ዳንኤል በቀለና ብርቱካን ሚደቅሳ? ታዬ ድንደስ? – ሰርፀ ደስታ

birtuሰሞኑን በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የጥናት መረጃውን ለሕዝብ ይፋ በማድረጉ ብዙ ሰው እየተቀባበለ ጉድ ሲል አይቻለሁ፡፡ ይሄ ግን ለእኔ ብዙ አዲስ አደለም፡፡ እኔ የኦሮሞ የጥላቻና የዘር ፖለቲካ ከዚህም የከፋ አደጋ ይዞ እንደሚመጣ መናገር ከጀመርኩ ቆይቻለሁ፡፡ በጣም አደገኛ የሆነ መርዝ እንዳለ ደግሞ ያወኩት በስማ በለው ሳይሆን በራሴ በሕይወቴ አልፌበት ነው፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ግን ነገሮች ይበልጥ ያስደነገጡኝ አሁን ለውጥ ተብሎ ወያኔ ወደመቀሌ ስትሄድ የመንግስትን መዋቅር አብይ አህመድና ቡድኑ በኦሮሞ ከተቆጣጠረ በኋላ እንደ ትግሬው ወያኔ ትንሽ እንኳን መታገስ አልቻሉም የመጀመሪያ ዓላማቸው አማራውን ሌላውንም መጤ ከኦሮሚያ በማጽዳት ያለውን ሐብት ሁሉ ዘርፈን እንበለጽጋለን የሚል ትልቅ ዘመቻ ሲደረግ በማስተዋሌ ነው፡፡ በኦሮሞ የዛሬው ምሁር በሉት ፖለቲከኛ አስተሳሰብ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ ወሎን ወደራሱ ካመጣ ሁሉም ነገር በእጁ ያለ ሆኖ የሚሰማው በጣም በሚያሳዝን ደረጃ የወረደ እይታ ያለው ነው፡፡ እኔ በሕዝብ ላይ እንደ ሕዝብ አንዳች ነገር አልፈርድም፡፡ የኦሮሞ ገበሬማ ዛሬም የእነሱ መሣሪያ እየሆነ በመከራ ነው ያለው፡፡ ዛሬም ከመሬት እየተነቀለ ነው፡፡ ይሄ እርግማን የተመቻቸው ፊደልን ቆጠርን የሚሎ ኦሮሞ አሁን በአብዛኛው ሳይሆን አይቀርም እኛ ምን ጉድ ናቸው የምንለውን አስተሳሰባቸውን እነሱ በጣም ተዋህዷቸው እንደ ትክክለኛ ነገር እያሰቡት ነው፡፡

በሰሞኑ በእነ ዳንኤል የምርመራ ውጤት የኦሮሞ የጤና ባሙያዎች ለተጎዱ ሰዎች በማንነታቸው ምክነያት ሕክምና መስጠት እምቢ እንዳሉ  የጸጥታ አካላቱ ደግሞ የተጎዱት ሕክምና እንዳያገኙ ሲያደርጉ እንደነበር አንብበናል፡፡ እንግዲህ በየትኛውም የጠላት ጦርነት እንኳን በሕይወት የያዝከውን ጠላት እንደ ሰብዓዊ ፍጡርነትህ ሕክምና ታደርግለታለህ፡፡ እንግዲህ ተጎድቶ አላክምም ያለ ምን አልባትም በሕክመና ሆን ብሎ ሊገድልህም ይችላል፡፡ ይሄ በግልጽ ሊተባበል የማይቻል ዛሬ ላይ ብዙ የኦሮሞን ምሁርና ወጣቱን የተለከፈው ልክፍት ነው፡፡

በጣም ጓደኛ ነን ብዬ ሳምናቸው የነበሩ ዛሬ ዘመኑ የኦሮሞ ነው በሚል በምን ያህል አስፈሪ ሁኔታ እንደተቀየሩ እኔ አውቃለሁ፡፡ ነገሩ ዛሬ የተቀየሩ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ውስጣቸው ደብቀውት የነበረ የጥላቻ ዘረኝነትና የበታችነት ስሜት መሆኑን የገባኝ አሁን ነው፡፡ ጓደኛ ስል ዝም ብሎ ተራ ጓደኝነት አይምሰላችሁ፡፡ እኔን የሚመስለኝ በጣም የምንተማመን ነበር፡፡ ስለዚህ ጉዳይ እንድ ቀን ሙሉውን እውነት አስነብባችሁ ይሆናል፡፡  እኔ የኦሮሞ ኦፒዲበሉት ኦነግ ያው ናቸው ዘረኝነታቸውን አሳምሬ አውቃሉ፡፡ እኔ በማንነቴ ሊጎዱኝ ብዙዎች ሞክረዋል፡፡ ጓደኞቼ የሆኑት ግን በዚህ ደረጃ ናቸው ብዬ ገምቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ በኦሮሞነት አብሮ ከሚጋጋው እኔ በቅንነት ጓደኛቸውም እንደሆንኩ ልባቸው ያውቃል፡፡  እንደማንኛውም ሰው ለጓደኛ መሆኔ ነበር እንጂ ዋጋ ልቀበልበት ያደረኩት ነገር የለም፡፡ አንዳንዶቹም በሕወታቸው ዛሬ ለመኖር ምክነያት የሆንኩላቸው አሉ፡፡  ይገርመኛል፡፡  ዛሬ እንደዛ አደለንም፡፡ አውሬነታቸው ዛሬ ጊዜው የኦሮሞ መስሏቸው ድንገት ባርቆባቸዋል፡፡ ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ ከትግሬ ወያኔዎችም እንዲሁ ያለ ነገር ገጥሞኛል፡፡ የእነሱ ግን በእነዚህ ደረጃ የከፋ አደለም፡፡ ሕሊና መዳኘት ካቆመ ሐይማኖት ብትል ባሕል ምንድናው? ምንም? አዝናለሁ፡፡

ዳንኤል በቀለ ማንነቱ አያስፈልገኝም በፊት ሲናገር እንደነበረው ዛሬም ያንኑ ተናገረ እንጂ፡፡ አንዳንዶች ዳንኤል ዘር ማጥፋት አላለም ሲሉም ትንሽ ሊወቅሱ ሞክረዋል፡፡ እንግዲህ ዘር ማጥፋት ነው አደለም የሚለውን ራስህ ተወጣው ሁሉን ነገር ዳንኤል እንዲሰራልህ አትፈልግ፡፡ በምርመራ ሪፖርቱ የተዘረዘሩት እኮ ግልጽ ናቸው፡፡ ዘር ማጥፋት እንደሆኑና እንዳልሆኑ በሕግ ፊት ማቅረብ እንግዲህ የሁሉም ድርሻ ነው፡፡ ይሄ የምርመራ ውጤት ከምርመራው ጀምሩ ከፍተኛ ፈተና እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በዚህም ሪፖርት ለመካተት እጅግ አስከፊ የሆኑ ጎዳዮችም ወደኋላ እንደተደረጉ እንገምታለን፡፡ ምክነያቱም ሁሉ ነገር ለሕዝብ ይፋ አይደረግምና፡፡ እጅግ ዘግናኝ ነውና፡፡

እንግዲህ ሁላችንም እናስተውል፡፡ ዛሬ ነገሮችን እየተለማመድን መጥተን በጅምላ መገደል ሳይሆን በግፍ የተገደሉንም በግፍ መገደላቸው ሳያንስ እጅግ አሳቃቂ በሆነ ሁኔታ በጅምላ ሲቀበሩ አይተናል፡፡ ገዳዮች ባለስልጣን በሆኑባት አገር ይሄ ምንም ችግ የለውም፡፡ ዜጎቼ የሚላቸው መንግስት ቢኖር ሲጀምር እንዲህ ባለ አረመኔያዊ ሁኔታ አይገደሉም ሲቀጥል ድንገት እንኳን ቢሆን አስከሬናቸው እንደየእምነታቸው፣ ባሕላቸው ከዛም በላይ አሳቃቂ ሁኔታ በመገደላቸው ጭምር በልዩ ክብር ባረፈ ነበር፡፡ ከወያኔ የተቀዱት የዛሬዎቹ ባለስልጣናት እንግዲህ የመንግስትን ስልጣን በያዙበት ምን እንጠብቃለን? ግፍ በኢትዮጵያ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፡፡ እርግጥ ነው ከበደኖ ጀምሮ ብዙዎች የማያውቁት አረመኔነት በስንት ቦታ ተፈጽሟል፡፡ የሆነ ሆኖ የዛሬ 6 ዓመት ገደማ በሊቢያ በረሀ ልጆቻችን አንገታቸው በሰይፍ ተቀልተው በሞቱ ጊዜ እጅግ ምርር ብሎን አዝነን ነበር፡፡ ከዛ በኋላ በደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች በወገኖቻችን ላይ ሲደርሱ የነበረው ከነነፍሳቸው በእሳት ማቃጠልን ጨምሮ አይተን ምን አረመኔዎች ናቸው ብለን ነበር፡፡ ዛሬ በይፋ ሊያውም ባለስልጣናቱ የሚመሩት ከሊቢያውም ከደቡብ አፍሪካውም የከፋ አረመኔነት በአገራችን እየሆነ ነው፡፡ በየፌስቡኩና ዩቲውቡም የሰውን አስከሬንና አሳቃቂ የሆኑ ምስሎችና ትዕይንቶችን መለጠፍ ምናችንም ሆኖ እየተሰማን አደለም፡፡ አረመኔነትን መለማመድ እንዲህ ነው፡፡ አዝናለሁ

መቼም ከአሁን በኋላ ኦሮሞ ሆኖ በስልጣን ላይ ያለ ጤነኛ አስተሳሰብ አለ ብለን ላናምን በተግባር በሚደረጉ ነገሮች አይተናል፡፡ ኢትዮጵያውያንን ለማታለለ ኢትዮጵያዊ መስሎ የመጣው ጠ/ሚኒስቴር ተብዬው ዋና ኢላማው ከኢትዮጵያዊነት እስካሁንም በሞታቸው እንኳን  ያላፈገፈጉት አማራና ኦርቶዶክስ እንደሆኑ በተግባር አሳይቶናል፡፡ ሌላ ሌላውን ትተን አሁን ባለው የአብይ አህመድ የስልጣን ሰንሰለት ስንት ኦርቶዶክስ አለ? ስንትስ አማራ አለ? አማራ ስል አማርኛ ተናጋሪ ማለቴ አደለም፡፡ ብዙዎች አማርኛ አፍመፍቻቸው የሆነ አማራ ጠሎች አሉና፡፡  ባፈው አብይ አህመድ ወደመተከል አቅንቶ የነበረው ጉሙዝ አማራንና ሌሎች እነሱ ቀዮች የሚሏቸውን ለማረድ ምክነያታዊነታቸውን በሚዲያ ሊያቀርብልን ነበር፡፡ በተለይም የችግሩ ዋና መሠረት አማሮች እንጂ ጉሙዞች አደሉም የሚለውን አስተሳሰብ በሰፊው ለማናፈስ፡፡ ለዛም ነበር በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከተውና በቅርበትም የሚገኘው የአማራ መገናኛ ብዙሐን እያለ ኦቢኤንን ይዞ የሄደው፡፡  ይህ ግለሰብ (አብይ) እስከዛሬ የነበረውን ተቀባይነት እንደ ከለለ ተጠቅሞ የመንግስትን መዋቅር ከኦርቶዶክሳውያንና ከአማሮች ሲያጸዳ እንደነበር እናውቃለን፡፡ ጴንጤ ከሆነ በተለይ ደግሞ ጴንጤነትን ከኦሮሞ ያቀናጀ ከሆነ የትኛውም ስልጣን ላይ ሲያስቀምጥ አይተናል፡፡ ዛሬ የውጭ ጉዳይ አአማካሪ ያደረገው ሌንጮ ባቲ ኦነግ የሆነ በዜግነቱ አሜሪካዊም እንደነበር እናውቃለን፡፡ በሎስ አንጅለስ የኮነሲላ ኃላፊ አድርጎት የነበረውም ብርሐነ መስቀል መስፈርቱ ይሄው ነበር፡፡ ሌላው አስቂኝ ነገር የባህርዳር ከንቲባ ተደርጎ የነበረው ግለሰብ ከእነአካቴውም ባህርዳር ላይ የማይኖር ጴንጤ ብቻ ስለሆነ ከንቲባነቱ የተሰጠው አዲስ አበባ ቆጭ ብሎ ባሕርዳርን ሲዘርፍ ከርሞ በመጨረሻ አዲስ አበባም ስላልተመቸው ቶሮንቶ ካናዳ የባህርዳር ከንቲባ ሆኖ ከርሞ አይተናል፡፡ እነ ዳንኤል ክብረት ሲጀምር ምን ስልጣን እንዳለው ባይገባኝም ዋናው ከኦርቶዶክሶች ጥያቄ እንዳይነሳ ማደናገሪያ ሆኖ የተቀመጠ እንደሆነ አያለሁ፡፡

ሑሉም ሰው ሊያስተውል የሚገባው በተለይ ኦርቶደክስና አማራ የሆነ ሕዝብ በቂ ውክልና ነው እንዲኖረው ሊያስብ ግድ ይለዋል እጂ በዘረፋና በነፍስግድያ በአሳዳጊያቸው እዚህ በደረሱ ጴንጤ ባለስልጣናት ተወክሎ ፍትህና ሠላም አገኛለሁ ብሎ እንዳያሰብ፡፡ የችግሩ ቁልፍ እዚህ ጋር ነው ያለው፡፡ ሌላ ቀርቶ በሰራዊቱም ውስጥ ትልቅ ክፍተት እየተፈጠረ ያለው ከዚህ የመነጭ ነው፡፡ በነገራች ላይ ኦሮሞም ቢሖን ኦርቶዶክስ ከሆነ ሲጀምር ከነፍጠኛ ባልተናነሰ ነው የሚታየው ወደ ስልጣን እንዲመጣ አይፈለግም፡፡

ከላይ እነዳንኤልን አንስቼአለሁ፡፡ ዳንኤልና ብርቱካን በቀደመው የወያኔ ዘመን የግፍ ቀማሾች መሆናቸው ያመሳስላቸዋል፡፡ በዛን ዘመን ሁለቱንም ለሕሊናቸው የኖሩ ሆነው በሕዝብ ዘንድ ትልቅ ከበሬታ አቅኝተዋል፡፡ ዳንኤል ለዛ ለነበረው ሕሊና ዛሬም የተገዛ ይመስላል፡፡ ብርቱካንስ? እንደሚገባኝ ብርቱካን ወደ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት ከመጣች ቡርዱን በማደራጀትና የምርጫ ደንቦችንም በማሻሻል ቆይታለች፡፡ ለመሆኑ ግን አሁን ባለው ሕገ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ መካሄድ አለበት? የሚለው የእኔ ትልቁ ጥያቄ ነው፡፡ ለመሆኑ ክልሎች እየተጠቀሙበት ያለው ሕገ-መንግስት የሚባለው የመምረጥና መመረጥ መብቱን የሚሰጠው ለዜጎች ነው ወይስ ክልሉ ለተሰጠው ብሔረሰብ፡፡ በግልጽ ኦሮሚያ የኦሮሞ እንጂ የአማራ ወይም የትግሬ ወይም የሱማሌ አደለም፡፡  በክልሉም መምረጥም መመረጥም የሚችሉት ኦሮሞ ብቻ ነው፡፡  የሕግ አዋቂዋ ብርቱካን ይሄን ወዴት አደገርጋው ይሆን ዛሬ ከብልጽግና ቡድን ጋር ወግና ምርጫ መደረግ አለበት የምትለው፡፡ እሷንም ኦሮሞነት ጠልፏት ወይስ ሌላ? ከአማራ ክልል ሕገ-መንግስት በቀር ሁሉም ክልሎች የዜጎችን መብት አይፈቅዱም፡፡ በግልጽ፡፡ አብይና ቡድኑ ይሄንን ነው ቀባብቶ ሊያልፈው የሚፈልገው፡፡ ለመሆኑ ወደፊትም ለአዳማ በኦሮሞነት ከወለጋና አርሲ እየመጣ ከንቲባ ሊሆን ነው? ለነገሩ ለአዲስ አበባም እንደዛው ነው፡፡ ምርጫ ይደረግ ከተባለ እንደግዲህ እንያችኋ፡፡ አሁም አማራና አጋው በሞላበት በመተከል ጉሙዝ ሊያስተዳደር ነው? ወይስ አዋሳን ሲዳማ ነኝ በሚል የእኔ ነው እያለ ሊፈነጭ፡፡  እስኪ ወላይታና ሲዳማ አዋሳ ላይ ለሕዝብ ነጻ ተደርገው ይወዳደሩ፡፡ ማን ይበልጥ ድምጽ ያገኛል? ሁሉም ይጠንቀቅ፡፡ አሁንም ያለንበት ሁኔታው ራሱ አደገኛ ነው፡፡

ሌላው የኦሮሞ ባለስልጣናት እነ ታዬ ደንደአ የባሰባቸው ይመስላል፡፡ ጥሩ አደለም፡፡ ባለፈው አብንን ከኦነግ ጋር የሚሰራ እነ አምባቸውን ያስገደለ ምናምን የሚል የአብይ የቁማር መልዕክት መሠለኝ ሲዘራ ነበር፡፡ መቼም የተላከ ምን ማለት ነው ብሎ እንኳን ማሰብ አልቻለም፡፡ ለመሆኑ ኦነጉ ታዬ ደንደአ ነው ወይ ክርስቲያን ወይስ በለጠ፡፡ ለምን በግልጽ ኦነግ እንደሆነ የሚታወቀው ታዬ አብንን ከኦነግ ጋር ያበረ ሲል …. ለነገሩ እስክንድርንም እኮ ከእነጀዋር ጋር እየተናበቡ ስትል የዛሬዋ የአብይ የአዲስ አበባ ከንቲባ ተብዬ ስትናገር ነበር፡፡ በዚህም እስክንድር ዛሬ እስር ቤት ነው፡፡ አንድ ቀን ግን እሷ ያለችበትን ቦታ መያዙ አይቀርም፡፡ የእነአብይ ሴራ የት እንደሚደርስ እናያለን፡፡ ብልጽግናን ከአማራ ክልል የሚያስወግድ አብን እንደሆነ አሁን ፈርተዋል፡፡ ለዛ ነው እነታዬ ደንደአ እንዲህ የሚያስለፈልፋቸው፡፡ ባልደራስ የዛሬዎቹን የአዲስ አበባ ዘራፊ ወሮበሎች በሕዝብ ምርጫ ከሆነ ጠራርጎ እንደሚያስወጣቸው ግልፅ ነው፡፡ አብይ በሻሻ ሄዶ ሊመረጥ ይችላል ሆኖም ተመልሶ አሁን ያለበት ቦታ አይመጣም ነበር፡፡ እውነተኛ ምርጫ ቢካሄድ፡፡  ታዬ ዛሬ አስቂኝ የሚመስል ነገር ጽፎ አነበብኩ አብይን የገለጸበት በተግባር የሸገር ፓርኮችን በመስራት ያሳየን መሪ ሲል ነበር፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች አገር እየመሩ ምን ሊጠበቅ እንደሚችል አይገባኝም፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩ ራሱ የኢትዮጵያ ልክ ሲለው ነበር የከተማ መናፈሻን ሥራ፡፡ እንደው ለመሆኑ እንዴት እንዴት ነው የሚያስቡት እነዚህ ሰዎች? የከተማ መናፈሻ መስራት የጠ/ሚኒስቴሩ ወይስ የከተማው መዘጋጃ፡፡ ሲጀምር ተሰሩ የተባሉት መናፈሻዎች በክፍለ ከተማ ሊሰሩ  የሚችሉ ተራ ነገሮች እንጂ የከተማውም ልዩ ሥራ አደሉም፡፡ አንዳንዴ ለቱርስት ለመሳብ ይሉሀል፡፡ ችግሩ ሁሉም የመጡት ከወያኔ ሥሪት እንጂ እውቅት የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም፡፡ ቱሪስት ገንዘቡን አውጥቶ የአዲስ አበባን መናፈሻ ለማየት ከመጣ እብድ መሆን አለበት፡፡ ቱሪስቶች ኢትዮጵያ የሚመጡት ታሪካዊ ቦታዎችንና የተፈጥሮ ቦታዎችን ለመጎብኘት እንጂ መናፈሻ ለመጎብኘት አደለም፡፡

መናፈሻ አይጎበኝም አላልኩም በአለማችን የሚጎበኙ ታላላቅ የአትክልት ግቢዎች(ጋርደኖች አሉ)፡፡ ለምሳሌ በ ኒዘር ላንድ የሚገኘው ከውከንሆፍ ቱሊፕ በመባል የሚታወቅው አበባ ቦታ በሚከፈትበት አጭር አንድ ወር ገደማ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ1.5 ሚሊየን ሕዝብ በላይ ይጎበኘዋል፡፡ ይሄን ቦታ እኔም ለመጎብኘት እድሉን አግኝቻለሁ፡፡ ድንቅ ነው፡፡ ይልቁንስ ዛሬ የቁማር አንድ አካል የሆነው ጣናን ከእምቦች ባሻገር እንደ ከውክነሆፍ ልዩ ጋርደን በማደረግ ትልቅ የቱርስት መዳረሻና የአካባቢውንም ሕይወት በሚቀይር መልኩ ለመስራት የሚያስችል የንድፈ ሐሳብ ነበረኝ፡፡  ይሄን ሐሰብ የደረሳቸው ባለሥልጣናት አሉ፡፡ ሆኖም ያው እንደ አዲስ አበባው የከተማ ወንዞች ፕሮጀክት ሊያበለሹት እንደሚችሉ እገምታለሁ፡፡ በነገራችን ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ወንዞችን ማጽዳት ንድፈ ሐሳብ ከ8 ዓመት በፊት አዘጋጅቼ የከተማው የሚመለከታቸውን ለማነጋገር ሞክሬ ነበር፡፡ ማን የሰማሀል? ታዬ ሆይ የምትጽፈውን የሚያነቡት ምንም የማያቀው እናንተ እንደ እቃ የምትነግዱበት የኢትዮጵያ ደሀ ሕዝብ ሳይሆን ብዙ ልምድና እውቀት ያላቸውም ባለሙያዎች እንደሆኑ አስተውል፡፡ አብይ አህመድ የአረንጓዴ አሻራ የሚለውም የእሱ ሥራ አልነበረም፡፡ ሥንት ባለሙያዎች ባሉበት፡፡ በነገራችን ላይ ለአንባቢዎቼ እኔ ከምንም ተነስቼ አላወራም፡፡ በተግባር ለአገሬ የቻልኩትን ሁሉ ሞክሬ ነው፡፡ ችግኝ መትከል ከተባለ እኔ ከ1 ሚሊየን ያላነሰ የዛፍ ችግኝ ከምንም በመነሳት አፍልቼ ለተከላ አከፋፍያለሁ፡፡ የአቋቋምኳቸው የዛፍ ችግኝ ጣቢያዎች ቀጥለው ብዙ ሚሊየን አፍልተው ይሆናል፡፡  አብይ አህመድና እንደ ግርማ አመንቴ ያሉ ኦነግ ባለሙያ ነን የሚሉ ዛሬ ከፍተኛ ወጪ ከመንግስት ካዝና እያወጡ እንደሚበትኑትና በቢሊየን ተክለናል እንደሚሉት ሳይሆን የማወራው ስለሙያዊ ክህሎት ነው፡፡ በየዓመቱ እንደ በቆሎ ማሳ ዛፍ የሚተከልበት መሬት ሪፖርት መደረጉ ሳያንስ ገንዘብ ወጥቶባቸው የተፈሉ ችግኞች እንኳን በአግባቡ እንደየ ባሕሪያቸው በሚመቸው ቦታ ሆነው ለውጤት እንዳይሆኑ እየተደረገ ነው ያለው እውነታ፡፡  ለእነታዬ እንግዲህ እንዲህ ያለቦታው ገብቶ መቦጫረቁ ሳያንስ የሰዎችን ሥራ እያበላሸ የተሰጠውን ቦታ ላይ መስራት የነበረበትን ሥራ አንዳች ሳይሰራ እየቆመረ ያለው አብይ ነው መሪ፡፡ መከላከያውን ሠራም ይለናል፡፡ መከላከያው ቢሰራ ነው ከውስጥ በተነሱ ወንበዶዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ጦርነት የተከፈተው? ይሄ ነው ከብሔር ጽድቷል እየተባልን ሲነገረን የነበረው? ለማንኛውም መከላከያው ውስጥ ከዛም በከፋ ኦሮሞ-ኦነጋውያንም ከወያኔዎች ጋር እንደነበሩ ብንገምት ስህተት አይሆንብንም፡፡ በተለይ ተመርዞ መጣ የተባለው የሰሜን እዝ አዛዥ ነበር የተባለው አነጋጋሪ ነው፡፡ ሌሎችም እንዲሁ፡፡ ታዬ ደንደአ ተረጋጋና የራስህን ኦነጋዊነት ሴራህን ብታስተውል ጥሩ ነው፡፡ በአጠቃላይ እየሆነ ያለው የሚበጃችሁ አይመስለኝም፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

2 Comments

  1. ግሩም ነው፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያዙርልን። መንጋቱ አይቀርም፤ ይነጋል። እሥኪነጋ ግን ጨለማው መበርታቱ ያለ ነው። ለማንኛውም ጥሩ ልቦና አለን የምንል በርትተን እንጸልይ።

  2. ጎበዝ ትግሬዎች ኢትዮጵያን ሊወጉ ዋሻ ቆፍረው ምግብም አከማችተው ውስጡ ገቡ በከፈቱት ጦርነት ተሸንፈው ወደ ዋሻው ገቡ። የሌሊቱ ጅብም ሰው በጣም ስለለምደና የቀን ጅቦችን እየበላ ሆዱ ስለሰፋ ምሽጉ ውስጥ ያገኛቸውን የቀን ጅቦች መብላት ጀምሯል። እንዳይጮሁ ውጭ ሁነው ጀነራል አበባውና ጀነራል ባጫ ደበሌ ይጠብቃሉ ዝም እንዳይሉ የሌሊት ጅብ አንዱን ሳይጨርስ ሌላውን እየበላ ነው። ለማዘንም ለመሳቅም የቸገረ ነገር። የዛሬው ኦነግና ምልምሎቹ እጣ ፈንታችሁ ከዚህ የተለይ አይሆንም። ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ ብትችሉ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.