ሆዳም አማራ ዛሬም አሚካላ! – በላይነህ አባተ

ww1በላይነህ አባተ ([email protected])

በአማራ መቃብር መንደር ለመመስረት ከአምሳ ዓመታት በፊት እቅድ አውጥተው የተነሱት የትግሬና ወረሞ ነጣ አውጪ አረመኔዎች ዛሬም እንደ ትናንቱ በውጪም በውስጥም እንደገና ተደረጅተው ነፈጠኛ የሚል ኮድ የሰጡትን አማራ ቋንጃ ለመስበር የሞት የሽረት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሆዳም አማራዎች ግን አማራን ከመጥፋት ለማዳን ተነስተው የነበሩትን ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ጠልፈው እንደጣሉትና እንዳስገደሉት አሁንም አማራን ለመታደግ የተደራጁትንና የሕዝብ መገናኛ ማእከል ያቋቋሙትን ጠልፈው ለመጣል ሲውተረተሩ፣ ሆዳቸውን ለመቆዘር ጊዜ ተወንበር ለሰቀላቸው ከንቱዎች ሲያጎበድዱና ጥቅማቸውን ሲያሳድዱ ይታያሉ፡፡

አምሳ ዓመት ሙሉ የዘር ፍጅት የተፈጠመበት አማራው ሆኖ ሳለ በአማራ ላይ የዘር ፍጅት ፈጣሚዎች የከፋ ግፍ የደረሰባቸው መስለው የዓለምን አደባባይ ሲያጥለቀልቁትና ከሁሉም በላይ የተደበሉ መስለው የዓለምን ሕዝብ ሲያታልሉ ሆዳም አማራዎች ከርሳቸውን እየሞሉ ሆዳቸውን ሲገፉ ተመዋል ተሻግረው ተአማራ አጥፊዎች ጋር ተሰልፈው  አማራን ተክፉ ዘመን ለማውጣት የሚጥሩትን ሲያብጠለጥሉ ይውላሉ፡፡

አማራ እንደ ደን እየተጨፈጨፈ ህሊናቸውን ሳይቆጠቁጣቸው ሆዳቸውን እንደ አቆማዳ ሲሞሉ ኖረው ወደ ሞት የሚሄዱትን ከርሳም አማራ ምሁራን ቤት ይቁጠራቸው፡፡ ተምን ዘሃ ቢደሩ፣ ምን ሸማኔ ቢሰራቸውና ምን ሰፊ  እንደ ድሪቶ ቢደርታቸው እንደዚህ ሆነው እንደተፈጠሩ እግዜር ይወቀው፡፡ አማራ እንዳይወለድ የእናቱ ማህፀን ተወግቶ ፅንስ ሲገደል ያላዩና ያልሰሙ መስለው ሲጎሰጉሱ ኖረው አፈር ለመግባት እንዴት እንደመረጡ እግዚአብሔር ይፍታው፡፡

አንዳንድ “ምሁር ነን ወይም “ታዋቂ ነን” ባይ አማሮች ተእኛ “አማራ ራሱን መከላከል አለበት!” ብለን ተምንወተውተው የበለጠ አዋቂ፣ የበለጠ አስተሳሰበ ሰፊ፣ የበለጠ ኢትዮጵያንና አንድነትን የሚወዱ መስለው በዋና በር  “ኢትዮጵያ”ን እየጨፈሩ እስክስታ ያወርዳሉ፡፡ ወዲያው ደሞ በጓሮ በር ይሾልኩና ኢትዮጵያን ገዝግዘው ተቦጫጨቋት ነፍሰ ገዳይዎች “ሙሴዎቻችን” እያሉ ሲወባሩና ሲዳሩ ይውላሉ፡፡ በአስመሳይ ምላሳቸው ኢትዮጵያን የቦጫጨቋትን ካድሬዎች፣ ጆሮ ጠቢዎችና ነፍሰ ጋዳዮች የኢትዮጵያ መድህን አስመስለው ሲደሰኩሩ ይውላሉ፡፡ “ለኢትዮጵያ ስንል”  በሚል ሰበብ አስመሳይነታቸውን፣ አድርባይነታቸውንና ሆዳምነታቸውን ሸፋፍነው ኢትዮጵያን ለሰላሳ ዓመታት በአቀንጣጤአቸው እየዘነቸሩ በመንጋጋቸው ሲያመነዥኳት የኖሩ አውሬዎችን ጅራት ይከተላሉ፡፡ ካድሬዎቻቸው ሆነው ሬዲዮኑን፣ ቴሌቪዥኑን፣ ጋዜጣውንና ዌብ ሳይቱን ሲያጠብቡት ይውላሉ፡፡

እነዚህ በአማራዎች ነፍስ ቀላጅ “ምሁራን ነን፤ ታዋቂ ነን፣ ጋዜጠኛ ነን፣ ሽማግሌ ነን፣ ጳጳስ ነን፣ ሼክ ነን” የሚሉ አስመሳይና አድርባይ አማራዎች የአማራ ጽንሶች፣ ህፃናት፣ አሮጊት፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ጎልማሶች በመላ አገሪቱ ሲታረዱ መጀመርያ ባቄላ ጉረሮውን እንደጠረቀመው አውራ ዶሮ ጪጭ አሉ፡፡  ባቄላው ተጉረሯቸው ወረድ ሲል  አንዳንዶች ዘር ማጥፋት ወይም ጆኖሳይድ በአማራ ላይ አልተኪያሄደም እያሉ ተለገሰ ዜናዊና ተአብዮት አመዴም የበለጠ  የውሸትን ፈረስ ሽምጥ ጋልበው ካዱ፡፡ ዘር ያጠፉት ሰዎች “አማራን ገደልን፤ ነፍጠኛን ገደልን፣ ኦርቶዶክስን ገደልን” እያሉ ዘር ማጥፋታቸውን ሳይክዱ ዘሩ በመጥፋት ላይ ታለው አማራ የወጡ ሆዳም ምሁራንና ተዋቂ ሰዎች አሁንም “ለኢትዮጵያ ሲሉ” የአማራን ዘር መጥፋት ሽምጥ ከደው ዘር በማጥፋቱ ወንጀል የተባበረውን ይህ አድግ ነጣ ማውጣቱንና መደገፍን ቀጠሉ፡፡

ከዘር ፍጅት የተረፉ አማራዎች የይህ አድግ ታጣቂዎችና ሹሞች በዘር ፍጅት እንደተሳተፉ ደጋግመው እየተናገሩ እነዚህ ምሁራንና ተዋቂዎች ነን የሚሉ ሆዳም አማራዎች የግፍ ሰለባዎችን ቃል ትተው የግፍ ፈጣሚን ፕሮፓጋንዳ በመቀበል “ለኢትዮጵያ” ሲሉ ተዘር አጥፊዎች ጀርባ ማረጥረጡን ቀጠሉ፡፡ ተደራጅቶ የሚመክትና በሕግ የሚጠይቅ እንዳይፈጠር ተክቡር ፕሮፌሰር አስራት ጀምረው እነዚህ ሆዳም አማራዎች ሲከልክሉ ስልኖሩ በይህ አድግ  የድንጋይ ዘመን አረመኔዎች በይህ አድግ ታጣቂ እየታገዙ በብሉይ ኪዳን፣ በሀዲስ ኪዳንና በስልጣኔ ታሽቶ ርህራሄ ያለውን አማራን በጦርና በገጀራ መጨፍጨፉን ቀጠሉ፡፡

ግፉ እየከረፋ ሲሄድና ሕዝቡ ተዳርዳር ተቆጥቶ መላ መፍጠር ሲጀርምር ደግሞ እነዚህ አለቅላቂ ምሁራንና ታዋቂ ሰዎች ሌላ ሰበብ መፍጠር ጀመሩ፡፡ አንዳንዶቹ ነገሩን አለባብሶ ለማለፍና አቅጣጫ ለማስቀየር  እንደተለመደው ዓባይ ዓባይ፣ ግድብ ግድብ፣  ትራንፕ ትራንፕ፣ ግብፅ ግብፅ እያሉ መዝፈንና ማላዘን ቀጠሉ፡፡ ሌሎቹ ደሞ የዘር ጪፍጨፋው ምክንያት “ሕገ መንግስቱ ነው” አያሉ አህያው ላይ ሳይሆን ዳውላው ላይ መጮህ ጀመሩ፡፡

አህያው ላይ ሳይሆን ዳውላ ላይ በሚጮሁት ከሀዲ አማራ ምሁራን ወይም ታዋቂ ሰዎች ዘንድ ቀደም ሲል ወልቃይት፣ ሁመራ፣ በደኖ፣ አርባ ጉጉና ጉራ ፈርዳ ዛሬም  ሃረርጌ፣ ባሌ፣ አሩሲ፣ ከፋ፣ ወለጋ፣ መተከልና ሸዋ  አማራዎችን እየለየ የጨፈጨፋቸው ወይም እየለያችሁ አማራዎችን ጨፍጭፉ ያለው ሕገ መንግስት የሚሉት ድሪቶ ነው፡፡ ሙሴአቸው ሳይመጣ እነዚህ አለቅላቂ አማራዎች “ኢትዮጵያ ሕግ መንግስት የላትም!” ያሉትን ሙልጭ አርገው ካዱ፡፡

ለገሰ ዜናዊ አሳድጎ የቀባው ሙሴአቸው ሲመጣ ለገሰ ዜናዊ አማራን ለማጥፋት ደደቢት በርሃ የደረተውን ድሪቶ ያለማፈር ተቀብለውት አረፉ፡፡  አሁን ደግሞ ለገሰ ዜናዊ የቀባውንና የሕገ መንግስቱን ድሪቶ ተንከባካቢውን ሙሴ ጉልበት እየሳሙና ሌተ ተቀን በቀላማጅ አፋቸው እያሞገሱ ገጀራ ወይም ቀስት የሚሸከም እጅ የሌለውን ህገ መንግስቱን በዘር ማጥፋት ወንጀል ከሰሱ፡፡ ይህ የሚከሱት እጅ እግር የሌለው ድሪቶ ሕገ መንግስት በካድሬነት አደቁኖ፣ በጀሮ ጠቢነት አቀስሶና በዘረኝነት አመንኩሶ ቤተመንገስት የዶላቸውን የይህ አድግ ወንጀለኞች እየደገፉ ሆዳምነታቸውን፣ አድር ባይነታቸውን፣ አስመሳይነታቸውንና እታይ እታይ ባይነታቸውን ሕገ መንግስቱን በመውቀስ ሊሸፋፍኑት ይፍጨረጨራሉ፡፡ በዚህም አያቆሙ፡፡ ሕገ መንግስቱን ወቅሰው የዘር ፍጅት የፈጠሙትንና የተባበራቸውን አገዛዝ ተአማራ የዘር ፍጅት ደም ነፃ በማውጣት ሕዝብን፣ ታሪክንና እግዚአብሄርን ለዘላለም ያስቀይማሉ፡፡

ከርሳም፣ አድርባይና አለቅላቂ ምሁራንና ታዋቂዎች ሕገ መንግስቱን የነደፉት ድውይ ጭንቅላቶችና ሕገ መንግስቱን የጫሩትን እርጉም እጆች ትተው ሕገ መንገስቱ የሰፈረበትን ገኡዝ ወረቀትና ቀለም ይኮንናሉ፡፡ ሕገ መንግስቱን ተሚያስፈጽሙትና እንደ በኩር ልጅ ተሚንከባከቡት እርጉሞች ጋር ሲወባሩ እየዋሉ የሕገ መንግስት ጥራዝ ሲወቅሱ ይውላሉ፡፡  ለሆዳቸው፣ ለባዶ ክብራቸው፣ ዘላለም ለማትኖረዋ ነፍሳችውና በሌላም በሌላም ሽፍጥ የአማራን የዘር ፍጅት በመካዳቸው፣ በመሸፋፈናችውና ችላ በማለታችሁ ሕዝብና እግዚአብሔር ይይላቸው፡፡ ታሪክም ለዘላለም ይውቀሳቸው፡፡

እነዚህ አለቅላቂ ምሁራን  ሙሴአቸው ቤተመንግስት ሲገባ የኢትዮጵያ ዳግም ትንሳኤ አያሉ መንጋውን አታለው  በየከተማው በገጠሩ አስጨበጨቡ። አሁንም በዚህ ቁንፅል አስተሳሰባቸው ሕገ መንግስቱ ቢቀደድ ይህ አድግና  ወነግ እንደ ዋርካ ያገነገኑት ዘረኝነና ፀረ-አማራ አስተሳሰብ እንደ ቀትር ጉም በኖ የሚጠፋ አስመስለው መንጋውን ያታልላሉ፡፡ ሕገ መንግስት ተብየው ቢቀየር በፀረ-አማራ ፕሮፓጋንዳ ተቦክቶና ተጋግሮ የተሰራው የዚህ ትውልድ አንጎል በታምር ፀድቶ  ሕዝብ በሰላም ሊኖር እንደሚችል እየሰበኩ አማራ ተደራጅቶ እስከ ወዲያኛው ራሱን ከመጥፋት እንዳያድን ያዘናጋሉ፡፡ የህገ መንግስት መኖር እንኳን የኢትዮጵያን አውሬዎች አውሮጳንና አሜሪካንም ከዘረኝንት መንፈስ ነጻ እንዳላዋጣቸው በአድርባይነት ባህሪያቸው እየረሱ አማራ ተደራጅቶ ራሱንና ሌሎችንም ከመጥፋት እንዳያድን ያደናብራሉ፡፡

በዘር የመከፋፈልን ጠንቅ መገንዘብ ከእኛ በላይ ፉጨት ማሞጥሞጥ መሆኑን ስተው በአማራ መቃብር ሪፐብሊኮች ለመመስረት ተሰለጠኑ ጆሮ ጠቢዎች ጀርባ ተሰልፈው ያሞጠሙጣሉ፡፡ አማራ እንዳይደራጅ ደንቀራ እየሆኑ በዘር ተደራጅተው አማራን በመላ አገሪቱ እያስፈጁ ያሉትን ሙሴዎችና ሱሰኞች ይደግፋሉ፡፡ አማራን ከዘር ፍጅት ለማትረፍ የተደራጁትን አያብጠለጠሉ በዘረኝነት ተነቅረው ያደጉትን፣ በአማራ መቃበር ሪፐብሊክ በመመስረት ስብከት የደቆኑትን፣ በዘር ክልልና አማራን የማጥዳት ዲግሪ የቀሰሱትን ሙሴዎች የኢትዮጵያ አለኝታ አስመስለው ይሰብካሉ፡፡

እነዚህን ከንቱ ምሁራንና ታዋቂ አማራዎች ሆዳቸው፣ አድርባይነታቸው ወይም ደግም ከመድረክ የሚጠብቁት ቀፎው ክብራቸው ዓይነ ሞራቸውን ስለሸፈነው ባለፉት ሶስት ዓመታት የረገፈው አማራ አጋዚ በሃያ አምስት ዓመታት ውስጥ ተጨፈጨፈው አማራ አስር እጥፍ መሆኑን አላሳያቸው ብሏል፡፡ ሳይበላ ያበላቸውን፣ ሳይጠጣ ያጠጣቸውን፣ ሳይለብስ ያለበሳቸውን፣ ሳይማር ያስተማራቸውን የአማራ ሕዝብ ክደውታል፡፡ በየደቂቃው በድንጋይ ዘመን አረመኔዎች አንገቱ በቆንጨራ ሲቀላ፣ ዓይኑ በቀስት ሲወጋ፣ ደረቱና ሆዱ በሰይፍ ሲተረተር የሚፈሰው ደም አልትያቸው ብሏል፡፡

እነዚህ ሆዳሞች አማሮች በመላ አገሪቱ የሚገደሉት እንደ እነሱ አማራ ስለሆኑና እነሱ በአማራነታቸው ሲሞቱ የእነሱም አካል አብሮ እየሞተ መሆኑን አልገነዘብ ብለዋል፡፡  ገዳዮቹ የሚገሏቸውን ወገኖቻችንን አማራ፣ ነፍጠኛና  ኦርቶዶክስ እያሉ እየጠሯቸው ሳለ አነዚህ አስመሳይና ሆዳም ምሁራን “ዜጎች ተገደሉ” እያሉና አማራ የሚለውን ቃል ለመጥራት እየተሽኮረመሙ የገዳይዎችን የዘር ማጥፋት ወንጀል ሊሸፋፍኑ ሲጥሩ ኖረዋል፡፡

አስመሳይ ምሁራን ወይም ታዋቂ ሰዎች ትልቅ ሰው ለመባል እንደሚደሰኩሩት አማራን ዘሩን እያጠፋው ያለው ሕገመንግስቱ ሳይሆን በአማራ ጥላቻ የአበዱ አውሬዎች መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል፡፡ ስለዚህ አማራ ለእነዚህ አህያውን ትተው ዳውላውን ለሚኮንኑ  ሆዳም ምሁራንና ታዋቂ አማራዎች እርም  ማውጣት ይኖርበታል፡፡ እነዚህን አህያውን ትተው ዳውላው ላይ የሚጮኹትን አለቅላቂዎች ጆሮ ዳባ ብሎ አማራ ራሱን ከጥፋት የሚያድን ጠንካራና ውስብስብ ማእከል መፍጠር ይኖርበታል፡፡

“ነፃ አውጪዎች” ዛሬም በአማራ መቃብር መንደር ለመመስረት በውጪም በውስጥም እንደገና እየተዋቀሩ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በፀረ-አማራ ደዌ አብደው ነገም የአማራን እርስት ለመንጠቅ፣ የአማራ ሆድ ቀደው ፅንስ ለመግደል፣ ዓይን ለማውጣት፣ ብልትና አንገት በቆንጨራ ለመቁረጥ እየተዘጋጁ እንደሆነ ተሆዳም አማራ ጭንቅላት በስተቀር ሌላው ይረዳል፡፡  አውሬዎች እስከ ዳግም ምጣት ሕገ መንግስት፣ ፍቅርም ሆነ ትግስት ሊገባቸው እንደማይችል ሆዳም ያልሆነ አማራ ያውቃል፡ ሆዳም ያልሆንክ አማራ ቱርክን፣ ግብጥን፣ ጣሊያንንና ሌሎችም ተስፋፊዎች ድል በነሳህበት ወኔና ስልት ራስህን ከመጥፋት ለማዳን እንደ አራት ዓይናው ጎሹ አራት ዓይን አውጥተህ በጎበዝ አለቃ መደራጅት ይኖርብሃል፡፡ ትግልህ መለኮት የፈቀደው የመኖር ተጋድሎ ነውና ከስድስት ሺህ ዘመናት በላይ ስታመልከው የኖርከው አንድ አምላክ ይረዳሃል፡፡ አላማህ እግዜርን አምላኪው ሕዝብህ እርስቱን ተመነጠቅ፣ ፅንስን በጦር ተመወጋት፣ እናቶችን በቆንጨራ ተመቀላት፣ እስረኞችን በህኒ ቤት ተመሰለብ፣ ልጃገረዶችን በክኒንን ተመምከን ለማዳን ነውና እግዚአብሄር ተአሚካላው ሆዳም አማራም ይጠብቅሃል፡፡ መለኮት ይርዳህ! አሜን፡፡

 

ጥር ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.