ጊዜ ሚዛን – ሐመልማል አባተ ”ጊዜ ሚዛን” በሚለው ዘፈኗ እንዲህ ብላ ነግራን ነበር !

unnamed 20አወይ ጊዜ ጊዜ ደራሽ፣
መንገደኛ ሁሌ ገስጋሽ።
ጊዜ ደፋር ጊዜ አይፈሬ፣
ጊዜ ሚዛን አይቸኩሌ፣
ትናንት ዛሬም ነገም ሁሌ።
የተቀበረች ሀቅ ቋጥኝ የተጫናት፣
አራሙቻ ውሸት አረም የሸፈናት።
ቋጥኙን ፈልቅቆ አረሙን አርሞ፣
ያወጣት ጊዜ ነው ለጠበቀ ቆሞ።
አሁን ዛሬ የሞላለት የደመቀው ያመራበት፣
ሲያድር ነገ ይረገጣል የቀን ጽዋ ሲጎድልበት።
በውሎ አዳር በሂደቱ ሁሉም ነገር ይለወጣል፣
ጊዜ ካለ ለእያንዳንዱ ፍርድ ይሰጣል።
ጊዜ ተንታኝ ጊዜ አደራጅ፣
ጊዜ ዳኛ ጊዜ ፈራጅ።
ጊዜ ሰፊው ጊዜ ታጋሽ፣
ምስክር ነው ጊዜ ነቃሽ።
ዛሬ ነገን ባይሆን እንደቆመ ቢቀር፣
ሀሰት በምድሪቱ በነገሠ ነበር።
ይህ የአሁኑ ስራ የዛሬው ተደፍሮ፣
ማን ይገልጠው ነበር ጊዜ ባይኖር ኖሮ።
አያጋድል አያዛባ ህይወት ውሉን መች ይስታል፣
የሰው ስራው ተመዝኖ ቀን ጠብቆ ይከሰታል።
ጊዜ እንደሰው በማንነት አበላልጦ መች ያዳላል፣

ሁሉም ፍጡር በተግባሩ እንደስራው ይታደላል።

Alem T.


unnamed 21

 

 

1 Comment

  1. ህሊናቸውን ቀድመው ድፍን አድርገውት አይ የአምላክ ታምር ቢዘገየም አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ ወርደት ሌላስ ምን አለ፡፡ ወንበር ናፋቂዎች፣ በህዝብ ሃብት ደም እና ለቅሶ የሚቀልድ ሁሉ ከዚህ ሊማር ይገባል፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.