ይድረስ ለትውልደ ኢትዮጵያ ምሁራንና አገር ወዳዶች በሙሉ በያላችሁበት (ከአባዊርቱ)

a18896ba ethiopiapminsa 768x513 1
ይህ ጥሪ አላጋጮችን፣ የለየላችሁ ልሳናችንን የምታወሩ ግን  በገቢር የኢትዮጵያ ጠላቶቻችን የሆናችሁትን  አይመለከትምና እዛው ፅልመት ስለተለያችሁ  እዝን ቤት አላዝኑ። አልሰሙኝም እንጅ እኔም በዚሁ ቤት በኩል ተው ብዬ ካንዴም ሁለቴ ተማልጄአቸውም  ነበር። እንደ  ጥጋብ አስከፊ በሽታ የለም ወገኖች።
የተቀራችሁ፣ ኢትዮጵያን ያላችሁ ፣ ባብላጫው ዛሬም “ከድል” በሁዋላ እንደ ትላንት በዝምታ ድባብ ተውጣችሁ አገራችሁን ለክፉዎች ለማስረከብ፣ (በቸልተኝነት መሆን አለበት) ” የምትተባበሩትን በሙሉ በፅሞና ተከታተሉኝ።
 ለመንደርደርያነት ከትግራዋይ ኢትዮጵያውያን ልነሳ እስቲ
ውድ ፣ ሀቀኞቹ ጥንት የማውቃችሁ የባለማተቦቹ ግዛት የትግራይ ልጆች ሆይ (ባንዳዎች ጥጋችሁን ያዙ – አይመለከታችሁምና)!
የናንተው ዝምታ በተለይ በዛሬው ወቅት ሊገባኝ አልቻለም በጭራሽ! ባንድ በኩል እንዴት ትግራይን በቁም ቢቀብሩ ነው እንዲህ ከዳያስፖራ አቅም እንኴ ነፃው አገር እየኖሩ በዝምታ የተሸበቡት አስብሎኛል። በትግርኛ የብእር ስም እንኴ የወያኔን ውግዘት ማንን ገደለ? አንድ አረጋዊ በርሄ ፣ አንድ ደግሞ ባለውለታ የሆኑ ስማቸው ጠፋኝ Australia የሚኖሩ ሰውዬ ብቻ እንዴት ሊሆኑ ይችላሉ? እንዴት ተፃራሪው ሁሉ ስመ “አማራና ዖሮሞ” ብቻ ይሆናል ለእይታ እንኩዋ ? አገርቤት ያላችሁ ምናልባት ከባድ የአይምሮ መረበሽም ውስጥ ብትሆኑ አይፈርድም ለ ሃምሳ አመታት ቁምስቅላችሁን ለብቻችሁ ተዘግቶባችሁ ታሽታችሁዋልና – ውጭ ባላችሁት ግን እጅግ አፍሬአለሁ። ሆኖም አሁን ቁጥራችን ብዙ ነውና አይዟችሁ አትፍሩ። መቼስ ወያኔ እንዴት አድርጎ መከላከያውን ከጀርባ እንደወጋ ለጆሮ እስኪቀፍ ሳትሰሙ አልቀራችሁም። የልጅነት መልካቸውን እናንተው መሀል የጨረሱትን ልጆቻችንን። አልተረበሻችሁም? ብዙ ጠብቄ ነበር በድል ማግስት ከናንተ በተለይም ከዳያስፖራው ተወላጆች። በምንም ስሌት መቼስ ሁላችሁም የነዚህ ከይሲዎች አቀንቃኞች ልትሆኑ አትችሉም። ይልቅ ጥቅሙ ለናንተም ነውና በጊዜ አንድ ላይ ላገራችን እንሰለፍ።
ይቺን አጭር መልእክት እንድለጥፍ ያደረገኝ ፣ መምህርት መስከረም አበራ ስለሻለቃ ዳዊት ምስክርነት ላይ በሰጡት  አስተያየትና የኔውን መልስ ተከትሎ አንዲት fiqirte የተባሉ ወገን አይምሮ የሚኮረኩር ጥያቄዎች  ዶር አቢይን  አስመልክቶ ስለጠየቁኝ፣ ይህንኑ አጋጣሚ  በመንተራስ ምናልባት ሁላችንም እንማማርበት ይሆናል በትንሹም ከሚል  የአቅሜን ወገናዊ ምልከታ ነው። ደጋግሜ እንዳልኩት አገሬ ኢትዮጵያ  እንዳብዛኛው ዳያስፖራ ርቄአትም ኖሬ ከውስጤ ስለማትርቅ ሆኖ ነው እንጅ የግለሰቦችን ጥያቄ በማንሳት መልስ ለመስጠት አልጃጃልም ነበር።
1) ዶር አቢይ ለክቡሩ የሰዉ ህይወት መጥፋት የሚሰጡት ቦታ ከአንድ የተከሉት ችግኛቸው መድረቅ ያነሰ ነው  ይላሉ fikirte።
፩) ለዚህ አጭር መልሴ ባራክ ዖባማ ባንድ ወቅት የሂለሪ ትሁን መኬን የንዲህ አይነት ንዝነዛ ሲበዛባቸው “ማስቲካ እያኘኩም መሮጥ ይቻላል” ይሆናል ነው:: አለበለዛማ መሪነታቸው ቀርቶ የ morgue  ዘበኛ ሊሆኑብን ነው። ነስንሰው ሀዘን ከመቀመጥ ችግኝ እየተከሉም አገሪቱን መታደግ ይቻላልና ነው ቅንነቱ ካለ. የአቢይ ቅንነት ደግሞ በጉልህ ይታያል፣  ቢያንስ በኔ እይታ።
 2) @fikirte  “ባለሙያን ማስጠጋት ፈፅሞ አይወዱም በተለይም ለኢትዮጵየዊነቱና ኢ/ያዋጋ የሚሰጥን ሁሉሸሽተው ስጋ ጥራ ቢሉት—–አይነትexpired( ለአገላለፄ ይቅርታ)የሆኑና እዚህ ያደረሱንን ክፉ እሳቤ የተጣባቸው ሰወች በዙሪያው የከበበው በእርስዎና አኔ ምርጫ አይደለምና”  ብለው ብዙ አብራርተዋል።
 ፪)  ይህን እኔ አባዊርቱ  ለመቀበል በጣም  የምቸገረውን እኔም እስከነውርዎ እዚሁ ለጥፌሎታለሁ። አገላለፆም የወረደ ነው -ይቅርታ የለውም።  የሰውዬውን ለትምህርት ያላቸውን ጥማት፣ ለሳይንስ ያላቸውን አድንቆት፣ ለስልጣን ሳይሆን ለስልጣኔ ያላቸውን ጥማት ሳስተውል አስደማሚ ነው።  ካየሁዋቸው የወጣትነታቸው ቪዲዮና በየዩቱቡ ካየሁት ሁሉ እንደውም ሰውዬውን የባሰ እንዳደንቅ ያደረገኝ ይህ ለእወቀትና ስልጣኔ ቀናኢነታቸው ነው። ኢትዮጵያዊው ወገን ያልተረዳው ወይም እንዲረዳው ያልፈለገው ነገር አለ እኔን እስከ ገባኝ። አገሪቱ በአፍ መፍቻ ከተከለለች ከዚያች ክፉ ግንቦት  ሰማንያአንድ ጀምሮ የትምህርት ይሁን ክህሎት ይዞታው በሙሉ በጎጥ ነው። ሰውዬው የፈለቁት ከ ኦፒዲ ነው፣ የሚመሩት ብልፅግና የየጎሳዎቹ ጥምረት ነው። እያንዳንዱ የብልፅግና ሰው ምናልባት ከአቶ ሙስጠፌ በቀር የአንድ ሰንበቴ ልጆች አይደሉም ወይ? የስራስ expectation ድልድል ላይ “የለም ከናንተ ውስጥ ሳይሆን ፣ ወይ ከዳያስፖራ፣ ወይ ከተቃራኒ  ፓርቲ” ልሹም ቢሉ በአንዲት ለሊት ያጠፉዋቸዋል ይመስለኛል። ለምን? አልተለመደማ። ስለሆነ ለምን ለመፍረድ ትቅበዘበዛላችሁ? ለዚያውም በትንሹም እኮ ከውጭም አማካሪዎች አሉ ብዬ እገምታለሁ፣ ግን እንደ አማካሪው ብዛት ስንቱንስ ቀጥረው ሊዘልቁ ነው? የኔ ምኞት የነበረው ገና ሲጀምሩ በነ አል ማርያም የሚመራ የምሁራን ቲንክታንክ ቢመሰረትና አየር ላይ ነፃ ካውንስሊንግ አይነት ቢኖር ነበር። ሁሉ ከየራሱ አጀንዳ አልታረቀምና ለዚህ የታደልን አይመስለኝም። ጥቂት ሰዎች አሉ  አሁን ድረስ ምሁራዊ ምክራቸውን ለአየር የሚያበቁ። ስም ጥቅስ ብትሉ ዶር አክሎግ ቢራራ የሚባሉ አሉ። እንደ ብዛት ግን አልሆንብኝ ብሎ እንጅ ። በትግሉ ዘመን የሳምንቱ እንግዳ እያለ ያ ሲሳይ አጌና ድንቅ ሰዎችን ያወያይ ነበር። መቼስ የኢሳት ውለታ ዛሬ ድረስ አይረሳም።  የሚገርመኝ እንዴት ይረሳል ምን አይነት ደባ በአገሪቱ ላይ እነዛ ከይሲዎች ሲፈፅሙ እንደኖሩ? ሲስተሙ እኮ እንዳለ ነው ያለውና ገና ብዙ ይቀረናል። በዚህ ጉዳይ ሳጠቃልል እስካሁን አቢይን ይውረድ ወይም ለቦታው አይመጥንም ለምትሉ ወገኖች እከሌ ይሻላል በሉንና ለፈጣሪና ህሊና ስንል እያስተያየን እንተች። ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ የምለምናችሁ ይህንን ነው። እንዴት ማፍረስ ቀላል እንደሆነና መገንባት ኤቨረስትን የመውጣት በላይ አድካሚ መሆኑ ይጠፋችሁዋል?
 3)  እንዲህም አሉ fikirte ። ይህን ሳልገንዘው እንዳለ ደግሜዋለሁ።
  ” በመሰረቱ አብይጠ/ሚ የሆኑባት አገር በኔ እምነት ቢያንስ ብሄርን/እምነትን ወይምሌላ የመለያ መስፈርትን ያደረጉ የዘር ማጥፋቶች፣በደል አና ኢፍትሀዊነት ታሪክ ሊሆኑ ይገባ ነበር (ከresumeአቸው እንደተገነዘብሁ የphd መመረቂያ ጥናታቸው intercommunal/interfaith conflict resolution ላይ ነው። ይህም ማለት ከአብዛኞቻችን በተሻለ እንዲህ ያሉ ችግሮችን አስቀድመው anticipate/predict በማድረግ ጦራቸውን ቦታ አሲዞ ምስኪን ድሆችንና ሰለባዎችን መታደግም ሆነ አስቀድሞ ማህበረሰብን ራሱን እንዲጠብቅ ማንቃት ነበረባቸው። እሳቸውና ሹመኞቻቸውግን 100%በሚባል ሁኔታ የሬሳ ስተቲሰቲክስ ለመዘገብ ብቻ ነው ብቃታቸው እሱንም ወግና መቅኔ ባጣ አእምሮ ላለው ደግሞ እጅግ በሚቆጠቁጥ ሁኔታ(እርግጥ ልክ ነሽ የፈጸመው ጄኖሳይድ ነው ነገርግን ጄኖሳይድ ተፈፀመ ብለን ካልን ጄኖሳይድ የተፈፀመበት ህዝብ አለ፣ ጄኖሳይድም ፈፃሚ ህዝብም አለ መለታችን ስለሆነ ይህ ደግሞ መባል የለበትም ህዝባችን አቃፊ ስለሆነ ጄኖሳይድ ቢፈጸምም ማለት ግን የለብንም ብለው በናሁ ቲቪ ቀርበው ለሳምንታት እንዲያመኝም ብቻየን እንድስቅም እንደረጉኝ የኦሮምያ ሹመኛ ማለት ነው)።ስለዚህ ወይ ሙያቸውን ትኩረት ሰጥተው ተግባራዊ ያላደረጉትና ይህሁሉ ዜጋ የተጨረሰው አንድም የአማራና ኦሮሞ ያልሆነን ነፍስ ከሚንሰፈሰፉላቸው ችግኞች ዝቅአርገው በማየታቸው ነው ወይም ከጭፍጨፋው የሚያተርፉት ትርፍ አለ ወይምደግሞ ይህን ከበድ ያለ ሙያና አላማውን ፈጽሞ አያውቁትም።የኔ እምነት ሁሉም ናቸዉ ምክንያቱም የዚህ ክቡር ሙያ ባለቤት ለዚያውም በተጨማሪ ኮሎኔል የሆነ መሪ ያለን “ህዝቦች” በየቀኑ ሰው ተበልቶ እየተበላ የመቀሌ ጦርነት ባለቀ ማግስትየምንጠብቅ የነበረ የሂዊና መሰል ስምአይጠሩዎችን በአሸባሪነት የፈርጃሉ “ህገ መንግስታቸውን” ይቀይራሉ ወዘተ ሲሆን (እኔ እንጅል ጠብቄ ነበር)እሳቸው እቴ “ለምን ኬክ አይበሉም”እንዳለችው ልእልት ቀጥ ብለው ጎርጎራ፣ ኮይሻ ምናምን ሲሉ በቲቪ ታዩ እኔም ትእግስቴ አለቀና በተለያየ ጊዜ ለአጭር ጊዜ ተደምሬም ደግፌም በነበረ ጊዜ በልጆቼ ውትወታ የተገዙና የቤታችንን ፍሪጅ ላይ የፍራፍሬና አትክልት ፖስተሮች ጨፍልቀውና አፈናቅለው የተለጠፉ የ”ሙሴውና ቲማቸው” ፎቶዎችን አንስቼ ፍሪጄን ከመሸወድ አንፅቻለሁ ሌሎቻችሁስ?
በቃኝ፡ በቸር እንቆይ”
የተከበሩ fikirte ሆይ! አዎ ይብቃዎ!
ይህ የመጨረሻው አስተያየትዎ ባብላጫው ሲጀመርም ሳያጤኑ ተደምረው ወዲያው የተቀነሱትን እርስዎን ባላውቆትም  በቲቪ የማውቃቸው ክቡር ለማ መገርሳም አድርገውታልና ምን ይደንቃል ብለው ነው?። እኔን እንደገባኝ አቢይም የመከሩን መፅሀፉን በቅጡ ሳታነቡና ምስጢሩ ሳይገባችሁ አትደመሩብኝ ብለዋል እኮ ማ ስማቸው እንጅ ። እኔ በበኩሌ የኢትዮጵያ አምላክ ውስብስብ ማንነታችንን አይቶ ከላይ  በጠቀሱት ሙያ የተካነ መሪ አይቶ ስጥቶን ነበር – አያያዙን አጥተንበት ሰውዬው ብቻቸውን ተንገዋለው ሊቀሩብን እየመሰለ ነው እንጅ ። ይልቅስ አብረዋቸው ከተሰለፉት  ኢትዮጵያዊነቱ ሰረስራቸው ውስጥ ገብቶ እንደ አቢይ የማይነዝራቸው ባለመብዛታቸውና የሰውዬውን መልካም ስራ (on balance) የተንሸዋረረ ማድረጋቸው እንጅ ብዙ አሉ። ምናልባት የነሱና የአቢይ ኢትዮጵያ እይታ ሳይቀናጅ ቀርቶም ብዙ ስራ ይጠይቅ ይሆናል። ይህ ደግሞ ሊገርመን አይገባም ለአርባ አመታት ኢትዮጵያዊነትን በመንግስት እቅድ ከትቤት እስከ ቤተ እምነት ከህዝቡ አይምሮ ለመለየት በተዘየደው ፕላን። መቼስ አይን አለን እናያለን፣ ጆሮ አለን እንሰማለን – እድሜም መስታወት ነው ከተሞክሮ ጋር።  እነ ሱማሌ እኮ እንደ ጨርቅ የተበጣጠሱት አስር አመታት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው። እንደውም መሰረታችን እጅግ የጠነከረ መሆኑ እንጅ እንደተሰራብን ደባ ተጠፋፍተን ባለቅን ነበር።
ሌላው የጥንት ግሩም አባባል አለ ቢፈቀድልኝ። የባልን መልካምነት የምታጎላ በስውር የምትገድፈዋ ሚስት ናት። በሁሉም ባህል አለ ይህ አባባል ለነገሩ። በኛው አገር የስውሩ ድጋፍ ቀርቶ በአደባባይ ት/ቤት የሚያሰሩትን ቀዳማዊ እመቤት ትምህርት የተጠማ ወጣት የበዛበት አገር ሆኖ እንደምን ይህን ” ከባድ ወንጀል” ፈፀሙ ተብሎ ስማቸውን ማጠልሸት ተጀምሯል ። ሊያውም ባብላጫው ጥሪቱ ከባለቤታቸው መደመር ሽያጭ በተገኝ ገንዘብ – ከዚህ በላይስ ዝቅጠት ምን ይኖር ይሆን? ምን ለማለት ፈልጌ ነው፣ ቅንነቱ ውስጣችን ቢኖር ኢትዮጵያዊነት በመመንመኑና አቢይ ብዙ ረዳት በጣቢያቸው አለመኖር ባሳተሳሰረን ነበር። ታሪካችንን እንደገና ሀ ብለን በላጲስ ያጠፉብንን ለመመለስ እየዳከርን እኮ ነው ኢትዮጵያውያን። ያውም ህዝባችን እየሞተ።
ወገኖች!
አቃቂር ማውጣትና የገፈቱ ቀማሽ ሆኖ ረመጡ ውስጥ ተነክሮ ይቺን አስቸጋሪ አገር መምራት ለየቅል ናቸው። ኸረ በፈጠረን አንዱ ሌላው ጫማ እየገባ ከሌላው ፖይንት ኦፍ ሪፈረንስ ይመልከት። ብዙ ተዛብቶብናል። 40 አመታት የአገራችን የውጭ ፖሊሲ ምን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ውስጥ እኮ ነው ያለነው።  ጠላቶቻችን ብዙ ሲያቦኩና ሲጋግሩልን መኖራቸው እነሆ በአራቱ ማእዘን ጠላት እንዲህ በዝቶብን እኛ “በቀበሌ ቤት ደረጃ” እንፋለጣለን። እንዴት ነው ጉዳዩ ወገኖች? ምንድነው የጠበቃችሁ በወያኔ ስልስት  ይሁን አርባና ሰማንያ? አልጋባልጋ ትራንስፎርሜሺን ነበር? ምን ትቤት ነበርና? ምንስ ምሁራን አሉንና ነው ሆን ብለው አገራችንን በቁም ገድለው በኮሚኒስት አይሉት የፅልመት ፖሊሲ ልጆቻችንን ናላቸውን በጫትና ሺሻ ቀብረው ምን ተአምር ጠበቃችሁ ወገኖች? ደግሞስ ከቀድሞ ኦዲፒ ይሁን አዴፓ መቼስ ይሁን ብለን ፣ ከውስጣቸው እነ ዶር አቢይና ቲም ነጥረው ወጡልን ብለን እንጅ ወደ ሁዋላ ከሄድን ያው ሁሉም የፅልመት አዝመራ ውጤት አይደሉም ወይ? ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?
ህገመንገስቱ!
ይህ ህገመንግስቱ አቢይ አለወጠውም፣ ወይም ከጦርነቱ በሁዋላ አቢይ እንዲቀይር የጠበቃችሁ እውነትም ጅሎች ናችሁ ከይቅርታ ጋር። ለምን? ፩) ሂደት አለው ፪) የድሮው ስርአት ጦርነቱ ስላበቃ አልተለወጠም ፫) አቢይ  ቢፈልጉ እንኴ አይችሉትም- በዬትኛው ማንዴት። የእቁብ ቤት መተዳደርያ ህግ እንኴ ብዙ ፕሮሰስ አለው እንኴን የአንድ አገር ቀርቶ። በዚህ ጉዳይ ብዙ ብያለሁና ከዚህ ቀደም ይቅርብኝ።
ፊደል የቆጠረው ህዝብ ችግርና የኢትዮጵያ መፃኢ እድል!
ስለዚህ ጉዳይ ሳስብ እጅግ አዝናለሁ። ባብላጫው ገና ከራሳችን አልታረቅንም። ይህ ደግሞ ምን አገራችንን ብንወድ ከአገራችን ኢንተረስት እንዳንታረቅ አድርጎናል ባይ ነኝ። ሆን ብዬ ስመረምረው ምን እንደተፈለገ እንኴ ሊገባኝ አልቻለም። ባለፈው አንድ በለጠፍኩት የአገር አድን ጥሪ ክፍል ፭ ምርጫው ይቆየን የኢትዮጵያ አዋላጅ ካውንስል አቢይ ከሰራዊቱ በመቀናጀት አምጠው ይውለዱ ስል ለኔ አባዊርቱ የስልጣን እርከን መርገጫ ወይም ለአክስቴ ልጅ ፓርቲ አሸናፊነት አይደለም – አገር እንደ አገር ረግታ ነገ ለምንገነባው ዴሞክራሲ አገሪቱን በህይወት ለማቆየት ታስቦ እንጅ ። አሁን ሳስበው ብዙዎቹ ምርጫ ይተላለፍ የሚሉት ዛሬ ምርጫው ቢደረግ አቢይ እንደሚያሸንፉ ስላወቁት ጊዜ መግደያ መሆኑ ነው። ያሳዝናል። ለምን ይቺ ምስኪን አገር እንደማታሳዝን አይገባኝም። ለአንዲት አመት እንኴ የራስን ኢንተረስት ከአገር በታች ማድረግ አይቻልም?  ሌላው የታዘብኩት አሁንም ብዙ የኢጎ ጉዳይ አለ። የእናት አገር ጉዳይና ኢጎ አብረው አይሄዱምና አደራ አስቡበት ምሁራን። አንድ ሳልጠቅሳቸው የማላልፋቸው ሰውዬ አሉ ደጋግመው ” እኔ ብጠየቅ ኖሮ፣ ማ ጠየቀኝ እንጅ” ይህን፣ ያን የቀመርኩት እኔ ነኝ ሰሚ አጣሁ እንጅ ፣ የሚሉ ሰውዬ ስማቸውን ባልጠራም ይታወቃሉና አደራ የሚመለከተው አካል አቅርቦ ያዋያቸው። ምሁራንን በደንብ ካልያዝናቸው ጉዳቱ ለአገር ነውና።
ሌላው ሳልጠቅስ የማላልፈው ይህ ደጋግሞ የሚነሳ የአቢይ በአማራው ላይ አለ ተብሎ የሚታማው ስውር ደባ ነው። ብዙዎቻችሁ ይህን የምትሉ ቡድኖች ሁኑ ግለሰቦች እንደታዘብኩት አቢይን ስውር የዖነግ ተልእኮ ጉዳይ አስፈፃሚ አድርጋችሁ ነው። የሰው ልጅ መቼስ የሚለካው በሚሰራውና በምግባሩ ነው። ይህ ከሆነ ክቡር አቢይ እስቲ ምን የዖነግን አጀንዳ ሲያስፈፅም አይታችሁዋል? በትእግስቱ ከሆነ ዋንኞቹን ፅልመቶችም ፪ አመት ታግሶ እነሱው ባነደዱት እሳት መልሶ ለበለባቸው እንጅ ሁሉንም ነው በትእግስት ፋታ ሰጥቶ ያስተናገዳቸው። ይህንንም ለማለት ያው እሱ በመሆኑ ነው ለመተንፈስ የተበቃው። የሚገርም ፍረጃ ነው። የመተከል ይሁን የማይካድራ እልቂት የአቢይ የስራ ውጤት ነው ለማለት ነው ወይስ ምን ታስቦ እንደሆነ ከቶ ሊገባኝ ያልቻለ ጉዳይ ነው። ለነገሩ ጤነኛ አይምሮ ያለው ወገን ይህን አይልም እንዳልል ወዳጄ (በዘመኑ አጠራር አማራ )የሆነ በሙሉ እምነት እንዲህ ስላለኝና ልቤ ስለተሰበረም ነው። እውነት አቢይ አህመድ እንዲህ አይነት ደባ ቢያስብ አብሮት ደመቀ መኮንን ይሁን ዳንኤል ክብረት ማእድ ይቀመጣሉ? ወይስ እነዚህ ሰዎች ስለተገፋውና ደሀው አማራ ያውም ዛሬ የፅልመት መንጋ ዞር ብሎላቸው አስችሎአቸው ዝም ብለው አብረው ይመሳጠራሉ? ኢትዮጵያዊነት እንኴ ቢቀር እንደአማራነታቸው ማለቴ ነው። እጅግ ያሳዝናል። ስንት የሚያነጋግር፣ የሚያወያይና የሚያከራክር ጉዳይ እያለ ጠላት በአራት ማዘን ከቦን እንቡዋጨቃለን።
የአገርቤት ምሁራን ሆናችሁ ዳያስፖራ!
ወቅቱ ጥሬ ስጋ የምንበላበት፣ ዳንኪራ የምናዘወትርበት እንዳይደለ ልቦናችሁ ያውቀዋል። ብዙ የምታዘበው ስላለ ነው – በተለይ አቤል የሚሉትን ሰራዊቱ ያሳደገውንና ያተረፈውን ህፃን ልጅ ሰቆቃ ከሰማሁ በሁዋላ። አገራችን ብዙ ትጠብቃለች ከኛ። ብዙዎችም እየረዳን ነው ፈጣሪ ይመስገነውና – ብዙ ግን ይቀረናል።  በቅርቡ የዳያስፖራ አቀናጆች እዚሁ ዘሀበሻ ቤት ያወጣችሁትን ማስታወቅያ ሁሌ አድርጉት። በአመት አንዴ አይበቃም። እንደብዛታችን ብዙ አንለግስም። 500 K dollar ለ መቶ ሺ ወገን 5 በነፍስ መሆኑም አይደል?  ይቻላል እየተስተዋለ ለማለት ነው እድሜን ከለላ በማድረግ በይቅርታ ግሳፄም ጭምር።
ፈጣሪ አገራችንን ከገባችበት ማጥ እንደቸርነቱ ያውጣልን። ያለቁትን ወገኖች ሁሉ ነፍስ ይማርልን።
ታህሣሥ 2013.

5 Comments

 1. አባ ዊርቱ፣
  አድናቂህ ነኝ። ሳትታክት ሃሳብህን ከ ማጋራት ችላ እንዳትል እማጸንሃላሁ። ህዝባችን አስታዋሽና ህሊናውን የሚኮረኩረው ይፈልጋልና።
  እኔም በጣም የሚገርሙኝ አቢይ ይውረድ የሚሉ ሰዎች ናቸው። አቢይ ላይ ብዙ ቅሬታ ቢኖረኝም እሱን የሚተካ ሰው አለ ብዬ ግን አላምንም። ስለዚህ አቢይ ድክመቱን እያሻሻለ ለ ዘለአለም ይምራ። ኢትዮጵያ እንደ ቻይና በ አንድ ፓርቲ ብትመራ የሚሻል ይመስለኛል። ከ መቶ በላይ ፓርቲዎች አቋቁመው ፓርቲ እመራለሁ የሚሉ ሰዎች ጤነኞች አይመስሉኝም። እንደነዚህ አይነት ምሁራን ተብዬዎች በሚኖሩባት አገር ዲሞክራሲ ይሠራል ብዬ አላምንምና።
  ከ ሁሉ ነገር በፊት ጠ/ሚ አቢይ የ ጎሳ ግጭቶችን ማስቆም አለበት። ይህንንም ተግባር ለ ማስቆም ተጠቂዎችን እራሳቸውን እንዲከላከሉ ማስታጥቅ አለበት። የ ጥቃት መፍትሄው ይህ ብቻ ነው።
  በ ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የ ዜጎችን መብትና ፍትህ ማስከበር አለበት።
  እነዚህን ተግባሮች ከ አሟላ ሌሎች ነገሮች ጊዜው በፈቀደ ጊዜ ሊሟሉ ይችላሉ።

  ፈጣሪ ህዝባችንን በ ሰላም እና ፍቅር ተሳስበው እንዲኖሩ ያድርግልን።

 2. ወንድሜ አባዊርቱ መፃፅፍህን አነበብኩት በብሽቀት ሆነህ ይሁን የአብይን ለመደበቅ ብዙ መባዘንህ አሳዘንከኝ!በአንድ ወቅት እየሱስ ክርስቶስ ይከተሉት ለንበሩት የተናገረውን እንዳስታውስ አደረገኝ!’አይን አላችው አያዩም ጆሮ አላቸው አይሰሙም አእምሮ አላቸው አያስተውሉም” ነበር ያለው ይህ አባባል አሁንም ይስተዋላል::በቁላሉ በዚህ ሁለት ዓመታት በኢትዮጽያ እየሆነ ያለውን በእውነት የተመለከተ የችግሩ ምንጭም አልድርቅ ብል ከእለት እለት እየባስበት ሲሄድ አንዳንድ ልበስውራን ወንድሞቼ በየዋህነት ልበለው እውንትን ለመጋረድ ለእራሳቸው የማያሳምን እንዲሁ በዘመኑ የዘር ግንድና እምነት ሳብያ በድረቁ አብይ ሲደግፉ ይስተዋላል ይህ ክፉ ባህርይ ነው ለእኔ ግና ድክመትን እንደመስተዋት አጥርቷ በማሳየት እንዲይታረም ማድረግ ብልህነት ነው!ሁላችንም አገራችንን በማስብንና እንደስው በሀገራችን ከፍ ሲልም በአለም ላይ ያልታየ በመንግስት ወይም በአብይ ቸልተኝነት ውይም ችሎታ ማነስ አልያም ድርጊቱ እንዲፈፀም በመፈለግ በአንዱ ምክንያት ሆኖ እየሆነ ያለ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም!

  ወንድሜ አባዊርቱ! አብይ ሙሉ ስልጣ እንዳለው ትንሽዋ ማሳያ አቶ ታከለን እንዴት ህጉን አስቀይሮ አዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ሲያመጣው ክፉ መሰሪ ስራውን ለመስራት አሁን የምናየውን ስውር ስራ ለምስፈፀም ነበር እኮ? እንዴ እነግ ከነ ትጥቁ ኢትዮጽያ እንንዲገባ ሲፈቅድና ለግብት 7 እና አርበኞች እኮ መሳርያ አስፈትቶ ነበር!ታድያ ለምን?
  ከስማንያ በላይ ይህ የታጠቀ ቡድን ባንክ ሲዘርፍ መከላከል አቅቶ ነብር ትለኝ ይሆን?ገሚሱ ይኦነግ ጦር የትነው የገባው ?በቀጥታ መከላከያና ፖሊስ የገባው! እነ ዲማ ነገዎ ሌንጮ ባቲ ኦነጎችን አማካሪ አድርጎ ቤተመንት ሲያስቀምጥቸው ኢትዮጵያ የተማረ አጥታ ይሆን?አብይ ኦነግነቱን ሲያሳየን ነው!ዛሬኮ እልነብረም አብይ ያኔም ኢንሳ ሆኖ ለኦነግ መረጃ ይሰጥ አልነበር?
  አማራ ክልል ያንን ሁሉ ከትጥቅ ማስፍታት የእነ ዶር አምብቸውና ና የመከላክያ ሚስትሩ ግድያ ኮ በአብይ ይተቀነባበረ ነበር!በእነ ዶር እምባቸው ግድያ ቅን እብይ መከላክያ ሱን ለብሶ ባህዳር ነበር በቴሌቭዥንም ታይቷል!
  አባዊርቱ ! አባክህ በእዚአብሔር ይሁንብህ አታበሳጨን!ሁሉንም እንውቃለን!ይንተን ጭንብል ለብሶ ለመሸፋፈን ቅጥፈት አያዋጣም ና ለእውንት እንጅ በዘረኝነት ጭንብልለመሽፈን ከምትዳክር ዝም ማለትም እኮ እውቀት ክብር ነው!
  እግዚእብሔር ለሁላችን የምናይብት እይ ይምንስብበት አእምሮ የምንሰማበት አእምሮ ይስጠን!

 3. አባዊርቱ በዚህ ድረገጽ አዘውትረው ሀሳቦትን ይገልጻሉ ይህ በጣም ቆንጆ ነገር ግን እኔ የማይገባኝና የማልስማማው ሁሉም እንደርስዎ ብዙ ጊዜ የማይሰጡ ስህተቶችና ጉድለቶች ቅድሚያ ተሰጥቶ መታረም ሲገባቸው ቀስ ብለው ቢተገበሩ ጉዳት በማያስከትሉ ጉድዮች ላይ መወጠር አግባብ አይደለም ወይንም ከዛፍ ቺግኝ ዛፉን ተካይ ለሆኑ በየቦታው ታፍነው ለሚጠፉ ፣ በየመንገዱ ለሚረሸኑ ቅድሚያ ይሰጥ መባሉን እንደ ወንጀል አድርገው ማብጠልጠሎት ነው ። ዶክተር አብይ የምጠቅማቸው እንደርስዎ በጭፍን የሚደግፉ ሳይሆኑ ምክኒያታዊ ትችት አድራጊዎች ናቸው ። የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር ህግና ስነስርአት ማስከበር ሆኖ ሳለ ያንን ተግባር መፈጸም ሳይችል ቀርቶ ቤተሰቡን ያጣን ሀዘንተኛ ወገን “ነስንሰው ሀዘን ከመቀመጥ ችግኝ እየተከሉም አገሪቱን መታደግ ይቻላል” ብሎ በሰው ቁስል እንጨት መስደድ ያስተዛዝባል ። ተቻለሁ ብለው ለትቺት የተዳረጉበት ጽሁፍ ላይ ብዙ ማለት ይቻል ነበር ነገር ግን አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማምና ትቸዋለሁ ።

 4. ለነገሩ አባዊርቱ ነኝ ባይ ፅሁፉን አቅርቧል ፣በውስጡ ግን የጠፋው አቶ ጫላ ማንነቱን ያነፀባርቃል።
  ወጣም ወረደ ከበላይ ሁለቱ አንባብያን በትህትና መልስና የምታውቀውን ግና የምትሸፍጠውን ደግመው ነግረውሃል ።በተለያየ ድረ ገፅ አምልኮትህንና መልሰህነ ደጋግመህ አብስርሃል። አንተን የሃሳብ ድጋፍህን ብቻ ሳይሆን የሰውዪው መለኮታዊነትም በሰፊው አብስረሃል። ይህ ሂደትህ የ prosperity gospel የአምልኮት አካሄድን በሰፊው ያንፀባርቃል ። ሌላ ሃይማኖት ለምን ይኖራል ሳይሆን አሁን በኢትዮጵያ ተንሰራፎ ያለው የነብያቶችን ብዛት ያስረዳናል ፣ብሎም በሰውዪው በያለበት በምን ደረጃ በሹመት እንዳሰራጫቸው የምናየው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንዲያውም በ Hollywood የ Scientology ተብዪው የሃይማኖት ስምሪት ቅጂ ነው። ራስን ወዳድነት አምልኩኝ ባይነት መለያቸው ነው።
  ወሮ/ሮ ፍቅርተ ላቀረበችው መወያያ ነጥብ አንድም ማስተባበያ ሆነ ማረሚያ ሃሳብ አላቀረብክም።ፓርክ ተሰራ፣ ቤተመንግሥት አደሰ፣ ችግኝ ተከላ ወዘተ…ሁላችንም የምናየው ሁኔታን ነው።ይሄ ግን የአሁኑን የኢትዮጵያን ሁኔታ የሚፈታ ሳይሆን የችግራችን መጋረጃ ለማድረግ ታቅዶ የሚሰራ ነው። ምነው ቢባል. የኦሮሙማን አልጠግብ ባይ ሂደትን ማወናበጃ ነው።ድርጊታቸውን መዘርዘሩን ትቼ ሥማቸውን ስጠቅስ ምንና ማን ፣የማን መሆናቸው ህዝብ ያውቀዋል ፣አንተም። ለማ ፣ታዪ፣ሽመልስ ፣ታከለ፣አበበች ……ከሚታወቁት በጥቂቱ ሲሆኑ፣በቀበሌው ፣በወረዳው ፣በየዞኑ ፣በየመስሪያ ቤቱ የሰገሰጉት የኦሮሙማ ሰራዊት የማንም ሳይሆን የአብይ ውጤቶች ናቸው።
  በየክልሉ የሚካሄደውን በአማራው ላይ የሚደረገውን የዘር ጭፍጨፋ አላየሁም አልሰማሁም የሚለው ያንተው ሰውዪው ብቻ ሳይሆን የጭፍጨፋው ሀሳብ ሰጭዎች ጭምር ነው።አንተም የሂደቱ ክህደት አስተጋቢ ነህ። መጀመሪያ ቃል ነበር፣ቃል ከሌለም ድርጊት አይከተልም።ይህ አባባል የኔ ሳይሆን ዘፍጥረት መመልከት ይበቃል ። አምልኮት ስለምትወድ ብዪ ነው።
  በዚህ ሁለት አመት ተኩል የሰውየው. እኩይ ተግባር ህዝቡ ገብቶታል።ምርጫውንም አያሸንፍም ግን እንደ ትራምፕ ማበጣበጡ አይቀርም ።
  በመጨረሻም ፣የለጠፍከው የአይን መሳቢያ ፎቶ በጥሞና ለተመለከተው ማንነትህን ያንፀባርቃል።በጣምም የወረደ አስተሳሰብ ነው። ለማደናገር አንዳንዴም እውቀት ያስፈልጋል ።

  የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቀን።

 5. 1)ዱባ እንደ መሪዉ ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  አባዊርቱ ይረዱኛል ብየ ነበር አውቆ የተኛ ሆኑ፡ ይሁን በአንድ በአንድ አንቀፅ ሶስትአራት ነገሮች እጠቅሳለሁ ለሰጧቸው ምንም ማስረጃ የሌላቸው መልሶች/አስተያየተት። መሪጌታ ጉግልን ጠይቀው ያንብቧቸዉና ቢችሉ ለሙሴዎት ያድርሱልኝ (ፒራሚዷ እንዳትቀር) ሌሎቹ የኦዴፓ ሰወች ከአራት neurons በላይ ስለሌላቸው አይድከሙ አይገባቸዉም።

  2)The only thing that is necessary for the triumph of EVIL is for good men do NOTHING….NOTHING ……NOTHING Edmund Burke(1729-1797)
  What are you doing about it???????
  We all are looking at the proverbial BIG WHITE ELEPHANT and still not adressing it properly. Where did all the good men go?????????
  Please everyone do watch the movie Schindler’s list, it is about a true story of a man who saved lives.
  ጥያቄየ ለእርስዎ አባዊርቱ፣ ለክቡር ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም እና ለዲያቆን ዳንኤል ክብረት ትሁንልኝ። የኔ በር ሲንኳኳ አንድ ይዤ ልወድቅ እችላለሁ ከልጆቼ በፊት በሚል፤ ይህስልጡን መንገድ ነውወይ??

  3)የማስቲካዉ ማነፃፀር ቦታው አይደለም ጥንተ-አብሶ/Original Sin ናት ምንም የማይመስልወት ሞቱ እንዲነሳ የማይፈልጉት የማህበረሰብ ከፍል መኖሩን ራስዎን አጋልጠዋል እንደ አቶ ታየ ብልጭ ትላለች ስለዚህ ይቅር ብየወታለሁ። ስለነፍስ የሚገድዎት መስሎኝ ነበር ወጣቱን በሶማሊ ከልል ሰበብ ከኦሮማያ ኮርነሮች ሞቢላይዝ/ዲሞቢላይዝ የተደረገዉንና እያየን የማንነጋገርበትን ከፖለቲካ ውጭ በሆነ መልኩ scientific በሆነ መልኩ እና ለእነሱም ወጣት ስለሆኑ motivational intervention, streaming movies relevant to the issue at hand and so on. ገዥዎቻችንን ትተናቸው የራሳችንን ሙከራ እናድርግ ለማለት ነበር።

  በታሪክ ባንዴ ሁለት ነገር የሚሰራ በሙሉ አስተውሎት/with equal focus ከወንድ ጠቢቡ ሰለሞን/ሱሌይማን ብቻ ነበር multi tasking ይባላል፤ይህንንም ጥበብ የተጠማችቱ እናታችን የአዜብ ንግስት ፈትናዉ አረጋግጣ የአምላኩን ታላቅነት መስክራ ተመልሳለች(የደብተራ ነው ወይስ የውገና ድርሰት ነው ያሉን) ። ኦው የቱ መፅሀፍ ላይ ነበር ይሄ የተፃፈዉ? የገዳ ስርአት ላይ ነው ወይስ”ፍካሬ ማርያም”? አግኝቸዋለሁ “ውዳሴ ሚካኤል” ነው። FYI women do much better at multi tasking. It’s callus to make fun about the slaughter of innocent lives esp when this is happening while PM is at the helm.
  Leaders were supposed to be trend setters, trail blazers indeed.

  4)Ever heard of the name Abraham Maslow? May be not Both Torah & the holy Koran says፦
  “ANY ONE WHO SAVES A SINGLE LIFE IS CONSIDERED AS IF HE SAVED AN ENTIRE HUMANITY”!!!!
  “ጌታችንስ በምድር ላይ ሳለ ስለጠፋችው ላንዲት በግ ሲል 99ኙን ትቶ ወደሷ ፍለጋ ይሂድ አላለም ወይ?
  “ሙሴው” እነኛን territorial የሆኑ ቀበሮዎች ጎብኝተው፣ ያንን የነፍጠኛ ምልክት የሆነ አንበሳ ገረፍ ገረፍ ካደረጉ በኋላ ልክ አግብተው የድሮ ስርአት ናፋቂ ብለዉ ካሸማቀቁት በኋላ ኩንስንስ ያለችውን ፒኮካቸውን dietitianኗ ያዘዘላት ምርጥ ጥራጠሬ ከመገቡ በኋላ የሰዉ ነፍስ ያድኑ በሉልኝ ሲመቻቸዉ።እርስዎ ግን አባዊሪርቱ አንድ እድል ይቀርዎታል ወጣቶቹን እናስተምር ልልወት ነበር ኮመንትወት በዚያ ልክ ዲጀነሬት ሲያደር ተበሳጨሁ ይቅርታ።
  Coming back to my point, Abraham Maslow was a psychologist who introduced the concept/theory known as “THE HIERARCHY OF NEEDS”. After seventy years it still is popular and people in diverse professions use it like management trainings for CEOs, teachers traininigs in both middle and high schools, most recently even military management & corporate finance. So one can choose where to buy ones commodities since there is Machiavelli’s The Prince or something healthy.

  ወደአማርኛ በአንድ አረፍተነገር ላስቀምጥላችሁና ከጠቀመ ተገልገሉበት፦
  “ሰዎች እባካችሁ እባካችሁ አሁንም እባካችሁ በድንግል ማርያም/ስለአላህ እንዲሁም በምታምኑት ሁሉ እለምናችኋለሁ መቅደም ያለበትን አስቀድሙ አራት ነጥብ”
  እኔ ክቡሩን የሰዉ ህይኸት ማዳን ይቀድምብኛል ከ1-10 ሌላዉ ሁሉ ከ11ኛ ነዉ። If you are your brothers/sisters keepers I think this the time to do so.
  አባዊርቱ አና ሌሎቻችሁም ከመሪጌታ ጉግል ላይብረሬ ይህችን የአቶ አብርሀም ማስሎው ፅንሰ-ሀሳብ ፈለግ አድርጓትና ገላጭ የሆነች ቄንጠኛ በቀለም ያሸበረቀች ፒራሚድ አለቻታ ፖስት አርጓትና ገዥዎቻችንን ምን እንደሚድም አስተምሩልኝ (የፌስቡከም ሆነ ትዊተር ተጠቃሚ ስላይደለሁ ነዉ) ለሻለቃ ዳዊትም አድርሱ አመሰግናለሁ። ደግሜም አልመጣም።
  መደመርን ለኔ ሬኮመንድ ከማረግዎ በፊት ትራምፕን የእ/ርን ጉዳይ አስፈፃሚ አርጎ ከሚወስድና አምልኮተ ነዋይ፣ የአክራሪ ነጭ የቀኝ ፅንፈኛ አካባቢ የመነጨ ነገር መሆኑን ያዉቃሉ ወይ??ያዲሳባ ሰዉማ ከአንድሺህ ብር ጀምሮ ልቡን ሲወቀር የት ነበሩ???በመጨረሻም ለሁሉም ሰፊ የቲቪ ሽፋን ተሰጥቶት ሁሉም በቻለው ልክ ተወቅሯል።
  Ever heard of QAnon???

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.