ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን  የሚሰጥ ፤የሚነሳ ማን ይሆን ? – ማላጂ

በቀደመ ዘመን በታሪክ አጋጣሚ ወራሪ ጠላት አገሪቷን (ኢትዮጵያን) በቅኝ ግዛት መደፍ ስር ለማድረግ በተደረገ ተደጋጋሚ ግብግብ ዕቢ ላአገሬ ዕቢ ለነጻነቴ ብለዉ የህይዎት እና የደም ዋጋ የከፈሉ ጅግኖች ኢትዮጵያዉያን መኖራቸዉን ጠላቶቻችን ሳይቀሩ የመሰከሩት ሀቅ ነዉ ፡፡

1280px Ethiopia 1991 1995.svg

በአንድ ወቅት የታላቋ አሜሪካ  ፌዴሬሽኖች ሊቀመንበር/ መሪ (president )የነበሩት ጆን .ኤፍ ኬኔዲ  ስለ አፍሪካ ሲናገሩ ጀግንነት፣ ድፍረት፣ልበሙሉነት፣ ቁርጠኝነት  ከ “ሚኒሊክ”  በላይ ማን ሊባል እንዳሉ እንረዳል ፡፡

በዳግም የኢጣሊ ወረራራ ጀግኖች እጅግ ተመጣጣኝ ባልሆነ የኃይል አሰላለፍ እና ኋላ ቀር መሳሪያ ከ፵ ዓመት በኋላ ለዳግም ወረራ ኢጣሊ  ኢትዮያ ስትገባ  ጀግኖች የጠላትን ኃይል መግቢያ መዉጫ ሲያሳጡ ስግብግቦች እና ራስ ወዳዶች የቻሉት ስደት ፤ያልቻሉት በየመንደሩ አንደ ፍልፈል አፈር (መሬት) ሲሻሙ እና ሲገፉ የነበሩት ከነጻነት በኋላ ተጠቃሚ እና ተሸላሚ(ሹም) ነበሩ ፡፡

ሆኖም በአምስት ዓመት የነጻነት ትግል ዘመን ከፍተኛዉን ተጋድሎ ያደረጉት ስመ ጥር የኢትዮጵያ ልጆች በዱር በገደል፣ ደጋ ቆላ ወጥተዉ ወርደዉ ዳር ድንበሯን፣ ነጻነቷን ያስጠበቁ ልጆች ወደ ግዞት ፣አስር እና ሞት ሲታጩ ከዚህ በተቃራኒ የነበሩት ሲሾሙ ፤ሲሸለሙ መኖራቸዉ ከታሪክ የምንረዳዉ ሲሆን ዛሬም በእኛ ዘመን የአገርን ዳንብር ያስደፈሩ፣ ሉዓላዊነትን ያሳነሱ፣ የህዝብ እና የአገር አንድነትን የበረዙ ፣ ዕዉነተኛ ታረክን የሰረዙ ፣የአገሪቷን አንጡራ ሀብት የመዘበሩ እና እየመዘበሩ ያሉት በስልጣን ላይ ስልጣን ፣በበደል ላይ በደል እንዲጨምሩ ተጨማሪ ማበረታቻ እና ይሁን ባይነት ሲያገኙ ማየት አዲስ ነገር አይደለም ፡፡

ምን አልባትም ዮፍታሄ ንጉሴ

ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ ፣

የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ !!! የሚለዉ የ ፻ ዓመት  ዘመን የዕድሜ ባለቤት ሊሆን ሩብ ፈሪ የኢትዮጵያን መገለጫ ዛሬም ስለሚታይ

ኢትዮጵያ ለሞቱላት እና ለኖሩላት የምትሆን አገር እንድትሆን የየጊዜዉ ባለጊዜ ኃላፊነት ሳይሆን ለህዝብ እና ለታሪክ ብሎም ለብሄራዊ አንድነት መሰራት አለበት ፡፡

የኢትዮጵያ የ፭ ዓመት (ከ 1928 አስከ 1933 ዓ.ም.) የነጻነት ትግል ቀንዲል የሆኑት እነ ደጃች   በላይ ዘለቀ  ባደረጉት ተጋድሎ የኢትዮጵያ ሠንቀደቅ ዓላማ ኦሜድላ(ጎጃም-መተከል) ንጉስ ከእንግሊዝ መልስ ከፍ ማድረጋቸዉ ጀግኖችን ብቻ ሳይሆን ቦታዉን ታሪካዊ እና ሊዘከር የሚገባዉ መሆኑን እንኳን አለማሰባችን ምን እንደሆነ አሁንም ወደ ኋላ ተመልሰን ወደ ፊት ልንደረደር እንደሚገባ ማሳያ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሥህነ - ቤዛ! ቅኝተ - ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ! - ከሥርጉተ ሥላሴ

የኋላዉን እያሳነሱ የወደፊት ታላቅነት ተረት እንጅ ዕዉነት አይሆንም ፡፡

ለዚህ መነሻየ በቅርቡ ስለቀድሞዉ የአገራችን መሪ  ጓድ ሊቀመንበር /ከሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ስለሚባሉ እና ስለሆኑት ዞትር የሚሰማንን እና ወደ አገር ቤት የመመለስ ጉዳይ ብዙዎች ብዙ ሲሉ ይስተዋላል ፡፡

ለመሆኑ ለአንድ አገር ዜጋ ለዚያዉም ከልጅነት አስከ ዕዉቀት አገራቸዉን በሙሉ አገራዊ ፍቅር ፣ወኔ እና ለአገር አንድነት እና ልማት ከፍተኛ ስራ የሰሩትን ኢትዮጵያዊ መሪ ለአገራቸዉ አፈር እና ምድር የመከልከል እና የመስጠት ጉዳይ ፈቃድ እና ይሁንታ የሚጠየቅ አለ ወይ ፡፡

ርግጥ ነዉ በአስተዳደር ዘመናቸዉ ሁሉንም ያስደሰተ ተግባር ወይም በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የህዝቦች ብሄራዊ ጥቅም ላይ ለመቆም እና የራሳቸዉን እና የጡት አባቶቻቸዉን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሌት ተቀን ሲባዝኑ እና እየባዘኑ ላሉት ኮ/ልም ሆኖ መንግስታቸዉ የጎረሮ አጥንት እንደነበሩ ዓለም እና የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉያን ጠላቶች ጠንቅቀዉ የሚያዉቁት ነዉ ፡፡

እዚህ ጋ በ1966 ዓ.ም በነበረዉ ህዝባዊ የለዉጥ ጉዞ በታሪክ አጋጣሚ የህዝብን ብሶት እና ዕቢ ባይነት ተገን በማድረግ የዉስጥ እና የዉጭ ኃይሎች ለድብቅ ዓላማቸዉ ሴራ በዕብሪት እና በማንአህሎን አመለካከት በለዉጥ ሂደት ግንባር ቀደም ዕንቅስቃሴ የነበረዉን የጦር ኃይል በማጥላላት እና በማሳነስ የተደረገዉ ትንቅንቅ እና ጊዚያዊ አስተዳደሩም የህዝባዊ ንቅናቄዉን እና አገሪቷን ከመበታተን ለመታደግ የመከላከል ጥረት ስህተተቶች አልነበሩም አይባልም ፡፡

በአገር አንድነት ፣በህዝቦች አብሮነት ፣ በሰባዊ መብት ረገጣ ሆነ አጠቃላይ የአገሪቷንም ሆነ የህዝብን ክብር በማዋረድ እንዲሁም በዓለም ታሪክ ለምንኖርበት ክ/ዘ የማይመጥን በራስ አገር እና ህዝብ ከፍተኛ ዕልቂት ፣ ሞት ፣ስደት ፣ድህነት ፣ረሃብ ፣ቸነፈር ፣ ኢሰባዊ ድርጊት እና ከርዕዮተዓለም ልዩነት ዉጭ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ማንነት እና ይዘት በህዝብ ላይ በደል የተፈፀመዉ በማን እና በየትኛዉ ስርዓት እንደሆነ ብናዉቅ የመሪዎቻችንን አይደለም የማንም ኢትዮጵያዊ ጥፋቱ በጥፋትነቱ ይታያል እንጅ ተፈጥሯዊ መብቱን መከልከል የሚቻለን እና እነ ማን ነን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፖለቲካ እውነትም ሸር…ጣ  ነው! - ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ደግሞስ እንኳን ለኢትዮጵያ አንድነት እና ብልፅግና የሰሩት መሪ በቂ ጥበቃ ፣ ክብር እና ግምት ብንሰጣቸዉ ከርሳቸዉ ትዉልድ እና አገር ይማርበታል እንጅ ምን እናጣበታለን ፡፡

ከለዉጥ ማግስት መጋቢት 24/2010 ዓ.ም.ወራት በኋላ መስከረም 2011 ዓ.ም አካባቢ ይመስለኛል ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ የቀድሞዉ የኢህዴግ ባለስልጣኖች ፣ የኤርትራዉ ፕ/ት …….ሲጋበዙ  ኮ/ል መንግስቱን ተገቢዉ ክብር እና ጥበቃ አድርጎ መጋበዝ የዕኛን ፣የህዝባችንን እና የመንግስታችንን አርቆ ተመልካችነት የሚያሳይ አንዲሁም በዓለም ፊት ከጥላቻ እና ከአድርባይነት ወጥተን ዕዉነተኛ ማንነታችንን መረጋጋጫ እንጅ ምን ይሆን ነበር ፡፡

ዕዉነት ከላይ በወቅቱ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ከተጋበዙት እና ከከ/ል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ለአገገራችን እና ለህዝባችን በዕዉነት እና በዕዉቀት የሰራ አይደለም የዕርሳቸዉን 1/5 ኛ የሚሆን ነበር ፡፡

በስርዓቱ ያልደረሰን ቢሆንም በስርዓቱ የተሰሩትን እና በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚታዩትን እና ዛሬ በግል ባለሀብትነት ስም የጥቂቶች መፈንጫ እና ማላገጫ የሆኑነትን የአገሪቱን እና ህዝቦች ሀብት ለሚመመዘብሩት ጥበቃ እና ከለላ ለምሰጥ አገር እንዴት ለባለቤት ትነፍጋለች፡፡

ርግጥ ነዉ ከ/ል መንግስቱም ሆኑ ቀደምት መሪዎች ወገን/ህዝብ እንጅ ብሄር አልነበራቸዉም አያዉቁም፣ በአገራዊ ፍቅር እና ክብር አይደራደሩም ነበር ፣ በአገር ዳር ድንበር ፣ በባህር በር ለስልጣንም ሆነ የራሳቸዉን አገር እና ህዝብ ለመበቀል ሊስማሙ የሚችሉ አልነበረም ፡፡

እነርሱ ቤተሰባቸዉ የህዝብ ልጅ እንጅ ብሀረሰብ ወይም የመንደር ልጅ ወይም ያብራክ ክፋይ ብቻ ነዉ ብለዉ አስበዉ ፣ሰርተዉ ሆነ አሳይተዉ አያዉቁም ፡፡

ኢትዮጵያን ከነሙሉ ማንነት ለማስጠበቅ የህይወት እና ደም ዋጋ የከፈሉትን በማግለል አገር እና ህዝብ ያደሙትን ማባበል እና ማግተልተል አስከመቸ እንደሚቀጥል ባይታወቅም መሪዎችን በጎ ተግባር  እና ምግባር በመደበቅ በጥላቻ እና በአድር ባይነት ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ ማንነት እና ዕድገት ማሰብ አጉል ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅማንት ጉዳይ | ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ኢትዮጲያዊነት ኢትዮጲያዊነት አይደለም

ጥበቃ እና የደህንነት ዋስትናስ ቢሆን እንኳን ለኢትዮጵያዉያን መሪዎች አይደለም ኢትዮጵያን እና አንድነቷን አሳልፈዉ ለሰጡ እና አሁን አገሪቷ እና ኅዝቧ ለሚገኙበት ፍዳ እና ዕዳ ለዳረጉት እንኳ እየተደረገ አይደለም ፡፡

ከዚህም በላይ የምንላቸዉ አሉ ግን ሠዉነትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት እየኖሩ ማሳየት እንጅ በግላጭ  ብንናገር  ግዑዝ ለሆነ ዕርባና ቢስ  ነገር የአገር ሀብት እና ንብረት ለሚባክንባት እናት አገር ለዕዉነተኛ እና የቁርጥ ቀን ልጆች አፈር ስትከለክል የመጀመሪዋ እንዳልሆነም ብዙ ማሳያወች አሉ ፡፡

የሆነዉ ሆኖ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መሪ መንግስቱ ኃይለ ማርያም በአገር አንድነት እና በህዝብ ጥቅም ላይ ያላቸዉ አቋም ፣ አርቆ ተመልካችነት እና የኢትዮጵያን ሁኔታ እና የጠላት ምኞት ከግማሽ ክ/ዘመን አስቀድሞ በግልፅ እና በማያሻማ ሁኔታ መናገራቸዉ እና ይህም በአገራችን ላለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት እና አስካሁን እየታየ  መሆኑ መሪ ብቻ ሳይሆን ትንቢተኛ ስለሚያሰኛቸዉ ይህን በጎ ስራ እና ዕይታቸዉን ብቻ ሳይሆን ስማቸዉ ሲጠቀስ የሚያቅለሸልሻቸዉ መኖራቸዉን ከ 10ዓመት አስቀድሞ በተግባር እናዉቀዋለን ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ መንግስት እና ይህ የዕኛ ትዉልድ ግን መቸም የሰዉ ልጅ እንደ ሸክላ ተሰባሪ ፤ እንደ አበባ ረጋፊ ነዉ እና በአገር መሪነታቸዉም ሆነ በግል ህይወታቸዉ ስለዚች አገር የሚሉት እና የሚያስተምሩት እጅግ ብዙ ብዙ ስላለ፣ስለሚኖር ይህን ዕድል ማጣት ስለማይገባ በክብር እና በፍቅር ለአገራቸዉ እና ለሚወዱት ህዝብ በቀሪ ዕድሜያቸዉ የሚሉትን ለታሪክ እና ለትዉልድ እንዲያስተላልፉ ቢሆን ምኞቴም ፤ፍላጎቴም ነዉ፡፡

በመጨረሻም አገርን የሚሰጥ እና የሚነሳ ማን ይሆን ? አስኪ ይጠየቅ  ! እንጃ ብቻ  በኮሚቴ እንዳንል !!!

ምንጊዜም እናት ፤አገር !!!

ማላጂ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.