ሶስትህም አማራ ክንድህን አጣምረህ እንደ ጀግና አያቶችህ የሚበላህን አውሬ መከላከል ይኖርብሃል!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ከአለፉት አርባ ዓመታት በከፋ ሁኔታ ከሶስት ዓመታት ወዲህ አማራ የሰው ቆዳ በለበሱ አውሬዎች ሌት ተቀን እየተበላህ ነው፡፡ የዳር አገሩ አማራ ስትጠቃ የመሐል አገሩ አማራ እንዳይደርስልህ በአማራ መቃብር መንደር ለመመስረት የተነሱ ጭራቆች አሽከር የሆነው እርጉሙ ብአዴን ጪፍጨፋውን በመሸፋፈንና በአንገትህ እንደ ቀንበር በመውደቅ የዘር ፍጅትህን እያባባሰ ይገኛል፡፡

የመሐሉ አገሩ አማራ ስትጠቃም የዳር አገሩ አማራ እንዳይደርስልህ ጭራቆች በክልል እግር ብረት ጠፍረው እንዳትንቀሳቀስ ይከለክሉሃል፡፡ ባህር ማዶ የምትገኘው ተሰዳጁ አማራም ተመሐሉና ተዳር አገሩ አማራ ተጣምረህ እንዳትሰራ ብአዴን ድንግልናቸውን የወሰደባቸው ካድሬዎቹ፣ በቴሌቪዥን የድስኩር ጣታቸውን የሚያፍተለትሉትና እንደ ቡችላ በጥቅም እየተገዙት “ምሁራን” ይከፋፍሉሃል፡፡ በዚህም ምክንያት እንኳን ራስህንና  አገርህን አፍሪካንና ደቡብ አሜሪካንም  በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ነጣ ለማውጣት አስተዋጣኦ ያደረከውን አንተን አማራውን በገዛ አገርህ  አውሬዎች መበላቱን ቀጥለዋል፡፡

የመሐሉ፣ የዳር አገሩም ሆነ የባህር ማዶው አማራ ልብ በል! ከአርባ አመታት በፊት የአማራ ዘር ፍጅት በወልቃይት፣ ሁመራና ራያ ሲፈጠም ኢህዴን የተባለው እርኩስ ቡድን እየሸፋፈነ እንኳን ባህር ማዶ ያለው የመሐሉና የዳር አገሩም አማራ እምብዛም እንዳያውቅ አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ በስዬ አብርሃና በታምራት ላይኔ “የነፍጠኛን በለው” ቅስቀሳ በበደኖ፣ አርባ ጉጉና በሌሎችም የዳር አገር ሥፍራዎች አማራ ገደል ሲወረወርና ሲጨፈጨፍ የትግሬው ነጣ አውጪ መንትኛውን የወረሞውን ነጣ አውጪ በፖሊስ ጠራርጎ እስታባረረበት ድርስ ደብቆት ቆይቷል፡፡ አብረው የፈጠሙትን የዘር ፍጅት በወረሞው ነጣ አውጪ ለማላከክ ተበደኖ ገደል የወገኖቻችንን እሬሳ እየጎተተ በቴሌቪዥን እንዳሳዬ ይታወቃል፡፡

የትግሬው ነጣ አውጪ እንደ አምባሻ ጠፍጥፎ የሰራውን የኢህዴንን ጭንብል እንደ እንሺላሊት ቆዳ ገሽልጦ ብአዴን የሚባል ሌላ ለምድ ታለበሰው በኋላም የወልቃይቱ፣ የሁመራውና የራያው የዘር ፍጅት እንደ ቀጠለ ይታወቃል፡፡ ከጠቅላላው ሕዝብ ከስልሳ በመቶ በላይ የሆነው የሀረርና የድሬዳዋ አማራ፣ ከሰባ አምስት በመቶ በላይ የሆነው የናዝሬት፣ ደብረ ዘይት፣ አዋሳ፣ ይርጋለም፣ ጅማና ሌሎችም የአገርቱ ክፍሎች አያቶቹ በገነቡት አገር መብት አልባ ሆኖ ከስልጣን ብቻ ሳይሆን ከትምህርትና ንብረት ከማፍራት መብትም ተገድቦ እንደ ኖረ ይታወቃል፡፡ ይኸንን ደባ መሐል አገርም ሆነ የባህር ማዶ ያለኸው አማራ በሚገባ እንዳታውቅ በአማራ መቃበር የራሳቸውን መንደር ለመመስረት የተነሱት ብአዴንን እንደ ምራቅ መትፊያ ድምጥ ማጉያ፣ እንደ ንፍጥ መናፈጫ መሐረብና እንደ ሽንት ቤት መጠቀሚያ ወረቀትም እየተጠቀሙ ሲሸፋፍኑት እንደ ኖሩ ታሪክ ዘግቦታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰላም ምንድነው? (ታደሰ ብሩ)

የመሐሉና የዳር አገሩ አማራ በክልል እግር በረት ታጉሮ እንደ ተለያዬ፣ የባህር ማዶው አማራም ከጥቂቶች በስተቀር እንጀራውን ሲያባርር የወልቃይት፣ ሑመራና ራያ አማራ በጪፍጨፋም፣ በመታሰርም በስደትም እንደ መነመነ በተለያዬ ጊዜ ተዘግቧል፡፡ እንደ ጉራ ፈርዳ ታሉ የአገሪቱ ክፍሎች የዳር አገሩ አማራ እንደ ሙሴ ዘመኑ የዘፀአት አይሁዳውያን በለገሰ ዜናዊ አዛዥነት፣ በሽፈራው ሽጉጤ አስፈጣሚነትና በብአዴን ተመልካችነት እንደ ተሰደደ ታሪክ ከትቦ ይዞታል፡፡

ይኸንን የዘር ማጥራት እርኩስ ተግባርና በመላው አማራ የሚደርሰውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ የተቃወሙ የመሐል አገርና የዳር አገር አማራዎች እየተለቀሙ በወህኒ እንደ ተጠበሱ፣ ዘር እንዳይተኩ ከርቼሌ እንደ ተሰለቡ፣ ህክምና እየተከለከሉ በበሽታ እንደ አለቁ ህሊናችን ያስታውሳል፡፡ በመላው አማራ በሚደርሰው የዘር ፍጅት ተቆጥቶ በአምባ ጊዮርጊስ፣ በጎንደር፣ በደብረ ታቦር፣ በባህርዳር፣ በዳንግላ፣ በቡሬ፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልድያ፣ በማጄቴና በሌሎችም ከተሞች ሕዝብ ለሰልፍ ሲወጣ በትግሬ ነጣ አውጪ መራሽነትና በብአዴን ተባባሪነት ተብአዴን ቢሮ በመሸገ ስናይፐር እንደ ተጨፈጨፈ ሲመዘግብ የከረመው አይምሯችን ያስታውሰናል፡፡

የሕዝብ የቁጣ ማእበል እየበረታ ሲሄድ የትግሬ ነጣ አውጪ በሰራው በዓለም ታይቶ በማይታወቀው ግፍ እነደ ጎርፍ ተጠርጎ እንደሚሄድ የተገዘቡት እነ ኸርማን ኮን ለገሰ ዜናዊን በሰቀሉበት የቆሸሸ እንጃቸው አብዮት አመዴን ሰቅለው ሌላ የብአዴን ጌታ እንደፈጠሩ ይታወቃል፡፡ አዲሱ የብአዴን ጌታ አሳዳጊ አባቱ ለገሰ ዜናዊ እንዳደረገው ሁሉ ብአዴን የሚለውን አሮጌ ቆዳ እንደ ሌጦ ገሽልጦ አዴፓ የሚል የበሰበሰ አንጋሬ እንዳለበሰው አይተናል፡፡ ወዲያው ደግሞ ይኸንን አንጋሬ የፈላ ውሀ ውስጥ እንደ ገባ ዶሮ ሞሽልቆ ብልጥግና የሚባል ቆርበት እንዳለበሰው አይተናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከሃይለማሪያም በስተጀርባ ያለው " ስሁል ሚካኤል " ማን ነው? - ቬሮኒካ መላኩ

ተትናት በስቲያ ኢህዴን፣ ትናንትና ብአዴን ይባል የነበረው የእንግዴህ ልጅ ብልጥግና የሚለውን ቆርበት ተለበሰበት ሶስት ዓመታት ወዲህ ለሰላሳ ዓመታት ታለቀው አስር እጥፍ አማራ በዘሩ እንደተጨፈጨፈ ይታወቃል፡፡ ይኸንን ጭፍጨፋም ብልጥግና የሚል የከረፋ ቆርበት የለበሰው ብአዴን እንደ ልማዱ እየታዘዘ ለመደበቅ አሁንም ሲፍጨረጨር ይታያል፡፡ ብአዴን የአማራን ሐብት እንደ ቅንቡርስ እየዋጠ እንደ አያቶቹ ዘራፍ ብሎ የተነሳውን ፋኖን እያንገላታ የአማራን ዘር ፍጅት እያባባሰ እንደሚገኝ በየቦታው የሚያልቀውና የሚሰደደው አማራ እየመሰከረ ይገኛል፡፡ ብአዴን በወልቃይትና በራያ ሲያደርገው እንደኖረው መተከልም ፋኖ ለወገኑ እንዳይደርስ በተደጋጋሚ ከልክሏል፡፡ የመሐል አገሩ አማራ ለዳር አገሩ አማራ እንዳይደርስለት አሳፋሪው ብአዴን በሰው ክልል አያገባኝም እያለ ስንቱን ሲያስፈጅ እንደኖረ የዳር አገሩ አማራ ታሪክ ያትታል፡፡

የመሐል አገር፣ የዳር አገርና የባህር ማዶ አማራ ሆይ! ለግማሽ ክፍለ-ዘመን በመቃብርህ አገር ሊቀልሱ ባቀዱት ጭራቆች የቅጥፈት ታሪክ ትረካ ለሺህ ዘመናት ያሰለጠንካቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ አውሬነት ተቀይረው አንገትህን፣ ኩላሊትህንና ጉበትህን እየዘነቸሩህ ይገኛል፡፡ አያቶችህ ግንባራቸውን እያሉ የመለሷቸው የውጭ ጠላቶችም አሲረውብሃል፡፡ ይህ ወቅት ተምንጊዜው በላይ በመሐል አገርም፣ በዳር አገርም ሆነ ባህር ማዶ የምትገኝ አማራ እንደ ቅድመ አያቶችህ በአንድነት በአርበኝነት እንድትሰለፍ ጠይቋል፡፡

የመሐል አገር፣ የዳር አገርና የባህር ማዶ አማራ ሆይ! ትናንት በወልቃይትና ራያ፣ ዛሬ ደሞ በካርዳ ወንዝ፣ በመተከል፣ በደራ፣ በሻሸመኔ፣ ዝዋይ፣ በአሩሲና ወለጋ የሚፈጠመው እልቂት ነገ ናዝሬትና አዲስ አበባ ላለመድረሱ ምን ዋስትና ይዘኻል? በጊዜ ታልተቀጨ ናዝሬትና አዲስ አበባ ዛሬ የሚፈጠምብህ ቁማራና ደባስ ነገ ደብረ ብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ጎንደር፣ ደብረታቦር፣ ባህርዳር፣ ደብረ ማርቆስና ሌሎችም ቦታዎች እንዳይደርስ ምን ዝግጅት አድርገሃል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ግርማዊነታቸው የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ሲያቆሙ የተናገሩት

የመሐል አገር፤ የዳር አገርና የባህር ማዶ አማራ ሆይ! የአያቶችህ ብሂል እንደሚያስተምረው ዳር ሲፈታ መሐሉ ዳር ይሆናል! የዓይን ችግር ለሌለበት የዳር ዳሩ መቃጠል መሐሉን ሲለበልበው ይታያል፡፡ ካድራ ወንዝ ሲቃጠል ደብረ ብርሃን አይደርስም ብለህ ከተንዘላዘልክ ተማሞ ቂሎም የባስክ ጅል ሆነኻል፡፡ መተከል ሲቃጠል አዲስ አበባና ናዝሬት አይደርስም ብልህ ታደፈጥክ ክቡር ፕሮፌሰር አስራት ሆዳም ታሏቸው አማራዎችም ብሰህ ጅብ ታፋውን የሚነጨው የጋማ ከብት ሆነኻል፡፡ ሀረርና ወለጋ የሚደርሰው የአማራ ዘር ጪፍጨፋ ዋሽንግተን ዲሲ አይደርስም በሚል ዝም ብለህ ፒዛህናን ሐምበርገርህን ስትገምጥ ኖረህ ለመሞት ተወሰንክ አፈር ለአፈር ተሚርመሰመስ ቅርንቡርስም አንሰሃል፡፡

የመሐል አገር፣ የዳር አገርና የባህር ማዶ አማራ ሆይ! አማራ ህጣናት፣ እናቶች፣ አባቶችና ልጆች በመላ አገሪቱ እየታረዱ ያሉት አንተም በለበስከው በአማራ ባህላቸው፣ ታሪካቸው፣ መልካቸው፣ ቋንቋቸና ሃይማኖታቸው መሆኑን ተገንዝበህ ይኸንን የዘር ፍጅት ለማስቆም እንኳን ተምድር ማርስ ላይ ብትኖርም አስተዋጽኦ የማድረግ ተፈጥሯዊ አደራ ተጥሎብሃል፡፡ ሶስትህም አማራ ጥኑ  ክንዶችህን አጣምረህ የሚበላህን አውሬ እንደ ጀግና አያቶችህ መከላከል ይኖርብሃል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ጥር ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ. .

3 Comments

  1. የአማራ ህዝብ በ መጀመሪያ ደረጃ እራስን በ መከላከል መግደል በ ምድርም ሆነ በ ሰማይ ቤት እንደማያስጠይቅ ማመን አለበት። ትልቁ የ አማራ ችግር እንዴት የ ሰው ሕይወት አጠፋለሁ፤ ሲኦል እገባለሁ በሚል አስተሳሰብ ታስሮ መገኘቱ ነው። ይህን ዕምነቱን ትቶ ለ መብቱ እና ለ ህልውናው ከ አልተዋደቀ በ አጭር ጊዜ ( እግዚአብሄር አያድርገውና) ጠፊ ነው። መከበር በ ሃይል ብቻ ነው። ሌላ ምንም አማራጭ የለም። ሁሉም እንደ አቅሙ አልደፈርም ብሎ የድርሻውን መወጣት አለበት። አቅም ያለው ሚስቱን እና ልጆቹን ጥሎ መሮጥ የ ወንጀል ወንጀል ነው። እሱ የሚቻለውን ሁሉ አድርጎ ከዚያ የሚሞተው ቢሞት ይሻላል። ለ ሌሎች ወገኖቹ ሕይወት መትረፍ ምክኛት ይሆናልና። ገዳዮች ሊገድሉ ሲሞክሩ እነሱም እንደሚሞቱ ይረዳሉና። ሃገር ቤት ህዝባችን እራሱን መከላከል ከ ጀመረ ውጭ ሃገር የሚኖሩም ዕርዳታ ማድረግ ይጀምራሉ። ሁልጊዜ እዚህ እና እዚያ ተገደሉ እንርዳ ማለቱ መፍትሔ የለውም። ህዝባችን የሚከበረው ህብረት እንጂ በ መንግሥት ወይም በ ውጭ ሃገራት እርዳታ አይደለም።

  2. አቶ በላይነህ መጀመሪያ ያንተና የህዝብህን ጠላት አላወክም። ለትውልድ ሀገርህ ጎጃም ማነስን ለሕዝበ ጎጃም ውርደትን ያወረሰ አንተ አማራ ከምትለው አካባቢ የወጡ ገዥወችና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስትያን ናቸው። መንግሥታት የጎጃምን ታዋቂ ሰዎች መንጥረው በማጥፋት ሰው አሳጧት። ተዋህዶ ቤ/ክርስትያን ደግሞ አቡነ ተ/ሀይማኖት፣ ክርስቶስ ሰምራ፣ አቡነ ገ/መንፈስቅዱስ፣— የሚባሉ መጽሀፍቅዱስ የማያውቃቸውን ቅዱሳን ፈጥራ ገድል ጻፈችላቸው። የእነዚህ ቅዱስ የተባሉ ሰወች ገድል ላይ ጎጃምን በሙሉ ከሰው ምድብ አውጥተው ከሰይጣንና ካጋንንት ጋር መድበውታል። ጎጃም ቡዳ ነው። ጎጃም ሰው ይበላል። ጎጃም ጅብ ይጋልባል። ፈጣሪ ለጎጃሞች ምህረት አላደርግም ብሏል የሚሉ ክፉ ነገሮች በነዚህ ሰወች ገድል ላይ ተጽፏል። ፌስቡክ ስለማትከታተል ይሆናል ያልሰማሀው። መጀመሪያ ለአንተና ለቤተሰቦችህ ታገል። ከቻልክ እነዚህ መጻህፍት ተቀደው እንዲጣሉ፣ ቤተክርስትያንም ይቅርታ እንድትጠይቅ ታገል

  3. Jillu Kinew

    እንከፍ ነህ! አንተ ይህንን ፀሐፊ ልታስተምር ትላላጣለህ!
    ሂድና በዝቅተኝነት መንፈስ ጋላ ተባልን አንበጣ ተባልን እያሉ ከሐምሳ አመት በላይ ያላዘኑትን አንተን መሳይ ጂሎች ስበክ! ሰይጣን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.