የዚህን ዘመን ተዓምር ማን ይጻፈው!? የወያኔ መጨረሻ! – ሰርፀ ደስታ

በመጽሐፍ የምናነበው እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ተዓምራት  ስንሰማ ተረት ተረት ወይም ድሮ እንጂ አሁን ተዓመር የሌለ ይመስለናል፡፡ እግዚአብሔር ግን በየቀኑ በአይናችን ፊት ታላላቅ ተዓምራትን ያደርጋል፡፡ ሆኖም ክስተቶችን በራሳችን እውቀት ልክ ምክነያት እየሰጠናቸው ተዓምሩ ልክ እንደተራ ነገር ሆኖ በሰዎች ዘንድ እየታለፈ እንዲሁ በራሳችንም ላይ መጥቶ ለማስተዋል ያዳግተናል፡፡ ዛሬ የወያኔ አወዳደቅ የእግዚአብሔርን አሰራርና ተዓምሩን የሚከታተሉና የሚያስተውሉ የጥንቶቸ ጸሐፊዎች ቢያገኙት ታላቅ ተዓምር እንደሆነ ጽፈውልን ባለፉ ነበር፡፡ ዘመኑ ግን እንደዛ የሚያስተውል የነጠፈበት ስለሆነ ወያኔን በጦርነት በመከላከያ የተሸነፈች አድርገንዋል፡፡  አዎ ነው ግን ለመከላከያው ማን እነደረዳው ግን አላስተዋልንም፡፡

136669359 4163736983655269 343174896682156509 n 1

ወያኔ ለዘመናት በአረመኔነት የሰራቸው ግፍ እንድ በአንድ የተሰፈር በመሆኑ በዚህ አረመኔ ስራ ዋና የሆኑ ሁሉ እንዳይቀርላቸው ከላይ ትዕዛዝ ስለወጣ ነው የምናየው ሁሉ የሆነው፡፡ የኃይሎም አርዓያ ባለቤት የነበረቸውን ከምትኖርበት አሜሪካ እስከ ቆላ ተንቤን የወሰዳት መቼም በየትኛውም መስፈርት ተዓምር ከመሆን በቀር ምክነያት ሊሰጠው የሚችል እውነት አደለም፡፡  የሰናክሬምን ታሪክ በመጽሐፍ ቅዱስ አንብበናል ቢያንስ፡፡ ወያኔ ለጦርነቱ በቂ ዝግጅት ማድረግ ብቻም ሳይሆን በትክክለውም ቀላል የማይባሉ ሰዎች ከውስጥ መከላከያውን ዛሬ የምናየውን ድል ይቅርና ሁለተኛም በማይኖርበት ሁኔታ አመቻችተውላቸው ነበር፡፡ በዚህ እጅግ አዝናለሁ፡፡ መከላከያው እንደተባለው እንቅልፍ ላይ በመሆኑ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ሲሴርበት እንደነበርና ግንኙነት እንዳይኖረው ሆን ተብሎ እንደተሰራ እናያለን፡፡ በትግሬ ወያኔ ሳይሆን በሌሎችም ከወያኔ ጋር በተባበሩ ምን ዓልባትም ዛሬ ደግሞ በሌላ ገፅ ጀግና እየተባሉ እየተወደሱ ያሉ መሠሪዎች፡፡ የነበረውን ሂደት ስናስተውል የሆነው ይሄን ይመስላል፡፡

የሆነ ሆኖ ስብሐት ነጋን የዛሬ አምስት ዓመት ገደማ ጎንዴሬዎቹ የተናገሩበት ትንቢት ሲፈጸም አይተናል፡፡ በእርግጥም ገና ከመነሻቸውም ተነግሯቸው ነበር ይባላል፡፡ መለስም ከአማራ ጋር ጦርነት እንገጥማለን ብላችሁ የትግሬን ታሪክ እንዳታበላሹ፡፡ ከአማራ ጋር ምንም ቢሆን ጦርነት እንዳትገጥሙ ብሎ ተናዞ ነበር ይባላል፡፡ እንደውም በዛን ሰሞን ሳሞራ ይሄንኑ ዛሬ ከየጎሬው አስከሬናቸውና በሕይወትም የተገኙት እየተለቀሙ ያሉትን ነግሬአቸው ነበር ደብረጺዮን ይሄን ነገር እናስብበት ሲል አባይ ፀሐይዬና ስብሀት ነጋ ሳቁበት አለ ተብሎ ሲናፈስ አይቼ ነበር፡፡ በእርግጥም ለወያኔ አረመኔዎቹ ተነግሯቸው ነበር፡፡

ደብረጺዮን እንዲሁ እንደተምታታበት ይሄው እሱም አልቀረለትም፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ በጺዮን ማሪያም በካባና አክሊል በአውደ ምህረት ላይ በድፍረት ተቀምጦ አይተንው ነበር፡፡ ይህ ከድፍረትም ድፍረት ነበር፡፡ እውን እግዚአብሔር ዝም ስላለ የለሌ መሠለን? ያችን ቀን ትንሽ በልቡ ራሱን ዝቅ አድርጎ አይገባኝም ቢልና እንደተሰጠው ማዕረግ ቦታውን በማክበር ለእግዚአብሔር ትንሽ ክብር ቢያሳይ ዛሬ የሆነበት አይሆንም የሚል እምነት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር ሲመጣና ሲቀጣ በየት እንደሆነ አናውቅም፡፡ አሁንም በጦርነት ተሸነፉ የሚል ተራ ምክነያት እንጂ የሆነውን እውነት አናስተውልም፡፡

136373955 10225028277403494 7730998992559749397 n

ወያኔ በዚህ ጦርነት እንደምታሸነፍ መቶ በመቶ እርግጠኛ ነበረች፡፡ ለዛም ይመስላል የኃይሎም አረዓያ ሚስት ከአሜሪካ መጥታ መቀሌ እየተዝናናች በቅርብ ሆና በየቀኑ የሚነገረውን ድል እየሰማች ለመፈንደቅ አስባ የነበረው፡፡ ብዙዎችም ከአዲስ አበባ ወደመቀሌ ሄደዋል፡፡ ምክነያቱም መቀሌ ፌሽታና ጭፈራ ሲሆን አዲስ አበባ የጦርነት አውድማ ሆና ዋይታዋን እያዩ ሊጨፍሩ ነበር፡፡ ይሄ ሁሉ እንደሚሆን እርግጠኞች ነበሩ፡፡  በእርግጥም ለዘመናት ተዘጋጅተው 80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የአገሪቱን መከላከያ መትተውና መሳሪያውን በእጃቸው አግብተው ላይሆን የሚችልበት አንዳች ምድራዊ ምክነያት ሊኖር ባልቻለ ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ዛሬ ተሳካለን በችሎታችንና በልዩ ብቃታችን አሸነፍን የሚለው መከላከያ የወያኔን ይሄን የሚያህል መጠነሰፊ ዝግጅት አላየሁም ሳናስብ ነው ይሉናል፡፡ በእርግጥም ችግሩን በደንብ ያሰቡት ነበሩ ሆኖም ሆን ተብሎ የሰሜን እዝ በወያኔ እጅ እንዲወድቅ የተደረገው አሁንም ተገልብጠው ድል አብሳሪ በሆኑ አደገኛ የመከላከያው አባላት እንደሆነ እናስባለን፡፡ የምናያቸው እውነቶች ሁሉ የሚተቁሙን ይሄን የሚመስል ነውና፡፡ እግዚአብሔር ግን በዚህ ሁሉ ዝግጅትና ሴራ ይመለከት ነበር፡፡ ጊዲዮንን በራስህ ኃይል እንዳሸነፍክ አድርገሕ እንዳትመካ ሶስ መቶ ሰራዊት ብቻ ይዘህ ጦርነት ውጣ ያለው እግዚአብሔር ካስተዋልን ወያኔ ሁሉንም ነገር ይዛና ከውስጥ ትግሬ የሆኑትን ሳይጨምር እዙን ሁሉ ተቆጣጥራ  እንዳለችውምና አንዳንዶቹን ከአሜሪካ ድረስ ሌሎችን ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ለጭፈራና ፌሽታ እንዲሰበሰቡ አድርጎ መከላከያው ባዶ በሆነ ጊዜ ወያኔን ለዘመናት በአላገጠችበት በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ እጅ ጣላት፡፡ ዋናዎቹ ጦርነቶች የተደረጉት በራያና ሁመራ ግንባር ነበር፡፡ በእነዚህ ወጊያዎች ደግሞ ዋና ተዋናዩ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ነው መከላከያው ማንሰራራት የቻለው፡፡

እንግዲህ ተዓምር ከዚህ በላይ ምን ቢፈጠር ይሆን ተዓምር የሚባለው? ተዓምረ ማሪያም ብትል ሌላ ተዓምር እየተባለ የሚነበብልህ እንዲህ ያለ ክስተትን ነው፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ዘመን እኛ ስለታወርን አናስተውልም፡፡ ለነገሩ የኖህ ዘመን ሰዎችም እንዲሁ እስከአንገታቸው ባሕር ሲሞላ ምክነያት እየሰጡ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በዚች አገር ላይ ሁሌም ተዓመር ሲሰራ ኖሯል፡፡ ዛሬ ድረስ ክብራችን የሆነው የዓለምን ታሪክ የቀየረው የአደዋው ድል የእግዚአብሔር ተዓምር መገለጫው ነበር፡፡ ጀግኖችን በጀግንነት እንዲዋጉ የሚያደርገውም እግዚአብሔር ነው፡፡ ዛሬ ላይ ከሜዳ የመጣ ማንም እየተነሳ አፉን የሚያሟሽበት ታላቁመ ሚኒሊክ ግን ሲነሳ እግዚአብሔር እስከዛሬም አላሳፈረኝም ዛሬም እንደማያሳፍረኝ አምናለሁ ብሎ ነበር ገና ከአገር ግንባታው ጦርነቶች የተመለሰው ሚኒሊክ በሥሩ ያሉትን ይዞ ወደ አደዋ የተመመው፡፡  ዛሬ ወራዶችና የጣሊያን የባንዳ ይልጅ ልጆች እውን በኢትዮጵያ ላይ እንዳሰቡት እንዳይሆን ስለ እነዛ ምድሪቱን ለጣሊያን እንዳትገዛ ያወገዙ  ወዳጆቹ አባቶቻችን  እግዚአብሔር ተበቀላቸው፡፡

136751511 3826315070794574 4651230186191987932 n

ብዙ ግፍ ዛሬም ቀጥሏል፡፡ ለተረኛ ግፈኞች ትምህርት ቢሆናቸው የሆነው ሁሉ ከላይ እንዳነሳሁት እንጂ በሰራዊተና በመሳሪያ ብዛት እንዳልሆነማ ግልጽ ነው፡፡ መብረቃዊ በሆነ ሁኔታ ሰራዊቱን በተንው ያለው ሰው ከአማራ ተወልዶ ከጅምሩ በጸረ-አማራና ኦርቶዶክስ ከተነሳው አረመኔው ወያኔ ጋር ያበረ አረመኔ በመሆኑ የዛሬው ሞቱ ብቻም ሳይሆን በድንፋታ የተናገረውም ዛሬ ኢትዮጵያን ለመወንጀል አስፍስፈው ባሉም ምስክር እንዲሆንባቸው የጦርነቱ ጀማሪ ወያኔ እንደሆነች እግዚአብሔር አስለፈለፈው፡፡ ሳትወድ ትናገራታለህ! አማራና ኦርቶዶክስን አከርካሪውን ሰብረንዋል ያሉት አዛውንትም ይሄው በዚህ እድሜ እንኳን እንዳያስተውሉ አድርጎ ዛሬ አራጊ ፈጣሪ በሆኑበት አገር የአረመኔነታቸው ልክ ሊዳኝ ቀርበዋል፡፡ እንደ ባህላችን አንቱ ማለት ስላለብኝ ነው፡፡  የኃያሎም አርዓያ ሚስት ብቻም ሳትሆን ብዙዎች በአሜሪካና በተለያዩ ዓለም ቅምጥል ሕይወት የጀመሩ ናቸው የጥጋባቸው ልክ ስላሰከራቸው አስከሬናቸው እየተለቀመ ያለው፡፡ የአዛውንቱ ስብሐት ነጋ ልጆችን ጨምሮ፡፡

136355582 10225028277843505 1536985553810873787 nበጣም ያሳዝናል፡፡ በውጭ ያሉት ቀሪዎቹ ይሄው ከእብደት ባልተናነሰ የሚሰሩትን አሳጥቷቸዋል፡፡ ዛሬ በአውስተራሊያ በጥቁር ፕላስቲክ ተጠቅልለው እንደሬሳ ሆነው አደባባይ ወጥተው ታይተዋል፡፡ የወደዱት እንዳይሆንላቸው እሰጋለሁ፡፡ ይገርማል፡፡ እጅግ የተመረዘ አስተሳሰብ በምን መድሀኒት ጤነኛ ይሆናል? ዛሬ ወያኔ ተሸኝቷል፡፡ ተረኛው ኦነግ በቦታው እያቅራራ አሁንም ችግር ቀጥሏል፡፡ የ50 ዓመቱ የኦነግ የዘረኝነት፣ የጥላቻና የበታችነት መርዝ በርካታ የሚባለውን ኦሮሞን አዋርዶታል፡፡ የታላላቅ ጀግኖች አባቶቹን ታሪክ ክዶ የወረዶች ሐሳብ ባርነት ሥር ወድቆና ከማንነቱ ወጥቶ አገር አልባ ባዶ ሆኗል፡፡  አዝናለሁ! ትንሽ ቆይቶ ግን ኦሮሞ እንደሕዝብ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ እሰጋለሁ፡፡ ይሄን የምለው በወያኔ ደጋፊ ትግሬዎች ያየሁትን እንደወረደ በኦነጋውያን ደጋፊዎች በማየቴ ነው፡፡ እምነት፣ ሕሊና፣ ስብዕና ሙሉ በሙሉ በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የከፋ የበታችነት ስሜት ደብዛቸው ከትውልድ እየጠፋ ነው፡፡ በኦሮሞነት ምክነያት ሰዎች እምነታቸውን እየተው የአባቶቻቸውን ታሪክ እያረከሱ ምንም ምልክት የሌለው በጥላቻና ዘረኝነት ተሞልተዋል፡፡ በስልጣን ላይ ያሉት በእርግጥም አስተዳደጋቸውም በወያኔ በመሆኑም አይናቸው እያየ ዛሬም እየተማሩ አደለም፡፡ አዝናለሁ!  ዛሬ ኦሮሚያ ውስጥ እየሆነ ያለውን ከኋላ ሆነው የሚያሴሩት በግልጽ እየታወቁ ይድበሰበሳል፡፡ መቼም ኦሮሞነት እየቆየ የማይደርስበት የለም ብርቱካን ሚደቅሳም በዚሁ ልክፍት ሳትጠለፍ አልቀረችም፡፡ ሰሞኑን የምንሰማቸው ነገሮች ጥሩ አደሉም፡፡ በኦሮሞነት ሰው ከእስር ማስፈታት ጀምራለች አሉ፡፡ በግፍ የታሰሩ እነ እስክንድር ነጋ አማራና ኦርቶዶክስ በመሆናቸው ዛሬም እስር ቤት ናቸው፡፡  ውጭ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ ተወሮ ዛሬ ከሱዳንና ግብጽ ጋር ያለው ጉዳይ እየተቆመረበት እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ በእኔ እይታ ዲና ሙፍቲ፣ ሌንጮ ባቲ ውጭ ጉዳዩን እየዘወሩት ነገሮች ጥሩ ይሆናሉ ተብሎ አይታመንም፡፡ ሌላው  አሁንም ሁሉም ሰው እንዲያስተውለው የምፈልገው፡፡ አሁን በወያኔ ላይ ድል አገኘሁ የሚለው መከላከያ የአገር ዳር ድንበር ሲደፈር ይሄው ዝም ብሎ እያየ ነው፡፡ አዎ ይገባኛል አገር እየተገፋ ያለው አሁንም በአማራ ክልል በኩል በመሆኑ ይመስላል፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

 

2 Comments

  1. ትክክለኛ ግንዛቤ ነው። እኔም የማምነው ወያኔ የተሸነፈው በ እግዚአብሔር ተዓምራዊ ሥራ እንጂ በ ኢትዮጵያ ሠራዊት እና የ አማራ ሃይሎች ነው ብዬ አላምንም። ይህንንም የምልበት ምክንያት እኔው እራሴ በ ቅድመ ወያኔ በ ትግሬዎች መረዳዳት የ አለቃዬን ወንጀል በማያሳምን መንገድ እኔ ላይ አላከው ከ አገር እንድወጣ ስላደረጉኝ ነው። እንኳን ያልበደላቸውን የ እነሱን ሰው አሳልፈው ሊሰጡ የ በደላቸውን እንኳን አሳልፈው እንደማይሰጡ ስላየሁ ነበር። እኔን በ አለቃዬ ወንጀል ያሳሰሩኝ ” ሰብና ናውጻአዮ” ማትም ሰዋችንን እናድን በ ማለት ከላይ እስከ ታች ተነቃንቀው ነበር። ህብረታቸው እጅግ በጣም ጠንካራ ነው። ስለዚህም ነው ውድቀታቸው ተአምር የሆነብኝ።

  2. ወንድሜ ስርፀ ደስታ እጅግ የምወህ እንደነብይም የምታናገራቸው ጠብ የማይሉ እየሆኑ ያሉ ነገር ግ ልቦና የናሳቸው ልበ ስውራን አይናቸው ይታወር ጆሮአቸው እልስማ ያለ አይናቸው አላይ ያለ የተወር መሪአችን ጠቅላይ ምንስትር አብይና በዙያቸው ያስለፉአቸው ምስሌ ደንገጡሮች ይህን ፈፅሞ በስው ጥበብ ሃይልና ችሎታ ያልሆነ በድንቁ ሃያል አምላክ እግዚአብሔር በኢትዮጵያ በተለይም በአማራና በኦርቶዶክስ ይሆን የነበረውን ዛሬ እንዴት እየስበረው እንዳለ አሁንም አልተማሩም! ማን እንደ ወያኔ በአንድ ብሄር በአንድ ቋንቋ በአንድ ቤተስብ በእንድ የግትራይ የበላይንት ፅንፈኝነት አለ የሚባለውን አደረጃጀት ገንዘብ መሳርያ የትቀረውንየህገሪቱ ክፍልና ብሄር በባሪያ አሳዳሪ ስርአት አይነት ጠፍረው እየገዙና እርስ ብእርስ እያፋጁ በመታበይ አይነኬ አይነት ስርእትና መንግስት ፈጥረው በግፍ ይገዙ እንደነበረ በእየንበት እይን ዛሬ ብፈጣሪ ፈቃድና ሃይል እጅግ ትዋርደው እይነኬዎቹ እጃቸው ላይ ካቴና ገብቶ ተጎሳቅለው ማየት ለትቀረነው ዛሬ በተራ ስልጣን ላይ ያለውየእብይ መንግስት ምን ያህል እየተማረበት ነው ለማለት አንችልም!ዛሬም ኦርቶዶክስና አማራ ላይ እጅግ አስቃቂ ግድያ እይተፈፀመ አልበቃ ብሎ የሱዳን ወራሪ በአማራ ክልል በኩል ድንብር ጥሶ ያንን የሚያህል ጥቃት ሲያደርስ ኢትዮጵያን እየመራው ያለው የአብይ መንግስት በኣሮምያ በኩል እስከአልመጣ በሚመስል መልኩ ዝምታ መርጦ አግሪቱ ድንብርን የሚከላከል ሃይልና መንግስት እንደሌላት አይነት ሆኖ ስናይ ስንስማ ያሳዝናል !ይህ በማንም አገር መንግስት ፈፅሞ ታይቶ ተስምቶ የማያውቅ ነው!አብይ እራሱን በኦነጎች አስከቦ የድነዘ አይኖቹ ይታወሩ ጆሮው የደንቆረ አእምሮው የተስለብ ሆኖል!
    ወንድሜ አንተ ግን እግዚአብሔር የገለጠልህን ብርሃንህን ከመህለፅ አትቆጠብ!ግዜው ቅርብ ነው ሁሉም የልኩን የብድራቱን የሚከፍል አምላክ ሁሉንም ያያል ፈጥሮናልና አይተነውም እስከዛው ዝም እትበል!ብርታልኝ የኔ ኩራት የኔ ጀግና!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.