የጥፋት ስትራቴጂስቱ እና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሐት ነጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

137515624 3825888390837242 1043531993075993589 o

የጥፋት ስትራቴጂስቱ እና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሐት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ገለጸ።

በአገራችን ላለፉት 27 ዓመታት የማተራመስ ስትራቴጂ የነደፈ ያስተባበረ እና ያደራጀ በመጨረሻም ጦርነት እንዲቀሰቀስ በማድረግ በሀገራችን ሠራዊት ላይ እጅግ ዘግናኝ ጦርነት በመክፈት ሠራዊቱን ያስጨፈጨፈው የጁንታው ቁንጮ፣ ስብሐት ነጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፣ የጁንታው ቁንጮ አመራር ስብሐት ነጋ ከተደበቀበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል።

136829005 3575240855929096 191730528276607798 nየጁንታውን ቁንጮ ስብሐት፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀውት እንደነበር ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ ገልጸው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻ እና አሰሳ፣ ከተደበቀበት በማውጣት በቁጥጥር ስር አውለውታል።

በተጨማሪም ከመከላከያ የከዱ ሌሎች ከሀዲ የጁንታው ቡድን አመራሮች ከጁንታው መሪ ስብሐት ነጋ ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመልክተዋል።

እነዚሁ ከመከላከያ የከዱ የጁንታው ቡድን አመራሮች የጁንታውን ታጣቂ ኃይል በማዋጋት እና በማሠልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ሲሠሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ በመጨረሻም የጁንታውን አመራር ዙሪያ ጥበቃ ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሠራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሓላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።

እነዚህኑ የጁንታው አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ኃይልም መደምሰሱን ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት በቁጥጥር ስር የዋሉት፣
1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት ስብሐት ነጋ
2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሐት ነጋ ባለቤት እና ቀደም ሲል በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሐኪም የነበረች በኋላም በጡረታ የተገለለች
3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ-ከመከላከያ የከዳ
4. ኮሎኔል የማነ ካህሣይ-ከመከላከያ የከዳ
5. አስገደ ገ/ክርስቶስ-ከመሀል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለ እና ለጊዜው ሓላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣
6. ኮማንደር በርሄ ግርማ-የክልሉ ልዩ ኃይል ሎጂስቲክስ ሓላፊ የነበረ
7. አምደማርያም ተሰማ ተወልደ-የክልሉ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ሓላፊ የነበረ
8. የሜጀር ጀነራል ኃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረች እና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረችው ወ/ሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ሕይወቷ ማለፉን ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ገልጸዋል።

SOURCE: Ethiopian Broadcasting Cooperation

137521784 2879266852304773 1324662934611751442 n

የሜጀር ጄነራል ሀየሎም አርዕያ የትግል ባለቤት የነበረችው እና አሜሪካን ሀገር ስትኖር ቆይታ በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ የጁንታው ኃይልን የተቀላቀለችው ተጋዳሊት አልጋነሽ መለስ ገደል ውስጥ ገብታ መሞቷን መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ!!
አድዋ ተወልዳ ያደገችው እና ዳንኤል እና ብርሀነ መስቀል የተባሉ ሁለት ልጆችን ከባለቤቷ ከሀየሎም የወለደችው ተጋዳሊት አልጋነሽ ከመከላከያ አሰሳ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል ውስጥ ገብታ ህይወቷ እንዳለፈ ታውቋል!!
136492326 2879266882304770 1157475885066454977 n
ሽጉጥ ታጥቆ ወደ ገደል ፈርጥጦ ከመሞት ይሰውራችሁ!
በቃ በህወኃት ቤት እንኮ እራስን ማጥፋት እራስን መከላከል ምናምን የሚባል የጀግንነት ታሪክ አይሞከሩም”

3 Comments

  1. I am pretty sure Abyi will release them, his love for TPLF is deep in his bone. Alganesh Melse’s case is really funny, she came all the way from US to commit crime and she end up in side cliff, I wish if computer device was installed on her to study the situation she was in when she dive to the cliff. Before the corpuses was rescued the hyenas may split her criminal body into pieces. She came all the way to kill Ethiopians sadly she killed herself. Sad for their children father was a killer and mother was a killer.

  2. እጅግ የሚገርሙ ጉዶች ባሏን ሀየሎምን ካስገደሉ ሽፍቶች ጋር በሀገር ክህደት ተሰማርታ ሞተች :: ማንም በህይወት ቢቆይ መልካም ነው:: ስብሀት ነጋ አባቱ የጣልያን ባንዳ የሞተበት የተምቤን ዋሻ ብዙ ህዝብ ካስገደለ በሗላ እሱ ፈሪ ስለሆነ ተማረከ:: ይህ የእግዚአብሄር ፍርድ ካልሆነ ምን ይባላል:: ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ ወዶ አይደለም በዘራችሁ አይድረስ ብሎ ህዝብን የመረቀው

  3. ወደ ቤተክርስቲያን ለቁርባን በመሄጃ ጊዜ ዋሻ ለዋሻ መጨረሻው ይሄው ነው፡፡ የስንቱ ደም እና ሰቆቆ ገና ያክለፈልፋል፡፡ ግማሹም ገደል ይገባል እርስ በእርስም ይበላላል፡፡
    እንደውም ሞተው ከሚገላገሉ እንደዚህ በሕይወት እየተያዙ ስለ መከራና ስቃይ በእስር ቤት ቢያዩት (ምንም እንኳን እነሱ ሲፈፅሙት እንደነበረው የማረሚያ ቤት በደል አሁን ሊፈፀም ባይችልም) እና ስለሀጢያታቸው ቢናዘዙ ጥሩ ነበር፡፡ ለነገሩ ምን ህልና አላቸው፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.