የትግራይ ክልልን መልሶ የማቋቋም መርሐ-ግብር ተነድፎ ወደ ተግባር ተገብቷል… – ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

137628455 2851365201772607 8174752566903290251 oመንግሥት በትግራይ ክልል የወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ መጠናቀቅን ተከትሎ በአፋጣኝ የመልሶ ማቋቋም መርሐ ግብር በመንደፍ ወደ ተግባር መግባቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
በቅርቡ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉ ሰላማዊ ዜጎችን ለመደገፍ በብሪታኒያ ለሦስት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የበይነ-መረብ የገቢ ማሰባሰበያ ዝግጅት ተጠናቋል።
በዝግጅቱ መጠናቀቂያ ላይ አቶ ደመቀ መኮንን እንደተናገሩት፣ መንግሥት ላለፉት ሁለት ዓመታት ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ሂደት ውስጥ መግባቱን አስታውሰው፣ በሌላ በኩል መንግሥት በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ እያካሄደ ያለው ሪፎርም ባልተዋጠላቸው የውስጥ እና የውጭ አካላት በተገመደ ሴራ ሕዝባችን ለችግር እና ለጥፋት ሲዳረግ ቆይቷል ብለዋል።
መንግሥት ክህደት በፈፀሙ ኃይሎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሕግ ማስከበር እና ሀገርን የመታደግ ተግባር አከናውኗል፤ በተደረገውም ሁለገብ ርብርብ ጁንታው ፈጽሞ በማያገግምበት መልኩ ግብዓተ መሬቱ ተጠናቋል፤ ርዝራዦቹም በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ብለዋል አቶ ደመቀ።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በኤምባሲዎች አስተባባሪነት በዚህ መልኩ ወገኖቻቸውን ለመደገፍ እና ለማቋቋም የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባር በማካሄዳቸው አመስግነዋል።
መንግሥት ዳያስፖራው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገር ግንባታ ላይ እንዲሳተፍ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች እና ተቋማት የማደራጀት ተግባራት ማከናወኑን ገልፀው፣ ዳያስፖራው በሰላም ግንባታ፣ በማህበራዊ ዘርፍ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህልና በቱሪዝም በተናጠልም ሆነ በጋራ የሃገራችንን ‘እድገትና ብልፅግና በመተባበር እንዲያፋጥን ምቹ ሁኔታዎች መፈጥራቸም ገልፀዋል።
ሪፎርሙን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ለመንግሥት አስፈላጊ የሆነው የውጭ ምንዛሪ ችግርን ለመፍታት ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ በመላክ የጥቁር ገበያን የገንዘብ ዝውውርን ለማምከን በሚደረገው ጥረትም የበኩላችሁን ሚና እንድትጫወቱ ጥሪ አቀርባለው ብለዋል ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ብርቱካን አያኖ እንደተናገሩት በብሪታኒያ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቀደም ሲል ሀገራቸውን ለመደገፍ የገንዘብ ፣ የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋችውሁ አስታወሰው። አሁንም የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ለምታደርጉት የገንዘብ ማሰባሰብ ጥረት ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ሲሉ መግለጻቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ድጋፍ የማሰባሰብ ስራው በተቀናጀ መልኩ በሁሉም አቅጣጫ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉት የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በቂ ልምድ ያለን በመሆኑ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ብለዋል።
የዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም ዳዊት በበኩላቸው የዳያስፖራውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እንዲቻል መንግሥት የዳያስፖራ ኤጀንሲ በማቋቋም ከሴክተር ተቋማት ጋር በመቀናጀት የዳያስፖራውን ተሳትፎ የማሳደግ ስራ በትኩረት በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል።
በብሪታኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ዳያስፖራው ሪፎርሙን በመደገፍ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን በርካታ ማሳያዎችን ማቅረብ እንደሚቻል ገልጸው በሀገራችን ብሄራዊ ጥቅሞች ዙሪያ የዛሬውን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ጨምሮ በህዳሴ ግድብ የገንዘብ ድጋፍ የማድረግ ፣ በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ለቀረበው ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በገንዘብ እና በህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
ኢዜአ

7 Comments

 1. ስለ ሱዳን ወረራ ምነው ዝም ተባለ??? ሚኒሻው ብቻውን እየታገለ ነው፡፡ ከትህነግ ጋር ሲሰራ የነበረ ሌላው የጁንታ ግሩፕ እንቅስቃሴ አፋጣኝ እርምጃ ያስፈልጋል፡፡ የሰላም ድርድሩ ጥሩ ቢሆንም የሱዳን መንግስት አካሄድ ግን በደንብ ሊታይ ይገባል፡፡ ስንት አመት ሙሉ ደቡብ እና ሰሜን ሱዳን እየተባሉ በዳርፉርም ህዝቡን ለመከራ ሲያቃዩ የነበሩ እንደገና ጦርነት ይፈልጋሉ፡፡ አንድ አየር ሃይል ጀት እኮ በቂ ነው ግን ወደአልተፈለገ ጦርነት ለምን??? በእብሪተኝነት ወታደርን ወደ ጦርነት መገፋፋት ውድቀትን ለማፋጠን እንደሆነ ከትህነግ ጁንታ ውድቀት ሁሉም ሊማር ይገባል፡፡ ኢትዮጵያን የነካ አወዳደቁ አየምርም እና፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

 2. ምን ማለት ነው መልሶ ማቋቋም ማለት? መልሶ መቋቋም የሚፈልገው እኮ የትግራይ ክልል ብቻ አይደለም። በሃገሪቱ በዘራቸው የተነሳ ከቀያቸው ተባረው በየስፍራው ለወደቁ ከሞት ተራፊዎች የምትለው አለህ? እኔ የሃገሪቱ መሪ ነን የሚሉ ሁሉ የሚሰሩት ሥራ ግራ ያጋባል። ወዶ፤ ፈልጎ፤ ተመሳጥሮ፤ ታጥቆና አስታጥቆ ጦርነት በጉያው ካለው የሃገሪቱ ሰራዊት ጋር ግብ ግብ የገጠመን ቡድንና ህዝብ በመላሾ ደርስንላችሁሃል በማለት ዝም ማድረግ አይቻልም። በሃገሪቱ ታሪክ ሁሉም ሃገር አፍራሽና የወራሪ ሃይል ጦርነቶች ከሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የመነጩ ናቸው። ሰው ሰላምን የሚያውቀው የሰውን ሰውነት ሲረዳ ነው። የሞተ የራሱን ታጋይ አንገት የሚቆርጥ የእብድ ክምር አሁን ምድሪቱን በትራፊና በአዲስ ሃይል ማተራመሱ አይቀሬ ነው። ሞቱ ተቀበሩ ወዘተ የሚባለው ሁሉ ለፓለቲካ ፍጆታ እንጂ ሰው ካስረከበው የጦር መሳሪያ የላቀ ቆፍሮ የቀበረ፤ ከሚናገረው ይልቅ ልቡ የሸፈተ፤ ሰላምን እያወራ ሰላም የሚነሳ ለመሆኑ አሁን በመቀሌ የሚደረገው ዝርፊያና የሴቶች መደፈር አመላካች ነው።
  በየስፍራው እሳት እየለኮሱና አረቦች የእስልምና ማምለኪያ ቦታዎች ተጠቁ ብሎ ያው በፔትሮ ዶላር የሰከረውን እይታቸውን ይዘው እንዲያስታጥቋቸው በዚህም በዚያም ክብሪት የሚጭሩት የተያዙት ወያኔዎች ወይም በውጊያ ላይ የረገፉት አይደሉም። 45 ዓመት ከበሮ እየተመታለት በወያኔ የታሪክ ትንተናና የፓለቲካ እይታ በዘሩ የሰከረው ሁሉ እንጂ። የትግራይ ህዝብ ጠላቶች እናውቅልሃለን የሚሉት ናቸው። ዛሬ በገጠሩ የትግራይ ክፍል ገበሬውን ያለውን የእለት ጉርስ የሚቀሙት 45 ዓመት በስሙ ሲነግድ የነበሩ የወያኔ ትራፊዎች ናቸው። መረዳት ያለበት የትግራይ ህዝብ ስልክ፤ መብራት፤ ያልገባለት፤ በወያኔ የተረሳው የገጠሩ ገበሬ እንጂ የከተማው ሰው እማ ከእነርሱ ጋር አብሮ ሲበላና ሲዘርፍ የኖረ ነው። ስለሆነም እርዳታው የገጠሩን የዋህ ህዝብ የሚደግፍ እስካልሆነ ድረስ የወያኔ የከተማ ካድሬዎች ልባቸው ተለውጦ ከሰላም ጋር ይቆማሉ ብሎ ማሰብ ጊንጥን በኪስ ይዞ አልነደፍም እንደማለት ነው። የስንቱ ሰው ደም በእጃቸው አለ? ስንቶች አምልጠው በህዝቡ መካከል ይርመሰመሳሉ፤ እንደገና ለማንሰራራት ሴራ ይጎነጉናሉ? ማስተዋል መቻል አለብን። በ 45 ዓመት የሃገሪቱ የዘረፋ ዘመን ውስጥ ወያኔ የዘነጋው ይህ ህዝብ አሁን ልብ ብሎ ሰላምን ሽቶ ክወያኔ መርዝ ራሱን አላቆ እፎይ ብሎ ባጭር ጊዜ ውስጥ ይኖራል የሚል ጭራሽ ጅል ነው። ገና በዚያች ምድር ላይ ብዙ ነገር እናያለን። ሰው የሚያስበው በጠበንጃ አፈሙዝና በጡጫው እስከሆነ ድረስ መፋለም አይቀሬ ነው። ወያኔ ለትግራይ ህዝብ ያስተማረው እኛ ደርግን የደመሰስን ጀግኖች፤ ተራራ ያንቀጠቀጥን ትውልዶች እያለ ነው። ይህ ሁሉ ጉራ እንጂ ለፈተሸው የደርግ መፈራረስ የራሱ ደንባራነት እንጂ ተዋጊ ሃይል ጠፍቶ አይደለም። ግን የፓለቲካ ንፋስ ወደ ፈለገው አይደል የሚነፍሰው ለዛ ነው ትላንትም ዛሬን የሚመስለው።
  ስለሆነም አቶ ደመቀና ጓዶቻቸው ከትግራይ ህዝብ የበለጠ መከራ ውስጥ የገባ ወገን በየስፍራው ተበትኗል። እቅድ የሚነደፈው ሜዳ ላይ በብርድና በዝናብ ለረሃብ ለተጋለጡት፤ በየቀኑ በዘራቸው የተነሳ ያገኘው ሁሉ እንደ አራዊት የሚገላቸውንና የሚያርዳቸውን በምስራቅ/በምእራብ/በደቡብ የተጎድ ወገኖቻችን እስካላካተተ ድረስ በሰሜኑ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ተገቢ አይመስለኝም። በትግራይ የሚደረጉ የእርዳታ/የመልሶ ማቋቋም ፕላን ሁሉ ከገጠሩ ክፍል ይጀምር። በቃኝ!

  • “በሃገሪቱ ታሪክ ሁሉም ሃገር አፍራሽና የወራሪ ሃይል ጦርነቶች ከሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የመነጩ ናቸው። ”

   Wie bitte ? komm zur Sache Schätzchen ! ካለ ብዙ መጥመዝመዝ የልብን መናገር የሚመስሉት ነገር የለምና፣ ይልቁንስ ብርታቱን ይስጠንና በጥቅስ ካወረድኩት አባባልህ በኋላ የተደበቀውን እንትፋው እንጂ……….! ወይንስ በርግጥም ከኢዛና እስከ አፄ ቴዎድሮስ፣ እንዲሁም ከሽረ እስከ ህንድ ውቅያኖስ የተካሄዱትን ለመዘከር ነውን………..?! ኮሎኒያሊስቶች ባህርን ተሻግረው የሚመጡበት አቅጣጫም ባብዛኛው ለሰሜኑ ክፍለ ሃገራችን ወይንም ለሱማሌ ይቀርባሉና ታድያ ተፈጥሮና ጂኦግራፊን እንዴት እና ምን እናድርጋቸው ?!

   • ዘረ-ያዕቖብ – እንደ አቦይ ስብሃት ጋጃ ታጨሳለህ እንዴ? አሁን የእኔን አባባል ከመልክዓ ምድር አቀማመጥ ጋር ምን አገናኘው? እኔ እምለው ለሴራው ፓለቲካ ሃገር ለመሸጥ ለመለወጥ፤ ባህር ተሻግረው ከመጡ ነጭም ሆኑ ዓረብ ወራሪዎች ጋር ለመተባበር በዚህም በዛም የሰውን ባህሪ ነው የኮነንኩት። አልፎ ተርፎም የባንዳዎቹ ልጆች ተሰባስበው ለ 45 ዓመት ሃገሪቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለው እያላተሙን እንዳሉ መረዳት አዋቂነት ነው። ሰው ራሱን እንጂ የተወለደበትን የመሬት አቀማመጥ ወይም የዘር ሃረግ መለወጥ አይቻለውም። ለዚህም ይመስለኛል ሰው በሰውነቱ ይለካ የምንለው። የአንተ አማራ፤ ትግሬ፤ ኦሮሞ፤ አደሬ ወይም ጉራጌ ወዘተ መሆን ከሰፈር ጡሩንባ አያልፍም። በአለም አቀፍ መድረክ በሰውነት ተራ ተሰልፎ ዛሬም ትላንትም በቆዳቸው ብቻ ለሚጨቆኑት ለጥቁር ህዝቦች ፍትህ እንሰለፍ ነው አባባሌ። እስቲ አስበው በትግራይ እኮ የወያኔን ሃሳብ የተቃወሙ ሁሉ “ባንዳ” ይባሉ ነበር። እስቲ ማን ይሙት ተንጋሎ መትፋት ትፋቱን ከራስ ላይ ያርቀዋል?ባንዳን ባንዳ ሲለው እብደት ለመሆኑ እንዴት የሰው ልጅ አይገባውም። ባንዳ ማለት ሃገርን፤ ወገንን ለራሱ ጥቅም ሲል አሳልፎ የሰጠ ማለት ነው። ለዚህ ወያኔ ሃውልት የቆመለት ተምሳሌ ነው።
    እናማ ወገኔ እኔ ከሃገራችን የመሬት አቀማመጥ ጋር ችግር የለኝም። ከሰው አስተሳሰብ ጋር እንጂ! ዛሬ በጋምቤላ፤ ቤኒሻንጉል፤ በአፋር፤ በደቡብ ክልል የምናየው አንድ አንድ መግደልና ማባረር የእንስሳ ባህሪ አይደለም የሚል በዘሩ የተሰለፈ፤ ከሰው ልጆች ተራ የወጣ እንስሳ ብቻ ነው። 45 ዓመት ከወያኔ ጋር ሲሸጥ ሲለውጥ የኖረው የሱዳን መንግስት አሁን የሃገራችን ድንበር መውረሩ ለወያኔ ደረስኩልህ ለማለትና የግብጽ ተላላኪ ለመሆን እንደሆነ ጭርቁን ያወለቀ ሳይቀር ይረዳዋል። ግን የጥቁር ህዝብ ጠላቱ ራሱ ነው። ሱዳን እልፍ መከራ የከበባት አሁን በአሜሪካ አይዞህ ባይነት የቆመች በቅርቡ Secretary of the Treasury Steven T. Mnuchin ካርቱም ላይ በመገኘት ከእዳ ከምር ላይ ሌላ የእዳ ክምር አሸክሞ የሱዳን መንግስትን አይዞአቹሁ ብሎ እንደተመለስ እናውቃለን። የአለም ፓለቲካ ሁለት መልክ ብቻ አለው። ሌላው ሁሉ እሳት የበላው ማገዶ ነው። የነዳጅ ዘይት ናፍቆትና የነጭ የበላይነት። በሊቢያ፤ በኢራቅ፤ በሶሪያ፤ በቬንዚወላ ወዘተ የሚደረጉ ፍትጊያዎች ሁሉ የነዳጅ ጥቅም ለማስጠበቅና የነጭ የበላይነትን ለማስቀጠል ነው። እንንቃ! በቃኝ!

    • ስለ TPLF ቁስላችንን እየነካኩና እየዘፈኑልን ያደረሱብን መለክያ የለሽ በደልን ለእኔ ለማስረዳት መንደፋደፍ “ቀባሪዋን አረድዋት” አይነት ጉዳይ ለመሆኑ ይሄንን ዌብ እና ሌሎችንም የሚያነብ ሁሉ ምስክሬ ነው ! ደርግን በማባረራቸው ስደግፋቸው በተረፈ ግን ሌሎች ተግባሮቻቸውን አስመልክቶ ከ40 አመታት በላይ በተቻለኝ መጠን ታግያቸዋለሁኝ:: የናንተንም Lobby ከግቦ ጋራ ለመቀላቀል ዝግጁ ስላልሆንኩኝ ብቻዬን ቆሜ በምገኝበትም ስዓታት ላይ ሁሉ ሳይቀር::
     ማጨስን አስመልክቶ ግን ስጋራንም ማጨስ ካቆምኩኝ ወደ 26 ዓመታት ሆኖኛል፣ Was ጋጃ sein soll, habe ich auch keine Ahnung ! ምናልባት አናንተ ከነሱው ጋራ ሆናችሁ የሰው ልጆችን አጥንትም ጭምር ሳይቀር በጋጣችሁበት ጊዝያቶች ላይ አላምጠሄው ሊሆን ይችላል፣
     ወልፍኻ እንተሓቲትኳ ክትቅፅል’ውን ትኽእል ኢኻ !
     “በሃገሪቱ ታሪክ ሁሉም ሃገር አፍራሽና የወራሪ ሃይል ጦርነቶች ከሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የመነጩ ናቸው። ” የሚለውን ዘላለማዊው ፀረ ትግራይ አቋምህን ግን እስካልለቀቅህ ጊዜ ድረስ፣ ዝም ብለን የምናየው “የደረቅ ምንትሴዎችን” ሰምና ወርቅ ልሁን ባይነትን ሳይሆን፣ ባንፃሩ የመቋቋም ሃላፊነት አለብን……….!!!

     • ዘረ-ያዕቖብ – እውነትና ፌዝ ተቀላቅሎብሃል። እኔ ሃሳብክን ነበር የወረፍኩት። አንተነትክን አልነበረም። ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብለህ ብትመለክተ የሃገራችን ችግር ይበልጡ የሚመነጨው ከስሜኑ ክፍል ነው። ቱርኮች፤ ግብጾች፤ እንግሊዞች፤ ጣሊያኖች ሁለት ጊዜ በዚያ በኩል ነው የገቡትና ወረራ ያደረሱት። አንተን እና እኔን ምንም የሚያጣላን ነገር የለም። ማጭስ ማቆምህ ማለፊያ ነው። ኑርልኝ። የጋንጃ ማጨሱ ጉዳይ ቧልት ነበር። ግን አምረህ ተቀበልከው። ይቅርታ!

 3. አሁንስ መላቅጣችሁን አጣችሁ ትግሬ ካንሰሩ ተቆርጦለታል ይልቅ ሽመልስ አብዲሳና ታየ ደንዳን አባርራችሁ የዜጋን ግድያ አታስቆሙም? አብይ እያለ ባንተ በኩል ማስነገሩ የጤንነት አይመስልም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.