አጭር ነገር ለአንዳንድ ሙስሊም ወዳጆቼ ! – ጣህር መሀመድ

tah( ይህ መልዕክት የተዛባ እይታ ውስጥ ገብተዋል ብየ ላሰብኳቸው ውስን ሰዎች የተላለፈ ነው ብዙሐኑን አይመለከትም። )

በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደት ላይ ታሪካዊው የነጃሽ መስጅድ ጉዳት እንደደረሰበት ተመልክተናል ይሄ እጂግ የሚያሳዝን ነው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በርካቶች ብስጭታችሁን ስትገልፁ ተመልክቻለሁ። እውነት ነው ለእምነቱ ቀናዒ የሆነ ሰው ቀርቶ ማንኛውም ሰው የተከበረው የአላህ ቤት ጉዳት ሲደርስበት ማዘኑ አይቀርም።

በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደት በቀጠለበት ወቅት የአሸባሪው የትህነግ ቡድን አባላት ነገሮችን ለማወሳሰብ እና ስስ የሆነውን የሐይማኖት ጉዳይ መጫዎቻ ካርድ ለማድረግ የሐይማኖት ቦታዎችን ከለላ ለማድረግ እየተጠቀሙባቸው መሆኑን መረጃዎች እየወጡ ስንሰማ ነበር። ይህ ጉዳትም የዚያ ውጤት እንደሆነ አያጠራጥርም።
የእኔ ጥያቄ ?
አካባቢው በከባድ ጦርነት ውስጥ እንደመቆየቱ በመስጅዱ ላይ የደረሰውን ጉዳት ታስቦበት እንደተደረገ ( ታስቦበት ከሆነም ከትህነግ በላይ ሴረኛ የለም ! ) አድርጎ የተለየ ትርጉም መስጠት ተገቢ ነው ወይ ?

እንደ ሀገር በትህነግ ልክ የሌለው እብሪት ወደዚህ አላስፈላጊ የጠብ-መንጃ መፍትሔ ከመግባታችን በፊት ይህ አሸባሪ ቡድን በበርካታ ቦታዎች ለንፁሐን መገደል ተጠያቂ ነው። የሰሜን እዝ ወታደሮችም የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ታዲያ የዛሬው ዘመቻ የመስጅዱ ጉዳት ከሰብዓዊ ፍጥሮች በልጦ ነው ወይ የዛሬው ጩኸት ከፍየሏ በላይ የሆነው ?

በማይካድራ ፣ መተከል ፣ ጉራፈርዳ እንዲሁም በወለጋ ዛሬም ድረስ ያላባራ የንፁሐን አሰቃቂ ግድያ እንደቀጠለ ነው። የእነዚህ ንፁሐን ግድያ የተፈፀመባቸው ምክኒያት አማራ ስለሆኑ ብቻ ነው። ይህ ግልፅ የሆነ የዘር ማጥፋት ነው። ይህንን ኢሰበዓዊ ድርጊት ለምንድን ነው ማውገዝ የተሳነን ?

የአንዲትን ነፍስ በግፍ መገደል አቅልሎ የማይመለከተው እስልምና ውስጥ ሆነን ይህንን ግፍ የማናወግዘው ሰዎች ከመስጅድ ስለማይበልጡ ነው ? ወይስ የወጡበት አካባቢ ጠላት ስለሆነ ?

የምንጨነቀው ሐይማኖት መርጠን ከሆነ እና ሰብዓዊነቱን ከዘነጋነው እንኳን በመተከልም ሆነ በጉራርዳ እንዲሁም አንዳንዶቻችሁ እንደ ኢስላሚክ ስቴት በምትመፃደቁበት ኦሮሚያ ክልል በርካታ ሙስሊም አማራዎች በማንነታቸው ምክኒያት በግፍ ተገድለዋል። የእነዚህ ሰዎች ህይወትስ ከመስጅዱ ነው ወይስ በውስጡ ካሉት መቃብሮች ያነሰው ?

በጥቅሉ የፈረሰው መስጅድ በቀላሉ መታደስ ይችላል፤ ንብረትም ቢሆን ይተካል ! የሟች ነፍስ ግን ተመልሶ አይመጣም ! ሚዛናችን መሳት ግን ተገቢ አይደለም። ከእንዲህ አይነቱ የተዛባ አተያይ ወጥተን ተገቢ የሆነውን መንገድ አላህ ይምራን ስል መልዕክቴን እቋጫለሁ።

መልካም ቀን !

ጣህር

2 Comments

  1. ጣሂር መሀመድ በእንድ ስብሰባ ላይ የሰጠኸዉን ገለጻ አዳመጥሁ ከዚህ በፊት አላዉቅህም ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ እድለኛ ነች አልኩ እነ አህመዲን ጀበል ፤እንደ አቡበከር አይነቶቹ በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈዉ ለግብጽ ረጂም እጂ ሲሆኑና አገር ሲፈለቅቁ ቤተክርስቲያናትን እሳት ለኩሱ ብለዉ ለመንጋዎቻቸዉ በፓልቶክ ክፍሎች እየቀረቡ መመሪያ ሲሰጡ አንተ ደግሞ በላይኛዉ እርከን ቁጭ ብለህ አገር የሚያሻግር ትልቅ ሀሳብ ስታስደምጠን ተመስገን ብለናለ። ኢትዮጵያዊ ክብር ላንተ ይሁን ክብር ያለህ ዜጋ ነህ አገር ከምንም በላይ ነች ለሀገርህ ታማኝ ሁን ወንድማችን። ከየት ፈልገዉ አገኙህ ግን በጣም ደስ ይላል። በነገራችን ላይ አህመዲን ጀበልና አቡበከር በፓልቶክ ለመንጋዎቻቸዉ የሰጡት ኦዲዮ በእጃችን ይገኛል መዋሸት አይችሉም።

  2. ይገርማል እነ አህመዲን ጀበል ስራቸዉ ሁሉ እንዲህ መናኛ ይሁን? እንዲህ ድብልቅልቅ ባለ ጦርነት ዉስጥ ሚሳየሎች መድፎች እየለዩ ይምቱ ነዉ የምትሉን? አረ ሆነ ብላችሁ ሰዉን አታደንቁሩት። ምክንያቱን በደምብ ታዉቁታላችሁ ለቀጣሪዎቻችሁ ለነ ግብጽ ምን ይዘን እንቅረብ ካልሆነ በስተቀር ጦርነት ዉስጥ ለደረሱ ዉድመቶች ተጠያቂዉ ጡርነቱን የጀመረዉ ወገን ከመሆኑም በላይ ከህንጻ በላይ ሰብአዊ ፍጥረት እየተገደለ ስለሆነ ህንጻ ተመታ ብሎ ነገር ማካበድ ለግብጾች ደሞዝ ጨምሩ የማለት ያህል ነዉ። በጣም አሳፋሪ የኢትዮጵያ ጠላቶች ናችሁ የጊዜ ጉዳይ ነዉ ስራችሁ ሁሉ ተመዝግቧል ወይ ግብፃዊ ወይ ኢትዮጵያዊ ትሆናለህ በሁለት ካርድ አትጫወትም። ጣሂር እናመስግናለን ስለ ትክክለኛ ግንዛቤህ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.