በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡተጨማሪ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ

 ጽህፈት ቤቱ ከ760 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርጓል
133211140 10219306985767197 8018897590610452838 n በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡተጨማሪ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ
በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በመገንባት ላይ የሚገኙ ግንባታቸው ከዚህ ቀደም ተጠናቆ ለአገልግሎት ከበቁ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ።
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ፋንታ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የሚያስገነባቸው የትምህርት ተቋማት ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ ከጀመሩት በተጨማሪ የስምንት ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጠናቆ ለርክክብና ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።
ግንባታቸው ተጠናቆ ርክክብ የሚፈጸምባቸው ትምህርት ቤቶች በአፋር ክልል ዱብቲ፣ በጋምቤላ አኝዋክ ዞን፣ በቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ እና መተከል ዞን ፣ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ዞን 02 እና 06 ቀበሌዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ደባርቅ ከተማ እና ዋግኸምራ ዞን ሳህላ ሰለምት ወረዳ የተገነቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
134474047 10219306986007203 3301772688509643769 n በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነቡተጨማሪ ስምንት ትምህርት ቤቶች ለርክክብ ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸግንባታቸው ቀድመው የተጠናቀቁና ርክክባቸው ተፈጽሞ ስራ የጀመሩት አምስት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤ በአማራ ክልል ጎንደር ሎዛ ቀበሌ፣ ደቡብ ወሎ ጦሳ ፈላና ቀበሌ (አልብኮ ወረዳ)፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጭቋላ ቀበለ (ቢሾፍቱ አካባቢ)፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ጃቴ ቀበሌ (ሙከጡሪ አካባቢ) የሚገኙት መሆናቸውንና አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተናገድ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ግንባታቸው እስከ ታህሳስ 30/2013 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቁ አራት ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፤ ትምህርት ቤቶቹም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ሸካ ዞን፣ ጌዲኦ ዞን፣ ደቡብ ኦሞ እና በኦሮሚያ ክልል ሐዊ ጉዲና ወረዳ ሐሮ ቢሊቃ ቀበሌም እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በአዲስ አበባ የተሰራው የሕጻናት ማሳደጊያ፣ በሰበታ ከተማ የሚገኘውን ማየት የተሳናቸው ትምህርት ቤት እና በተለያዩ ክልሎች የተገነቡትን ክፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ገንብቶ ለማጠናቀቅ ጽህፈት ቤቱ እስካሁን 760 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንአስታውቀዋል። ገንዘቡም ከተለያዩ የውጭ አገራት ረጂ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህ ዓመትም 10 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዞ የአምስቱ የግንባታ ቦታ መለየቱን የጠቀሱት አቶ ሙሉቀን፤ የእነዚህ ፕሮጀክቶች ወጪ የሚሸፈነውም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመደመር መጽሀፍ ሽያጭ ያገኙትንና ለጽህፈት ቤቱ ባበረከቱት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል።
አዲስ ዘመን ታህሳስ 21/2013
መሀመድ ሁሴን

1 Comment

  1. የሚያኮራ ተግባር ነው። ይህ መርሃግብር መታገዝ አለበት። ምናልባትም ቀዳማዊት እመቤት ከ ዲያስፖራ ዕርዳታ ብትጠይቅ ለ ጥቂት ትምህርት ቤቶች መሥሪያ ልታገኝ ትችል ይሆናል።
    ትምህርት ቤቶቹ የ ሙያ ትምህርት ቤቶች ቢሆኑ ለ አገራችን እድገት ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል። በተለይ ደግሞ የ ግብርና ዘዴዎች ማስፋፊያ ቢሆኑ ይመረጣል። አድልዎ እንዳይኖርም ትምህርት ቤቶቹ የሚሰሩባቸው ቦታዎች ሎተሪ በ ማውጣት ቢሆን ቅሬታዎችን እና አለመግባባትን ያስወግዳል። ሁሉም ነገር የሚተገበረው በ ሎተሪ ቢሆን በ አገራችን ሰላም ይሰፍናል ብዬ አምናለሁ። ሰላም ለ ህዝባችን።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.