እንዘንላቸዉ ወይስ እንፍራቸዉ? – ዶ/ር መኮንን ብሩ

133278757 10208140837955478 5938741845527660513 n
በዚያ ሰሞን ፓርላማ ብቅ ብለዉ ብዙ የተደበቁ ሚስጥሮችን ሲያጫዉቱን በርካቶቻችን ከመገረም አልፈን ለእሳቸዉም ሆነ ለቀድሞዉም ጠቅላይ ሚኒስትር ከልብ ሐዝነን ነበር። የሀገር መሪ የሆነ ሰዉ የቢሮዉ በር እንደ ወንጀለኛ ተቆልፎበት ሲዉል መስማት የማያስገርም ካልሆነ ምን ያስገርም ይሁን? …. ቢሆንም ያ የቁም እስረኛነታቸዉ ጊዜ ታሪክ መሆኑን ከመናገራቸዉም በላይ አሳሪዎቻቸዉን ጁንታ የሚል ስያሜ በመስጠት ለዘመናት በብሶትና ሕልህ ሲንገፈገፍ የነበረዉን የአማራ ሚሊሻ ከጎናቸዉ አሰልፈዉ ጁንታዉን የገባበት ገብተዉ ተበቀሉት። እኛም ደስ አለን። እሳቸዉም ከድል ማግስት ሙሉ የወታደር ልብሳቸዉን ተጎናፅፈዉ ድሉን አበሰሩን። የድል ጀግኖቻችንንም ተረኩልን። ትንታጉን፣ ንስሩን፣ አነፍናፊዉን፣ ሌሎቹንም አስተዋወቁንና እንደ ሀገር ኮራን። ኢትዮጵያም አሸነፈችም ብለን ብዙዎቻችን በሐሴት ተሞላን።
135124189 420244182661230 8696175998632617303 n
ይሁን እንጂ አብዲ ሂሌን ዘብጥያ የከተተዉ ቁርጠኝነታቸዉ፣ ተገፍተዉም ቢሆን ሃያ ሰባት ዓመታት አልከስክሶ የገዛንን ወያኔን በሁለት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ መቃብር ያስገባዉ ብልሃተኝነታቸዉና ጥንካሬያቸዉ አልፎ አልፎ ከእሳቸዉ ሲርቅ ስናይ ግራ መጋባታችን አልቀረም። ይህም በመሆኑ ብዙ ብንበሰጫጭ አልያም እንደ ሕዝብ ብንቆጣ እንደተመሪ የሚያስወቅሰን አይመስለኝም።
ልጁ ተማሪ ቤት ብላ ወጥታ በወንበዴዎች ታፍና ከዓመት በላይ ደብዛዋ የጠፋበት አባት ፍትህ ሲያጣ አይደለም የአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን የእራሱም መኖርን ሊፀፀትበት እንደሚችል ለማወቅ አያስቸግርም።
135001752 420244212661227 8171524645801902708 n
ትናንት ጁንታ ሲል ፈርጆ የሀገር ሉሃላዊነትን ለማስከበር ሲያፋልም በየበረሃዉ የወደቁት የትግራይ ልዩ ኃይል ዜጎቻችን አስክሬን በየበርሃዉ ወድቆ ሳይነሳ ዛሬ ሌላ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማስመረቅን የተረዳ ኢትዮጵያዊ የጠቅላዩ ማንነት ግራ አጋብቶት ቢቆጣ ወይም ስልጣን ይልቀቁ ቢል ለምን ይፈረድበታል? ….
አብዲ ሂሌን አልያም ጁንታዎቹ በጠራራ ፀሐይ 207 ሰዉ አስገድለዉ ቀብረዋል እንዴ ? …. አዎን የወያኔ ግፍ ለከት አልነበረዉም። ቢሆንም ግን እንደ ቤንሻንጉል የሰዉ ልጅ እንደ ቆሻሻ ጉርጓድ ዉስጥ ሲጣል የትም አላሳዩንም። ታዲያ ይህን አሰቃቂ የጅምላ ቀብር ጠቅላዩ አላዩም? ከተመለከቱ ኢትዮጵያዊ ቁጭታቸዉ እና ወኒያቸዉ የት ሄደ?
135345276 420244245994557 7578597690786233587 n
መቼም ይህን ቁጭት ስፅፍ ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነዉ የሚሉኝ ብዙዎች አሉ። ሊሆን ይችላል:: አዎን ለእኔ ቀላልም ነዉ። ግን እሳቸዉስ ለምን የቸገራቸዉን አይነግሩንም? … ስናዉቅ ልናዝንላቸዉ እንችላለን፤ አለዚያ ግን ሁሌም በር ይቆለፍብኝ ነበር የሚለዉ ብሄል ማምለጫ አይሆንም።
ታዬ ደንደኣ አጠገባቸዉ እንደ ጌታቸዉ ረዳ ሲፎክር፤ ሌንጮ ባቲ እንደ አሉላ ሰለሞን ጦርነት ባሕላዊ ጫወታችን ነዉ በሚል መልኩ ሲሽሞኖሞን አልታዘቡስ ወይስ እኛ የማናዉቀዉ ግን ሊነግሩን የማይችሉት ነገር አለ? ….. የኢትዮጵያዊነት ወኔና መቆርቆር ለሁሉም ይሁን። አለበለዚያ ሁሉም የሚያምነዉንና የሚቆረቆርለትን መከተሉ አይቀርም። ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር።
ዶ/ር መኮንን ብሩ

3 Comments

  1. ግሩም ብለሃል መኴ! ይህ ልዝብ ሰይጣን ይህችን ቅድሥት ሀገር ሣያጠፋ ዕረፍት አያገኝም። ግን ግን እግዜሩ ይቀድመዋል! ብዙ የምንጠብቀው ቀድሞ የተነገረ ነገር አለና በሚሆነው ሁሉ አንደናገጥም።

  2. ይሄ ሰዉዬ እድሜ ልኩን ስራ ሰርቶ የማያዉቀ የጠ/ሚኒስተሩ አማካሪ ሲሆን አገር ለመምራት ምን ይባላል? አይ አብይ የዘየድክ መስሎሀል አንተን ነዉ ይዘዉ የሚሰምጡት ታየዋለህ።

  3. ይሄ ሁሉ የኦሮሞ ጦር ምነዉ ትግሬዎች ሲወሩን ልምድ ለማግኘት እንኳን ወደዛ ቢዘምት? ጠላቱ የዉጭ ሳይሆን ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ አማራ ላይ በሁለት ዙር ሲከለከሉ ኦሮሞ 33 አስመረቀ እሰቲ የጭንቅ ቀን ሲመጣ ምን እንደምትሆኑ ያየ ሰዉ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.