የቀድሞው የትግራይ ርዕሰ መስተዳደርና ምክትል ሚኒስትር በቁጥጥር ስር ዋሉ

21111

ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ የጁንታው አመራሮች እርምጃ ተወሰደባቸው
አዲስ አበባ፤ ጥር 2/2013(ኢዜአ) አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው በውጊያ ላይ እያሉ እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።
ብርጋዴል ጄኔራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል።
ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ እንደገለፁት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-
1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ
2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ
3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች
4ኛ – ሁለት መስመራዊ መኮንኖች
5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።
በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።
እነዚህም
1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ
2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ
3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ
4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ
5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ
6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ
7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ለኢዜአ ገልፀዋል።
ኢዜአ
137597925 5181283675245165 2118569971061858043 n
ኢዜአ
138356147 5181284001911799 3428528723699679951 n 138287530 5181283828578483 6054227363166193872 n
ተጨማሪ ያንብቡ:  ደባርቅ የተማሪ አመፅ ተነስቷል | ዳባት ከፍተኛ ውጥረት አለ | አንድ ወጣት ተገሏል

1 Comment

  1. እነዚህ ሰዎች በስልጣን ላይ እያሉ ባደረሱት ወንጀል፤በደል’ዘረፋ፤ግድያ በሁዋላም የተኛ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በማረድ በማይካድራን እና አካባቢዉ በፈጸሙትና ባስፈጸሙት በደል ወደ ሲቪል ሳይሆን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ተላልፈዉ የሚገባቸዉን ቅጣት ማግኘኘት ይገባቸዋል እንጂ በዘረፉት ገንዘብ አሁንም ሲቪል ፍርድ ቤት ቁመዉ ባያላግጡብን መልካም መሰለኝ። በነሱ ምክንያት የወደመዉ የሀገር ንብረት የጠፋዉ የሀገር ሀብት የታረደዉ ዜጋ ስለተላመድነዉ ቀለል እየተደረገ መታይት ላይ ነዉ። ለነገሩ እነ ተወልደን እዚህ ከፍተኛ ቦታ ላይ አስቀምጦ አርከበ እቁባይን የጠሚ አማካሪ አድርጎ አዳነች አበቤንና ሞዴል መአዛ አሸናፊን እዛ ወምበር ላይ አስቀምጦ ፍትህ መጠበቅ ቂልነት ነዉ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.