በኢትዮጵያና በዜጎቿ ላይ ከሚፈጸመው ሴራ ጀርባ አብይ የለምን? = ሰርፀ ደስታ

127234885 5148216348529628 7144602635593361133 nበመጀመሪያ ከሁሉ አስቀድሜ ዜጎች በማንነታቸው እየታረዱበት ስላለው ጉዳይ ውስጤ እጅግ እያዘነ ነው፡፡ ሁሉም መሠረታዊ መፍትሄ ላይ ከመስራት ይልቅ ግፎችን በማያስቀር ነገር ተጠምዶ አይቻለሁ፡፡ የተጎዱና የተፈናቀሉትን ገንዘብ በማሰባሰብ መርዳት መልካም ነው፡፡ ሆኖም ይሄ ምን አልባጥም አደገኛ ሊሆንም ይችላል፡፡ ከምንጩ ያለውን ሴራ ማጽዳት ላይ ትኩረት ካልተደረገ በቀር ችግሩ ይቀጥላል፡፡ እንግዲህ ስንቱን በጎፈንድሚ ለማገዝ እንደሚቻል አይገባኝም፡፡ ከጌዲዎ ጀምሮ በመቶ ሺዎች እየተፈናቀሉ ነው፡፡ ሁሉም መፈናቀሎች ውስጥ ተመሳሳይ ሴራና ወያኔ ስንባል ከርመናል፡፡ እውነታው ግን ከወያኔም በከፋ አደገኛ የሆነ የኦነጋውያን ሴራ እንደሆነ ግልጽ ነበር፡፡ ሲጀምር የታዩት አረመኔያዊ ግፎችና መፈናቅሎች ሁሉ ከማይካድራው በቀር የሆነው በቀጥታ በኦሮሞ ፖለቲከኞች በሚመራ አረመኔ ቡድን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም ሁሉም የችግሩን መሠረት ከማወቅና ከምንጩ ማድረቅ ላይ እንዲያተኩር እላለሁ፡፡

የኦሮሞን የዘረኝነት፣ ጥላቻና ሴራ ይመራዋል ብዬ ከማባቸው አንዱና ዋነኛው ራሱ ጠ/ሚኒስቴር የተባለው አብይ እንደሆነ አስባለሁ፡፡ አብይ በተለይ በኦርቶዶክስና በአማራ ላይ ያለው ጥላቻ የከፋ እንደሆነ ከማያቸው ነገሮች አያለሁ፡፡ ኦርቶዶክሳውያኑ ግን አብይ ቤተክርስቲያናችንን አንድ አደረገልን በሚል መፈንደቅ ክፉኛ እንደተዘናጉ አስተውላለሁ፡፡ ችግሮች ተከሰቱ በተባለ ቁጥር አማራ ከእምነት ደግሞ ኦርቶዶክሶች ኢላማ እየተደረጉ ባለበት አገርና ግዙፉን የአገሪቱ ሕዝብ የዚሁ ማህበረሰብ በሆነባት ኢትዮጵያ በመንግስት መዋቅሩ ላይ ያለው በተለይ የኦርቶዶክሳውያን ቁጥር አስደንጋጭ በሚባል ሁኔታ ባዶ ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ አብዛኛው ሕዝብ ኦርቶዶክስ ሲቀጥል ሙስሊም በበዛበት አማራ በተባለው ክልል ሳይቀር ተፈልጎ ሥልጣን እየተሰጠው ያለው የጴንጤ እምነት ያለው እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡  የሆኑትን ክስተቶች ወደኋላ ስናስተውል የሚገርም ነው፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታ መዘናጋታችን ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን ለማሳካት ኢላማ የተደረገው የኦርቶዶክስ እምነት ቤተክርስቲያንና አማንያኑ ነበሩ፣ ሐጫሉ ሞተ ተብሎም የሆነው ይሄው ነው፡፡ በሐጫሉ ግድያም እነእስክንድር በኦርቶዶክስነት ተወንጅለው ታሰሩ፡፡ እዚህ መዘርዘር የማልችላቸው ሌሎች ብዙ ተመሳሳይ ክስተቶችን አይተናል፡፡ ለግንዛቤ ግን የሚከተለውን አንባቢ እንዲያስተውል እፈልጋለሁ፡፡

አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጣ ወቅት በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ያለውን ስሜት ስለተረዳ ኢትዮጵያዊነትን በደንብ ከሽኖ በመናገርና ኢትዮጵያውያን በወያኔ ምክነያት አጣንው ብለው የሚያስቡትን በተወሰነ ለማታለያነት በማቅረብ ሙሉ በሙሉ አመኔታ ተሰጠው፡፡ ኢትዮጵያውያን በዚህ በደንብ ተዘናግተው እያለ እሱ ግን በፍጥነት ለዘመናት ሲሴር የነበረን የመንግስትን መዋቅር በኦሮሞ ማስያዝ ሴራውን ሲያከናውን ከረመ፡፡ ሕዝብ ፍጹም ስለተዘናጋ ወያኔ እንኳን አድርጋው የማታውቀውን የአዲስ አበባን ከተማ ለማስተዳደር ከኦሮሚያ ታከለ ኡማን አመጣ፡፡ የታከለ ኡማም የተሰጠው ተልዕኮ በገፍ የአዲስ አበባን መዋቅሮች በተለይ የፀጥታ ኃይሉን በኦሮሞ መተካት ነበር፡፡ ከዚህ ሌላ በአዲስ አበባ ያለምንም ከልካይ በኦሮሞነት ብቻ ቦታዎች ለኦሮሞ ማደል ነበር፡፡ ይሄ በሕዝብ ገንዘብ የተሰሩ የነዋሪዎችን ኮንደሚኒየም ቤቶች ሳይቀር እስከመስጠት የደረሰ ግልጽ የሆነ ዘመቻ ነበር፡፡ እንግዲህ ምን ያህል ሕዝብ እንደፈዘዘ የምናየው እዚህ ጋር ነው፡፡ በሌላ ኩል እነ እስክንድር ነጋ ከጅምሩ እየሆነ ያለውን እውነት በይፋ በመናገራቸውና ሕዝብንም እንዲጠነቀቅ በማድረጋቸው ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚለው ሳይቀር እንዴት ሲጣጣሉ እንደነበር ታዝበናል፡፡ የፈዘዘ ሕዝብ እንዲህ ነው፡፡ በአብይ አህመድ አዚም የተደረገበት አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዛሬም ድረስ ከአዚሙ የወጣ አይመስለኝም፡፡ በመጨረሻም እነእስክንድር ግልጽ በሆነ ዘረኝነት የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ቡድን  ወደእስር ሲጨምር አሁንም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ብዙሐን የአብይ አህመድ አጫፋሪ ሆኖ ቀረ፡፡ 13 ሚሊየን ሄክታር መሬትና በሺዎች የሚቆጠሩ የሕዝብ የመኖሪያ ቤቶችን ለኦሮሞ ያደለውን ታከለን ለሌላ የዘረፋ ቦታ ሲሾም በድጋሜ አሁንም ከኦሮሚያ ለአዲስ አበባ ከንቲባ የሾመው አብይ አህመድ እንደሆነ እየታወቀ አሁንም ድረስ በአብይ በራሱ የሚቆመረውን ሴራ ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተረዱን አይመስልም፡፡

አብይ የግርግር አጋጣሚዎችን ሁሉ ለዚሁ ዜራው ሲጠቀምበት በግልጽ እያየን ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ወያኔ ጦርነት በከፈተቸው ወቅት ያደረገው የባለስልጣናት ሹምሽር የሴራው አጋጣሚውን ለሴራው እንደተጠቀመበት እንታዘባለን፡፡ የመከላከያው የታማጆር ሹም የነበሩት ጀነራል አደም ከቦታቸው ሲነሱ ብዙዎቻችን ገምተን የነበርን ምን አልባት ለወያኔ እገዛ የሚሆን ወይም ቸልተኝነት ብለን ነበር፡፡ ሆኖም ከሁኔታዎች እንደምንገነዘበው ከጅምሩም ጀነራሉ በቦታው ላይ በአግባቡ እንዲመሩ የተደረገ አለመሆኑንና አጠቃላይ መከላከያው እዝ አብይ ቤተመንግስት ሆኖ የሚቆጣጠረው እንደነበር ታዝበናል፡፡ ለወያኔ እዚህ መድረስም ዋናው ምክነያት ኋላ ከነጭርሱም መከላያው የመረጃ ትስስሩ ጠፍቶ ወያኔ እንደፈለገች ስታደርገው የነበረበትን ሁኔታ ያመቻቸው ይሄው የአብይ እዙን በራሱ ሥር ለማድረግ የሄደበት ቁማር እንደነበር እንታዘባለን፡፡ አብይ አነፍናፊው ሲል ሲያቆላምጠው የነበረው አስራት ዴኔሮ የተባለው ሰው ሲሞካሽ የሰማንው በአየንው ሁኔታ መከላከያውን ለአደጋ የዳረገ የመረጃ መረብን በማጋለጡ ካልሆነ መቼም በሠራው ሥራ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡

ሌላው የጦርነቱን አጋጣሚ ተጠቅሞ አብይ ገዱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነት ያነሳበት ሁኔታ እጅግ አደገኛ ሴራ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ይሄ ለብዙ ጊዜ ቦታውን በኦሮሞ ለማስያዝ ሲያሴረው ከነበረው አንዱ ነው፡፡ ሁሉንም ድንገት ቢያሲዝ ይነቃና ተዓማኒነቴን ያሳጣል በሚል ነው፡፡ ግርግሮችንም የሚጠቀመው ለዚህ እንደሆነ አገምታለሁ፡፡ በደንብ ካስተዋልን በተለይ በአባይ ግድብ ዙሪያ ገዱ የየዘው አቋም ጠንከር ያለ በመሆኑ ሱዳን ገዱ ከቦታው እስከተነሳበት ጊዜ ድረስ አቋሟ ከኢትዮጵያ ጋር ነበር፡፡ ዛሬ በፍጥነት ተገልብጣ እየሆነ ያለውን እያየን ነው፡፡ ይገርማል፡፡ ገዱ በውጭ ጉዳይ እያለ እንደገባኝ ከእነዲና ሙፍቲ ጋር አልተስማም፡፡ ዲና ሙፍቲ አብይ እንደተመረጠ ኬኒያ አምባሳደር ነበር፡፡ ከዛ በፊት ይሁን በኋላ በግብፅም አምባሳደር እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሌላው ግን የዚህ ግለሰብ አደገኛነት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ትፈርሳለች እያለ ሲያሴር የነበረ እንደነበር የቆዪ ምንጮች ያመላክታሉ፡፡ ይህ ግለሰብ በዛ ቦታ ከግብጽ ጋር ምን እያሴረም እንደሆነ ግልጽ አደለም፡፡ በቀን በቀን በሚናገራቸው የማሳሳቻ ቃላት ግን ሚዲያ ነን የሚሉ ሁሉ ሲያራግቡለት እያየን ነው፡፡ እውነታው ግን ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይህ ግለሰብ በኢትዮጵያ የደህንነት አደጋ ሲያሴር እንደነበር ምልክቶች አሉ፡፡ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ያበት ቦታ የተቀመጠበት መስፈርት ምን አልባትም ከኦሮሞነትም በዘለለ ከአብይ ጋር ልዩ የሆነ ሴራ ሊኖር ይችላል፡፡ ይሄውም ኢትዮጵያን ለውጭ ኃይሎች ማጋለጥ፡፡ አዝናለሁ፡፡ ይሄን ጉዳይ ቀደም ብዬም በአንዳንድ ጽሁፎቼ ለማሳሰብ ሞክሬ ነበር፡፡ ሆኖም ማን ይሰማል?

ውጭ ጉዳዩ ዛሬ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በተደራቢነት የተሰጠ ነው፡፡ አንድ ሰሞን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር የተባለው በየአገሩ መዞር ጀመረ፡፡ ከዛ በኋላ ግን የት እንዳለ እንኳን አይታወቅም፡፡ ሙሉበሙሉ በሚባል ዛሬ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እየተመራ ያለው በዲና ሙፍቲ ነው፡፡ ያም ቢሆን ከገዱ በላይ ደመቀን ለዛ ቦታ የማምነው ሰው አደለም፡፡ ብዙ ችግሮች አሉና፡፡ ደመቀ የሄደባቸው የዲፕሎማሳዊ ጉዞዎች ፋይዳቸውን አላየንም፡፡ ሲጀምር እንዲህ ያለ የሽርሽር የሚመስል ጉዞ አደለም የአገር ደህንነትን የሚያስጠብቅ፡፡ ወሳኝ የሆኑ አቋምን በመያዝና መረጃን በማጠናከር እንጂ፡፡ የሆነ ሆኖ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ በግልጽ ለወራሪ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ተጋልጣለች፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በአብይ አህመድና ሌሎች ኦነጋውያን ዘረኛ፣ በጥላቻ የተሞላ የበታችነትና  ስግብግብት እንደሆነ እናስተውል፡፡

አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ከተመረጠ ጀምሮ የሄደባቸውን የውጭ ግንኙነትም በአጽኖጽ አስተውሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከአረብ አገራት ጋር የልብ የሆነ ወዳጅነት ኖሯት አያውቅም፡፡ ኢትዮጵያ አባይን የሚያህል የአረብ አገራት ሁሉ የተባበሩበት ጠላት ያላት አገር ነች፡፡ የአረብ ሊግ የተባለው መቀመጫው ካይሮ የሆነውና በግብጥ የሚመራው ተቋም ዋነኛ ኢላማው ኢትዮጵያ እንደሆነች ግልጽ ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ ለብዙ አረብ አገራት እንደ ባላንጣ የምትታያው እስራኤል በአረብ ሊግ ትልቅ አጀንዳ አደለችም፡፡ ሲጀምር የአረብ ሊግን ያቋቋመችውና አሁንም ድረስ የምትመራው ግብጽ ነች፡፡ አብይ አህመድ የአባይን ግድብ አስመልክቶ ከግብጽ ጋር የገባውን ውል ምንም የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ባለፈው የአባይ ግድብ ጉዳይ ከተፋሰሱ አገራትና ከአፍሪካ ሕብረት ወጥቶ ወደአሜሪካ የሄደበት ምክነያቱም አብይ አህመድ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ሌላ ቀርቶ አብይ አህመድ ግድቡን ለፖለቲካ ፍጆታ የተጀመረ ሲል እንደተቸም ሰምተናል፡፡ እንግዲህ አስተውሉት የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስቴርነትን ቦታ የያዘው ሰው ይሄን እየተናገረ ስለአገር ደህንነት ሲቆረቆር፡፡ ይሄ እንግዲህ ከምንም በላይ አደገኛ የሆነ የአገር ስጋት ነው፡፡

አብይ ከኦሮሞ ውጭ ወደ መንግስት መዋቅር እንዲመጣ እንደማይፈልግ እያስተዋልን ነው፡፡ አሁን ዋና ዋና የተባሉ የፈደራሉ መዋቅሮችና በተለይም የአዲስ አበባ መዋቅሮች በኦሮሞ ተሞልተዋል፡፡ መከላከያው ሲጀምር በአፋሯ እንስት እንዲመራ ቢደረግም ወዲያው ነበር በኦሮሞ የተተካቸው፡፡ በነገራችን ላይ እኔ ዛሬም ቢሆን ለለማ መገርሳ ትልቅ ቦታ አለኝ፡፡ ዛሬ በሚዲያ እንደሚወራውም ነው ብይ አላምንም፡፡ የመከላከያው ቦታ ለማ መያዙ ሳይሆን መዋቅሮች ሆን ተብሎ በኦሮሞ እንዲሞሉ እየተደረገ ያለበት ሁኔታ ነው አደጋ ሆኖ ያየሁት፡፡  ከዛም በኋላ ለማ ሲነሳ አሁንም ያ ቦታ ምን እልባትም ቦታውን በማይመጥን ሰው በኦሮሞነት ብቻ እንደተያዘ እታዘባለሁ፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኦሮሞነትና በጴንጤነት ብቻ ከእነጭርሱም የባንክ አስተዳደር ልምድ በሌለው ግለሰብ ተይዞ ሆን ተብሎ ገንዘብ ለኦነግ ሲተላለፍበት እንደነበር አይተናል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሁን እየተመራ ያለው ከሙያ አንጻር የብቃት ችግር ባለበት ሰው ባይሆንም ዳግመኛ ካልጠፋ የባንኩ የራሱ ሰው ከኦሮሚያ ኢነተርናሽናል ባንክ በመጣው ግለሰብ መሆኑ ይሰመርበት፡፡ ይህ ግለሰብ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ይገመታል፡፡ ከኦሮሞነት (ዘረኝነት) ውጭም እንግዲህ ግለሰቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጥቅሞች ለኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሊያሳልፍ እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ እጅግ አደገኛ ነውና፡፡

የእኔ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ያሉ መዋቅሮችን በኦሮሞ ማስወረር ግን ከኢኮነሚያዊ ስጋት በላይ የደህንነት ስጋቱ ገዝፎ ይታየኛል፡፡ ዛሬ ኦነግ ሸኔ ምናምን እያሉ የሚጠሩት ቡድን ዋነኛ የገንዘብ ምንጩም ይሄው ባንክ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ዛሬ በየቀኑ የምንሰማው የዜጎችን እልቂት የሚፈጽሙ አረመኔዎች የገንዘብ ምንጫቸው ይሄው ባንክ እንደሚሆን ትልቅ ስጋት አለኝ፡፡ ባንኩ በርካታ ጊዜ በዘረፋ ሥም ገንዘብ ለእነዚሁ አረመኔዎች ገንዘብ ሲያስተላልፍ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ዛሬም አይነገር እንጂ በምን ሁኔታ እንዳለ አናውቅም፡፡ በነገራችን ላይ ኦነግ ሸኔ ምናምን የሚባ ነገር የለም፡፡ ኦነግ አንድ ሲሆን ዛሬ ኦነግ ሸኔ የሚባለው አዲስ አበባ ላይ ተቀምጠው ባሉ መሪዎች የሚታዘዘ የቡድኑ የአረመኔ ገዳዮች ክንፍ ነው፡፡ ለዛም ነው እንዲህ ቀልድ እስከሚመስል ደረስ የዜጎች ዘግናኝ በሆነ ሆኔታ መታረድ የቀጠለው፡፡ ይሄ ደግሞ ራሱ አብይ ጨምሮ እንዳለበት እገምታለሁ፡፡ ሁኔታዎችን እንደወረደ አስተውሉ፡፡

በነገራችን ላይ እኔ የአብይና የለማ ጸብ ዛሬ በሚዲያ እንደሚናፈሰው ነው ብዬ አላምንም፡፡ ለማ በብዙ መልኩ ለኦነጋውያን አስተሳሰብ ተቃራኒ ነበር፡፡ አሁን ቢሆን ወሬውን የሚያናፍሱት የአብይ ደጋፊዎች ስለሆኑ እንጂ ይሄን እውነት መቀየሩን እርግጠኞች አደለንም፡፡ እነጀዋርን ጨምሮ ከለማ ይልቅ ሲንከባከብ የነበረው አብይ ነው፡፡ በተቃራኒው ለማ እኛ ስንት መስዋዕት የከፈልንበትን ማንም ከሜዳ እየመጣ የለውጡ ዋና እኔ ነኝ አይለንም እያለ በተደጋጋሚ ሲናገር ነበር፡፡ እንደውም ምን ዓልባትም ለማን ከኦሮሚያ የማንሳቱ ሴራ በዚህ አቋሙ ምክነያትም ሊሆን እንሚችል እገምታለሁ፡፡ ለማ ከእነጀዋር ጋር ነበር ከሚለው ይልቅ አብይ ከእነጀዋር ጋር ይቆምር ነበር የሚለው በእጅጉ የቀረበ ነው፡፡ ከሚኒሶታ ጀምሮ የአብይ ከጀዋር ጋር የፈጠረው ሴራ ነበር፡፡ ሆኖም ቆይቶ በራሱ ላይ እንደመጣበት እንታዘባለን፡፡ እውነታዎች የሚያሳዩት ይሄን እንጂ ለማ ከአብይ ይልቅ በኦነጋውያን ተጠለፈ የሚለውን አደለም፡፡ ለማን በእነሽመልሽ አብዲሳ የመተካቱ ሴራ ነበር ይልቁንስ ትልቁ የኦነጋውያን ስኬት፡፡  አሁን ግን ሁሉም ነገር መሠረቱን የለቀቀ ይመስለኛል፡፡

አዝናለሁ፡፡ የኦሮሞ ዘረኛ፣ በጥላቻ የተመረዘ፣ በበታችነት የተሞላ ስግብግብነት የነገሰበት ፖለቲካ ኢትዮጵያን ወደከፋ አደጋ እየመራት ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከመቼውም ጊዜ ይለቅ ዛሬ መዘናጋታችሁን አስተውሉ፡፡ ለአገራችሁ ወሳኝ ሚና ለመጫወት ተዘጋጁ፡፡ ከባድ መስዋዕትነት የሚጠብቅ ጊዜ ሳይመጣ አይቀርም፡፡ እኔ በማንም ላይ በማንነቱ የተነሳ የምጠላው ሰው የለኝም፡፡ የኦሮሞን ፖለቲካ ከጅምሩ ሳሳስብ ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ኦሮሞ እንደሕዝብም ጭምር ከኢትዮጵያዊነት እየወጣ ነው፡፡ ለ50ና ምን ዓልባትም ከዛ በላይ በተሰራ ሴራ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ግዙፍ ሚና የነበራቸው የቀደሙ የኦሮሞ ጀግኖች አባቶች በዛሬው የኦሮሞ ትውልድ ሥማቸው እንዳይነሳና ሆን ተብሎ ታሪካቸው እንዲጠፋ በመደረጉ ዛሬ ላይ ያለው ብዙ ኦሮሞ ጀግኖቹ እነጀዋር እንጂ በአላም ሳይቀር ትልልቅ ዝና ያላቸው እኔ አብዲስ አጋ፣ ጎበና ዳጬ፣ አባ መላ (ፊት አውራሪ ሐብቴ)፣ ወይም ባልቻና ገበየሁ አደሉም፡፡ እንደውም የእነዚህ ጀግኖች ሥም ሲጠራ እንደ እብድ የሚያደርገውና የሚደነብር ትውልድ ነው የተፈጠረው፡፡ ዛሬ ጎበና ዳጬ በኦሮሞ ዘንድ ምን ሆኖ እንደተቀረጸ እናውቃለን፡፡ ግብጽና ሱዳን ዛሬ እየተማመኑበት ካላቻ ኃይል አንዱና ዋነኛው ይሄው በጥላቻ፣ ዘረኝነትና በበታችነት ስሜት እንዲጠፋ የተደረገው ብዙ የኦሮሞ ትውልድ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ እውነታዎቸ ፈጠው የመጡ ይመስለኛል፡፡ በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለአገሩ ይቁም፡፡ በተለይ ኦሮሞ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን (ያልተመረዛችሁ) ከማንም በፊት ወጥታችሁ እውነቱን ተጋፈጡ፡፡

ሌላው ትግሬን በብዛት የወያኔ ቅልቦች ዛሬ ከኢትዮጵያዊነት እያወጡት ነው፡፡ ወያኔ ለብዙ ደጋፊዎቹ እንደልባቸው መኖር እንዲችሉ አደረጋቸው እንጂ ትግራይ ላለው ትግሬ እንዳች እንዳልጠቀመው ይልቁንስ ከማንም በከፋ መከራ ሲያደርስበት እንደነበር እናውቃለን፡፡ የወያኔ መሪዎች ዛሬ በሆኑበት ሁኔታ ማየት እንኳንስ ትግሬውን ሌሎቻችንንም እንደ እውነቱ ጮቤ የሚያስረግጥ አደለም፡፡ ይልቁንስ አሳዛኝ እንጂ፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ የተከተሉት እርግማን እስከ ሽምግልናቸው ደርሶ በእነሱ እድሜ ያለ ሰው በእንዲህ ያለ አረመኔያዊ ተግባር ተሰማረቶ ማየት እጅግ ሕሊናን ይረብሻል፡፡ ሁሉንም እያጠፋቸው ያለው የተከተሉት እርግማን ወደራሳቸው እንዲመለስ እግዚአብሔር ስለፈረደ እንጂ በሰው እንዳልሆነ አስተውሉ፡፡ የወያኔ የጥቀም ተጋሪዎች ዛሬ አብድ ቢሆኑ አይደንቀንም፡፡ ሆኖም በግርግርና በስሜት እነሱን እየተከተላችሁ ያላችሁ ቀሪ ትግሬዎች አስበቡት፡፡ አሁን እያስተዋልኩ ያለሁት የወያኔ ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ትግሬዎች በስሜት ብቻ በጸረ-ኢትዮጵያዊነት ተሰማርተዋል፡፡ ይሄ ቆይቶ እንደ ልክፍት እንዳይጠናወታችሁ እሰጋለሁ፡፡ ይልቁንስ ለትግሬ ኢትዮጵያውያንም እላለሁ፡፡ አሁን አገራችሁ ትፈልጋችኋለች፡፡ ይህ ዳግም አደዋ ነው፡፡

የባለስልጣን አፈቀላጤ እከስመምሰል የደረሳችሁ ሚዲያዎችና ዩቲበሮች አስቡበት፡፡ ይህ አገርን ከመክዳት ያልተናነሰ ጉዳይ ነው፡፡ በየኔታ ቲዩብ በተደጋጋሚ እየቀረበ የተሳከረ መረጃ የሚሰጠው ስዩም ተሾመ በግልጽ የአብይ የመረጃ ማሳከር ምልምል እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ከአረቦች ይልቅ እስራኤለን የኢትዮጵያ ጠላት አድርጎ ሊያሳየን የሞክራል፡፡ ከአንዋር ሳዳት ጀምሮ የነበረን ትርክት ዛሬ ላይ አለ እያለ ለማሳመን የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም፡፡ እስራኤል ኢትዮጵያን የምትፈልጋት ለራሷ ስትል ጭምር ነው፡፡ እስራኤል ከኢትዮጵያ ይልቅ የሱዳን ወይም የግብፅ ወዳጅ የምትሆንበት አጋጣሚ ከተፈጠረም ከኢትዮጵያ መንግስት መዋቅሩን ከተቆጣጠሩት ጸረ-ኢትዮጵያውያን የሚመነጭ ነው፡፡ አብይ እስራኤልን በጎበኘበት ወቅት እስራኤል ያደረገቸው አቀባበል መልዕክቱ ግልጽ ነበር፡፡ አብይ ግን ከእስራኤል ይልቅ የአረብ ወዳጀነቱን ነው የመረጠው፡፡ ራስ ዳሸን ተቃጠለ ሲባል እስራኤል ሔሊኮፕተር የላከቸው እሳት ለማጥፋት ነው የሚል የጅል ግምት የለኝም፡፡ መልዕክቱ ግልጽ ነው፡፡ ከማንም በላይ እኔ ለኢትዮጵያ እቀርባለሁ የሚል እንደነበር፡፡ በእስራኤል እስራኤላዊ የሆኑ በርካታ የእኛው ዘመዶች እንዳሉ እንኳን ማስተዋል በቂ ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ስዩም ተሾመ ለዓብይ ሴራ ማሳከሪያ እንጂ እውነተኛ መረጃ እየተናገረ እንዳልሆነ ሁሉም ልብ ይበል፡፡ የአብይ ደጋፊ ሌሎች በርካታ ሚዲያዎች፡፡ መደገፍ ትችላላችሁ ሆኖም እውነትን እየካዳችሁ አሁን ከላይ ፈጠው የወጡ እውነቶችን ዘረዘርኩ እንጂ ያልታየ ነገርንም አደለም፡፡ ለምትደግፉትም ሰው የሚጠቅመው አልመሰለኝም፡፡ ነገሮች በፍጥነት እየሄዱበት ያለው አቅጣጫ ጥሩ አደለምና፡፡

 

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!  አሜን!

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.