በኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን ይዞ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 የደረሰበት አልታወቀም

ErSSpHTXAAAEaMhበኢንዶኔዥያ 50 ተጓዦችን አሳፍሮ ሲበር የነበረው ንብረትነቱ የስሪዊጃያ አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የደረሰበት አልታወቀም፡፡

አውሮፕላኑ ከኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ነው መሰወሩ የተነገረው፡፡

መዳረሻውንም በሀገሪቱ ምዕራብ ካሊማንታን አውራጃ ወደ ፖንቲያክ ሲጓዝ እንደነበር ነው ባለስልጣናቱ የገለጹት፡፡

የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር የነፍስ አድን ጥረት እና አሰሳ እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡

ስሪዊጃያ አየር መንገድ የሀገር ውስጥ በረራዎችን የሚያደርግ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃዎችን በመስብሰብ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

ይህ አሁን የደረሰበት ያልታወቀው አውሮፕላን ከዚህ ቀደም ሁለት ከባድ አደጋዎችን ካስተናገደው ከ737 ማክስ ጋር ይለያያሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.