይሄ የአጭበርባሪው ቡድን ነው፡፡ እንግዲህ የፕሮሰፔሪቲ ጎስበፔል የሚባለው ሊሆን ይችላል፡፡ በቀጥታም በአብይ አህመድ ተልዕኮ የተሰጣቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በእርግጥም እንደነምህረት ደበበና ዮናታን የአብይ አህመድ ልዑኮች ናቸው፡፡ ይሄ ነው የሠላምና እርቁ መንገድ?
 3. የአገሪቱን የመንግስት መዋቅር በኦሮሞ-ጴንጤዎች ማስያዝ፡- ዛሬ ላይ የአገሪቱ የመንግስት መዋቅሮች አዲስ አበባን መስተዳደርና የፌደራሉ ዋና ዋና የተባሉ መዋቅሮች ያለምንም እፍረት በኦሮሞ አንደተወረሩ ግልጽ ነው፡፡ እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልገባም፡፡ አሁን እየሆነ ያለውን ሕዝብ ራሱ እያወቅ ስለሆነ፡፡ እነ ዲያቆናት ይሄ ነው የአብይ ሠላምና እርቅ መንገድ?
 4. ማታለል፡- አብይ አህመድ በሲመተ እለቱ የተናገረውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ከልብ ደግፎት እንደነበር የምንረሳው አደለም፡፡ በወቅቱም ብዙ የተሻለ ነበር የመጣል ብለው ብዙዎች ጠብቀው ነበር፡፡ ዛሬ ላይ የአብይ አህመድን አታላይነት ብዙዎች እየተረዱት ነው፡፡ አለማቀፉ ማህበረሰብ ሳይቅር በመታለል ዓብይን የኖበል ተሸላም እስከማድረግ ደርሶ ነበር፡፡ ይሄ አሁን ላይ ይለም፡፡ ብዙ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ተስፋ ያደረጉ ሁሉ ዛሬ የሉም፡፡ ይሄ በማጭበርበር ሰኬት ይመጣል የሚል አባዜ ልኩን አልፉ እንዲህ አደባባይ በመውጣቱ ዛሬ የአብይ አምላኪዎች እንደነ ዲያቆናት ያሉ፣ ፌሚኒስትና፣ የጎስፔል ጴንጤዎች ካልሆኑ ማንም የሚያምነው የለም፡፡ የአገርን ድንበር ለሌላ አሳልፎ እንደሰጠ ሰጥቶ ዛሬ ሱዳን ሳትቀር እያፌዘች እናያታለን፡፡ በየመድረኩ የሚያወራቸው ነገሮች የራሱን ከፍታ ለመጨመር እንጂ አንዱም እውነት እንዳልሆነ እየታዘብን ነው፡፡ በየዓመቱ በዜኔ ከሚደረጉት ሴራዎች የራሱ ድራማዎች እንጂ አንዱም በሌላ እንዳልመጣ እንታዘባልን፡፡ ለዘንድሮ ሰኔ ደግሞ ምርጫውን በግንቦት ስላደረገ ያው ሰኔ ሌላ እልቂት ሊሆን እንዲሆን አስቦ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ሰውዬው የሰው ደም የሚገብር አውሬ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ እንግዲህ እነ ዲያቆናት የአብይ የሠላም መንገድ ይሄ ይሆን ለእናንተ
 5. በኢትዮጵያዊነት እያጭመረበሩ ሴራን ከኋላ መምራት፡- ሰሞኑን ሳይቀር በኦሮሚያና ሌሎች ቦታዎች የተደረጉ ሰልፎች ጥቅሶቹ ሳይቀር የተዘጋጁት አብይ በአዘጋጃቸው የሴራ አስፈጻሚ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ራሱን ከደሙ ንጹህ ለማድረግ ይሞክራል፡፡ አዝገራሚው ነገር የሰልፎቹ ዓላማ በራሱ አብይን መደገፍ የሚል መሆኑ ነው፡፡ ለመሆኑ አብይን መደገፍ የሚል ሰልፍ ምን ማለት ነው? አብይ በፓርላማ የሚመረጥ ጠ/ሚኒስቴር እንጂ በሕዝብ የሚመረጥ ነው? ወይስ ምን የሚሉት አይነት እይታ ነው? ግለሰቡ የመንግስትን መዋቅር ለራሱ ማንነት መቸርቸሪያ አድርጎት ሕዝቡ ምን እያደረገ እንኳን ሳይረዳ አብይን በመደገፍ በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ እይተናል፡፡ ብልጽግናን በመደገፍ ማለጽ እኮ የአባት ነው፡፡ አብይ ቢመረጥ በአንድ ወረዳ እንጂ እንደ ፕሬዘዳንት በሁሉም ቦታ አደለም፡፡ ይህ በሆነበት ነው እንግዲህ ሁሉም ሰልፎች አብይን በመደገፍ እያ የሚወጡት፡፡ አሳፋሪ ነው፡፡ በዚህ ሳይበቃ ሌሎችን በማውገዝና አሁንም ነፍጠኛ ይውጣ በሚል መፈክሮች የተጀበ ነው፡፡ እነ ዲያቆናት ይሄ ነው የአብይ ፈተና ገጥሞት የታያችሁ የሠላም መንገድ?
 6. የወያኔ-ሕግና-ሥርዓትን ለማስቀጠል የቆረጠ፡- ሁሉም ሰው ልብ ሊለው የሚገባው አብይን ጨምሮ ከተወሱኑት በቀር ሁሉም የወያኔ ማደጎዎች ናቸው፡፡ የወያኔ ዘረኛ ሕገ-መንግስት ከሌለ እነዚህ ሁሉ ቦታ እንደማይኖራቸው ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ወያኔ የሰራቸውን ሥርዓትና ሕገ-መንገስትም ሆነ ሌሎች ለአገርና ሕዝብ ጠንቅ የሆኑ ሕጎችን መቀየር አገሪቱን ወደ ሠላማዊና የመንግስት መዋቅሮችም በፍትህና ሕግ አግባብ ባለው ሰው ስለሚያዙ እነ አብይና የእሱ ተከታዮች ቦታ እንደማይኖራቸው ያውቃሉ፡፡ እነ ታዬ ደንደዓ ምን ቦታ ይኖራቸው ነበር አገር በሥርዓትና ሕግ ብትመራ? እንግዲህ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ በማጭመርበር የጀመረው አብይ በዚህ ሶስጥ ዓመት የወያኔን ሕገ-መንግስት ጨምሮ ሌሎች ጸረ-ሕዝብና አገር ሕግጋቶችን ቀይሮ በምትካቸው የሕዝብንና አገር ደህንነት የሚያስጠብቁ ሕግጋትን መተካት በቻለ ነበር፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በሕግ ማንነትን ተንተርሰው መደራጀትን ማገድ በቻለ፡፡ ለእነዚህ ሁሉ ትልቅ የሕዝብና የዓለም ዓቀፉንም ማህበረሰብ ድጋፍ ማግኘት በቻለ፡፡ ከተጠመቃት የወያኔ ዶግማ ማን ያላቀው፡፡ ራሱን እንደ የሐሳብ ምንጭ የሚቆጥረው ሰውዬ የተኮረጀና የተቀዳ ሐሳብ እንደተሞላ ዛሬ ሁሉም ተረድቶታል፡፡ አዝናለሁ እነ ዲያቆናት ይሄ ነው የአብይ የሠላምና እርቅ መንገድ?

እንደነ ዳንኤል ክብረትና ተረፈ የመሳሰላችሁ ዲያቆናት ሆይ ምን አለ ብትተውን፡፡ በእናንት የአብይን ሰባኪነት የምትከተሉትንም እምነት ሕዝብና አገርንም እየበደላችሁ እንደሆነ ልቦታ ሰጥቷችሁ ተረድታችሁ ከድርጊታችሁ ብትታቀቡ፡፡ ከላይ የዘረዘርኳቸው በአብይ አህመድ ዘመን የሆኑና በራሱም የተቀነባበሩ ናቸው፡፡ እንግዲህ የቱ ይሆን ለእናንተ የታያችሁ ለእኛ የማይታየን የአብይ አህመድ የሠላምና እርቅ መንገድ? አዝናለሁ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

– ሰርፀ ደስታ

2 Comments

 1. ሰርፀ ደስታ የተባሉት ሰውዬ በየጊዜው የሚለቁት ረዥም ሀተታ በወፍ በረር እንጂ በቁምነገር አይነበብም፡፡ ጽሁፉ ይህን ያህል የረዘመ ቢመስልም የጽሁፉ ዋና ጭብጥ በዶ/ር አብይ ወይም በኦሮሞ ሰዎች ያለዎትን የመረረ ጥላቻ ብቻ የሚያንጸባርቅ ነው፡፡በጣም የሚያስገርመው ደግሞ የራስዎን መረን የለቀቀ የጥላቻ ሀሳብ እንዳሻዎ እየጻፉ ሌሎች ሰዎችን ይህን አትደግፉ፣ ስለዚህ አትፃፉ ዓይነት ከልካይ ንጉሥ መሆነዎ ነው፡፡ በርግጥ በዚህ ገጽ የሚጽፉት ፊውዳላዊ/ አፍቃሪ አፄዎች የተጫጫናቸው ይበዛሉ፡፡
  በሁለት ተቃራኒ ጫፍ ከቆማችሁት መካከል የርሰዎና የዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ልዩነት ምድን ነው? (የሁለቱ ጽንፈኛ ጫፍ የሚያደርገው እሰጥ አገባ ሰላመዊ ሰዎች ሰለባ እየሆኑ ነው)
  ሰርፀ ደስታ፤ በአሁኑ መንገስት በተለይ በጠ/ሚንስተሩ የሚያንጸባርቁት ንቀትና ጥላቻ ልክ የለውም፤ እንዲወገዱም ፈልጋሉ፡፡ከሚጽፉት እንደታዘብኩት በኦሮሞ (ርስዎ ኦሮሙማ በማለት ይግልፁታል) ማህበረሰብ ላይ የመረረ ጥላቻ አለዎት፡፡
  ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ፤ በአሁኑ መንገስት በተለይ በጠ/ሚንስተሩ ያላቸው ንቀትና ጥላቻ ልክ የለውም፤በተለያየ ጊዜ ከሚሰጡት አስተያየት እንደተረዳሁት በአማራ ማህበረሰብ ላይ የመረረ ጥላቻ አላቸው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.