የፕሬዚዳንት ትራምፕ ድርጊት በጣም ያሳፍራል – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

44Twitter and Facebook locked President Trump’s account for the first time on Wednesday night, with both platforms saying he violated their policies, and Twitter going a step further to warn him that further violations of their rules would result in a “permanent suspension” of his account.

Twitter’s move came after the social media giant removed a video the president tweeted, in which he told protesters who had stormed the Capitol to “go home, ” while maintaining that the 2020 election had been “stolen.”

TRUMP SAYS ELECTION WAS ‘STOLEN’ AND ‘THESE ARE THE THINGS AND EVENTS THAT HAPPEN,’ TELLS PEOPLE TO ‘GO HOME’

Fox news

ከሥልጣናቸው መሰናበታቸው የማይቀረው የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ፣ ፈፅሞ በማይገመት ና ለአሜሪካ ዴሞክራሲ በማይመጥን መንገድ በቲዊተር አካውንታቸው ደጋፊዎቻቸውን ምርጫው ተጭበርብሯል ወይም ተዘርርፏል በማለት ለአመፅ እያነሳሱ በመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የፌሥ በክና የቲዊተር አካውንታቸው ተዘግቷል።

እነዚህ ግዙፍ የማህበራዊ ድረ ገፅ  ተቋማት የወሰዱት እርምጃ ተገቢ ነው። ሁላችሁም እንደምታውቁት በአፍሪካ ውሥጥ የሚደረግ ምርጫ ነው በእንከን የተሞላ እና ማጭበርበር የሚበዛበት።ከውጤቱም በኋላ ፣ውጤቱን በመቃወም አመፅ የሚቀሰቀስበት።በአውሮፖ ፣ በኢሲያ … እንዲህ አይነቱ ምርጫን ተከትሎ  የሚከሰት አተካራና ብጥብጥ አዘውትሮ አይከሰትም።

በታላቋ የዴሞክራሲ አገር በአሜሪካ እድሜ ለትራምፕ፣ ዛሬ የምናሥተውለው በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት እንደሚከሰተው ዓይነት የምርጫ ውዝግብ  ሁከት ማሥከተሉ ደግሞ የባሰ አሣፋሪ አድርጎታል ።(ለእኔ ይህ  ሁኔታ ልክ እነደሆሊውድ ፊልም ነው የሆነብኝ።ማመን ሥላቃተኝ።) ይሄን አሳፋሪ እና  ለታላቋ አገር የማይመጥን የምርጫ ውዝግብ ደግሞ ሆን ብለው እያባባሱት ያሉት ፕሬዝዳንቱ ናቸው።

ፕሬዝደንት ትራምፕ ከምርጫው በፊት መሸነፋቸውን እንደማይቀበሉ አሣውቀው ነበር።እናም ዛሬም በዚሁ አቋማቸው በመግፋት፣ በአሜሪካ ህግ አግባብ እንደመዳኘት በማህበራዊ ድረ ገፅ እየፎከሩ ፣ የዴሞክራሲ ተምሳሌት የሆነች ታላቅ አገር መልካም ሥም በማጠልሸት ላይ ይገኛሉ።

የታላቋን አገር መልካም ሥም ብቻ ሳይሆን ሰላሟንም በማደፍረሥ  ፣ለአገሪቷ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እየሆኑባት ነው።ይህቺ አገር ኮቪድ 19 የሚያደርሥባት ውድመት ይበቃታል።ተጨማሪ ውድመትን በሥልጣን ሥግብግብነት ሣብያ ለማሥከተል  መጣር ከአንድ የታላቅ አገር መሪ ፣ አይጠበቅም ። ይህ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድርጊት ዜጎቿን ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ተምሳሌት የሚያደርጓትንም ያሳፈረ ነው።

1 Comment

  1. የአሜሪካን ኢምፐርያሊዝም በዲሞክረሲ ስም፣ ኩባን፣ ቬትናምን፣ ቺሌን፣ አፍጋኒስታንን፣ ዒራቕን፣ ሊብያን፣ ሶርያንና ሌሎችንም ወወዘተ ሃገራትን ከደበደቡ በኋላ አሁን ደግሞ በገዛ ራሳቸው ላይ ጀመሩ እንዴ….! የተሻለ ቀን ብቻ ያምጣላቸው…!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.