የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ 

በተስፋለም ወልደየስ

Kebour Ghenna Ahadu TV 696x436 1  የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ክቡር ገና፤ በመጪው ምርጫ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን ወክለው በአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመወዳደር በዕጩነት ቀረቡ። በኢዜማ የመሪነት እና የምክትል መሪነት ስልጣን ያላቸው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዷለም አራጌ፤ ለተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመመረጥ ከሌሎች የፓርቲው እጩዎች ጋር በነገው ዕለት ይፎካከራሉ።

ኢዜማ፤ ፓርቲውን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤትም ሆነ ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የሚያስመርጠው፤ በየምርጫ ወረዳዎቹ ባሉ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት በሚሰጥ ድምጽ ነው። ፓርቲው አሉኝ ከሚላቸው 435 የምርጫ ወረዳዎች ውስጥ በ329ቱ የዕጩዎች ምርጫ አካሄዶ ማጠናቀቁን አስታውቋል። በዛሬ እና በነገው ዕለት ደግሞ በ71 የምርጫ ወረዳዎች የዕጩዎች ምርጫ ለማካሄድ ቀነ ቀጠሮ ይዟል።

ezema  የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ 

በነገው ዕለት ከሚካሄዱ የፓርቲው የምርጫ ዕጩዎች ፉክክር ውስጥ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረጉቱና ዕውቅ ግለሰቦች የሚሳተፉባቸው ውድድሮች የሚጠበቁ ሆነዋል። ከዚህ ቀደም ከኢዜማ ጋር በተያያዘ ስማቸው ተነስቶ ከማያውቀው ከአቶ ክቡር ገና በተጨማሪ ቀድሞ በግብርና ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታነት አገልግለው የነበሩት ዶ/ር በላይ በጋሻው በነገው የዕጩዎች ምርጫ እንደሚሳተፉ ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አቶ ክቡር ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ለመወዳደር በዕጩነት የቀረቡት በሚኖሩበት ወረዳ 21 እና 22 ነው።  የፓርቲው ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት አቶ ክቡር ኢዜማን በአባልነት የተቀላቀሉት ከሁለት ሳምንት በፊት ቢሆንም እርሳቸውን ለማግባባት ጥረቶች ሲደርጉ የቆዩት ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ ነው።

ኢዜማ “ለምክር ቤቶች የሚደረጉ የዕጩዎች ውድድርን” አስመልክቶ ያወጣው ህግ፤ አባል ከሆኑ ስድስት ወር ያልሞላቸው አባላት የመመረጥም ሆነ የመምረጥ መብት እንደሚኖራቸው ይደነግጋል። እነዚህ አዲስ አባላት ይህን መብት ለማግኘት ግን ወደ ኋላ ተመልሰው የስድስት ወር የአባልነት መዋጮ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ያትታል። ኢዜማ ይህን አካሄድ የተከተለው፤ ፓርቲው ከተመሰረተ አጭር ጊዜ አንጻር “ስድስት ወር ያልሞላው አባል መምረጥና መመረጥ እንዳይችል ማገድ የፓርቲውን የተሻሉ ዕጩዎች የማቅረብ አቅም የሚያጠብ በመሆኑ” እንደሆነ በህጉ ላይ አብራርቷል።

Dr Belay Begashaw  የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ 
 የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ  1

የዚህ ህግ ተጠቃሚ የሆኑት ሌላኛው ዕጩ ዶ/ር በላይ በጋሻው ናቸው። መኖሪያቸውን ለበርካታ ዓመታት በአሜሪካ ያደረጉት እኚሁ ተወዳዳሪ፤ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ በማሰብ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ፤ ኢዜማን በአባልነት የተቀላቀሉት የዛሬ ወር ገደማ መሆኑን የፓርቲው ምንጮች ተናግረዋል። ዶ/ር በላይ ኢዜማን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በተወዳዳሪነት ለመቅረብ የሚፎካከሩት በአዲስ አበባ ወረዳ 15 ነው።

ኢዜማ እንደ አቶ ክቡር እና ዶ/ር በላይ አይነት “በስራቸውም፣ በልምዳቸውም” የሚታወቁ ግለሰቦችን በመጪው ምርጫ በተወዳዳሪነት ለማሳተፍ ለበርካቶች ጥያቄዎች አቅርቦ እንደነበር የሚናገሩት አንድ የፓርቲው ምንጭ፤ ሆኖም ብዙዎቹ የፓርቲውን ጥያቄ ሳይቀበሉ በመቅረታቸው ጥረቱ ሳይሳካ መቅረቱን አስረድተዋል። ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፤ ፓርቲው በዚህ ምርጫ በህዝብ ዘንድ ከሚታወቁ ሰዎች ይልቅ፤ በሚኖሩባቸው አካባቢዎች አስፈላጊ ለሆኑ ሰዎች ይበልጥ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል።

ባለፉት ሳምንታት በተካሄዱ የዕጩ ተወዳዳሪ ምርጫዎች ኢዜማን እንዲወክሉ ከተመረጡት ውስጥ አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከ40 ዓመት በታች መሆኑ የጠቀሱት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው፤ ይህም ፓርቲው “ለወጣቶች እና የመስራት ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የሰጠውን ቦታ ያመለክታል” ብለዋል። በዕጩ ተወዳዳሪነት ከተመረጡት ውስጥ አብዛኞቹ “ትምህርት ቀመስ” መሆናቸውንም አክለዋል።

Yeshiwas Assefa 2000x1125  የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ 
 የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ  2

ኢዜማ እያካሄደው ባለው የዕጩዎች ምርጫ፤ በፓርቲው መዋቅር ውስጥ ቁልፍ ቦታ የያዙ ግለሰቦች በተወዳዳሪነት ሳይሳተፉ ቀርተዋል። ከተወዳዳሪነት ውጪ እንዲሆኑ ከተደረጉት ውስጥ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ ምክትላቸው ዶ/ር ጫኔ ከበደ እንዲሆም የፓርቲው ዋና ጸሀፊ አቶ አበበ አካሉ ይገኙበታል።

የፓርቲዎቹ አመራሮች በምርጫው የማይሳተፉት በፓርቲው ህገ ደንብ በተቀመጠባቸው ክልከላ ምክንያት እንደሆነ አቶ ናትናኤል ተናግረዋል። ከእነርሱ በተጨማሪ የፓርቲው የምርጫ ወረዳዎች በሊቀመንበርነት፣ በምክትል ሊቀመንበር እና በጸሀፊነት የሚያገለግሉ አመራሮችም በህገ ደንቡ መሰረት በተወዳዳሪነት እንደማይሳተፉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስረድተዋል። የኢዜማ ህገ ደንብ ከምርጫ ተሳትፎ የማያግዳቸው የፓርቲው መሪ እና ምክትላቸው ግን በነገው ዕለት በዕጩዎች ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።

የኢዜማ መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በመኖሪያቸው ወረዳ 23፤ ፓርቲውን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩነት ለመቅረብ ከሌሎች ሶስት የፓርቲው አባላት ጋር ነገ እሁድ ይወዳደራሉ። የእርሳቸው ምክትል የሆኑት አቶ አንዷለም አራጌም ተመሳሳይ ቁጥር ካላቸው ተፎካካሪዎች ጋር በወረዳ 12 እና 13 ለምርጫ ይቀርባሉ።

Dr Berjanu Nega   የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ 
 የኢዜማ መሪ እና ምክትላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ለመወዳደር ነገ በየምርጫ ወረዳዎቻቸው ይፎካከራሉ  3

እያንዳንዱ የፓርቲው የምርጫ ወረዳ፤ ለተወካዮች ምክር ቤት በዕጩ ተወዳዳሪነት የሚያሳልፈው አንድ ግለሰብ ቢሆንም በወረዳ 24 ግን በተቃውሞ ፖለቲካ ዝና ያላቸው ሁለት ግለሰቦች ለምርጫ እንደሚወዳደሩ ታውቋል። ተወዳዳሪዎቹ ዕውቁ ኢኮኖሚስት ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ እና በርካታ ዓመታትን በእስር ያሳለፈው ክንፈሚካኤል አበበ (አበበ ቀስቶ) ናቸው።

በአንድ ወቅት ብቸኛ የተቃዋሚ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ፤ ኢዜማን ወክለው በድጋሚ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ለመግባት በሚቀጥለው ሳምንት በሚኖሩበት ወረዳ 6 ከሌሎች ፓርቲ አባላቶች ጋር እንደሚፎካከሩ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የዕጩዎች ምዝገባ ከየካቲት 8 እስከ 21 ባሉት ቀናት ይካሄዳል። ዕጩዎቹ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወይም የምርጫ ዘመቻ እንዲያካሄዱ የተፈቀደላቸው ከየካቲት 8 እስከ ግንቦት 23 ባለው ጊዜ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

2 Comments

  1. Berhanu Nega was placed in Woreda 23 by Abiy Ahmed because Abiy Ahmed himself used to reside in Woreda 23 before he became a PM, that is how Abiy personally knows who is who in Woreda 23 , Abiy definitely knows he needs to win Woreda 23 from Balderas to keep his base in Addis Ababa intact ,because you can say Woreda 23 had been donating money to any initiatives he came up with no questions asked. Without Woreda 23 Abiy is just another OPDO from Bashasha but Woreda 23 gives him an identity of an Addis Ababaian since Abiy resided in with neighbors he befriended with in Woreda 23 for many years having children and raising children in the past . For Abiy Ahmed Woreda 23 means a big deal so to infiltrate the Woreda 23 Prosperity Party supporters and the non Prosperity Party supporters he placed Bethanu Nega in Woreda 23. Either way as long as Balderas or other parties (except Ezema and Prosperity party) win Woreda 23 Abiy Ahmed is in the clear

  2. በወያኔ ትህነግ ዘመን ወደ ነፈሰው ሲነፍሱ የነበሩ ህሊናቸው ያውቀዋል፡፡ በዛን ጊዜ እኮ ትምህርት ወይም ችሎታ ለመሾም መስፈርት አልነበረም የፖለቲካ ታመኝነት እንጂ ታዲያ ማነው ያለ ሹመት ሲያለግል የነበረ፡፡ የኢትዮጵያ እና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ክቡር ገና ለመወዳደር መቅረባቸው ችግር የለውም ነፍሳቸውን ይማረውና እንደነ ፕሮፌሰር መስፍን መሪዎችን ባይሞግቱም አንዳንድ በሚሰጡት ለዘብ ያለ ሃሳብ ህዝብ ያውቃቸዋል፡፡ አሁን ስልጣን የሚፈለግበት ዘመን አይደለም ሕዝብን እወክላለው የሚል እጩ ከዚህ በፊት ሲሰራው የነበረው ግፍ ለህዝብ ተናዞ በንፁህ ህሊና የተጎዳውን ህዝብ ለመካስ ከተወዳደረ እሰየው ነው፡፡

    አዳዲስ የኢዜማ ተፎካከሪዎችም ከዚህ በፊት ከነበሩ ብልሹ አስተዳደሮች ብዙ ተምረው ለዕጩ ተወዳዳነት መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምን አይነት ፓርላማ እና ምክር ቤት እንደነበረን እኮ የሚታወቅ ነበር ማጨብጨብ ብቻ ነበር ለቁጥር ማሟያ፡፡ ይህ ይቀየር በሚል ህዝቡ በተስፋ ይጠብቃል፡፡ በእጩነት ወረዳዎችን ለመሸፈን ግን ገና ይቀራል/Coverage/ በሁሉም ወረዳዎች እጩ ቢኖራችሁ ጥሩ ነው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.