የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ድረስ 45 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዳስገቡ ተገለፀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ሀገራዊ ምርጫን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከተጠቀሱት ተግባራት መካከል አንዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ ይገኝበታል፡፡ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ከጥር 13-24 ድረስ የምርጫ ምልክት ማስገቢያ እና መወሰኛ ጊዜ እንደሆነም ተቀምጧል።

election 1ቦርዱ ለምርጫ ምልክት ማስገቢያ እና መወሰኛ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እስካሁን 45 ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዳስገቡ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስት ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በዚህም መሰረት፡-

1. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

2. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

3. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ – የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

4. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ

5. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

6. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር – ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል) ብለዋል፡፡

የምርጫ ምልክታቸውን ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

አብመድ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.