በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የቀጠለዉ ግድያ – ነጋሳ ደሳለ

138133973 4072714769428255 3815111157280001612 o በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የቀጠለዉ ግድያ     ነጋሳ ደሳለበቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ፣ ወምበራ፣ ድባጢና ቡሌን ወረዳዎች ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ እስከ ዛሬው ማክሰኞ በደረሰ ጥቃት የሰው ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎቸ ገለፁ። በዞኑ ጉባ ወረዳ ትናንት ሰኞ በደረሰው ጥቃት ከ 11 ሰዎች ህይወት አልፎአል። በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ስፋራ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸዉን አጥተዋል፤በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች የአካባቢዉ አመልክቷል፡፡ አካባቢዉ ላይ ይኖሩ የነበሩና ጥቃቱ ሲከሰት የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች መኖራቸዉን ተጠቁመዋል፡፡ ከአካባቢው ኮማንድ ፖስት ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ያደረግነዉ ጥረት የስልክ ጥሪን ባለመቀበላቸዉ አልተሳካም፡፡
በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ አልመሽመሽ በተባለ ስፋራ ትናንት ከሰዓት ታጠቂዎቹ በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስ ጉዳት ማድረሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። የግለሰቦችን መኖሪያ ቤቶችንም ማቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን የተለያዩ የቁም እንስሳትን መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ በማንዱራ ወረዳ ጉዳት ማድረሳቸው ታዉቋል።
ከመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ከተማ በ40 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚትገኘዋ በጎንዲ በተበለ ስፋራ ከባለፈው ሃሙስ ጀምሮ የታጡቁ ሸማቂዎች ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ጉዳት ደረሰባቸው የአካቢው ነዋሪዎች በስልክ ለዶቼቬሌ ገልጸዋል። በዕለቱ ታጠቂዎቹ አድፍጠው በመጠበቅ በጸጥታ ኃይሎች ላይም ጥቃት መፈጸማቸውን ጠቁመዋል። በወምበራ ወረዳ ሰንኮራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ለሚ ሰንበታ በበጎንዲ የግብርና ስራ ተሰማርተው የነበሩ ሲሆን በስፋራ የደረሰውን ጥቃት ሸሽተው አሁን ከወረዳው ከተማ እነደሚገኙ አመልክቷል።
“ታጠቂዎቹ በጎንዲ ላይ ጥቃት ካደረሱ በኃላ ሁለት መኪኖችን አቃጥለዋል። የሞቱት ሰዎች 3ቱ የመነስቡ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ ሌሎቹ የሰንኮራ፣ ደብረዘይት፣ ጎጆር የተባለ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ናቸው። ሁለቱ ደግሞ የአንድ በተሰብ አባላት ሲሆኑ የጸጥታ ሀይሎችም ይገኙበታል። ወደ አስራ ስድስት ሰዎች ህወታቸው አልፈዋልም” ብለዋል።
በመተከል ዞን ድባጢ ወረዳ ዳላቲ በተባለ ቦታ ሌላ አደጋኛ ሁኔታ መፈጠሩን ከአካባቢው ዛሬ ከአካባቢዉ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ከክልሉ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ፣ከዞኑ አስቸካይ ጊዜ አስተዳደደር( ኮማንድ ፖስት) ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ ለማግኘት በስልክ ያረኩት ጥረት ስልክ ባለማሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ በቅርቡ በዞኑ የተቋቋመው ግብረ ኃይልም በዞኑ ሰላምን ለማስፈን ያስችላሉ የተባሉ ምክክሮችን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማድረጉን ከኢዜአ ያኘነው መረጃ ያመልክታል፡፡
ዘገባ፤ ነጋሳ ደሳለኝ «DW» ከአሶሳ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.