የኦዴፓ ብልፅግና የተረኛ ዘረኛ የዕዳ ቧንብ!!! የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ 2.01 ትሪሊየን ብር!!! በዓመት 510 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዕዳ!!!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል

33የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ 2.01 (ሁለት ነጥብ ዜሮ አንድ) ትሪሊየን ብር፣ በዓመት 510 (አምስት መቶ አስር) ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዕዳ፣ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ጋር ሲነፃፀር 50.8% ደርሷል!!! የአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት አሽቆልቆሎል፡፡ የኢትዮፕያ መንግስት ዕዳ ጥናታዊው ዘገባ እንሆ እንላለን፡፡ በሃገሪቱ  በአንበጣ ወረራ ምርት ቀንሶል፣ በኮቪድ አስራ ዘጠኝ ምርታማነት ቀንሶል፣ በትግራይ ጦርነት ብዙ ሰዎች ሞተዋል፣ ቆስለዋል፡፡ ሃገሪቱ በውጭ ምንዛሪ የገዛቻቸው የመከላከያ ከባባድ መሳሪያዎች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች፣ ሚሳኤሎች፣ ዙ ሃያ ሦስት፣ ቁምቡላ፣ቧንቧች፣ አርፒጄ፣ ሞርታል፣ ወዘተ በትንሹ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ወድሞል፡፡ በ2020 እኤአ የኢትዮጵያ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት (FDI Inward Flow ) 600 (ስድስት መቶ) ሚሊዮን  ዶላር  ሲወርድ አጠቃላይ በሃገሪቱ ያለ የውጭ ኢንቨስትመንት ክምችት (FDI Stock) 24.923 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ዩኤስ ዶላር ሆኖል፡፡ 2020እኤአ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት(አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) እድገት 1.9 በመቶ እንደሆነ አስታውቆ ነበር፡፡ የሸማቾች የሸቀጥ ዋጋ መናር በመቶ 20.2 በመቶ ተንብዬ ነበር፡፡

እንደ ኢትዩ 360 መረጃ መሠረት በአንድ በኩል በመላ ሃገሪቱ በትግራይ ጦርነት ምክንያት 2.2 ሚሊዩን ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ በትግራይ ከ50 ሽህ ሰዎች በላይ ወደ ሱዳን ተሰደዋል፣ በትግራይ መቐለ የውኃ ችግር ተባብሶል፣ በአማራ ክልል የአንድ ቢሊዮን ብር የሚገመት የእርሻ የሰብል ምርት በሱዳን ወታደሮች ተዘርፈዋል፣ በቤኒሻንጉል  ጉሙዝና በወለጋ በአማራ ዜጎች ላይ የዘር ማፅዳት የተነሳ ብዙ ሰዎች ታርደዋል ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ ተፈናቅለዋል፣ በደቡብ ክልል በአማሮና ቡርጅ ግጭት ሃያ ሰባት 27 ሽህ ሰው ተፈናቅሎል፣ ኮንሶ ሃምሳ ስድስት ሰዎች ተገደሉ፣ ከሃምሳ ስድስት ሽህ ሰዎች ይፈናቀላል ይሰደዳል፣ ይታመሳል፡፡

በሌላ በኩል ይህ በእዲህ እያለ ኦዴፓ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ ስሜት ከህወሓት ውድቀት ባለመማር፣ ኦነግ ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር ‹‹የገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን›› የአርባ ዓመት ፕላን ፕሮጀክት፣ በአፍሪካ ቀዳሚ አንደኛ የኦሮሚያ ሚዲያ 4.5 ቢሊየን ብር፣ የግብርና ሚኒስቴር ግንባታ በቢሊዮን ብር የሚገመት፣የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግንባታ በቢሊዮን ብር የሚገነባ፣ ለኦሮሚያ ገበሬዎች የትራክተርና የእርሻ ማሽኖች ተከፋፍሎል፣ በሁሉም ክልሎች በቢሊዮን ብር የሚቆጠር የኦሮሚፋ የቁቤ ትምህርት ቤቶች ግንባታ በመከናወን ላይ ይገኛል፣ ይሄ ሁሉ ግንባታ በብድር ገንዘብ የተገነባ የዘረኛና የተረኛ ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር የሚደረግ ጥረት ነው፡፡  ዶክተር አብይ አህመድ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን እንደ የህዳሴውን ግድብ ሥራ፣ የስኳር ፋብሪካዎችን፣ የኢንዱስትሪ ዞኖች፣ የአግሮ ኢንዱስትሪ ዞኖች ፣ መስኖ  ሥራዎች ወዘተ ፕሮጀክቶች ሳይጠናቀቁ አዲስ ፕሮጀክቶች አይገነቡም ብለው የነበረውን ቃላቸውን ከበሉት ቆይቶል ሃገሪቱ በዕዳ ወጥመድ (Debt Trap) ውስጥ ወድቃለች፡፡ ከብድር መታገድ ይቀጥላል! በዚህ አጠቃላይ ችግር ላይ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በየክልሎቹ ተጨማሪ ግጭትነ የህዝብ መፈናቀል እንደሚያስከትል የገብረ-ጉንዳን መንገድ መከተል አያሻም፡፡  ዶሞክራሲና ምርጫ እያለ ህወሓት/ኢህአዴግ ሃያ አምስት አመታት፣ አምስት ዙር ገንዘብ ባክኖል እንጅ ለህዝብ ዴሞክራሲ አላካፋለትም፡፡

የኢትዮጵያ ማዕከላዊ  መንግሥት ዕዳ

 • አገሪቱ እስከ ማርች 2019 እ.ኤ.አ. ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ5 (አንድ ነጥብ አምስት)ትሪሊን ብር ወይም 52.57 (ሃምሳ ሁለት ነጥብ ሃምሳ ሰባት)ቢሊዮን ዶላር ነበር፡፡
 • አገሪቱ እስከሴፕቴምበር 2020 እ.ኤ.አ. ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ01 (ሁለት ነጥብ ዚሮ አንድ) ትሪሊን ብር ወይም 54.7 ቢሊዮን ዶላር ተመንድጎል፡፡ የዕዳ መጠኑ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 50.8 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል
 • አገሪቱ ዕዳ ከማርች 2019 5 ትሪሊን ብር እስከ ሴፕቴምበር 2020 እኤአ 2.01 ትሪሊን ብር ደርሶል ልዩነቱ 510 (አምስት መቶ አስር) ቢሊዮን ብር የዕዳ እድገት አሳይቶል፡፡ ለምን ነገር እንደተበደርን ቢዘረዘር?

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሰሞኑን ይፋ ያደረገው አጠቃላይ የዕዳ መጠን መግለጫ ሰነድ፣   

 • የኢትዮጵያአጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ01 (ሁለት ነጥብ ዚሮ አንድ) ትሪሊየን ብር እስከ ሴፕቴምበር 2020 እኤአ መድረሱንና፣ የዕዳ መጠኑ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 50.8 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
 • የኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥትና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች ተበድረው ያልከፈሉት አጠቃላይ ዕዳ7 (ሃምሳ አራት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ሰነዱ ያሳያል፡፡ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትሩ የብድሩ ዝርዝር ቢገለፅ፣ የከበረ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
 • አጠቃላይዕዳ7 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘው 28.99 (ሃያ ስምንት ነጥብ ዘጠና ዘጠኝ) ቢሊዮን ዶላር ሲደመር ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘው 25.7 (ሃያ አምስት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር (54.7= 28.99 +25.7)
 • አጠቃላይዕዳ005 ትሪሊየን ብር ሲሆን ከውጭ  አበዳሪዎች የተገኘው 1.06 ትሪሊየን ብር ሲደመር ከአገር ውስጥ አበዳሪዎች የተገኘው 945 (ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት) ቢሊዮን ብር (2.005= 1.06 +945)
 • ከውጭአበዳሪዎች የተገኘው :-99 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ከውጭ የብደር ምንጮች የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሰልቶ 1.06 ትሪሊየን ብር እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል።
 • ከአገር ውስጥ አበዳሪዎችየተገኘው :-7 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች የሚከፈል የአገር ውስጥ ዕዳ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል። ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች መከፈል፣ ያለበት ዕዳ ይህ የዕዳ መጠን ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሠልቶ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ሥሌት መሠረት የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል። ከ945 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ እዳ ውስጥ 525 (አምስት መቶ ሃያ አምስት) ቢሊዮን  ብር የሚሆነውን ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቆማት ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡

አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዕዳ

 • አጠቃላይየማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ ሠላሣ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ፡-

ከአጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ አጠቃላይ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 56 በመቶ ማለትም 30.6 (ሠላሣ ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ይዞል፡፡

 • አጠቃላይ የመንግሥት ልማት ድርጅት ዕዳ ሃያ አራት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ዶላር፡-

ከአጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 44 በመቶ ማለትም 24.1 (ሃያ አራት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ዶላር ድርሻ ይዞል፡፡

አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት  (GDP)፡-

 • አጠቃላይ የመንግሥት ዕዳ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት  (GDP) 50.8 በመቶ ድርሻ ይዞል፡፡
 • አጠቃላይ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት  (GDP) 12.5 በመቶ ድርሻ ይዞል፡፡
 • የአገሪቱየውጭ ዕዳ አማካይ የመክፈያ ጊዜ 15 ዓመት መሆኑንም መረጃው ያመለክታል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከጥቂት ወራት በፊት ይህንኑ ሁኔታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስረዳታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ባደረጉት ንግግርም መንግሥታቸው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመውደቅ አደጋ ተጋርጦበት ነበር ማለታቸው አይዘነጋም።  መንግሥት እያደረጋቸው ከሚገኙ ሪፎርሞች መካከል የመንግሥት ልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ የመፍትሄ አማራጭ መሆኑን  ታውቆል፡፡

ከአጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ ለውጭ አበዳሪዎች የሚከፈለው 28.99 ቢሊዮን ዶላር ወይም 1.06 ትሪሊዮን ብር ግን አለመክፈል የሚቻልበት ሁኔታ ዝግ በመሆኑ፣ የኢትየጵያ ደግሞ በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ውስጥ በመውደቁ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ የራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህንን የውጭ ዕዳ ኢትዮጵያ መክፈል እንደማትችል ከተረጋገጠ ደግሞ አገሪቱን ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትሰፍርና በቀጣይ የውጭ ብድር ፍላጎቷ በር የሚዘጋ ሁኔታን ሊፈጥር እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ።

የውጭ ዕዳን ሙሉ በሙሉ ማሰረዝ አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፣ የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግሥታት በአሁኑ ወቅት ከፈረሰችው ሶቪዬት ህብረት ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ፣ አሁንም ድረስ በዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ተብሎ እስካሁን ተመዝግቦ እንደሚገኝ ይገልፃሉ፡፡

በብልፅግና ፓርቲ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመጋቢት  2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከመጋቢት  2010 እስከ መጋቢት 2011ዓ/ም ድረስ ባለው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ምን መሻሻል አሳየ፡፡ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮችን የዕዳ መጠን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አድርጎ ነበር፡፡  በዚህም መሠረት ዝርዝር የዕዳ መግለጫ ሰነድ እንደሚያስረዳው፣ 2

 • አገሪቱ ... እስከ ማርች 2019 ድረስ ያለባት ያልተከፈለ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ5 (አንድ ነጥብ አምስት) ትሪሊን ብር ወይም 52.57 (ሃምሳ ሁለት ነጥብ ሃምሳ ሰባት) ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡
 • የአገሪቱ አጠቃላይ የውጭና የአገር ውስጥ ብድሮች ዕዳ5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሌኮም የውጭ ብድር ዕዳ9 (መቶ አስራአንድ ነጥብ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • የሌሎቹ የልማት ድርጅቶች የውጭና የአገር ውስጥ አጠቃላይ የብድር ዕዳ 594 (አምስት መቶ ዘጠና አራት) ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • ማዕከላዊ መንግሥትና የልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ5 (አራት መቶ አስራ ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
 • መንግሥት ከንግድ ባንክ የወሰደውን ብድር መመለስ ባለመቻሉ በየዓመቱ እስከ 25 (ሃያ አምስት) ቢሊዮን ብር ወለድ እየከፈለ ነው
 • ከተጠቀሰው አጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ08 (ሰባት መቶ ስልሳ ዘጠኝነጥብ ዜሮ ስምንት) ቢሊዮን ብር ወይም 26.93 (ሃያ ስድስት ነጥብ ዘጠና ሦስት) ቢሊዮን ዶላር ከተለያዩ የውጭ አበዳሪዎች ተገኝቶ ያልተከፈለ ዕዳ ሲሆን፣
 • የተቀረው5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ወይም 25.6 (ሃያ አምስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ከአገር ውስጥ የመንግሥት ባንኮች ማለትም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክና ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣ እንዲሁም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (ጡረታ) ፈንዶች ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
 • አገሪቱ ካለባት የውጭ ዕዳ ውስጥ የማዕከላዊ መንግሥት (Centeral Government) ዕዳ7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር (15.73 ቢሊዮን ዶላር) ሲሆን፣ ቀሪው 319.3 ቢሊዮን ብር (11.17 ቢሊዮን ዶላር) ደግሞ የተለያዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መንግሥት በገባላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ (Loan Guarantee)፣ ሌሎች ሁለት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ደግሞ ያለ መንግሥት የብድር መክፈያ መተማመኛ፣ በራሳቸው ከውጭ አበዳሪዎች በቀጥታ ተበድረው ያልከፈሉት ዕዳ ነው፡፡
 • የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ 7 (አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ወይም (15.73 ቢሊዮን ዶላር)
 • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች3 (ሦስት መቶ አስራ ዘጠኝ ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ብር ወይም (11.17 ቢሊዮን ዶላር)
 • የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢትዮ ቴሎኮም ያለ መንግሥት ዋስትና የብድር መክፈያ መተማመኛ ከውጭ የተበደሩት እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር ወይም 111.96 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • ሎሎቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ገንዘብ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በገቡላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ በመጠቀም ከወሰዱት የውጭ ብድር ውስጥ እስከ ማርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት የዕዳ መጠን38 ቢሊዮን ብር (7.27 ቢሊዮን ዶላር) መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡
 • አጠቃላይ የውጭ ብድር ዕዳ እስከ ማርች 2019 ድረስ አገሪቱ ያለባትን ተመሳሳይ ወቅት ድረስ የተመዘገበው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ደግሞ5 ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡

አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ በሚመለከት በማዕከላዊ መንግሥትንና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን  የተወሰደው 730.5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር መድረሱን መረጃው ያመለክታል፡፡ በዚህም መሠረት  አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ (730.5=343.7+386.8)

 • የማዕከላዊ መንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ7 (ሦስት መቶ አርባ ሦስት ነጥብ ሰባት) ቢሊዮን ብር ሲሆን፣
 • የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለባቸው መረጃው በዝርዝር ያመለክታል፡፡

ማዕከላዊ መንግሥት ካለበት 343.7 ቢሊዮን ብር የአገር ውስጥ ዕዳ ከፍተኛው መጠን ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ ብድር የተወሰደ፣ እንዲሁም በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና (የጡረታ) ኤጀንሲዎች፣ ማለትም ከመንግሥት ሠራተኞችና ከግል ሠራተኞች የጡረታ ፈንድና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳ መሆኑን ከመረጃው ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህም መሠረት ማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ (343.7= 182+98.2+26.5+37)

 • ከብሔራዊ ባንክ ቀጥታ ብድር፣182 (መቶ ሰማንያ ሁለት) ቢሊዮን ብር
 • በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ አማካይነት ከሁለቱ የጡረታ ፈንዶች፣2 (ዘጠና ስምንት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር
 • ከንግድ ባንክ ብድር 5 (ሃያ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ነው፡፡
 • የተቀረው በመንግሥት ቦንድ ሽያጭ አማካይነት ከልማት ባንክና ከሌሎች ምንጮች ተወስዶ 37(ሠላሣ ሰባት) ቢሊዮን ብር እስከተገለጸው ወቅት ድረስ ያልተከፈለ የማዕከላዊ መንግሥት ዕዳ ነው፡፡

ከ730.5 (ሰባት መቶ ሠላሳ ነጥብ አምስት)ቢሊዮን ብር አጠቃላይ የአገር ውስጥ ዕዳ ማዕከላዊ መንግሥትን የሚመለከተው ተቀንሶ የሚቀረው 386.8 (ሦስት መቶ ሰማንያ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር ዕዳ፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮ ቴሌኮም ወጭ ያሉትን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚመለከት እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የመንግሥት ልማት ድርጅቶቹን የተናጠል ዕዳ ዘርዝሮ አያስቀምጥም፡፡ ከልማት ድርጅቶቹ አጠቃላይ ዕዳ ውስጥ 386 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተወሰደ ሲሆን፣ 800 (ስምንት መቶ) ሚሊዮን ብር ደግሞ የልማት ባንክ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ የመንግሥትን አጠቃላይ የዕዳ መጠንና ዝርዝሮቹን ከያዘው ሰነድ የተለያዩ ከፍተኛ ሥጋቶችን መመልከት የሚቻል ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጤንነት አደጋ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡ ሰነዱ ከያዛቸው አኃዞች ምልከታ መረዳት የሚቻለው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በቀጥታ፣ እንዲሁም የመንግሥትን የዕዳ ክፍያ መተማመኛ ሰነድ (ቦንድ) በማስያዝ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወሰዱት የረጅም ጊዜ ብድር፣ እንዲሁም ማዕከላዊ መንግሥት ከዚሁ ባንክ ተበድሮ ያልመለሰው የገንዘብ መጠን ድምር እ.ኤ.አ. እስከ ማርች 2019 ባለው ጊዜ ውስጥ 412.5 (አራት መቶ አስራ ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር ደርሶል፡፡

ባንኮች የሚሰጡት ብድር ስብጥር (Loan Portfolio) የገንዘብ ተቋማት ጤንነትን ለመለካት የሚያገለግል መሣርያ መሆኑን የሚገልጹት ሪፖርተር ያነጋገራቸው ባለሙያዎች፣ አንድ ባንክ የሚሰጠው ብድር ሰፊ ስብጥር ወይም በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተበዳሪዎች መሆን እንዳለበት፣ የተበዳሪዎች ስብጥር ሰፊ መሆን በተበዳሪዎች ላይ ሊደርስ የሚችል የንግድ ኪሳራ መጠንን በዚያው ልክ በመቀነስ፣ በባንኩ ብድር ላይ ሊፈጠር የሚችል ተጋላጭነትን ለመከላከል እንደሚያስችል ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ አንፃር ንግድ ባንክ የሰጠው 412.5 ቢሊዮን ብር ለመንግሥትና ለአራት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መሆኑ የብድር ክምችቱ በአንድ አካባቢ የተከማቸ እንዲሆን በማድረግ፣ ባንኩ ላይ ከፍተኛ ሥጋት እንዲያጠላ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡ ከዚህም በላይ የብድር ስብጥሩን እጅግ ጠባብ ያደረገው ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች ከተሰጠው ብድር ውስጥ ከ200 (ሁለት መቶ) ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆነው፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡

ሪፖርተር ያገኘው አጠቃላይ የአገሪቱ የብድር ሰነድ መረጃ እንደሚሳየው፣ ማዕከላዊ መንግሥትም ሆነ የልማት ድርጅቶቹ ያለባቸውን የንግድ ባንክ ብድር ላለፉት አምስት ዓመታት ከፍለው እንደማያወቁ፣ ነገር ግን ከ17 ቢሊዮን እስከ 25 ቢሊዮን ብር ወለድ ላለፉት ዓመታት በየዓመቱ እየከፈሉ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ ባንኩ ለስኳር ፕሮጀክቶች ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ቢሰጥም፣ በርካቶቹ ፕሮጀክቶች በማኔጅመንት ችግር መጠናቀቅ ባለመቻላቸው መንግሥት ባሉበት ሁኔታ በሽያጭ ወደ ግል ሊያዘዋውራቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ለእነዚህ ፕሮጀክቶች በብድር የፈሰሰውን 11 ቢሊዮን ብር ያባከነው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ብድሩን መክፈል እንደማይችል በመግለጽ፣ ይህንን ጨምሮ በአጠቃላይ 57 ቢሊዮን ብር እንዲሰረዘለት ሰሞኑን ለመንግሥት ጥያቄ እንደቀረበ ተዘግቦ ነበር፡፡ እንደ ባንክ ያሉ የገንዘብ ተቋማት ውጤታማነት መለኪያ ከሆኑት አንዱ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት መጠን፣ ባንኩ ከሰጠው አጠቃላይ ብድር መጠን ጋር የሚኖረው ምጣኔ ስለመሆኑ የባንክ ሙያ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እስከ ማርች 2019 ድረስ የነበረው አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 496 (አራት መቶ ዘጠና ስድስት) ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ ለግሉ ዘርፍ ያበደረውን ሳይጨምር እስከ ተጠቀሰው ወር ድረስ ለማዕከላዊ መንግሥትና ለልማት ድርጅቶች አበድሮ የተመለሰለት የብድር መጠን 412.5 (አራት መቶ አስራ ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር መሆኑ የባንኩን ጤንነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል፡፡

ዓርብ ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም. የበጀት ዓመቱን የሥራ አፈጻጸም ይፋ ያደረገው ባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ አጠቃላይ መጠን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ 541.2 (አምስት መቶ አርባ አንድ ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር መድረሱን የገለጸ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የሰጠው አዲስ ብድር 129 (መቶ ሃያ ዘጠኝ) ቢሊዮን ብር እንደሆነ አመልክቷል፡፡ ከሰጠው አዲስ የብድር መጠን ውስጥ 106.8 (መቶ ስድስት ነጥብ ስምንት) ቢሊዮን ብር መንግሥት የወሰደ ሲሆን፣ ቀሪው 22.2 (ሃያ ሁለት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው፡፡ ንግድ ባንክ ለመንግሥትና ለልማት ድርጅቶቹ የሰጠው ብድር ከፍተኛ መሆኑና የብድሩ መመለስን በተመለከተ ስለሚነሳው ሥጋት ሪፖርተር ጥያቄ ያቀረበላቸው የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ባጫ ጊና፣ ሥጋቱ ትክክለኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ባንኩ ለመንግሥትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ የሰጣቸው ብድሮች እንደሚመለሱ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ተበዳሪ የሆኑ የልማት ድርጅቶች ብድሩ እንዲሰረዝላቸው ስለጠየቁ ይሰረዛል ወይም ባንኩ ገንዘቡን ያጣል ማለት እንዳልሆነ የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ፣ “ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እንዴት እንደምንሄድበት እናውቃለን፡፡ ምክንያቱም ብድሩን ያበደርነው የመንግሥትን ዋስትና ይዘን ነው፤” ብለዋል፡፡ የአገሪቱን አጠቃላይ ብድር የያዘው መረጃ የሚያስገነዝበው ሌላው ጉዳይ፣ መንግሥት በአነስተኛ ወለድ የውጭ ብድር ቢያገኝ እንኳን በርካቶቹ የውጭ ዕዳዎቹ የክፍያ ጊዜ በማለፉ ወይም በመድረሱ ምክንያት የሚያገኘው አዲስ ብድር ተመልሶ ለዕዳ ክፍያ እየዋለ መሆኑን ነው፡፡ ለአብነት ያህል የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አስተዳደር እ.ኤ.አ እስከ ማርች 2019 ድረስ 2.2 (ሁለት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ዶላር አዲስ ብድር ያገኘ ቢሆንም፣ ለተገኘው አዲስ ብድር የአገልግሎት ክፍያ፣ ክፍያቸው የደረሱ ብድሮች ዋና ብድርና ወለዶች ተከፍሎ ወደ አገር የገባው የአዲሱ ብድር የተጣራ መጠን 700 (ሰባት መቶ) ሚሊዮን ዶላር ነው፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው ሌላ የማክሮ ኢኮኖሚ ባለሙያ በበኩላቸው፣ መንግሥት ካለበት አጠቃላይ የአገር ውስጥ ብድር ውስጥ 182 (መቶ ሰማንያ ሁለት) ቢሊዮን ብር ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ የተበደረው መሆኑ አሳሰቢ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ መንግሥታት ከብሔራዊ ባንኮቻቸው በቀጥታ መበደር የሚችል ቢሆንም፣ የብድር ጣሪያው በሕግ መወሰን እንደሚገባውና ብድሩ በተወሰደበት በዚያው ዓመት መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ እንዲከፈል በሕግ ካልተደረገ በስተቀር፣ ውጤቱ ገንዘብ እንደማተም እንደሚቆጠር ይህም ኢኮኖሚው ያላመነጨው ተጨማሪ ገንዘብ በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲሽከረከርና የዋጋ ግሽበት እንዲፈጠር የሚያደርግ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

በተጨማሪም መንግሥት ያለ ገደብ ከብሔራዊ ባንክ የሚበደርበት ሥርዓት አለ ማለት፣ ብሔራዊ ባንክ ማክሮ ኢኮኖሚውን ያለ መንግሥት ጣልቃ ገብነት ማስተዳደር አለመቻሉን እንደሚያሳይ ባለሙያው ገልጸዋል፡፡ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መውሰድ የሚችለው የቀጥታ ብድር ጣሪያ በ2000 ዓ.ም. እንዲነሳ ከተደረገ በኋላ፣ ከብሔራዊ ባንክ ያለ ገደብ እየተበደረ መሆኑ አሁን ለሚስተዋለው የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት የራሱ ድርሻ ማበርከቱን አክለዋል ነበር፡፡ አንዳንዶቹ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች እስከ አንገታቸው ድረስ በዕዳ የተዘፈቁና ተጨማሪ ካፒታል እንዲያገኙ ቢደረግ እንኳን መዳን የሚችሉ ባለመሆናቸው፣ በሽያጭ ወደ ግል ተዘዋውረው እንዲተርፉ ማድረግ ለመንግሥት የቀረው ብቸኛው አማራጭ መሆኑን፣ ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተካሄደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ውይይት ላይ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ገልጸው ነበር፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚሸጡትም ድርጅቶች ከላይ ከፍተኛ ዕዳ ውስጥ የተዘፈቁ መሆናቸው ገልፆል፡፡

 

ምንጭ፡-

Photo https://co.wikipedia.org/wiki File: Ethiopia-FinMin.jpg/Ministry of Finance and economic Development( Ethiopia)

{1} https://www.ethiopianreporter.com/article/20907/የአገሪቱ አጠቃላይ የውስጥና የውጭ ዕዳ 2.01 ትሪሊየን ብር መድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ | ሪፖርተር Ethiopian Reporter Amharic/3 January 2021/ ዮሐንስ አንበርብር

{2} ሪፖርተር ጋዜጣ/ የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ የብድር ዕዳ 1.5 ትሪሊዮን ብር ደርሷል/ August 19, 2019 Tዮሐንስ አንበርብር

 

4 Comments

 1. How much debt is too much debt? My friend!
  debt-to-GDP ratio በተመለከተ ታዋቂ ኢኮኖሚስቶቹም ቢሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ እርስ በርስ አይስማሙም፣ ለማንኛውም ግን ላደጉት አገሮች ከ80 % ባይበልጥ፣ በማደግ ላይ ላሉት ከ60 % ባይበልጥ ለጤናማ ኢኮኖሚ ይመረጣል የሚሉ አሉ፣ በአጠቃላይ በዚህ አባባልም የማይስማሙ አሉ።
  አቶ ሚሊዮን ዘአማኑኤል እንዲህ ይሉናል: ”የኢትዮጵያ መንግሥት ዕዳ 2.01 (ሁለት ነጥብ ዜሮ አንድ) ትሪሊየን ብር፣ በዓመት 510 (አምስት መቶ አስር) ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ዕዳ፣ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት ጋር ሲነፃፀር 50.8% ደርሷል!!! (አንርሳ 60 % የደረሰበትም ጊዜ ነበር)
  የአቶ ሚሊዮን ”ጉድ ፈላ ምን ሊውጠን ነው” ጩሀት ግን ለሚያውቀው ”ገንፎ ውስጥ ያለ ስንጥር” አያንቀውም። እውቀታቸውን እና አእምሮዋቸውን በኢትዮ 360 ላዳበሩ ግን የእኔ ምክር ”ገንፎውን” ስትውጡ እየተጠነቀቃችሁ:: ስንጥሩ ደግሞ የቃል አጋኖው ምልክት መሆኑን አትዘንጉ ”!!!”
  የሌሎች አገርን ስናይ ለምሳሌ እነ ጃፓንን፣ ግሪክ ኢጣሊያንን እንተዋቸው የሰለጠኑ አገራት ውስጥ ስለሚመደቡ እንጂ የእነሱንም ቢሆን ለመጥቀስ ካስፈለገ ከ130 – 230 % ይደርሳል። info ይህንን link በመጫን ማየት ይቻላል https://worldpopulationreview.com/country-rankings/debt-to-gdp-ratio-by-country
  ታዲያ እኛ አካባቢ ያሉትንስ ስናይ፣ አንጎላ 111.00%፣ ሞዛምቢክ 109፣ ጂቡቲ 104፣ DR ኮንጎ 98፣ሞሮኮ 66፣ ሱዳን 62 እያለ ይቀጥላል።
  ለሌላ የፖለቲካ ግብ ብለን አናጋን፣ አናዳንቅ! እሳት ባልተነሳበት የእሳት አደጋ መከላከያ አንጥራ!
  ሌላው በአቶ ሚሊዮን መጣጥፍ ላይ የገረመኝ ከኢኮኖሚስትነታቸው ወጥተው የሰሜን ዕዝ የሎጂስቲክስ መምሪያ ሀላፊ ይሆኑና በጦርነቱ የጠፋውን ንብረት አንድ በአንድ ያስቆጥሩንና በብር እንዲህ ያሰሉታል ” ሃገሪቱ በውጭ ምንዛሪ የገዛቻቸው የመከላከያ ከባባድ መሳሪያዎች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች፣ ሚሳኤሎች፣ ዙ ሃያ ሦስት፣ ቁምቡላ፣ቧንቧች፣ አርፒጄ፣ ሞርታል፣ ወዘተ በትንሹ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ወድሞል”፡፡ አቶ ሚሊዮን ወዘተ ብለው ቢያልፉትም ምነው ”የእጅ መሳሪያ እና ክላሽን” ሳይቆጥሩ ተውት ብላችሁ ብትጠይቋቸው የምታገኙት መልስ፣ እሱማ አልወደመም ”የእኛ ሰዎች” ለነፃነታቸው ሊታገሉ ይዘውት ዋሻ ገብተዋል ይሏችኋል። ግዴሎትም TPLF ኖት ብዬ አልጠረጥሮትም እንዲያው ብቻ ይሀች አባይ ፀሀዬን ያሳሳተች ”ስኳር” እርስዎም ጋ ደርሳ ትሆን (ይህቺ ”የስኳር” በሽታ እኮ መምጫዋ አይታወቅም በተለይ ብዙ የሚፅፉትንንና ተቀባይነት አላቸው የተባሉትን ሰዎች ታጠቃለች አሉ)
  አቶ ሚሊዮን! አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጲያዊን TPLF ን ለማጥፋት እስከ ስንት ብር እናውጣ ቢሉት ”ሁለት ቢሊዮን ዶላር” በጣም ትንሽ ነው እንደሚሎት አይጠራጠሩ:: እነሱስ በስልጣን ላይ እያሉ የዘረፉት ገንዘብ ”እርስዎ እንኳን በደንብ” የሚያውቁት ይመስለኛል፣ ኡ ኡ! አያሰኝም። ባይሆን ስለሱ ይፃፉና እብረን እንጩህ
  ቸር ይሰንብቱ አቶ ሚሊዮን! እርስዎም ይቻሉ፣ እኛም 27 ዓመት ችለናል።

 2. አንተ ደግሞ ትቀልዳለህ። በአለም ላይ እንደ እኛ ያለ ሃብታም የለም የሚሉት አሜሪካኖች ያለባቸውን የእዳ ጫና ታውቃለህ? ጠግቦ በልቶ የማያድር ህዝብ የሚኖርባት ኢትዮጵያ ከአንድ ክፋት ወደ ሌላው ታልፋ እየተሰጠች የዘራፊዎች መፈንጫ ሆና እያለ እዳ በዛባት ማለት ምን የሚሉት ጫዋታ ነው። የሃገሪቱ ችግር እኮ ግልጽ ነው። ዘራፊን ዘራፊ እየተካው ለእርዳታ የተሰጠው ገንዘብም ሆነ የብድሩ ዞሮ እየወጣ ቤት/ንግድ/ ሲከፈትበት አይናችን እያየ ነው። ሰው በሃገሩ ላለመኖር ሃብት በሚያሸሽባት የሃበሻይቱ ምድር የእዳ ክምር ሰማይ ጠቀስ ሆነ መባሉ ፌዝ ነው ለእኔ። መሪዎቻችን እኮ ለዛሬና ለእነርሱ ብቻ ነው እየኖሩ የሚያልፉት። የነበረን አፍርሶ፤ ሌላው በወረፋው የሌላውን ሃሳብና እይታ ደፍጥጦ በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በክልል በተዋቀረ ሃገር ላይ ሰው እዳ በዛብኝ ብሎ እንቅልፍ ያጣል እንዴ? እስቲ የወያኔ መኮንኖችና ባለስልጣኖች በልማት ስም ከባንክ የተበደሩትንና ሳይመልሱ የቀሩትን የገንዘብ አሃዝ ባንኮችን ጠይቃቸው። ብቻ ሆድ ይፍጀው ነው ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው።
  ሰው ሰውን በሰው ደረጃ አይቶ በዘሩ ጡርንባ ከመንፋት ባሻገር አለም አቀፋዊና ሰዋዊ እይታ ሲኖረው መረዳዳት፤ እዳን በጋራ ለመክፈል ጠንክሮ መስራት፤ አንድ አንድን ይረዳል። ትላንትም አሳደህ በለው፤ ዛሬም ጎራው ልቀቀኝ በሚባልባት ምድር ላይ እንዴት ተብሎ ነው ስለ እዳ የሚታሰበው? የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ይላሉ አበው። ብቻ ያለንበት ጊዜ ኡኡታ ተሰምቶ አለሁልህ የማይባልበት፤ እከሌ ሞተ ሲባል ዘር የሚጠየቅበት፤ ለቅሶአችን ሁሉ በዚሁ ዙሪያ ላይ ብቻ በመሆኑ የትላንትናው ገራፊ የዛሬ ታሳሪ፤ የያኔው አሳዳጅና ጉረኛ አሁን እንደ ዝንጀሮ ገደል ለገደል ተንከራታች፤ ባጭሩ የወረፋ ፓለቲካው ቀሪን አስገርሞ ሙታንን ከመቃብራቸው ቀስቃሽ ነው። ለመሆኑ የሰው መለኪያው ምንድን ነው? እስኪያሽልብ ድረስ ለመኖርስ ምን ያህል ንዋይ ያስፈልገዋል? አንድ የወያኔ ጄ/በአዲስ አበባ ቤት ሰርቶ በወር $12 ሺህ ዶላር እንደሚያከራይ አውቃለሁ። እንዴት እንዲህ በናጠጠ አለም እየኖሩ ሰራዊቱን ከጎን መወጋት መረጡ? ጡረታ ከወጡት ጀምሮ በሰራዊቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ እንዴት ይህን ነገር አሰቡት? እብሪት፤ እብደት፤ ከሰው ባህሪ ውጭ መሆን ያመጣው ለመሆኑ እጣት መቁጠር አያስፈልግም። ታዲያማ እንዲህ በየዘመናቱ በጠበንጃ አንጋቾችና በዘር ፓለቲከኞች የምትታመሰው ይህች ሃገር የእዳ ጫና ቢያጎብጣት የሚገርም ነው? ጭራሽ! የአሁኑም በወረፋው በልቶና አስበልቶ ተብላልቶ ለሌላ የተራበ ሥጋን ብቻ ሳይሆን አጥንትን ለሚግጥ አሳልፎ ይሰጣታል። ሃገር በዘርና በጎሳ በቋንቋና በሃይማኖት ተከፋፍሎ ሃገር የለም። በቃኝ!

 3. በተጨመላለቀ ፓለቲካ ውስጥ የዕዳ ጣራው ሰማይ መድረሱ አይደንቅም፡፡ በየጊዜው ተረኛ ፓለቲከኞች እንደፈለጉ የአለውን አንጡራ ሃብት እና የውጪ ፋይናንስን ባይቦጠቡጡት ይህቺ አገር የት በደረሰች ነበር፡፡ አሁንም ቀጣይ ዕዳ ለትውልዱ ላለማብዛት መንግስት እንዴት ዕዳውን መቀነስ እንደሚቻል በጣም መስራት አለበት፡፡ ለምሳሌ ያህል፣
  1. የውጪ ፖሊሲን ጥሩ በማድረግ ብድርን በስጦታ እና ምህረት /Concessional & grant loan/ መልክ እንዲሆን መጣር፣ ወለድ እንዲቀነስ ማድረግ በሚያዋጣ መልኩ፣
  2. በአገሪቷ ውስጥ የሚባክኑ አላስፈላጊ ወጪዎችን በመቀነስ ወደ ምርታማነት መቀየር በተረኛነት መንፈስ አሁንም ሃብት እንዳይባክን እና እንዳይዘረፍ በቂ መሰረት መጣል ፣
  3. መጪው አገራዊ ምርጫም ገንዘብ እና ሃብት ያለአግባ እንዳይባክንበት መጠንቀቅ፣
  4. በቀድሞ ጊዜ የተዘረፉ የህዝብ ሃብት፣ ተዘርፎ በውጪ አገር ባንኮች የሚገኙ ሃብት /Cash & fixed asset/ ወደ አገር ሃብት እንዲዞር በማድረግ ወይም በቀጥታ ሃብቱ ካለበት አገር መንግስት ጋር በመነጋገር በዛው የዕዳ መክፈያ እንዲሆን ማዞር፣
  5. በአገር ውስጥ ተዘርፎ የሚገኝ ሃብት በሙሉ በአግባቡ ተጣርቶ ወደ ህዝብ ሃብት ማዞር፡፡ ፀረ- ሙስና ኮምሽን ተብሎ በትህነግ ጊዜ ተቋቋሙ ለማስመሰል እና የተቀነባበረ ዝርፊያ ለማድረግ መጠቀሚያ መሆን ቀርቶ ኮምሽን እስከአሁን የሄደበትን አቅጣጫ ቀይሮ ለአገር እንዲሰራ ማድረግ፣
  6. በአገር ውስጥ ያሉ ትልልቅ ባለሃብቶች በተመረጡ የልማት ስራዎች ላይ ብቻ እንዲሳተፉ ማድረግ፣ አስገዳጅ በሆኑ ዘርፎች ላይ ብቻ ለነሱም በቂ ከለላ መስጠት፣ ማበረታቻ እንዲያኙ ማድረግ፣ ጠንካራ ፖሊሲ መዘርጋት ተጠያቂንት ያለው፡፡ ባለሃብቶቹም ገንዘቡን ከሚረጩት እና የብዙ ሚሊየን መኪና በመያዝ ለእይታ እና ጉራ ከሚየባክኑት ኢንቨስመንት ላይ ቢያውሉት፡፡
  7. ከብድር/ባንኮች/፣ ፋይናንስ፣ ኢንቨስትመንት፣ ንግድ ፈቃድ/ንግድ ሚኒስቴር/፣ ክፍለ ከተማ/መሬት አስተዳደር/ … ወዘተ ያለውን አሰራር በደንብ መፈተሸ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ስራዎች ፈትሾ በደንብ ማስቀረት ያስፈልጋል፡፡ እንደውም ሙስና መስጠት እና መቀበል ሞት ፍርድ ሊያሰጥ ይገባል፡፡ አሊዚያ ይህች አገር የትም አትደርስም፡፡ፀረ-ሙስና ኮምሽን ይህን ፍርድ ለፓርላማ በማስቀረብ ሊያጸድቅ ይገባል እውነት ለአገር ከታሰበ፡፡ በተጠቀሱት በ/ቤቶች እኮ ስንት ጉድ ነው ያለው፡፡

  8. የውጪ ኢንቨስትመንት/FDI/ ላይ በደንብ መስራት፡፡ አገሪቷን በሁሉም አካባቢ በደንብ ሰላም ለማድረግ በመጣር በ Mechanized agriculture, Manufacturing & Truism ላይ በደንብ መስራት፣

  9. በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የተቋቋመ የኢኮኖሚ ሙህራን ቦርድ በዚህ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ህዝብ በግልፅ እንዲያውቅ በማድረግ መስራት አለበት፡፡ ለቀጣይ ትውልድ ሌላ ተጨማሪ የብድር ዕዳ ለላማስተላለፍ በደንብ ሊሰሩ ይገባል፡፡

  10. መንግስትም እራሱን በደንብ መፈተሸ አለበት፡፡

 4. My fellow “Ethiopian”, the headline for your “news” story is so ridiculously misleading and intentionally divisive. It is extremely shameful to knowingly try to create and spread click-bait. Anyone with logic and reason could assume such a misleading action by a news media site is calculated and meant to sow discord and doubt into the work of our acting Prime Minister and his government. All of the debt that Ethiopia owes is money borrowed by TLPF from other countries but stolen for themselves and their allied ethnic groups. You need to do serious fact checks from reliable, unbiased sources instead of getting your information from people who are trying to cover up their past serious crimes of humanity by raising sudden fake concerns for the Ethiopian people. Those who support Abiye are not blind worshippers. If tomorrow, he says or does something wrong we will not hesitate to speak up and get him to correct his course. No leaders or politicians should be worshipped. So far, he has only done his very best to unite the people of Ethiopia and repair the decades of damage caused by the TPLF’s long abuse of power while simultaneously facing intense criticism and opposition from the groups who support the TPLF. You should be greatly ashamed of your actions with this headline. Please know that Ethiopia will still remain on the path to freedom, unity, and prosperity despite your clear attempts to derail us from that goal.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.