ኮለኔል መንግስቱ ሐ/ማርያም  ወደ ሀገራቸዉ ይመለሱ ለዉይይት የቀረበ ሀሳብ – ሰመረ አለሙ

mengistuየኢትዮጵያ ተማሪዎች በወቅቱ ቅድመ 1966 ማለት ነዉ አገር መበጥበጥና ትምህርትን ማቆም እንደ ዘይቤ ወስደዉ እግረ መንገዳቸዉን የሶሻሊስት ርእዮተ አለም የሚጠይቀዉን መስፈርት ለማሟላት ዋና ተዋንያኑን ባሌጎባ  በብድርና በቤተሰብ ጠብ ሸፍቶ ለዚያድ ባሬ ያደረዉን ጸረ ኢትዮጵያ ሐይል ዋቆ ጉቱን  የባሌ የገበሬዎች አመጽ መሪ አድረገዉ በመሳል  ጭቆና አንገሺግሿቸዉ ገበሬዎች ሸፈቱ ሲያስብሉ፤ ከሰሜን የመጡት እነ አረጋዊ በርሄ፤ስብሀት ነጋና መሰሎቻቸዉ ደግሞ ቤተሰቦቻቸዉ ለጠላት በማደራቸዉ የኢትዮጵያ አንድነትና ጀግንነትና  ስላኮሰሳቸዉ ለበቀል ሲነሱ፤  ኦነጋዉያኑ ደግሞ ታላላቅ የኦሮሞ ጀግኖችን ገድል በማሳነስ ተጨቁናችሗል ተብሎ ስለተነገራቸዉ ዶ/ር መራራ እንደሚሉት ደግሞ  ፈረንጂ ከብስኩት ጋር የኢትዮጵያን ጥላቻ ስለመገባቸዉ አይቅርብን በማለት  የጥፋት ጎራዉን ተቀላቅለዉ ሀገራቸዉ ኢትዮጵያ ላይ በጋራ አመጹ። ለነገሩ ሁሉም አልቀዋል ያሉትም አሉ ማለት አያስችልም ኢትዮጵያ ግን ቀጥላለች።

ለዚህ ንቅናቄ ከተጨቋኝ የኦሮሞና የትግሬ ጎሳ ሲመረጥ ከጨቋኝ ደግሞ  አማራ ተብሎ ተፈረጀ። ለዚህም ዋለልኝ መኮንን የተባለ እይታ ፈላጊ ሻቢያ  ጽፎ የሰጠዉን ወረቀት  በሴት ጓደኛዉ በማርታ መብርሀቱ (ኤርትራዊት) ተደፋፍሮ እዉነትነት የሌለዉን ታሪክ ነዛ።ስራቸዉ በጠላት ቅኝት የተቃኘ በመሆኑ ዋለልኝም፤ ተከታዮቹም፤ ተልእኮዉም ኢትዮጵያ ላይ በመሸፈታቸዉ እንደ ማይሆኑ ሁነዉ ቀሩ ። ኢትዮጵያ ግን ከአምላኳ ጋር ዛሬም ቀጥላለች  እንሱን ተከትሎ የመጣዉ ዳፋ ግን ዛሬም መቋጫ  አልተገኘለትም የባህር በሯም ተቀምጧታል በተከታታይ ያየናቸዉ መሪዎች በተለይም ከደርግ ዉድቀት በሗላ የሌላ ሀገር መሪ እንጂ የሀገራቸዉ መሪ አይመስሉም።

20171209 map502የኢትዮጵያ ጠላቶች ተማሪዎቹን ተጠቅመዉ  ያቀረቡት ዘገባና ትንታኔ እዉነትነት አለዉ  ወይ ተብሎ ዶናልድ ሌቪ ስለ ኢትዮጵያ ልዩ ምርምረ ያደረገዉ አሜሪካዊ  መልስ ሲሰጥ  የሶሻሊስትን ርእዮተ አለም ትግል የተሟላ ለማድረግ ጨቋኝና ተጨቋኝ መኖር ስላለበት ያለ በቂ ምክንያት ጨቋኝነትን   አማራዉ ላይ ጫኑበት  በማለት”ታላቋ ኢትዮጵያ” በሚባለዉ መጽሐፉ ላይ ሲገልጸዉ ፍረጃዉንም እጅግ ነዉረኛ ብሎታል።እንግዲህ  ልብ በሉ አሜሪካዊዉ ዶናልድ ለቪ ከአማራዉ ጋር  ኑሮ፤ ደበሎ ለብሶ ፤ አማርኛን አጥንቶ ኢትዮጵያን ከዉስጥ ወደ ዉጭ ከዉጭ ወደ ዉስጥ ያጠና ምሁር ነበር አፈሩ ይቅልለዉና።

እንግዲህ ከጉዳዬ በዚህ ተንደርድሬ ወደ ሚቀጥለዉ ሳዘግም እንዲህ እዉር ድምብሩ በጠፋበት ጉዞ ተማሪዎቹ ኮለኔል መንግስቱን ቆራጡ መሪ በማለት የሌላቸዉን እዉቀትና አርቆ አስተዋይነት በማጉላት የልብ ልብ ስለሰጧቸዉ  ኮለኔሉም ለካ ለራሴ እንዲህ  ባዳ ሁኜ ነበር በማለት እራሳቸዉን ካዋቂዎች ጎራ መድበዉ  ተቀናቃኞቻቸዉን በማስወገድ ትርክቱን ቀየሩት (ቆራጥነት ወደ ቆራጭነት ተሸጋገረ ማለት ነዉ)። እንግዲህ ሃሳባችንን ሰብሰብ አድርገን ስለሳቸዉ ለማዉራት እንጂ የደርግማ አመሰራረት እንደሚባለዉ ከየክፍለ ጦሩ ተመርጠዉ የተላኩት አዋኪዎችና በጥባጮች ከመሆናቸዉም በላይ ትንሺ በእዉቀትና በእድሜ የበሰለ ገብቶ ሚዛን እንዳያስጠብቅ ኢተዮጵያን ሲፈርድባትየምልመላዉ መስፈርት የበታች መኮንን ብቻ ነበር የሚለዉ ። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ነዉ ነበልባሉ መንግስቱ ሐይለ ማርያም ምድባቸዉ እረፍት እንዲያገኝ ከሞቱም ግልግል ነዉ በማለት ወደ ረመጡ የላካቸዉ።  በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከክፉ ስራቸዉ ተዳብሎ ሶሻሊስት ነኝ ብለዉ የምእራብ ሀገሮችን አስኮረፉ መቼም አሜሪካ ደካማ ነዉ ብላ ንቃ የምታልፈዉ ባለመኖሩ በመጨረሻ ገዝግዛ ጣለቻቸዉ ከዚያም አንድ ሰዉ እስኪቀር ያሉት ከሰዉ ሁሉ ቀድመዉ አገር ለቀዉ ወጡ።

mengistu 2

ኮለኔል መንግስቱ በግንዛቤያቸዉ ለሀገሬና ለአንድነት የሚበጀዉ ይህ ነዉ በማለት አንዴ የሀገራቸዉን ዳር ድምበር ለማስከበር ከጠረፍ ጠረፍ ሲባክኑ በሌላ ጊዜ ደግሞ ከወዲያ ወዲህ ብለዉ በዳሸቀ ኢኮኖሚያችንና የምእራቡ አለም ፊቱን ባዞረብን ጊዜ ባቅማቸዉ ኢትዮጵያን ሊያቀኑ ጥረዉ ነበር።  በትምህርት ትልቅ እርምጃ ሲያደርጉ በኢኮኖሚዉም እርባና ያለዉ ስራ ለመስራትም ሞክረዉ ነበር። የኢትዮጵያ ወጣቶች ደምና አጥንታቸዉ ሳይቆጠር በዉጤታቸዉ መስፈርት ብቻ ወደ ተለያየ ሀገሮች በገፍ ተልከዉ ሲማሩ ቤተሰቦቻቸዉ አገርን ሲከላከሉ ዳር ድምበር ለወደቁ ህጻናት ልዩ እንክብካቤ በማድረግና ወደ ባህር ማዶ በመላክ የጀግኖች ልጆችን አስታዉሰዋቸዋል እነሱም አባታችን ይሏቸዋል።

ነገረን ማየት በዘረፉ ነዉና  ኮለኔል መንግስቱ  በዘመነ ግዛታቸዉ ገንዘብ አሸሺተዉ የተንደላቀቀ ኑሮ ኑረዉ አልታዩም ለልጆቻቸዉም እንደ ህወአት ባለስልጣናት በየሀገሩ ሚሊዮን ዶላሮች ህንጻና ሌላም ነገር  አልተዉላቸዉም ። ደቀ መዝሙሩ እንደ መምህሩ እንዲሉ ሹሞቻቸዉም ዘመድ ለመጥቀም ተሳቅቀዉ በስልጣን ዘመናቸዉም ቤትም በግላቸዉ ሳይሰሩ ለመኖራቸዉ ቋሚ ምስክር ነዉ። ብርሀኑ ባዬህ የደርጉ ሁለተኛ ሰዉ መሰሉኝ የርሳቸዉ የእናትና አባት ልጅ የሆነችዉ ጭነት ማመላሰሻ ዉስጥ ሰፕላይ ክፍል መሰላል ላይ እየወጣችና እየወረደች የታዘዘዉን የመኪና እቃ ሰትሰቅል ስታወርድ ላያት ሴት በመሆኗ ብቻ ያንን አድካሚ ስራ በመስራቷ ያያት ሁሉ  ከልቡ ያዝን ነበር። ለጠየቋትም ምነዉ ወንድምሺ  አንድ ቦታ ቢፈለግልሺ ተብላ ስትጠየቅ በዚህ የመጣ ይቅርታ የለዉም እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ መኖር ነዉ ያለባችሁ እንደሚላት በጊዜዉ ተናግራ ነበር ከዚህም አልፎ እናታቸዉንም የሚረዱት ሌሎች ወንድሞቿ መሆናቸዉን መስክራለች ዛሬም በህይወት ካለች ይህንን ማረጋገጥ ትችላለች።

DjiG3k7XsAE0ladታዲያ ይህን ነገር ገልብጠን የትግሬ መሳፍንቶችን ስናያቸዉ የዘረፉት ንብረት ይህ ነዉ ብሎ ከመናገር ያልዘረፉትን መቁጠሩ በእጅጉ ይቀላል። ዶ/ር አብይም አባዱላን ለማዳን ብሎ እነዚህ ሰዎች የዘረፉትን ገንዘብ በሰልጣን ዘመናቸዉ ላደረሱት በደልና ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ቢወተወትም  ጆሮ ሊሰጠዉ አልፈለገም። ባጠቃላይ ሀገሩም ሆነ ህዝቡ የራሱ ሳይሆን ለ30 አመት የነዚህ የትግሬ መስፍኖች ንብረት ሁኖ ቆይቷል። በቅርቡ እንኳን ጦሩ እንደ ክርስቶስ ምሳሌ ሊሆን እግራቸዉን ቢያሻቸዉ ጥጋባቸዉ እስረኝነታቸዉን  አስረስቷቸዉ የሚያሳዩት ስነ ምግባር አሁንም ብዙ እንደሚቀራቸዉና በልባቸዉ በቀልን እንደ ሰነቁ ያሳያል።

እንግዲህ ይህን ካልን በሗላ ኮለኔል መንግስቱ በሀብት ዘረፋ እንደማይታሙ እንደዉም የኩዌት መንግስት አረብ ጠግቦ ሲደባደብ ለኩዌት በክፉ ቀን ኢትዮጵያ በመድረሷ በስማቸዉ የተሰጣቸዉን 20 ሚሊዮን ዶላር ቼክ ኢትዮጵያ ለችግሯ ትጠቀምበት በማለት ከናይሮቢ ለደመቀ ባንጃዉ ሰጥተዉት ወደ ኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ገብቶ ህወአቶች መከፋፈላቸዉ ተዘግቧል።ይህን ገንዘብ አዜብ መስፍን ወይ ስብሀት ነጋ ወይ አንዱ መስፍን ትግሬ ቢያገኘዉ ምን ሊያደርገዉ እንደሚችል መገንዘብ አይቸገርም። እንግዲህ  ኮለኔል መንግስቱ በዝርፊያ ካልታሙ የሚቀጥለዉ መተሳሰቢያችን በሳቸዉ መሪነት  ስላለቀዉ ዜጋ ነዉ።

ስብሀት ነጋ፤ስዩም መስፍን፤ሌንጮ ለታ፤ዳዉድ ኢብሳ፤ዲማ ነገዎ፤ታምራት ላይኔ፤በያን ሱጳ፤አረጋዊ በርሄ፤ጁዋር መሀመድ፤ሺመልስ አብዲሳ፤ግደይ ዘርአጽዮንን የመሳሰሉ ነብስ በላ ፋሺስቶች አንድም በፕሬዚዳንታዊ አቀባበል ተለምነዉ ወደ ሀገር ገብተዉ  መኖሪያና ቀለብ ተሰፍሮላቸዉ ሲኖሩ ሲሾሙ ስናያቸዉ  ኮለኔል መንግስቱ በተፈጠሩበት አገር ገብተዉ እንዳይኖሩ መከልከላቸዉ አግባብነት ያለዉ አይመስልም። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ወንጀለኞች ትንሺ ሺፍታ ሁነዉ ይህን ሁሉ ወንጀል ከፈጸሙ እንደ ኮለኔል መንግስቱ በትረ ስልጣን ቢጨብጡ ምን  እንደሚችሉ  መገመት አያዳግትም።;

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ክፉ ወንጀለኞች በክብር የሚያስተናግድ መንግስት  በ100 000 ለሚቆጠሩ ወጣት ኢትዮጵያዉያን እልቂት ምክንያት የሆነዉ ኢሳይያስ አፈወርቅ በኢትዮጵያ ምድርና ሰማዩ ላይ ሲዋልልበት መንግስቱ ሐይለ ማርያም ከበቂ በላይ ደጋፊ ያላቸዉ በሰዉ ሀገር መቆየታቸዉ አግባብ ስለማይሆን ለሌሎች ወንጀለኞች የተሰጠዉ ምህረትና  ለሳቸዉም ሊደርስ ይገባል እንላለን። ለእኛ መንግስቱ ሐይለ ማርያምም ሆነ ከላይ የተጠቀሱት ወንጀለኞች አንዱ ካንዱ የተሻሉ አይሆኑም አንዱ ካንዱ ካልተሻለ ደግሞ አንዱ በልዩ ክብር ቀለብ ተሰፍሮለት መኖሪያ ተሰጥቶት እንዲፏልል ከተደረገ መንግስቱ ሐይለ ማርያም ወደ ሀገራቸዉ ተመልሰዉ ስህተት ነበር ያሉትን አርመዉ፤ መጽሀፍ ጽፈዉ፤ ትዉልድ አስተምረዉ፤ ንስሀ ገብተዉ  ቤተክርስቲያን እየሳሙ እንዲኖሩ ቢደረግ ሚዛናዊ ይሆናል።

የመለስ ዜናዊ ልጂ በስካርና  ህዝብን በመናቅ መላ ቅጧን ሲያሳጣት የመንግስቱ ሐይለ ማርያም ልጆች ግን። የሀገር ተቆርቋሪነታቸዉን  በማጉላት ስለ ሀገራቸዉ ባሉበት ሀገር ሲታገሉና ኢትዮጵያዊነትን ሲያደምቁም  ተመልክተናል ወደፊትም ለሀገራቸዉ ብዙ እንደሚሰሩ ተስፋ አለን። እነዚህ ልጆች ከቤተሰባቸዉ ያገኙት ሀገር ወዳድነት እንጂ ኢትዮጵያን የለቀቁበት እድሜ በሄዱበት አገር ባህል ሰጥመዉ የሚያስቀራቸዉ  ነበር።  ወ/ሮ ዉባንች ቢሻዉም እንደ አዜብ መስፍን ለሺቶና ጫማ 2 ሚሊዮን ዶላር የመደቡ ሳይሆን እንደ ጥሩ ኢትዮጵያዊ የቤት እመቤት ተሰብስበዉ ልጆቻቸዉን በስርአት አርቀዉ ያሳደጉ ልታይ ልታይ ልታይ የማይሉ ክብር ያላቸዉ ሰዉ በመሆናቸዉ እሳቸዉም ያለጥፋታቸዉ በማይመቻቸዉ አገር መኖር ስለማይገባቸዉ ወደሀገራቸዉ ተመልሰዉ ከጎረቤቶቻቸዉ ጋር ቡና እየጠጡ፤ ቤተ ክርስቲያን እየሳሙ  በተፈጠሩበት አገር የሚኖሩበት ሁኔታ ቢመቻችላቸዉ ትክክለኛ ፍርድ ነዉ ብለን እናምናለን።

እንግዲህ ነገሬን ስቋጭ ለኮለኔል መንግስቱ ስስ ልብ ያለኝ አይደለሁም ከላይ ከብዙ በጥቂቱ የጠቀስኳቸዉ ወንጀለኞች ትክክለኛ ፍርዳቸዉን ከመስጠት ይልቅ ያንን የመሰለ ጥቅምና ክብር ሲሰጣቸዉ ኮለኔል መንግስቱ ብቻ ተነጥለዉ መቀጣታቸዉ ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አንድነት ሀይሎችን ለማስደሰት ካልሆነ በስተቀር ፍትሀዊነት የለዉም። አንድን ዜጋ በተፈጥሮ ያገኘዉን ሀገር መንጠቅ አይቻልም።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ሰመረ አለሙ (semere.[email protected])

7 Comments

 1. Dumb idea, Mr. Semere. Is it really Ethiopia`s burning issue? In a country where hundreds are killed everyday for a reason none other than being Amhara, you are concerned about a dictator wanting to come back to a country that he deserted and passed to woyane.

  The country is at the worst time in its history, internal political instability, invasion by Sudan, woyane regrouping in Sudan, a potential split b/n amhara and oromo bilgina party, hunting of Amahras throughout the country etc.

 2. I do not think the Haileselassie’s administrations supporters would like Mengistu back in Ethiopia same as they did not like Berhanu Bayeh’s and Addis Tedla’s release from the Italian embassy holding cell to freely reside in Ethiopia. Firstly Mengistu needs to ask for forgiveness from the countless Haileselassie regimes supporters , then maybe after that it will be appropriate for him to return to Ethiopia if they manage to collectively accept his apology otherwise him returning is a recepie for more division amongst Ethiopians. For now Mengistu maybe can return as a tourist for a visit but for him to live in Ethiopia is spreading salts on the wounds of the countless Hailesselasie’s administrations supporters who continue to suffer tremendously by his actions.

 3. Yewega I really appreciate your civilized approach, as I have mentioned in my article, if TPLF and OLF are allowed to live in Ethiopia and climbe the ladder of leadership, there is no reason to refrain him from coming to Ethiopia and get the same priveldge like them. I know all the crimes he committed, my comparison is with leaders and parties that are not different from him and actively engaged in Ethiopian politics including the notorious Esayiyas Afework. Look Aregawi Dawud and Lencho do you think they are more human than him I dont think. Let the people decide.

 4. አይነበብ የለ፣ ነገሩን አነበብኩትና፣ ባነበብኩበት ጊዜ ግን እንዲያው በድንገተኝነት (ብሃንደበት) ራሴን የመቱኝ አስተሳሰቦች:
  “ፊውዳሊዚም ይለምልም” የሚሉ አሁንም አሉ እንዴ!?
  ያኔ አንዳንድ ጠቅላይ ግዛቶች የአንድ ሰው ብቻ ንብረት ሆነው ጭሰኝነትም አብቦ እንደነበረው አይነት ምኞት!
  ግን “የፍየል ወጠጤ” የሚለው ቀረርቶ ብቻ እንዳያስከትል:: ፊውዳሊዝምን ሲመኙ ተፃርሮም ይኖራልና!
  የፅሁፉ ሁለመናው “ክበልዕዋያ ዝደለይዋ ኣባጉንባሕስ ጅግራ እያ ይብልዋ” እንዲሉት የፅዮን ልጆች፣ ነገር ነው!
  የኋላ ማርሽ ከትቶ መኪናውን ወደፊት አብራሪ ለሌሎችም ሆነ ለራሱ መጥፋት ሰበብ ኋኙ ደግሞ አሁንም መጣ እንዴ ብየ ተደናገጥኩንና፣ ማን ሊሆን እንደሚችልም ደረስኩበት!
  እኛስ እንኳንስ በፅሁፍ ይቅርና ሲስተገበርም የኢትዮጵያን ጭሰኝነት ስርአት አልፈንበታል፣ ግን በዚያን ጊዜ ያልነበሩትና እንዲያው በስማ በለው ብቻ የአባቶቻችውን ጭሰኝነት ህልፈት ታሪክ፣ በታሪክ ብቻ የሚያውቁት እነ ጁዋር መሀመድ፤ሺመልስ አብዲሳ ወዘ’አብይ አህመድም እንኳንስ እንደገና እንደ አደጋ ሆኖ ሊያንጃብብባቸው ይቅርና በምድራቸው ዘንዳ ተተግብሮ ለማለፉ ስለሚከነክናቸው ለዘላለሙ ይጠፋ ዘንዳ እንደሚንቀሳቀሱ ፀሃፊው መገመት ነበረበት!!
  ከዋለልኝ በፊት ግርማሜ ነዋይ (ወርቅነህ ገበየሁን ወደ መርካቶ እየወሰደ የኢትዮጵያውያን ድህነት ምን እንደሚመስል በማሳየት፣ አብሮ እንዲያምፅ በማግባባት) እና ወልደኣብ ወልደማርያም ስርአተ ሸዋን (“እዚኣቶምስ ኣይኮነን’ዶ ክገዝኡኻስ ንኽትገዝኦም’ውን ኣፀገምቲ እዮም” ወደሚለው አስተሳሰብ በመድረስ) ተቃውማቸውን አሳይተው አልነበር እንዴ! እናም ከነሱስ አሻፈረኝነትን ዋለልኝ ተቀብሎስ እንደሆን!?
  ዋለልኝ የህዝቦች በምድረ ኢትዮጵያ እኩልነትንና የመሬት ላራሹን መስበክ ሲጀምር፣ ሻዕቢያ አልነበረም፣ የነበሩት አንዳንድ በኋላ መሪዎች ለመሆን የበቁትና፣ ያኔ ግን በሱዳን በኩል ተኳልለው ወደ ባርካ ዘ-ጀብሃ የሰረጉት የሃይለ ስላሴ መንግስት ሰላዮች ነበሩ እንጂ!
  የስልሳዎቹ መረሸንና እንዲሁም በየቤቱ ደጃፍ በደርግ ጥይት የተረሸነውን ወጣት፣ ወላጀቹ ሊቀብሩት እንኳን ሬሳዉን ለመቀበል ገንዘብ መክፈል እንደነበረባቸውም አይረሳ!
  ስእሎችን አስመልክቶ፣ የመጀመርያውን ሳይ የኩባ ህዝብንና ካስትሮ ለዋሉልን የሶሊዳሪቲ አስተዋፅ ኦ እንደገና ሳመሰግን፣ ወረድ እያልኩኝ ስሄድና ወደ መጨረሻው አካባቢ ስደርስ ግን፣ የሸፍጠኞች “ኣህያ ላህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበር” አይነት ነገርም ጭንቅላቴን መታው (የኢትዮጵያን ህዝብ ነብስ እንደ አጥንት ጋጭ ሁሏ እስከነ ፀሃፊውም ጭምር፣ በየተገናኘበት መተቃቀፍ)

 5. መንግስቱ የሚባል ጭራቅ ኢትዮጵያን ገድሎ ለአረመኔው ወያኔ አሳልፎ የሰጠ ወንጀለኛ ነው:: ለእሱ ሽር ጉድ የሚሉ ጉዶች ወይንም ተባባሪ ወይንም ጭንቅላታቸው ያልበሰለ ቂላቂሎች ናቸው:: መንግስቱ እጁ በደም የታጠበ ጨቃኝ ነው:: ሌላው ቢቀር አክሊሉ ሀብተወልድ የኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ መሪ ከታሰሩበት ወስዶ ያለምንም ፍርድ ሲገድል ማን አጥጋቢ ምክንያት ይኖረዋል? እንደ ወያኔ እንኳ ያልሸፈቱ በፈቃዳቸው እጅ የሰጡ ምሁርና ታጋይ መሪ:: ይህ የበታችነት ያጠቃው ፈሪ መሪ ዛሬ ደካሞች ሊያጀግኑት ቢፍጨረጨሩም እሱን አይለውጠውም:: እኔ አንድም ዘመድ አልሞተብኝም:: ይህ ፀረ አማራ ጀግና ሆኖ ሲቀርብ ያመኛል::

 6. ይገርማል ጸሀፊው ጥሬ በትኖ በመድሀኒት ሀይል የሚኖሩ እድሜ ጠገብ ተሳዳቢዎችን ሰብስቦ ያዛቸው ማለት ነው? ወደ መቃብር እያዘገሙም የተሰሩበት አያፋልሳቸውም የጸሀፊው መሰረተ ሀሳብ እንደገባኝ ከመንግስቱ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያሉት ገዥዎች ለሀገሪቱ አልበጁም አንድ ወንጀለኛ ተለይቶ አይግባ ማለት አግባብነት ያለው አይሆንም ነው ያለው እንጅ መንግስቱ መልአክ ነው አላለም ይህንን በአጽንኦት ደጋግሞ ገልጿል። የተጻፈው ዝባዝንኬ አስተያየት ከጽሁፉ መሰረተ ሀሳብ ጋር ካለመያያዙም በላይ ጽሁፉንም ያነበቡት አይመስልም። በተረፈ መድሀኒታችሁን በየሰአቱ እየወሰዳችሁ ፖለቲካውን መደበሪያ አድርጉት መቼም እናንተ እስካላችሁ ሀገር መልክ ይዞ ይቀጥላል ማለት ዘበት ነው። የችግሩ አካል በመሆናችሁ ዛሬ ላይ የምትለወጡበት ዘመን ስላልሆነ በጥንቱ እሳቤያችሁ ተንገዛገዙ።

 7. እንዳንድ የንጉሡ ሥርአት ዘመን ኪራይ ሰብሳቢዎች ይተዳደሩባቸው የነበሩበትን ቤቶችን ህወሀት ተቀራምቶ የወረሳችውን የመኖሪያ ቤቶች ከኢህአዴግ ካድሬዎች ነጥቆ ለባለቤቶቻቸው ለማስመለስ የተጀመረውን ጥረት በቁርጥኝነት ለማገዝ ቃል ገብተዋል የኢትዮጵያ የቀድሞው ፕሬዚደንት ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.