የአማራ ኢትዮጵያ፣ የአማራ ሰንደቅ፣ የአማራ ሐይማኖት የአማራ ሽብሸባ – ሰርፀ ደስታ

እግዚአብሔርን (እውነትን) ለማወቅ ባልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ(ያስቡ፣ ያወሩ፣ ይሰሩ)ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የፈላስፋው ንግግር ሁል ጊዜ ጭንቅላቴ ውስጥ ያቃጭላል፡፡ ዛሬ ላይ የብዙ ኢትዮጵያውያን አስተሳሰብ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል፡፡ ለምን እንዲህ እናስባለን ብለው ቆም ብለው እንዳያስተውሉ እውነቱን ለመረዳት ፍላጎት ጭምር በማጣታቸው ለማይረባ አእምሮ የተሰጡ ይመስላል፡፡ በአማራና ኦርቶዶክስ ጥላቻ ላይ እውቀታቸውን መስርተው በተከተሉት የስህተት ትርክት ልክ አሁን አሁን በእርግጥን ሰዎች አእምሮአቸው ፍጹም እንዳያስተውል ሆኖ ለክፉ እንደተሰጠ እየታዘብን ነው፡፡ አማራ ወይም ኦርቶዶክስ የሆናችሁ የታደላችሁ መሰለኝ ከእንዲህ ያለው አስተሳሰብ ባርነት ባለመያዛችሁ፡፡ ይገርማል ከዳር ሆኖ ለሚያስተውለው፡፡

እስኪ አንዳንድ ጉዳዮችን ለማስተዋል ይረዳ እንደሁ በድፍረት ልናገራቸው፡፡ እስከዛሬ ለሰው ለማውራት ይከብደኝ ነበር፡፡ ምክነያቱም ብዙ ሰው የሚያምነው እኔ ፍጹም ሊገባኝ ያልቻለ ነገር ስለሆነ ነው፡፡ ለመሆኑ እንዲህ ያለው አለማስተዋልና የማይረባ አእምሮ ከምን ይመጣል?

ከማንበብ፡- እንግዲህ እስከዛሬ መቼም ማንበብ አእምሮን ያበላሻል የሚል ሰው ሰምታችሁ ላታውቁ ትችላላችሁ፡፡ እኔን እስከሚገባኝ ግን ማንበብ ከምንም በላይ አደገኛ የሆነ የአእምሮ መሠለብን የሚያስከትል ነገር ነው፡፡ እርግጥ ነው ማንበብ ሁሉ ሳይሆን ብዙው ዛሬ ዛሬ ሰዎች እናነባለን የሚሉት ነገር እጅግ አደገኛና ከማንነት አውጥቶ የመጻፉ ደራሲ የአስተሳሰብ ባሪያ መሆን ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከጅምሩ የማርክሲስት ሌኒኒስትን አስተሳሰብ (ፍልስፍና ማለት አልፈልግም) ያነበበው ያ የ60ዎቹ ትውልድ የራሱን ተፈጥሮኣዊ ፍልስፍና ሙሉ በሙሉ ጥሎ ማርክስ እንዳለው፣ እንግልስ እንዳለው፣ ሌኒን እንዳለው እያለ የእነዚህና የተመሳሳይ ሐሳብ ያላቸውን አስተሳሰብ ባሪያ ሆነ፡፡ ያ ይሄው የዛሬውን የእኛን አገር የመሠለች ከእውቀት የፀዳ የሌሎች ሐሳብ ባሪያዎች የበዙባትን አገርና ትውልድ ፈጠረ፡፡ ከዛ በኋላ የእነ ሌኒን እንዳለው የአስተሳሰብ ባሪያዎች የጻፏቸውን እያነበበ የበለጠ ገደል ገባ፡፡ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ጥቅት ብቻ እውቀትን የተከተሉ የተማረ የሚል የተለጠፈባቸው ሰዎች የቀሩ መሠለኝ፡፡ በአንጻሩ ያልተማረው ሕዝባችን በተሻለ በተፈጥሮአዊ እውቀቱ ይኖራል፡፡

እንግዲህ ማንበብ ሙሉ ያደርጋል እያለን ያገኘንውን ሁሉ ስናግበሰብስ ምን እየሆንን እንደሆነ እናስተውል፡፡ ዛሬ ፍጹም በሚባል ደረጃ እየጠፋ ያለው ትውልድ በሐሰት ትርክት እንደሆነ አስተውል፡፡ ከጥበብ መጻኅፍጽ በቀር ሁሉም በሚባል ደረጃ መጻህፍት የእውቀትን አድማስ የሚጨምሩ ሳይሆኑ የጸሐፊው ሐሳብ ባሪያ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ አንባቢ አደለሁም እላለሁ ለጓደኞቼ፡፡ በውስጤም የማንበብን አደጋ እያሰብኩ፡፡ ሆኖም ማንበብ አደጋ ነው የሚለውን ለጥቂቶች በቀር አልናገረውም፡፡ ብናገረውም ማን ይቀበለኛል፡፡ በዚህ ሳምንት አንድ የፒ ኤች ዲ ዲግሪዋን እየሰራች ካለች የድሮ ጓደኛዬ ጋር ለጥናቷ የሚያግዛትን እንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን እየነገርኳት እያለ እሷ በምታጠናው መስክ ያለኝን እውቀት እያደነቀች በጣም የማነብ አይነት አድርጋ ስላሰበች እኔ አንባቢ አደለሁም ማንበብ አደጋ ነው ስላት ቃል በቃል ያለችኝ ታዲያ ከየት አባህ አምጥተህ ነው ይሄን ሁሉ ነገር የምታውቀው አለችኝ፡፡ እውነት ነው፡፡ በእርግጥም እኔ አንባቢ አደለሁም፡፡ ከመጀመሪያ ዲግሪ ጀምሮ ጓደኞቼ በደንብ ስለኔ ዛሬ ቢጠየቁ አስታውሰው ሊናገሩት የሚችሉት ነገር ቢኖር ተማሪ አለ የተባለ ሸክም የሚያካክል መጻሕፍ ይዞ ሲሯሯጥ እኔ እዛ ውስጥ የለሁም፡፡ ያ ማለት ግን ከነጭርሱ አላነብም እያልኩ አደለም፡፡ እኔ የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስማር ስለምማራው ትምህርት ላይብራሬ ገብቼ ያነበብኩበት ቀን ትዝ አይለኝም፡፡ ላይብራሪ ከገባሁ የማነበው ባይሆን ኢንሳይክሎፒዲያና መሠል የአጠቃላይ እውቀት መጻህፍትን ነው፡፡  ታዲያ እንዴት ነው ትምርቱን የምትወጣው ብትሉኝ እንማር የነበረው ትምህርት እንደእውነቱ የዛን ያህል ንባብም አያስፈልገውም፡፡ ሆኖም ስለተማርንው ነገር በደንብ ማስተዋልና ማወቅ አለብን፡፡

ከዚሁ ሳልወጣ ማስተዋል ስል ዛሬም ድረስ እኔ አለማንበቤ ብቻ ሳይሆን ስለማነበው ነገር መሠረታዊ ጫፍ ካልተያዘልኝ አንብቦ ለመረዳትም ወይም ፈተናም ከሆነ ሽምድድ አድርጎ እሱኑ መጻፍን እቸገራለሁ፡፡ ስለሆነም ነገሩን በተቻለ መጠን ከሥሩ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ነው የእኔ ትልቁ ጉልበት የሚባክነው፡፡ ከዛ በኋላ አገር ምድር መጻህፍ አነበብኩ የሚለው ሰውም የማይረዳውን መረዳት እችላለሁ፡፡ አሁን ባለሁበት ሞያዬም ቢሆን እንደእውነቱ ይሄ ነው የተባለ መጻፍ አንበቤ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ስለ መሠረታዊ ነገሩ ለማወቅ ወስጄ ነበር፡፡ ለዛም ነው ከላይ የጠቀስኳት ጓደኛዬን ያላሳመናት፡፡ በዚህ ሂደት አወናበጅ (ጀርገን) የሳይንስ ቃላቶችን ምን ማለት እንደሆኑ መረዳት ላይ እንጂ ቃላቶቹን መናገር ራሱ አይመቸኝም፡፡ ሰሞኑን ዮናታን የተባለ የጴንጤ ሰባኪ ስለ አማራ ሽብሸባ ባወራ ጊዜ ስለዲኤንኤም ትንተና ሲሰጥ ነበር አሉ፡፡ እኔ አልሰማሁትም ለዛ ነው፡፡ የምር ግን እንዲህ የመቀባጥሩ ሰዎችን መስማት አልችልም፡፡ አሁንም ሰዎች በጣም መሀበራዊ ገጽ ላይ ስላበዙት ነው፡፡ ዲኤን ኤ አንዱ ሳይንሱ በደንብ ያልገባቸው በመስኩ ያሉ ራሱ አንዱ አወናባጅ ቃል ነው፡፡  ዲኤን ኤ ግን ምን ማለትና ምን እንደሚሰራ ሲገባን ዲኤንኤ የሚለው ቃል ይደብረናል፡፡ እንደምሳሌ ነው፡፡ ጓደኛዬ ታዲያ እንዲሁ የጀርገን ቃላት ተሸክማ ብዙዎቹን ነገሮች ከመሠረታቸው አልተረዳቻቸውም ነበር፡፡ እኔ ግን ነገሮቹን የማስረዳትና የነበረው ከሳይነሳዊ አንጻር ሳይሆን በእውን ከምንኖረው እውነት አንጻር ነበር፡፡ በቃ ሳይንስ አፈር ድሜ ገባች ማለት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ብዙዎች ስለሚያጠኑት ነገር ብዙም ሳይገባቸው እንደዛው ጀርገን ቃላቶችን ሰካክተው ትልቅ መጽሐፍ ሁሉ ሊጽፉ ይችላሉ፡፡ አንባቢውም ይቀጥላል፡፡ ጉዳቸው የሚገለጠው ነገሮችን የተረዳው ሰው አግኝቶ ካነበባቸው ነው፡፡

በመሆኑም ከምንም በፊት የራሳችንን ተፈጥሮአዊ እውቀት እናሰራ፡፡ በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን እናስተውል፡፡ የምንማረውን ከራሳችን ሕይወትና ከምናውቀው ነገር ጋር እናስተሳስር፡፡ ፍለስስፍና ማለት ይሄ ነው፡፡ ከዛ ማንበብም ካለብን ያልገባንን ነገር ለማወቅ አቅደን እናነባለን፡፡ ስናነብም ይገባናል፡፡ ሆኖም ማንም እየተነሳ የደረሰውን ድርሰት ማንበብ እውቀት ይሆናል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ይልቁንስ አደጋ ነው፡፡ አብዛኞቹ ልብ ወለዶች የሚጻፉት በደራሲው የአስተሳሰብ ልክ ነው፡፡ የእኛው አገር የዘመኑ ታሪክ ጸሐፊ ነን ባዮች እየደረሷቸው ያሉ መጻሕፍትማ እጅግ አደገኛ ናቸው፡፡ ባለፈው ስለፈረስ፣ ስለ አጋዝያንና መሰል ጉዳዮች አንስቼላችሁ ነበር፡፡ አስቡት ፈረስ የኦሮሞ ነው የሚለው ስህተት እንደሆነና ፈረስ ይልቁንም የሚኒሊክ ዘሮች የሆኑት የሸዋዎች እንደሆነ ለመገንዘብ የእነ ተስፋዬ ገብረአብን ድረሰት መታጨቅ ባላስፈለገ፡፡ ከእነ አካቴውም አንዳች ነገር ሳናነብ ፈረስ የት ይኖራል በቆላ በደጋ፣ ኦሮሞ የመጣው ከቆላ ነው ከደጋ፡፡ እና ቆላ ፈረስ ከሌላ ኦሮሞ ፈረስ ያወቀው ወደ ደጋ ሲመጣ እንደነበር ለመረዳት ሳይንስ አደለም፡፡ በቃ፡፡ የአጋአዚውም እውነት እንዲሁ ነው ሌሎችም ዛሬ ማንም እየተነሳ የሚጨፍርባቸው አልቆ መሳፍርት የሐሰት ትርክቶች፡፡

ስብከት፡- ሌላው ከምንም በላይ አደገኛ የሆነው ሰዎችን በአስተሳሰብ ባርነት የሚከት ስብከት ነው፡፡ እኛ የአስተሳሰብ አድማሳችን ከልጅነት ጀምሮ በጥንቃቄ ከተያዘ ተዓምረኛ ልንሆን እንችላለን፡፡ የብዙ ማህበረሰብ ችግር ግን ይሄን ባለመገንዘብ ልጆችን ከዛም አዋቂዎችን ያውቃሉ በሚሉ ሰዎች ላይ ተስፋ ጥሎ መሠረታዊ እውቀቶችን አለማስያዝ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ብዙ ማህበረሰብ እስከዛሬም በባርነት ይኖራል፡፡ ስብከት ሐይማኖታዊ ፍልስፍናን ለማሳደግ አይሆንም፡፡ በየትኛውም እምነት ቢሆን እውቅት የሚገበየው በእውቀት የበሰሉና ፍልስፍናን በሚያስተምሩ ነው፡፡ ይሄ በክርስትናውም፣ በአይሁዱም፣ በቡዳውም፣ በሂነዱውም በሌላውም ይታወቃል፡፡ ስብከት የሚለው ቦታ ሲመጣ ግን ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ጊዜ፡፡ ሲጀምር ሰባኪው እውቀት ያለው ሳይሆን እንዴት ሰዎችን ማጥመድ እንደሚችል የተካነ ነው፡፡ ሲቀጥል ራሱን እንጂ አብዛኛው ሰባኪ ከመሠረታዊ ሐማኖት ትምህርት ጋር የሚገናኝ ነገር አያወራም፡፡ የሰሞኑ የዮናታ የታለው ግለሰብም ያደረገው ይሄን ነው፡፡ መጨረሻውም ዓላማው አማራና ኦርቶዶክስን እንዴት መተቸት እንዳለበት ስለሀነበር ይሄኑ አድርጓል፡፡ እኔ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ፡፡ እኔ ግን ሰባኪ አልሰማም፡፡ ቢቻል አስተማሪዎችን እሰማለሁ፡፡ ስለኦርቶዶክስ እምነት ፍልስፍና እንጂ አሁንም  ጳውሎስ እንዳለው፣ ጴጥሮስ እንዳለው የሚል ነገር መስማት አልፈልግም፡፡ ጳውሎስ ስላለው ሳይሆን ጳውሎስ ያለው ነገር ከገባኝ ነው ዋናው ቁም ነገርና፡፡ ቅድም አላነብም ያልኳችሁ መጻፈ ቅዱሱን አነበዋለሁ፡፡ በዘመናት የነበሩ እውቀትም በዚህ መጻሕፍ አለና፡፡ ያ ማለት ግን መጻፈ-ቅዱስ ስላለና ስላላለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ እግዚአብሔር ፍርድ ይሆንብን ዘንድ ለሁላችንም እውቀት ሰጥቶናል፡፡ ስላልተማርኩ ማለትም የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ሁለት ትዛዞች አሉ አምላክህ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብኅ፣ ነብስህ፣ ጉልበትህ አምልክ የሚልና ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የሚል፡፡ ማንም ቢሆን ባልንጀራውን እንደራሱ መውደድ ከቻለ የጽደቅ ሁሉ ጥግ የሆነውን ፈጽሟል፡፡ ይሄን ሲያደርግ የማያየውን እግዚአብሔርን የሚያምንበት ልዩ አቅም ይሰጠዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ይሄን ሁሉ የጻፍኩት እንድታስተውሉ ነው፡፡ በዚሁ ወደተነሳሁበት ልመልሳችሁ፡፡ አማራና ኦርቶዶክስ ጠል ርዮት የተጠናወተው ትውልድ ከ60ዎቹ ጀምሮ አሁን በከፋ ሁኔታ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ ላይ ለብዙዎች የአእምሮ በሽታ እስከሚሆንባቸው ድረስ የደረሰ ጥላቻ ሆኗል፡፡ እንደቀልድ ወደው የተከተሉት ጥላቻ ዛሬ ላይ ቢፈልጉ እንኳን የሚተዋቸው አልሆነም፡፡ ኢትዮጵያን ለአማራና ኦርቶዶክስ ሰጥቶ ባዶውን የቀረ ትውልድ ያሳዝናል፡፡ ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር በአንድ ወቅት እንዲሁ የተለመደውን ማደናገሪያ ጎንደር ላይ ስለ ፋሲለደስ ሲነገር ስለ በካፋ ኦሮሞነት ግን አይነገርም ተናግሮ ነበር፡፡ አሳዛኝ ነው፡፡ ይሄው ነግግር ታዲያ ብዙዎች ድንቅ ሆኖባቸው ዛሬም ድረስ እየተቀባበሉት አይቻለሁ፡፡ አስቂኙ ነገር ግን ፋሲልም አማራ ነኝ ወይም የሆነ ብሔር ነኝ አላለም፡፡ በታሪክ መዝገብ ከሆነ ግን ሁለቱም ተቀምጠዋል፡፡ ሌላው አስቂኝ እውነት በዛ ወቅት ኦሮሞ የሚባል ቃል እራሱ አለመኖሩ ነው፡፡ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይቀጥላሉ ሶሲኒዮስ ኦሮሞ እንደሆነ አልተነገረም ይሉናል፡፡ ኧረ ባካችሁ ወደራሳችሁ ተመለሱ ለሞሆኑ ግን ዛሬ እኛ አማራ ናቸው አልናቸው እንጂ የትኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ነው ብሔሩ ተጠቅሶ ታሪክ የተጻፈለት? ምን አልባት አፄ ዮሐንስ? እሳቸውም ቢሆኑ አገሩ ትግሬ ይባል ስለነበር እንጂ ዛሬ የምናስበው የትግሬ ብሔረሰብ ለማለት አይመስለኝም፡፡ እንግዲህ ማስተዋል ከሌለን እንዲህ ነው የሚያረጉን፡፡

እኔ ደጋግሜ ስለኦሮሞ ጽፌያለሁ፡፡ ይገርመኛል፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ዛሬ ኦሮሞ ከተባለው ማህበረሰብ ታላላቅ መሪዎችና ጀግኖች እንደተነሱ ተጽፏል፡፡ አንድም ሳይቀር፡፡ በእርግጥ ነው ኦሮሞ ናቸው ተብሎ አደለም፡፡ የሚገርመው ግን የእነዚህ ጀግኖች ታሪክ እጅግ አስደማሚና ለዛሬው ትውልድ ማንነቱን ሊቀርጽባቸው የሚችሉ ምልክቶቹ ነበሩ፡፡ ከላይ እንደነገርኳችሁን ግን ትውልዱ የሐሰት ትርክት የጻፉለትንና ደጋግመው የሰበኩትን ተከትሎ አባቶቹን ጣለ ብቻም ሳይሆን እንደ ልዩ እርኩሰት ሆነው ተሳሉበት፡፡ በቃ ለማይረባ አእምሮ ተሰጠ፡፡ ዛሬ ለሚነግዱበት የአስተሳሰብ ባርነት ወድቆ መቼም ቢሆን ስለነዛ ታላላቅ አባቶች ከላተጸጸተ ከባርነት ላይወጣ እስከወዲያኛው ጠፍቷል፡፡ አሁን ማስብ አልተቻለም፡፡ አደጋ ላይ ነው ትውልዱ፡፡ ዛሬ የእነዛ አባቶች ታሪክና ምልክት ያስበረግገዋል፡፡ ኦሮሞ ዛሬ የእነዛ አባቶች ሰንደቅ የሆነችው የኢትዮጵያ ባንዲራን ሲያይ ይደነብራል፡፡ ይረበሻል፡፡ ሰሞኑን አደዋ እየተባለ ነው፡፡ የእነዛ ታላላቅ ጀግኖች መሪ ሚኒሊክ  ሥም ያስበረገግገዋል፡፡ ከጥላቻ አልፎ አሁን የአእምሮ ሕመም ሆኖበታል፡፡ ሰሞኑን በቡራዩ ባለፈውም ለጥምቀት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ጥለት የለበሱ የኦርቶዶክስ ተከታዮችን በጥላቻ እየተመረዘ የሰለጠነ ፖሊስ ተብዬ ሲደበደብ ነበር፡፡ አሁን ኦርቶዶክስም አማራም ከኦሮሞ እየተነጠለ ነው፡፡ ባዶውን ሲቀር የሚሆነውን ታዘቡ፡፡ ይሄ የአእምሮ በሽታ በጊዜ እልባት ካላገኘ ኦሮሞ የሚባው ሕዝብ ሊጠፋ እንደሚችል እሰጋለሁ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ኦሮሞ በተባለ ሕዝብ ላይ ሁሉም ጦርነት እንደሚያነሳ እሰጋለሁ፡፡ ይሄን ለማሰብ ነብይነት አይጠይቅም፡፡

የአሁን ጠ/ሚኒስቴር የሚጽፉትም ሆነ የሚናገሩት አደገኛ የሆነ ነገርን ቆም ብለው ቢያስቡበት አላለሁ፡፡ ቅድም እንደነገርኳችሁ ነው፡፡ ጀርግን (ማወናበጃ) ነገር አልወድም፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩ በቃላት ሕዝቡን ሊደልሉት ይሞክራሉ፡፡ በተግባር የምናየው አውነት ግን ከሚመጣው አደጋ በቅድሚያ ጠ/ሚኒስቴሩን ቀጥሎ ሌላውን የሚያድን አይመስለኝም፡፡ በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት የተበላሸ አእምሮን እያሳደጉና እያስፋፉ የቃላት ድለላ ከጥፋት አያድንም፡፡ በአለፉት ሶስት ዐመት አንድም ይሄ ነው የሚባል አገርን ወደማረጋጋት የሚወስድ በሕግ የታገዘ ለውጥ ሳይደረግ ይባስ በዚሁ አገርና ሕዝብን እያፈረሰ ባለ ሥርዓት ለመቀጠል እንደቆረጡ በግልጽ እናየለን፡፡ ከወያኔ ይምራሉ ብዬ ጠብቄ ነበር፡፡ ያሳዝናል፡፡ እስከዛሬ ሕገ-መንግስቱ የአፈጻጸም ችግር ነው ያለበት ለሚሉት አሁን ላይ በትክክል ሕገ-መንግስቱ እየተፈጸመ እንደሆነ ሁሉም ያስተውል፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት የሆነው በወያኔ 27 ዓመት እንኳን አልሆነም፡፡ በሀሉም ቦታ ዜጎች በማንነታቸው አሳቃቂ በሆነ ሁኔታ እየታረዱ ናቸው፡፡ የሕገ-መንገስት ተብዬው አፈጻጻም እንግዲህ ይሄ ነው፡፡ ዜጎች በፈለጉበት ቦታ እንዳይኖሩ አገሩን በብሔር የሸነሸነው ሕገ-መንግስት ዛሬ ብዙዎችን ለማረድ መብት ሰጥቷል፡፡ ይሄን ጠ/ሚኒስቴር ተብዬው ፍጹም እንዲቀየር አይፈልጉም፡፡ ዜጎች እንዲታረዱ ሕግ ሰርቶ በቃላት ለመደለል ይሞክራሉ፡፡ ከላይ እንደተናገርኩት እኔ ማወናበጃዎችን የሚቀበል አእምሮ የለኝም፡፡ ጠ/ሚኒሰቴሩ የሚያወሩትን ነገር እንደ እኔ ሆኖ ለሚሰማው እጅግ አሳፋሪ ነው፡፡ የቃላት ጋጋታ፡፡ በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የራሳቸው ሳይበቃ ብዙዎች ትውልድን የሚያደነዝዙ ግለሰቦችን አሰማርተዋል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ወጣቶች ሰብሰብ ስለ ነጻ አስተሳሰብ ሲሰብክ የነበረው ምህረት ደበበ የተባለ ግለሰብ በአሳዛን ሁኔታ የአስተሳሰብ ነጻነት በሚል የራሱን አስተሳሰብ ሲጭንባቸው እንደነበር ታዝቤያለሁ፡፡ ብዙ ተመሳሳይ ሰዎችን አሰማርቷል፡፡

በመጨረሻም ጠ/ሚኒስቴሩ እንደሚያወሩት ሳይሆን ከኋላ እያሴሩ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ዘላቂነቱ ላይ በራሳቸው ላይ እንደሚመለስ ሳስብ አዝናለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴር በማኒፌስቶ ሳይቀር የራሳቸውን እምነት ለማስፋፋት እንደተነሱ እናያለን፡፡ አዝናለሁ፡፡ ወያኔ በግልጽ በአማራ ላይ በጥላቻ ማኒፌስቶ ተነስታ ነው ዛሬ ሁሉንም አጥምቃ አማራ የሚለው ቃል ማስፈራሪያ የሆነበት፡፡ እንግዲህ ጠ/ሚኒስቴሩ ከታች የምታነቡትን የሚል ማኒፌስቶ አዘጋጅተው እንደመጡ አስተውሉ፡፡  ፕሮቲስታነቲኒዝም ለዲሞክራሲ አማቺ ሲሆን ሌሎች እምነቶች አይመቹም ይሉናል፡፡ እንግዲህ ይሄን እስከመጻፍና የሚመሩትም ፓርቲ ማኒፌስቶ እስከማድረግ ድረስ ለሚያሴሩት ሴራ በተግባር እየሰሩ ሲሆን የሚደልሉባቸውን የቃላት ጋጋታ ግን እንዷንም በተግባር ሲያደርጉት አላየንም፡፡  ሲጀምር በፕሮቲስታንቲኒዝም የበለጸገ አገር እኔ ከቶውንም አላውቅም፡፡ ዓለም ላይ ታላላቅና ምጡቅም አእምሮ ያላቸው አገራት ከእነጭርሱም ፕሮቲስታነት እምነት ተከታይ የላቸውም፡፡ ሌላ ቀርቶ በአሜሪካ እንኳን ታላላቅ የአእምሮ ባለቤቶች መሠረታቸው ኦሮቶዶክስ (ለምሳሌ ኒኮላስ ተስላ የባለ 300 ፓተንት ምጡቅ)፣ ሌሎቹ አይሁድና ካቶሊክ ናቸው፡፡ የሚገርመው ጀርመን በአብዛኛው የፕሮቲስታነት እምነት ተከታይ ሲሆን የጀርምን ትልቁ የሥልጣኔና ሐብት መከማቻ ግን በአብዛኛው ካቶሊክ የሆነው የበየርን ግዛት ነው፡፡ ባይርን ካልወሰነ መራሄ መንግስት እንኳን መኆን አይቻልም፡፡ እንግዲህ ከዲሞክራሲ አንጻር ከተባለ ዲሞክራሲን የሚያመጣው የምጣኔ ሐብት ልዕልና ነው፡፡ ሐብትን የሚያመጣው ደግሞ ማሰብ የሚችልና የሚሰራ ሲኖር ነው፡፡ እነ ጃፓት ከእነ ጭርሱም ክርስትናም እስልምናም አደሉም (ሴኤቶና ቡዳ ናቸው)፣ ቻይና እንደዛው ነው፡፡ ዛሬ እያደገች ያለቸው ሕንድ እንዲሁ፡፡ የዓለማችን ምጡቅ አእምሮዎች ያሉባት ራሺያ በአብዛኛው ኦረቶዶክስ ካልሆነ ሙስሊም ነው፡፡ እውነቱን እንነገጋር ከተባለ ደግሞ በኢትዮጵያም ለኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ከኢትዮጵያኖቹ እምነት ባለይ ፕሮቲስታንቲኒዝም የሚረዳ ሆኖ አደለም፡፡ ይልቁንም ፕሮቲስታንቲኒዝም በተለይም ደግሞ ወደ አፍሪካ የገባበት ሁኔታ በደንብ ሊጤን በተገባው፡፡ አብዛኛው ጥቁር በአንጻሩ የፕሮቲስታነት እምነት ተከታይ ነው፡፡ በሰሜን አሜሪካ የጥቁሮቹ እምነት ይሄው ነው፡፡ ይልቁንስ ፕሮቲስታንቲኒዝም ለጥቁሮች ማሰሪያ እንደሆነ እናያለን፡፡ በአብዛኞች በኢትዮጵያ የምናያቸው የፕሮቲስታነት እምነት ተከታይ ቦታዎችም መሠረታዊ የሕዝብን እሴቶች ሳይቀር ያጠፉ ናቸው፡፡ ይሄ በተለይ በአፍሪካ በልዩ ሁኔታ የተጫነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኢላማ የሆነችበት አንዱ ምክነያትም ሌሎች እንደልባቸው በአገሪቱ ለመግባት ወጥመድ ስለሆነችባቸው ነው፡፡ አብዛኛውን የአፍሪካ አገር በቅኝ ግዛት የወረሩት በክርስትና ስም ነው፡፡ የኢትዮጵያዋ ቤተክርስትያን ግን ቀደም ብላ በኢትዮጵያ በክርስትናው ዓለም ከሚያውቀውም በላይ  መሠረት ስለጣለች  ለቅኝ ገዥዎች አልተመቸችም፡፡ ሰሞኑን ለማክበር የምንዘጋጅለት አደዋ የማሸነፋችን ሚስጢር አንዱ ይሄ ነው፡፡ ጣሊያንም አማራና ኦርቶዶክስ ከዛች ምድር እስካልጠፉ ድረስ ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም ብሎ የተበለው ለዚሁ ነው፡፡ ዛሬ በአማራና ኦሮቶዶክስ ላይ የተከፈተውም ዘመቻ የዚሁ ሴራ አካል አንደሆነ ግልጽ ና፡፡ ከታች አብይ የዛሬው ጠ/ሚኒስቴር አብይ አህመድ የጻፈው ነው፡፡

454 የአማራ ኢትዮጵያ፣ የአማራ ሰንደቅ፣ የአማራ ሐይማኖት የአማራ ሽብሸባ – ሰርፀ ደስታ

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.