ለአወል አሎ፡-እውን ሕገ መንግሰቱ የአፈጻጸም ችግር ብቻ   ነው ያለበት? – ሰርፀ ደስታ

ለኦርቶዶክሳውያን ሁሉ  እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!

በየቦታው የጥምቀትን በዓል እንዳታከብሩ የተከለከላችሁ ኦርቶዶክሳውያን እግዚብሔር ስለመገፋታችሁ ያያልና እጅግ አትዘኑ! በሕግና በመዋቅር በማንነታችሁ እየተገን እንደሆነ አስተውሉ፡፡ የመንግስት መዋቅሮች ሆን ተብሎ በጸረ-ኦርቶዶክሳውያን ተይዘው ፍትህን ከዚህ ሥርዓት መጠበቅ አይቻልም፡፡

ሰሞኑን በቪኦኤ አወል አሎና ደረጄ ደምሴ ቡልቱ ስለ ሕገ መንግስት የተከራከሩበትን ለመስማት ሞከርኩ፡፡ በቅድሚያ እኔ የሕግም፣ የፖለቲካም ሰው አደለሁም፡፡ በዚህ ጉዳይ ቀድሜ ራሴን ትልቅ አዋቂ በማድረግ አንባቢን ብዥታ መፍጠር የለብኝም፡፡ እኔ ግን በፍልስፍና መርሆዎች በጽኑ የማምን ሰው ነኝ፡፡ ፍልስፍና መሠረት የሚያደርገው በአመክንዮዋዊ አገላለጽ እንጂ ራሲን ቀድሞ አግዝፎ በማቅረብ አድማጭ ሁሉ ምሁር ነው እያለ እንዲያደምጥ ወይም እንዲሰማ አደለም፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆነው የፍልስፍና መርሆ ግን በብዙ ቦታ በተለይም ምሁር ነን በሚሉ ሲጣስና ከአመክንዮዋዊ አቀራረብ ይልቅ እራስን በማግዘፍ አድማጭን ወይም ተመልካችን ወይም አንባቢን ለማሳከር ሲሞከር አያለሁ፡፡ በጽሁፍ እንኳን በሚቀርቡ አስተያየቶች አብዛኞች ከፊትና ከኋላ ራሳቸውን ዶ/ር እያሉ ሲጽፉ ይገርመኛል፡፡ እዴት ሰው ራሱን ዶ/ር ይላል? የሆነ ሆኖ ማሳሳቻዎችንና(ፋላሲስ) አመክንዮዋዊ እውነታዎችን መለየት በነጻነትና በተወዳዳሪነት ሐሳብን ለማቅረብ ትልቁ የፍልስፍና መርሆ ነው፡፡

OLFአወል አሎ ስለ ሕገ መንግስቱ ምን ያህል እንደሚያውቅ ሊነግረን ፈልጎ ይሄን ሕገ-መንግስት አስተምሬዋለሁ ይለናል፡፡ አስተምሮት ይሆናል፡፡ ከተነሳው የሕገመንግስቱ ትክክል ነው አይደለም ክርክር ጋር ግን የእሱ ሕገመንግስቱን ማስተማር አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ እሱ ስላስተማረው ሕገመንግስቱ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ነገሩ ሕገ መንግስቱን ከሌላኛው ተከራካሪ በላይ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ የሚል አንድምታ ለማስቀመጥና በዚሁ መልኩ አድማጭን ለማወናበድ ይመስለል፡፡ ይህ በፍልስፍና ማሳከሪያ (ፋላሲ) ነው፡፡  ከፍልስፍናዊ ስነምግባር አንጻር ደግሞ ነውር ነው፡፡ ሙከራው ሌላኛውን ተከራካሪ አንተ አታውቀውም የማለት ያህል ነውና፡፡

የሆነ ሆኖ አወል አሎ አስተማርኩት የሚለውንና ሑሉን ያካተተ በሚል የሚናገርለትን ሕገመንግስት ግድፈት እኔ የሕግም የፖለቲካም ሰው ያልሆንኩት እንደው ለማሳያነት ጥቂት መሠረታዊ ግድፈቶችን ልጠቁም፡፡ ይህ አወል አሎ የሚያደንቀው ሕገ-መንግስት የተባለው ሰነድ ገነ ሲጀምር “እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ሕዝቦች” ይላል፡፡ የሚገርመው የእነዚህ ቃላቶች ትርጉም ምን እንደሆነ እንኳን አይገልጽም፡፡ ሲጀምር በአንድ ሉዓላዊት አገር የሚኖር ሕዝብ ሕዝብ እንጂ ሕዝቦች ተብሎ አይጠራም፡፡ ሕዝቦች እያልክ እኛ ማለት አትችልም፡፡ ሕዝቦች ካልክ ወዲያ የኢትዮጵያ የሚል ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት እያለ የገዛ ሕዝቡን ሕዝቦች (አህዛብ) እያለ የሚጠራ ሕገ መንግስት በሌላ አገር ለመኖሩ እጠራጠራለሁ፡፡ ከአለም ሥህተት ነው፡፡ በዚሁ ሐረግ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች የተባሉትም ማንና ምን እንደሆኑ አይታወቅም፡፡ እንደ እውነቱ እነዚህን ቃላቶች አማርኛም ጠንቅቄ አውቃለሁ የሚል ምሁር ምን ያህል እንደሚረዳቸው አላውቅም፡፡ በኢንግሊዘኛው Nations and Nationalities ተብሏል፡፡የሆነ ሆኖ በዚህ ደረጃ የተዳፈኑ ቃላት ሲጠቀም ትርጉማቸውን በውል ማስቀመጥ ደግሞ ያባት ነው፡፡ ከኢንግሊዘኛው ስንነሳ ግን ብሔር የተባለውና ብሔረሰብ የተባለው በተለያየ ደረጃ የሚገኙ አደሉም፡፡  አገርና ዜጋ እንደማለት ነው፡፡  ይህ ሰነድ ከጅምሩ ለሴራ ስለሆነ አዘገጃጀቱ ነገሮች ጥርት እንዲሉ አልተፈለገም፡፡ እንግዲህ ከዚህ ይጀምራል የሕገመንግስቱ ሴረኝነት፡፡ ለዚህም ይመስላል የኢንገሊዘኛው nationalities የሚለው ከዚህ ዘረኛ ሕገ-መንግስ በኋላ በኢንግሊዘኛምበኦክስፎርድ ዲክሽነሪ አዲስ የሚመስል ትርጉም የተሰጠው፡፡  በቀጥታም ይሄው ዲክሽነሪ የኢትዮጵያን ብሔረሰቦች የሚለውን ቃል እንደ ምሳሌ ያስቀምጣል፡፡ በጎሳ የተከፋፈሉ በአንድነት የሚፈጥሩት የጋራ ማሕበረሰብ ሲል ይተረጉመዋል፡፡ እኛንው እንደምሳሌ አስቀምጦ፡፡ ሕገ-መንግስት ተብዬው ላይ የተቀመጠው እንግዲህ ይሄ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሕዝባዊ ጥያቄዎችን በማፈንና አደባባይ በመከልከል መገደብ በህግም በታሪክም ያስጠይቃል!! ሲሉ አንድነትና በ33ቱ ፓርቲዎች በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የዚህን ሰነድ አደገኛ ቃላቶቻና ግድፈቶች አንድ በአንድ ለመዘርዘር ችሎታው የለኝም ሆኖም አንድ ሌላ በጉልሕ የሚታይ ሴራን ላንሳና ራሳችሁ እንድትታዘቡት መረጃዎችን ላቅርብ፡፡ ይሄውም በምዕራፍ ሁለት አንቀጽ ስምንት ላይ የሕዝብ ሉዓላዊነት ይልና በዚሁ አንቀጽ ቁጥር አንድ ላይ የኢትዮጵያ ብሐየሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው ይላል፡፡ እዚህ ጋር ያለው ሉዓላዊ ምናምን የሚል የቃላት ጋጋታውንና ማሳከሪያውን የበለጠ ቋንቋና ሕግ ለሚረዱ ልተወውና በዚህ አንቀፅና ቁጥር ተቀምጦ የምናየው በቀጥታ ዛሬ በየእየክልሎቹ ዜጎች በማንነታቸው እየታረዱበት ያለ ሕጋው ፍቃድ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ የየክልሎቹ ሕገ-መንግሰት የሚባለውም የሚቀዳው ከዚህ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ለማነጻጸር ግን ይሄው የሴራ ሰነድ ዝቅ ብሎ በአንቀጽ ዘጠኝ ላይ ሕገ መንግስቱ የበላይ ሕግ ነው፡፡ ማንኛውም ሕግ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም ይላል፡፡

ወደየክልሎቹ ሕገ-መንግስት ስንመጣ በተመሳሳይ በምዕራፍ ሁለት አንቀጾቻቸው የሚያስቀምጡትን ግልጽ የሆነ ዘረኝነትና የዜጎች መብቶችሙሉ በሙሉ የተጣሱበትን አስደንጋጭ ሐረጎችን እናነባለን፡፡ ይህ በሁሉም ክልሎች ሕገ-መንግስተ ባሉት የተቀመጠ ሲሆን በኣማራ ክልል ሕገ-መንግስ ብቻ ዜጎችን በማንነታቸው መብታቸውን አይከፋፍልም፡፡ ለምሳሌ የኦሮሚያን ሕገ መንግስት ብናይ ገና የክልሉን ወሰን ሲገልጽ የኦሮሞ ሕዝብና ሌሎች በኦሮሚያ ለመኖር የመረጡ ሕዝቦች የሠፈሩበት ይልሀል፡፡ የክልልን ወሰን ለመወሰን ተንጠራርቶ ማንነትን በደንብ አንዱን ከአንዱ በመለየት ኦሮሞና ሌሎች ሲል ይጀምራል፡፡ ዝቅ ሲል በምዕራፍ ሁለት ከዋናው ሕገ-መንግሰት መሠረት በማድረግ የኦሮሞ ሕዝብ የክልሉ የበላይ ሥልጣን ባለቤት ነው ይላል፡፡ ይህ ማለት በኦሮሚያ መምረጥም መመረጥም ለኦሮሞ እንጂ ለሌላ አልተሰጠም እንደማለት ነው፡፡ ከላይ ሌሎች የተባሉት በዚህ ስልጣን ላይ አልተጠቀሱም፡፡ ከላይ ያነሳሁት ሥልጣንን በዘር/ጎሳ የመሥጠቱ ሴራ እንዲህ በግልጽ በተዋረድ ሲፈጸም እናየዋለን፡፡  ቀጥሎም በአንቀጽ ዘጠኝ ላይ ይህ ሕገ-መንግስት የክልሉ የበላይ ሕግ ነው ይላል፡፡ ቀጥሎም ማንኛውም ሕግ ልማዳዊ አሰራር እንዲሁም የመንግስት አካል ወይም ባለስልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ እዚህ ጋር በግልጽ ይምናየው የፌደራሉ ሕገ-መንግስት በተዋረድ በክልሎች በቀጥታ ሲፈጸም ነው፡፡ አስገራሚው ነገር ግን የኦሮሞ ሕዝብ የክለሉ ሥልጣን ባለቤት ነው ይልና የሕዝቡ ሥልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጠው በሚመርጣቸው ተወካዮችና ራሱ በቀጥታ በሚያደርገው ዲሞክራሳዊ ተሳትፎ ነው ይላል፡፡  ልብ በሉ አሁን መራጩ ኦሮሞ መሆኑ ነው፡፡ ሆኖም በየትኛውም ምርጫ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብት አላቻው ይባላል፡፡ ሲጀምር መራጭ ግለሰብ እንጂ ብሔረሰብ እንዳልሆነ በደንብ ይሰመርበት፡፡ የዚህ ሕገ-መንግስት ዓላማ ግን የዜጎችን መብት ሙሉ በሙሉ በእንዲህ ያሌ ሴራ ማገድ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ሪፖርት መድረሻው | “የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታለን፤ ሰልጣን ግን አንለቅም” መሆኑ ነው?

image 3

ሌላ አንድ ምሳሌ ልጨምር፡፡ ዛሬ ዜጎች በአረመኔዎች በማንነታቸው እየታሩዱበት ባለው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክለል በሕገ-መንግስቱ በግልጽ ከጉሙዝ፣ በርታ፣ ማኦና ኮሞ በቀር ሌሎች መብት እንደሌላቸው ይደነግጋል፡፡ የዚህን ክልል ሕገ-መንግስት አነቀጽ ሁሉት ያንብቡት፡፡ እነዚህ ሁሉ የተቀዱት ከዋናው ሕገ መንግስት እንደሆነ ልብ ይበሉ፡፡  ሕገ-መንስቱን አስተምሬዋለሁ በደንብ አውቀዋለሁ ሁሉንም የዜጎች መብቶች አካቷል እያለ የሚናገረው አወል አሉ የሕገ መንግስት አስተማሪ ከነበረና በእርግጥም የሕግ ባለሙያም እንደመሆኑ እነዚህን ሁሉ አንብቧቸዋል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ያሉ እጅግ ዘረኛ ዜጎችን በግልጽ በማንነታቸው ፍጹም ሰብዓዊ የሆነ መብታቸውን እየደፈሩ የሉ ሰነዶችን በሕግ ደንግጎ በዓለ ሥርዓት የሕገ መንግስቱ ችግር አደለም ማለት ምን ማለት ነው? ሲጀምር ይሄ ዛሬ ሕገ-መንግሰት የተባለው ሰነድ ብዜ ሴራዎችን ለማካተት ሲባል እጅግ በሕገ-መንግስት ይቅርና በተራ ሪፖርት እንኳን መቀለጽ ያልነበረባቸውን ቃላት ነው የሚጠቀመው፡፡ የክልሎቹን ሕገመንግስትማ ተውት፡፡ በተለይ ደግሞ የኦሮሞው ሕገ-መንግስት በሚያሳዝን ሁኔታ ገና ከመግቢያው የሚጀምረው በጥላቻና፣ እሮሮ ሲሆን የሕገመንግስቱም ዓላማ በቀለኝነት እንደሆነ ግልጽ ሆኖ ተጽፏል፡፡ የዚሁኑ ሕገ-መንግስት ተብዬ ሰነድ በቀለኝነትን፣ ዘረኝነትንና የበታችነትን ስሜት የተንጸባረቀበትን መግቢያ ጽሁፍ ራሳችሁ እንድታነቡት እዝሕ ላይ ልተውላችሁ

እንግዲህ እንዲህ ያሉ ቃላትን የታጨቀው ሰነድ ነው ሕግ የሚባለው፡፡ ለማንኛውም አሁን ያለው ነበራዊ እውነት በትክክለም በሕግ ተደግፎ የሚደረግ ማንነትን መሠረት ያደረገ አረመኔያዊ ድርጊት እንደሆነ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ከዚህ ሌላ ጋዜጠኞች ስትጠይቁ ስለመትጠይቁት ጉዳይ በቂ መረጃ ቀድማችሁ ብታሰባስቡ ማንም ምሁር ነኝ በሚል ብቻ አሳሳች መረጃን ሊያውም በሚዲያ እድል ተሰጥቶት ከማሰራጨት ይታደጋል፡፡ በዚህ ረገድ ሁለቱን ግለሰቦች ይጠይቅ የነበረው የቪኦኤው ጋዜጠኛ ትልቅ ክፍተት አይቼበታለሁ፡፡ እነዚህን ሰነዶች ራሱ ካነበበ በኋላ መጠየቅ ሲገባው በሰነዶቹ ምን እንዳሉ ስለማያውቅ የተናጋሪዎቹን ንግግር ለማረቅ አለመቻል ብቻም ሳይሆን በቪኦኤ የተናጋሪዎችን የግል ፍላጎት በሕዝብ ላይ እየጫነ እንደሆነ ቢረዳ እላለሁ፡፡ ዛሬ ኢትዮጵያ ውስት ዜጎች በማንነታቸው እየታረዱ ያሉት በሕገ-መንግስት በተባለው የወሮበሎች ሰነድ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በተጨማሪ ግን ባለስልጣናት አሁንም በሰነዱ ከአስቀመጡትም በላይ ስላልበቃቸው የተጻፈውንም እያለፉ እንደልባቸው የሚሆኑባቸው ሕጎች አሏቸው፡፡ በዚህ ሕገ-መንግስት በተባለ ሰነድ ዘጠኝ ክልሎች አሉ፡፡ ሲዳማ እንደ አዲስ ክልል ለመፍቀድ ግን ሕገ-መንገስት ማሻሻል አላስፈለጋቸውም፡፡ የሌለው ዜጋ ጥያቄ ሲሆን ደግሞ ሕገ-መንግስቱን ለመናድ ይሉሀል፡፡ ለማንኛውም ይሄ ሕገ-መንግስት በተለይ ኢትዮጵያውያንን አይወክልም፡፡ ኢትዮጵያ ቅኝ ገዝታናለች የሚሉ በጥላቻ፣ ዘረኝነትና በበታችነት ስሜት የተበከሉ ኢትዮጵያውያንን ለመበቀል ያወጡት ሕግ ነው፡፡ በተግባርም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ በዛሬው እለት እንኳን እየተከበረ ያለው በዓለም አቀፍ ደረጃ ሳይቀር ልዩ እውቅና ያለው የጥምቀት በዓል እንዳይከበር እየተደረገ ያለው ድርጊት ብዙ መልስ ይሰጣል፡፡ በዘረኝነት፣ ጥላቻና የበታችነት ስሜት ሕዝብን ከቀን ወደ ቀን ወደ ከፋ ባርነት እየከተተ ኢትዮጵያዊነትን እያወደመ ያለ ሰነድና አስፈጻሚዎቹ ከኢትዮጵያ ምድር እስካልተወገዱ ድረስ ዛሬ ከብሔር በተለይ በአማራ ከእምነት በኦርቶዶክስ ላይ እየደረሰ ያለው አረመኔያዊ ግፍ ሁሉም ይደርሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጥሞና ጊዜ ለትግራይ ተወላጆች! - አንድነት ይበልጣል - ሐዋሳ 

 

ቅዱስ እግዚአብሐየር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

2 Comments

  1. ልክ ነው ሰርጸ ስህተቱ የሱ ሳይሆን ትልቅ ሊቅ ተደርጎ በተሰጠው እድል ስብሀት የታሰረበትን ወንጀል እሱ ማንበሩ ነው። ሲጀመር አስተምሬዋለሁ ይላል እናሳ ነጭ የበላይ ነው ጥቁር ማሰቢያው ከነጭ ያንሳል በኛ ሀገር ደግሞ ራስ ዳሸን ትግራይ ውስጥ ነው ተብሎ ተምረዋል አስተማሪዎች በማስተማራቸው ስህተቶች ልክ ናቸው ማለት አይደለም።
    ሲጀመር ነገር ማካበጃ እንጅ አላስተማረውም ግለሰቡ የሚያስተምርበትን ኮሌጅ ካገኙ በሁዋላ course outline መመልከት ነው። እንደሚገባኝ ኑሮው እንግሊዝ ነው የእንግሊዝ ጠ/ሚኒስተር የነበሩት ጎርደን ብራዎን በዘራቸው ስኮቲሽ ናቸው ለውድድር የቀረቡትም በፓርቲያቸው ሌበርን ወክለው እንጅ ስኮትሽን ወክለው አይደለም።
    በኢትዮጵያ ያለው ፌደራሊዝም እሱ ሊያምታታው እንደሞከረው ሳይሆን በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ ሲስተሙ በፈጣሪው በመለስ ዜናዊ ስምሽተሰይሞ ዜናዊዝም(zenawizm) ነው የሚባለው። ግለሰቡ አካዳሚክስ ስራ ላይ ከማተኮር ይልቅ የአረብ ተላላኪ ሁኖ ለአክራሪ እስላም ሲሰራ የነበረና ለዚህ ለጥፋት ስራው በመሰሎቹ የተዘጋጀለትን የእውቅና ሰርቲፊኬት ከሀጅ ነጅብ የተሽለመ የአንድነት ጠላት ነው። ስነስርአቱንም ጎግሎ መመልከት ይቻላል። ለማንኛውም ታፔላ እያዩ የሚያጀግኑ ባሉበት ወደፊትም እንዲህ አይነቱ ይቀጥላል የአንድነት ሀይሉ ግን መመከት ግዴታው ነው። ባጠቃላይ ይህ ግለሰብ ሰልፉ ከጁዋር መሀመድ ጎን መሆኑን ዜጋ ሊገነዘብ ግድ ይላል። ሰርጸ እናመሰግናለን እኔም ሰምቼ ስገረም ነበር።

  2. You guys, you are always following the oldies style of life and could not able to graduate from primitive societal savagery style of political system. Where were you during the last 30 years apart from crying today after you are told that TPLF has gone?

    Stupidity never bring unity!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.