ኢትዮጵያ ወንዝ ታቅፋ የምትጠማ፣ለም መሬት ይዛ የምትራብ – መስከረም አበራ

 49608158 2134351749964417 4962935204172791808 nኢትዮጵያ ወንዝ ታቅፋ የምትጠማ፣ለም መሬት ይዛ የምትራብ ሆና አታበቃም-አዋቂ ሞልቷት እውቀት ያጠራትም ጭምር ነች፨ የእኛ ሃገር እውቀት ይመራት ዘንድ እድሏ አልቀናም፨ አዋቂዎች ዳር ተቀምጠው ለአላዋቂ ከበሮ ይደለቃል፨ ካቢኔው፣ ኮሚቴው ፣ኮሚሽኑ ሁሉ በአላዋቂ ይታጀላል፨ መሾሙ እውቀት የሚሆን የሚመስለው ብዙ ነው፨
አውቆ መሾም አልሆን ካለ ከተሾሙ በሃላ እውቀትን መሻትም ያባት ነው፨ ይህ እንዲሆን ልምድ ከእውቀት ያጣመሩ ሰዎችን ማቅረብ ፣ከእነሱ መስማት ደግ ነው፨
እውቀት ከልምድ ካሰናሰሉ፣ ሊሰሙ ከሚገባቸው ሰዎች አንዱ የሃገር ሰው ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊወርጊስ አንዱ ናቸው፨ በውትድርናው ዘውግ ሻለቃ ሲሆኑ በአሜሪካ ሃገር ከሚገኘው ታዋቂው የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ በህግ የማስተርስ ዲግሪ አላቸው፨በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሶስት መፅሃፍት ፅፈዋል፨ “Red Tears” የሚለው መፅሃፍ እኔ ካነበብኳቸው ምርጥ መፅሃፍቶቼ አንዱ ነው፨ በሃገራዊ እና አህጉራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በእንግሊዝኛ የሚ ፅፏቸው ፖለቲካዊ፣ ጅኦ-ፖለቲካዊ እና የፀጥታ ጉዳዮችን ያጣመሩ ፅሁፎች ብዙ ተምሬያለሁ፨
ሻለቃ ዳዊት የውትድርና እና ጸጥታ ሳይንስ እውቀታቸው ለሃገር ቀርቶ ለአህጉር የሚተርፍ ነው፨ ስለ ሰላም ፀጥታቸው መላ ፍለጋ ሻለቃ ዳዊትን ያላማከረ የአፍሪካ ሃገር የለም፨ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግራ ላጋባው የአፍሪካ ጉዳይ ሻለቃ ዳዊትን በአማካሪነት ይዞ የተጓዘበት አጋጣሚ ብዙ ነው፨ ሃገራቸውን የሚወዱበት ሃያል ፍቅር ልዩ ነው፨ ሁልቀን በዋናነት ሊያስጨንቀን የሚገባው የኢትዮጵያ እንደ ሃገር መቀጠል እንደሆነ አጥብቀው ይናገራሉ፨
ከታላላቆች መስማት የምወድ እኔ በዙከንበርግ ግዛት መስመር ላይ ባየሁዋቸው ቁጥር ወሬ እጀምራለሁ፨ ብዙ እናወራለን፨ ጓደኛን እንደማዋራት ባለ ምቹ ስሜት የተሰማኝን በተሰማኝ ሁኔታ ስናገር በደንብ አድምጠውኝ ግራቀኝ እንዳስተውል የሚያደርገኝን ሃሳብ ያጋሩኛል፨ አሁን ፈጣሪ ብሎ ለቪዥን ኢትዮጵያ የጥናት ወረቀት ሊያቀርቡ በመጡበት በአካል አገኘሁዋቸው፨ ጥናታቸውን ሊያቀርቡ በቆሙበት መድረክ ላይ ሃገራቸው ከረዥም ዘመን በሃላ ስለመመለሳቸው ለመናገር ሲጀምሩ እንባ ቀደማቸው፨ አዳራሹ ውስጥ ያለው ሰው ሴት ወንዱ በእንባ አጀባቸው፨ የሃገር ፍቅሩ አይሎባቸው እንጅ ዝም ብለው የሚያለቅሱ ሰው ሆነው አይመስለኝም፨
49185131 2134351859964406 2573325012538753024 nየሚያለቅሱላት ሃገራቸው ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ ፀጥታዋ በተናጋበት ወቅት ስለሰላሟ መላ እንዲሉ የእሳቸውን እርዳታ የምትሻበት ነው፨ የመንግስት የፀጥታ እና ደህነት ሹመኞች ይህን ትልቅ ሰው አግኝተው ማነጋገር ቢችሉ ጥቅሙ ለሃገር ነው፨ ሻለቃ ዳዊት ቀርቦ የሚጠይቃቸው ቢኖር ለሃገራቸው ነፍሳቸውን ሳይቀር ለመስጠት የማያመነቱ ሰው ናቸው፨
መስከረም አበራ

12 Comments

 1. ስለሻለቃው ፕሮሞሺን መሆኑ ነው? ጭራሽ ከነፎቶ? “ጉድ ሳይታይ የፈረንጅ አዲስ ዓመት አይገባም” አለች ቦኒታ!
  ሻለቃ ዳዊት ስለአቢይ ጉዳይ አንዴ አዳለጣቸው፤ መነሳትም አልቻሉም፤፤ ከዚያ ወዲህም “አባን ከና” የሚላቸው ጠፋ፤፤ ቢቸግራቸው ርዮት ሚዲያ ላይ ቴዲ ስለአቢይ መጥፎ መጥፎውን እንዲያጎሉለት አፋቸው ላይ ቃላት ሲወረውርባቸው “እኔ እንደሱ አላልኩም” እያሉ ቃለ ምልልሱን ጨረሱት፤፤ እንደተጸጸቱ ግልጥ ነበር፤፤ “ከአፍ የወጣ አፋፍ” ሆነ! ከዚያ ጠፉ፤፤ ለካስ መልክታቸው በቲቸር መስከረም በኩል ስለሚተላለፍ ነው፤ እሷ እስካለችው ድረስ “እኔ እንደጲላጦስ ከደሙ ንጹህ ነኝ” ብለው ማለት ነው፡፤አይ ቲቸር መስከረም፤ በይ ተይው!
  ለማንኛውም ሻለቃ ዳዊት ምጡቅ ምጡቃን ለአፍሪካም ለአለምም ለጨረቃም ለጸሃይም የሚተርፉ ሊሆኑ ይችላሉ፤ የሚያውቋት እትዮጵያ ግን ከ40 ዓመት በፊት ትተዋት የሄዱትን ነው፤፤ [ክይቅርታ ጋር] አያስፈልጉም! ጡረታቸውን እያጣጣሙ ቀሪ ዘመናቸውን በንስሃ እና በጸሎት መጨረስ ይሻላቸዋል፤ ካላስ!
  ኮ/ል መግስቱ ስለሻለቃው ምን ነበር ያሉት? አይ ይቅር!

 2. ይድረስ ለመስከረም አበራ – ሳላስበው ረዘመብኝ
  ይልቅ ኢትዮጵያስ ከወንዝ ይልቅ ምሁራንን ነው የተጠማችው ንገረኝ ካልሺኝ። ወንዙንስ በትንሹም ቢሆን እየተቃመስን ነው።

  መስኪ፣ የሻለቃ ዳዊትን ክህሎት አይቼም ነበር የዛሬ ሁለት አመት ለየት አድርጌ ለሻለቃውና ኮለኔል ጎሹ ማመልከቻ የፃፍኩት እዚሁ ሳተናዎቹ ይሁን ዘሀበሻ ቤት። ኢትዮጵያ ተመለሱ ማለትን እንደሰማሁ አኩርፈው ወጡን ወዲያው ደገሙኝ እንጅ ። ይባስ ብለው ጭራሽ ኢትዮጵያን failed state የሚል ጠላት የማይሰራውን መሰሪ ሙዋርት ከነወያኔ ቀድመው ደሰኮሩብን። እጅግ ነው አድናቂዎቻቸውን ልባችንን የሰበሩት። ሰድቦ ለሰዳቢ ይሉሻል ይህ ነው። ለመሆኑ እንደ ሻለቃ ክህሎትና ብቃት እንደምን አገሬ ለ 40 አመታት በወያኔ ማነቆ ስር መሆኑዋን ዘንግተው ልክ አቢይ አህመድ አዘቅት እንደከተታት ነገር በአደባባይ ያዋርዱናል? ዳዊት ሲፅፉና መስከረም አበራ ስትፅፍ ለየቅል ነው። ሰፍ ብሎ አዳማጩ የኢንተርናሽናሉ ኮሚኒቲ በተለይም ጠላቶቻችን እነ ግብፅና ኮልኮሌዎቹዋ በፈገግታ መሆኑ አይጠፋሺም መቼስ። እናም ከባድ ስህተት ሰርተዋል ዳዊት። አቢይ አህመድ የቁም እስረኛ ሆኖ ነው ኢትዮጵያን የታደጋት እንጅ አዘቅት እንድትገባ አላደረጋትም። እሽ ያኔስ የእድሜ ልክ ክህሎታቸው ይህንን ሀቅ እንዲያዩት አላስቻላቸውም ልበል፣ ዛሬስ? ስህተት ሰርቻለሁ ብለው ይቅርታ መጠየቅ ማንን ገደለ? አገር ፍቅር እንደዛ ነው። የሚነዳን የአገር ፍቅር እንጅ የአቢይ ፍቅር ወይም ጥላቻ መሆን የለበትም ባይ ነኝ። የሻለቃው ኮለምቢያ መማር ሰበር አድርጎ ይህን ካላስደረጋቸው መማራቸው ለምኑ ነው? ለኔ ጀግናዎቹ ምናልባት ኮሎምቢያ መሄዳቸውን ባላጣራም እነ ግስላው ባጫ ደበሌና ሳተናው አበባው ታደሠ ናቸው። ለምን? ተገፍተው ፣ እንደኮሲ ተጥለው ከነበረበት በአገር ፍቅር ቁጭት ዘለው ገብተው ወያኔን መቅ ስለከተቱልን። አንቺም ቁጭትሽን፣ ወኔሽን፣ አገርፍቅርሽ እንደተጠበቀ ሆኖ የአቢይን አበሳ ታበዢዋለሽ። ምን ያድርግ ብቻውን ይህ ሰውዬ? “እርቃኑን” እኮ ነው ያለው ። ደግሞስ ምሁር ተብዬው ሁላ ለምንድነው ጥሪ የሚፈልገው ቅንነቱ ካለ? ለምን አገር ገንቢ የሆኑ መጣጥፎችን ስው አናጋሪ ወይም ወደ መንግስት አቅራቢ እንኩዋ ቢጠፋ አየር ላይ ለምን አይለቀቅም ልክ ይህን የሻለቃን ምስክርነት እንደሰጠሺው? ለምን መሰለሽ ባብላጫው መሰሪነት ስለሚነዳን ብቻ ነው። እኔ እንኩዋ እንዳቅሚቲ “የሀገርና ወገን አድን ጥሪ—–” እያልኩ የምለፋው ቢሰሙም ባይሰሙም ለህሊናዬ መልካም የመሰለኝን በመተንፈስ እወጣዋለሁ። እናም እስቲ ይሰሙሽ እንደሆነ እንዲህ በይልኝ ሻለቃን። ለአንቺም ፈጣሪ ቅንነቱን ይስጥሽ።

  ሻለቃ ዳዊት ሆይ!

  አቢይ አህመድ ባለፈው ፓርላማው ላይ እንዳስረዳን ያለፉትን ፫ አመታት በስውር የወያኔ ካቴና በእጁና እግሩ እንደጠለቀ ብዙ ብቃት ያለው ውጤት አላሳየም? የ ፫ ሳምንታቱ ወታደራዊ ክህሎትና አመራር አላስደመሞትም? ኢትዮጵያን ይህ ሰው እየቀበረ ነው ወይስ ትንሣኤዋን ባይናችን በብሌኑ ነፍሳችን እያለች ሌላው ቢቀር ጭላንጭሉን እያሳየን ነው? እውነት ህይወቱን ገብሮ ከአማራውና ዖሮሞው ፅንፈኛ ሌት ተቀን እየተዋጋ ያለን ቆፍጣና ወታደር አማራጠል አይነት ጥላሸት መቀባት በሰውና ፈጣሪስ ዘንድ አያስወቅስም? በበኩሌ እኔ አንድ ተራ የጥንት አድናቂ ዜጋ በርስዎ አዝኛለሁ። ምንም ማለት አይደለም፣ ግን እውነት ኢትዮጵያን ከልብ የሚወዱ ከሆነ ስህተት መስራቶን በአደባባይ ይቀበሉ። በአፍሪካና አለም ጉዳይ የዋጣሎት ገምጋሚና አማካሪ ኖት። ትክክል ነው። በኢትዮጵያችን ጉዳይ ግን ባለፈው አመት ይሁን ሁለት “ያበቃላት አገር” ብለው ከፃፉ በሁዋላ ነው የርስዎ ነገር ያበቃልኝ። ዛሬ እኮ ኢትዮጵያን በቁም ከቀበሩ መንጋጋ በ አንድ ቆፍጣና አቢይ አመራር ነው እያንሰራራን ያለው። እልቂት አለ? አሳምሮ አለ። ገና ፈንጅውን በለቀምን ቁጥር እነዛ ሞገደኞች የቀበሩልን የመሬት ክልል ሰፊ ስለሆነ በረገጥን ቁጥር ይኖራል። አረጋገጣችንን እየተጠነቀቅን ከሆነ ፍንዳታው ይከስምና እልቂቱም ይቀንሳል። ይህ ቆፍጣና አቢይ ግን የሁላችንንም እርዳታ ይፈልጋል እንጅ ለትችትማ የነግብፅና ሱዳንም አሽሙር ይበቃናል።

  ስለሆነም!

  ስህተት ሰርተዋል – ይቅርታ ይጠይቁና ወደሚያምርቦት አናሊስስ ይግቡ። አቢይ ባይጋብዞት አየር ላይ ያውሉት። የሚያደርስለት አይጠፋምና. ይህው ነው።

  ከይቅርታ ጋር

  አባዊርቱ ነኝ

 3. ለተከበሩ አባዊርቱ
  አባዊርቱ: ጠፍተዉ ነበርና እንኳን በደህና ተመለሱ! ለረዥም ጊዜ አንባቢዎ እና አድናቂወ ነኝ። ከሰሞኑ ለፃፏቸው ሁለት ልጥፎች መልስ ልሰጥ መጻፍ ጀምሬ መልሼ ትቻለሁ ። ይህን አስተያየትወትን ግን ማለፍ ፈፅሞ አልተቻለኝም ይህም በሶስት መሰረታዊ ምክንያቶች ነው:1)እርስዎን ያህል ትልቅ አዋቂና የኢትዮጵያዊነት ማሳያ የሆኑ ሰዉ(በአካልም ሆነ በሌላ መልኩ አላዉቅዎትም ነገር ግን ከሚፅፉት ተነስቼ የሰጠሁዎት በጣም ጥሩ የሆነ “ኢትዮጵያዊ ስብዐና” አለ በሀገር ፍቅር በበሳልና አሰባሳቢነት፣በጨዋነት፣ትህትናና ራስን ዝቅ አድርጎ/humilityየማቅረብ)ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብይን የነካ የማርያም ጠላት አይነት አብዝተው ማየቴ እንግዳ ስለሆነብኝ። መቅደም ያለባት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ስለሆኑ
  2)ጠ/ሚዉ ማንም ይሁኑ እየተከተሉት ያለዉ መንገድ ሁሉንም(ህዝቤ ብለው በግላጭም በድብቅም የሚውተረተሩለትን የኦሮሞ ህዝብ ጭምር) አክሳሪ/zero sum game መሆኑን እርስዎንና እንደእርስዎ ሁሉ ፈፅሞ የማላዉቃቸው የማያውቁኝ በሚያስነብቡን ድንቅ መጣጥፎች ለአጎትነት የቀረበ ውዴታ በእኔና ጥቂት ጓኞቼ ዘንድ ያተረፉትፕ/ርአለማየሁ ገ/ማርያም(ስናጠፋ/ከመስመር ስንወጣ በዚያ ጣፋጭ እንግሊዝኛና ላቲናቸው እየቆየ የሚገባን ሽንቆጣ ቢጤ ሁሉ እንዲለግሱን በመፈለግ) እንዴት እንደ ሳታችሁት አልገባ ስላለኝ
  3)የእርስዎና መሰል ሰዎች ጠ/ሚውን መደገፍ አብዛኛዉን ሰላምና አገር ወዳድ አዘናግቶ ወደመታረጃችን የሚወስድ ስለሆነና ሻለቃ ዳዊት በተለያየ ጊዜ በፃፏቸው articles ዉስጥ ያስቀመጧቸው ነገሮች በትክክል ሙያዊ ስለነበሩ ሁሉም አንድ ሳይቀር ተራ በተራ ተፈፅመዋል የቀረ/የጎደለዉ ቁጥር ብቻ ነበር እሱም አሁን በየቀኑ ሪፖርትየሚደረገዉን በቻ ለደመረ ሰዉ ወደሩዋንዳ እንደሆነ ጉዟችን ግልፅ ነው። በተለይም ደግሞ “መንግስታችን” ተብየዉ ምርጫ ላደርግ ነው ማለቱን ከሰማሁ በኋላ የኔ አቋም ልጆቻችንን ማትረፊያው መንገድ መፈለግ ብቻ ነው(የሁለት ህፃናት እናት ነኝ)። መንግስት ነኝ ባዩ በትክክልም “failed state” መሆኑን ለመረዳት ከፈለጉ እዚህቹ አኔ በምገኝባት አ/አበባ ቦሌ ክ/ከ ለሁለት ወይም ሶስት ቀናት ቢገኙ ይገነዘቡ ነበር።
  ለማንኛውም ላሳጥረውና እባክዎን እርስዎ “ሙሴዎን” መደገፍ መብትዎ መሆኑን እየገለጥሁ ከብዙ አክብሮት ጋር አዳሜን እንዲያዉም ባለ short memory ነዉናአያዘናጉ ቢያንስ ሰዉ ልጁን ቆሞ ማሳረድ የለበትምና “መንግስታቸውን” መቃወም እንደትሁቱ እስክንድ ቢያስቀስፍም ቢያንስ ልጆቻችንን መደበቂያ ጉድጓድም ሆነ ምሽግ ቢጤ በግዜ ማዘጋጀት ግን በነዝዋይ/ዴራ/ሻሼ/ጅማ/መተከል ወዘተ ከአየነውና ከሰማነው የጠሀዩ መንግስት “ነበልባልና ግስላ” ህግ አስከባሪዎች ለአንድ ጠላት ብለው ለፈረጁት ወገን አውቀው የመተኛትና ያለመስማት ችግር ያድናል።
  አብይ ምርጫው ግልፅ ነው ይኸዉም አነ ዲማ ነገዎ፣ኩማ ደመቅሳ፣አባዱላ(በከፍተኛ ልዩ አማካሪነት እኛው በምንከፍለውግብር የቀጠራቸው ሲሆን) ከሰሞኑነ በአሀዱ ቲቪ ዲማዉ የሰጡትን ቃለመጠይቅ እባክዎት ይመልከቱት ስለሀሰትና ጥላቻ ትርክት ተጠናክሮ ቀጣይነት ይረዳሉ። ከዚሁ በተያያዘ ከሰሞኑን ገዥዎቻችን ሊያሰምሩበት የፈለጉትና በማያሻማ ሁናቴ በተለይ ለ በድኑ ብአዴን እና “ያሻግሩናል”በለን ለተጃጃልን ሁሉ በተጠናና የተቀናጀ ሁኔታ ከአባዱላ ገመዳ(የኦፒዲኦ/ፒፒ የጡት አባት)በአርትስቲቪ፣ ኩማ ደመቅሳ በዋልታ ወይም ፋና እና ዲማ ነገዎ በአሀዱ በግልፅም በቅኔም ነግረውናልና አዳሜ ህገ መንግስቱ አይነካም(ኩማ ‘ “አንዳንዶች” አልተወከልንም እያሉ እንደሚዋሹ ነገር ግን እሳቸው ጭምር ያዋለዱት ይህ “ብርቅየ”ሰነድ ሁሉንም ማሳተፉንና የትም እንደማይሄድ’ ነግረዉናል። ስለ የሀሰት ትርክትና አኖሌን በተመለከተም ታሪካዊ በደል ደርሶብኛል የሚል ህዝብ እያለ እናንተ እነማንናችሁና ሌሎችም ከስም ስያሜ(አበበ፣ከበደ ወዘተ)እስከ ብሄር ፌዴራሊዝሙ ቀጣይነት፣እንዲሁም ሙስና/ስርቆት/አድሏዊነት/ኢፍትሀዊ አስተዳደር የግለሰብን ኪስ ለሙላት ሳይሆን ለ”አንድህዝብ”ጥቅም ከሆነ የተደረገዉ ወንጀል እንዳይደለና “ሌላውም ህዝብ”በዚሁ መልኩ ተገንዘቡት ከሚል አንደምታጋርና በመጨረሻም ትግሉ ሲጀመር የነበሩ የብሄርና የድርጅት መስተፃምሮች(ኦሮማራ???)ከሂዊ ዉድቀት በኋላ ቢካዱ ወይም የታለመ እኩል ተጠቃሚነት ባይረጋገጥ የፖለቲካ ባህሪ ስለሆነ miscalculate ያደረጉ ሰዎች this is politics በሚል መረዳተ መዉሰድ እንደሚገባ ከጡት አባት ሰምተናል/ነግረውናል። ሶስቱም ሰዎች የሰጡትን ቃለመጠይቅ እባካችሁ እዩት የምትገነዘቡት ብዙ አይን ገለጭ ቁምነገር አለና ተመልከቱትና ቁርጣችንን ተረዱት።
  እኔ በበኩሌግን ይህን እላለሁ፦ የሚደርስልን ማንም የለምና ፖለቲካው ቀርቶ በቅጡ ዘር ማስቀጠል(ነፍስ ያላወቁ ልጆቻችንን) ማትረፍ እንቻል። ኢትዮጵያ እንደምናውቃት(Ethiopia as we know her/it is no more) አለች ማለት የዋህነት ነው እርግጥ ነው ሆድ የባሳቸው የስነጥበብ ወርቆቻችን በራስሆቴል አዳራሽ አለሽ ሲሏት አርትስ ቲቪ ላይ አይና አልቅሼም ተፅናንቼም አተኛለሁ በሳምንት አንድ ቀን።
  አባዊርቱየ ዉትወታዎ ኢትዮጵያን በማለት ነው ብየስለማምን ብቻነው ይህን የጻፍሁት እኔ ፈጽሞ የፖለቲካም ሰዉ አይደለሁም የማህበራዊ መገናኛ(fb) ተጠቃሚም አይደለሁም ነገር ግን ጠዋት ወደስራም ሆነ ት/ቤት ለመሄድ ከቤት ከመውጣት በፊት እንኳን የሚያምኑትን የዜና መንጭ browse አድርጎ ሰላም መሆኑን ቼክ ማድረገ አስፈላጊየሆነበተ ጊዜ ላይ ነንና እባክዎን reflect ያድርጉ። ይህችን ጥያቄ ብቻ ይመልሱልኝ፦እንዲው በጠ/ሚሩ ዘንድ በትክክል ለመምራት ዋነኛ የቸገራቸው ምንድን ነው በእርስዎ እይታ? በኔ እምነት1) ለክቡሩ የሰዉ ህይወት መጥፋት የሚሰጡት ቦታ ከአንድ የተከሉት ችግኛቸው መድረቅ ያነሰ ነው 2)ባለሙያን ማስጠጋት ፈፅሞ አይወዱም በተለይም ለኢትዮጵየዊነቱና ኢ/ያዋጋ የሚሰጥን ሁሉሸሽተው ስጋ ጥራ ቢሉት—–አይነትexpired( ለአገላለፄ ይቅርታ)የሆኑና እዚህ ያደረሱንን ክፉ እሳቤ የተጣባቸው ሰወች በዙሪያው የከበበው በእርስዎና አኔ ምርጫ አይደለምና። በመሰረቱ አብይጠ/ሚ የሆኑባት አገር በኔ እምነት ቢያንስ ብሄርን/እምነትን ወይምሌላ የመለያ መስፈርትን ያደረጉ የዘር ማጥፋቶች፣በደል አና ኢፍትሀዊነት ታሪክ ሊሆኑ ይገባ ነበር (ከresumeአቸው እንደተገነዘብሁ የphd መመረቂያ ጥናታቸው intercommunal/interfaith conflict resolution ላይ ነው። ይህም ማለት ከአብዛኞቻችን በተሻለ እንዲህ ያሉ ችግሮችን አስቀድመው anticipate/predict በማድረግ ጦራቸውን ቦታ አሲዞ ምስኪን ድሆችንና ሰለባዎችን መታደግም ሆነ አስቀድሞ ማህበረሰብን ራሱን እንዲጠብቅ ማንቃት ነበረባቸው። እሳቸውና ሹመኞቻቸውግን 100%በሚባል ሁኔታ የሬሳ ስተቲሰቲክስ ለመዘገብ ብቻ ነው ብቃታቸው እሱንም ወግና መቅኔ ባጣ አእምሮ ላለው ደግሞ እጅግ በሚቆጠቁጥ ሁኔታ(እርግጥ ልክ ነሽ የፈጸመው ጄኖሳይድ ነው ነገርግን ጄኖሳይድ ተፈፀመ ብለን ካልን ጄኖሳይድ የተፈፀመበት ህዝብ አለ፣ ጄኖሳይድም ፈፃሚ ህዝብም አለ መለታችን ስለሆነ ይህ ደግሞ መባል የለበትም ህዝባችን አቃፊ ስለሆነ ጄኖሳይድ ቢፈጸምም ማለት ግን የለብንም ብለው በናሁ ቲቪ ቀርበው ለሳምንታት እንዲያመኝም ብቻየን እንድስቅም እንደረጉኝ የኦሮምያ ሹመኛ ማለት ነው)።ስለዚህ ወይ ሙያቸውን ትኩረት ሰጥተው ተግባራዊ ያላደረጉትና ይህሁሉ ዜጋ የተጨረሰው አንድም የአማራና ኦሮሞ ያልሆነን ነፍስ ከሚንሰፈሰፉላቸው ችግኞች ዝቅአርገው በማየታቸው ነው ወይም ከጭፍጨፋው የሚያተርፉት ትርፍ አለ ወይምደግሞ ይህን ከበድ ያለ ሙያና አላማውን ፈጽሞ አያውቁትም።የኔ እምነት ሁሉም ናቸዉ ምክንያቱም የዚህ ክቡር ሙያ ባለቤት ለዚያውም በተጨማሪ ኮሎኔል የሆነ መሪ ያለን “ህዝቦች” በየቀኑ ሰው ተበልቶ እየተበላ የመቀሌ ጦርነት ባለቀ ማግስትየምንጠብቅ የነበረ የሂዊና መሰል ስምአይጠሩዎችን በአሸባሪነት የፈርጃሉ “ህገ መንግስታቸውን” ይቀይራሉ ወዘተ ሲሆን (እኔ እንጅል ጠብቄ ነበር)እሳቸው እቴ “ለምን ኬክ አይበሉም”እንዳለችው ልእልት ቀጥ ብለው ጎርጎራ፣ ኮይሻ ምናምን ሲሉ በቲቪ ታዩ እኔም ትእግስቴ አለቀና በተለያየ ጊዜ ለአጭር ጊዜ ተደምሬም ደግፌም በነበረ ጊዜ በልጆቼ ውትወታ የተገዙና የቤታችንን ፍሪጅ ላይ የፍራፍሬና አትክልት ፖስተሮች ጨፍልቀውና አፈናቅለው የተለጠፉ የ”ሙሴውና ቲማቸው” ፎቶዎችን አንስቼ ፍሪጄን ከመሸወድ አንፅቻለሁ ሌሎቻችሁስ?
  በቃኝ፡ በቸር እንቆይ

 4. “ሻለቃ ዳዊት ቀርቦ የሚጠይቃቸው ቢኖር ለሃገራቸው ነፍሳቸውን ሳይቀር ለመስጠት የማያመነቱ ሰው ናቸው፨”

  ትክክል ብለሻል አንቺ አቃጣሪ
  ሻለቃ ዳዊት ሀገራቸዉን እጅግ በጣም ስለምወዱ ነዉ ኢትዮጵያ በአለቃቸዉ መንግስቱ ሃይለ ማርያም የጭቆና አገዛዝ ስር የወደቀች ጊዜ ፈርጥጠዉ አገር ጥለዉ የወጡት።

  • John smith ጭንቅላትህ ላይ ትንሽ ቁንጮ ከውስጡ ደግሞ ትንሽ አይብ የተቀመጠልህ ቄሮ በመሆንህ ስድብ ተፈቅዶልሀል። ካልተሳደብክ ምን ማድረግ ትችላለህ? ስልጠናህ ስድብ በመሆኑ አባ ዊርቱ በረቀቀ መንገድ ብቅ ሲሉ እናንተ እየወጣችሁ ታበላሹባቸዋላችሁ እንደ ዶር አብይና ሽመልስ አብዲሳ መሆኑ ነው።።

 5. ስድብ መልስ አይሆንም ፣በተለይም ምንም አይነት የመወያያ ሀሳብ ሳያቀርቡ። ማንም ሰው የመሰለውን የመናገር መብት አለው። መወያየትና መከራከር የአባት ነው። ለምንድነው የአብይ አጎብጓቢዎች ድርብ የሚቀናችሁ። እንደምታመልኩት ሰውዪ ፣መወያየት የሚባለውን አታውቁም ።መሳደብ ወ/ማስፈራራት ይቀድማችኋል። አምልኮ በሐይማኖት አይከለከልም ሰውን ማምለክ ግን የራስን ትንሽነት ይመሰክራል ። አባዊርቱ የለየለት የአድባር አጋፋሪ ለመሆኑ ቀድሞ አስመስክሯል።

 6. ደስ ስትሉ ክብር ያላችሁ ኢትዮጵያዉያን ሻለቃ ዳዊት መስከረም አበራ ለሀገራችሁ ለምታደርጉት ሚዛን ማስጠበቅ ስራ እናመሰግናለን ከላይ የሚሳደቡት በሀሳብ የተጎዱ ዜጎች ስለሆኑ እዘኑላቸዉ ምክርና ትምህርታችሁን አታቋርጡ ምናልባት ምናልባት ሊመለሱ ይችሉ ይሆናል።

 7. ለከድር ሰተቴ መልስ መስጠት በሱ ደረጃ መውረድ ስለሆነ ድንቁርናው ስለተመቸው በጥልቅ ሀሳብ አላስቸግረውም። አባዊርቱን በተመለከተ ለአብይ ኦሮሙማ ቀናኢነታቸው ዱላ ይዘው ከሚንገላወዱ ቁንጮ ቄሮዎች የሚያንስ አይደለም። ለሳቸው ታየ ደንዳም ሆነ ሽመልሳ አብዲሳ ቄሮን ዘመን የሚያሻግሩ ናቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት የህዝብ አንድ ቁጥር ጠላት ባልደራስና አብን ናቸው ኦነግ አይደለም።ቀደም ባለው ጊዜ ሻቢያን አጥብቀው ይጠሉ ነበር ከአብይ ፍቅር ሲሆኑ እሳቸውም አፈቀሩት።
  ስለ ሻለቃ ዳዊት world class ስለሆነ ማብራሪያ አያስፈልግም።
  በተረፈ በረጅሙ ስለ አባዊርቱ የጻፍሽው የአጻጻፍ ስልታቸው እንደ ፓስተር ስብከት እያዋዛ መንገድ ስለሚያስት አልፈርድብሽም። የአጻጻፍ ስልታቸው ደስ ይላል። አለቃ ክንፉ ደብር ቅኔ ራጉኤል ድቁና ሳይቀበሉ አይቀሩም እኔም ጽሁፋቸውን ሳላነብ ሀሳቡን ጠንቅቄ ባውቀውም አነበዋለሁ። 360 የሚለውን ቁጥር በኢትዮ 360 ምክንያት ጠልተውታል ጋዜጠኞቹን የማይሏቸው የለም። እሳቸው ኦሮሞ ነኝ ነው የሚሉት አገር ሲረጋጋ የ DNA ማሽን ይዤ እገባና እሳቸውም እንደ ነጋሶ ጊዳዳ ብርሀኑ ጁላ ሌንጮ ለታ ጉዴላ ሁነው ያርፉታል። መተራረድም ይቆማል የኔ ነው የሚባለው ቀርቶ የኛ ነው ይጀመራል ያላቅማቸው የተቀመጡበት ወምበርም ችሎታ ላለው ይሰጣል።
  ሰላም ሁኑ ሁላችሁም

 8. አቶ ሰመረ ኢትዮጵያዊ ይመስሉኝ ነበር የፅልመት አሽቃናጭ ኖት ብዬ በጭራሽ አልጠበኩም ነበር:: ለምን ይበሉኝ?

  1) የ 360 ጋዜጠኞች ለኔ አንድ ኤርምያስ ነው እሱም የፅልመትአንጋች በመሆኑና ፀረ ኢትዮጵያ አቁዋሙ እነቅፈዋለሁ – ጥላቻ የጅሎችና ደናቁርት መሳርያ ነው

  2 ) የአቶ ታዬን በቁርጠኝነቱና ግልፅነቱ አዎ አድናቂው ነኝ:: አቶ ሺመልስ ግን ጅምሩ ላይ እንጅ ስራውን አላደንቅም:: የህዝባችን አንድ ቁጥር ጠላት ድንቁርና ነው:: ባልደራስ: አብን ሆኑ ኦነጎች ኦፖርቹኒስቶች ናቸው:: አገር በመፈክር ወይም ባነር ወይም ቀረርቶ ወይም በቢላና ገጀራ አትገነባም። ቀደም ባለው ጊዜ አዎ ሻቢያን አጥብቄ እቃወም ነበር :: ለምን? አገሬ ላይ በሰሩት ደባ:: ለምን? እነዚን አሁን እንዲህ እንደጉም ሊተኑ , የፅልመትን ሰራዊት ፈተው ባገሬ ላይ በመልቀቃቸው:: ዛሬስ? ተፀፅተው ይቅርታ ጠይቀው አብረውን ማእድ ቆርሰው : ቤታችን ለፀበል መጥተው እኛም ሄደን, ይቅር ለግዜር ተባብለን , ከፅልመት ተምች ያመለጠን መሄጃ ያጣን ሰራዊት አብልተው አልብሰው የመለሱልንን መልካም ጎረቤት : ክቡር ህዝብ አለማድነቅ ተልካሻነት ነው:: አስተዳደጌ ውለታ ያውቃል:: እኔ አቢይን ብሆን እንደውም በሚቀጥለው ፋሲካ ኢሳያስን ጋብዤ አብሬ ፈስኬ ከፍተኛውን የክብር ኒሻን አጎናፅፍ ነበር::

  3) ስለ ሻለቃ ዳዊት world class ስለሆነ ማብራሪያ አያስፈልግም ያሉት – አዎ አያስፈልግም ግን እንድያ መሆን ከስህተት አላዳናቸውም – ይቅርታ ይጠይቁ ሻለቃው ተሳስተዋልን እንጅ መች ክላስነታቸውን አስተባበልኩ?

  4)የአጻጻፍ ስልቴ እንደ ፓስተር ስብከት እያዋዛ መንገድ የሚያስት የመሰልዎ እውነትን ስለምፅፍ ነው:: የልቤን ስለሆነ ለ አፃፃፌ አሽቃናጮች ምን ይላሉን ሳይሆን ከንሸሴ ምን ይላልን ነው የማዘወትረው:: እንኩዋን በዚህ እድሜ በወጣትነቴም ውዳሴ ከንቱን እፀየፋለሁ::

  5)እርሶም እንደ አባጫላ ዖሮሞ አይደለህም ነው ቅኔው:: ለምን ቢሉ ግእዝን ፊደል ሰለማቀላጥፍ:: አስሩን ማቀላጠፌን ማን በነገርዎ:: ቅቅቅ እንደውም አገር ሲረጋጋ ጉዴላ ሆኜ እንደማርፈው አብስረውኛል:: ጉዴላ መጥፎ እንደሆነ ነገር:: መልካም ኢትዮጵያዊ ስነምግባር ከወደዛ አካባቢ መፍለቁን ቢያውቁት እርሶም የሚያምርቦትን ዲቤና ጭብጦ ቢጤ እንዳንጠለጠሉ በሀፍረት ዘመድዎችዎ በድሮን የጋዩበት ጉድጉዋድ ይገቡዋት ነበር:: በዛሬ ዘመን እንዲህ ይላሉ? ያሳዝናል:: ሌላው ቅኔውን ለመቀኘት ይሁን ለመዝረፍ ተወልደን ባደግንባት ሸዋ ሊቃውንት ከዋሸራና ዋልድባ ሳይሆን ከወደ ደብረሊባኖስ ነው የሚመጡልን:: እዛ ደግሞ እነ አባ ሀይለመለኮትና መምሬ ለቺሳ ይበዛሉ:: አሃ! ለካ ለርስዎ እነ መምሬ ለቺሣ ምንም ማለት አይደሉም:: ይህ የድል ማግስት ብዙ አሳየን:: ይልቅ እስቲ እዝን ይድረሱ:: እነዘርአይ አሰግዶም ተሰውተዋል አሉ – ከምፀት ጋር!!

  • “ዛሬስ? ተፀፅተው ይቅርታ ጠይቀው አብረውን ማእድ ቆርሰው : ቤታችን ለፀበል መጥተው እኛም ሄደን, ይቅር ለግዜር ተባብለን ”

   Ha-Ha….! ትደልይኦ’ሞ ይዝንግዐክን…….! Du bist entweder dumm oder du schummelst dämlich.
   ዘላለማችሁን ሌላው የሰራውን ተግባራትን የኔ ነው እያላችሁ መኖርን አትሰለቹምን ?
   ጃፓኖ አሜሪካኖው ባቀነባበረው የአፍሪቃ ቀንድ ፀረ ጅቡቲ ላይ በቅርቡ በተዘረጋው ከቻይና ውጭ ሚገኘው የቻይና ታላቁ ወደብ ስትራተጂ ግብድድ ላይ፣ የአንተ የአውዳመት ተገባባዥ ሆነህ ለመገኘት በድፍኑ ስነ አእምሮህ ማንቁዋለጥህን ሳያሳፍርህ ወይንም ሳይገባህ ማንነትህን ከፍተህ ለሁሉም እንደ እግዝቢሽን ማሳየት……! ይሄንና ይሄን የመሳሰለ መደድየነት እኮ’ነው ቴክኒካሊ በመጠቁት ሃገራት (“በሰለጠኑት ሃገራት”) በቀላሉ የሚያስበላን ያለው…….!
   ነገሮች ሁሉ የምሽንን ጥጦ ከመማግ በላይም አለፍ ያለ ውጥንቅጥነትም ሊኖራቸው እንደሚችል ለመገመት መጣር፣ globally ከሌሎች ጋራ ጠለቅ ባለ መልኩ ለማሰብ ይጠቅማል …….! Denke globbaly, handle lokaly ….!

 9. አባ ዊርቱ ለኔ ተናግረዉልኝ ለኔ መልሰዉልኛል መልካም ነዉ እኔ ጉዴላ ሊሆኑ ይችላሉ ያልኩት በተለያየ የገዳ ኦፕሬሺን እዛ አካባቢ ምን እንደተደረገ ስለማዉቅ ነዉ እንጂ በዛሬ ጊዜ ማን ከማን ይበልጣል ብለዉ ነዉ? ሌላዉን ትቼ ለኔ የኢሳይያስ ፍቅር ዛሬም ቢሆን አይዋጥልኝም ጦርነቱ ሲጀመር ትግሬዎቹን ያላቸዉ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ወደኔ ኑ ነዉ ያለዉ ።ይዘዉት የገቡት አልተመለሰም እሱም ገብቶ ቀሪዉን ወስዷል ኪሳራ ላይ የወደቀች ኢትዮጵያ ነች አልሰሙ እንደሆን ዉሳኔ ባልተሰጠበት ክልል የሻቢያ ሰራዊት ሰፍሮበታል። ለማንኛዉም ትንሿ የድሮ ግዛታችን እንደ አሜሪካ መታየቷ ይገርመኛል መሪዎቿ ቁርስ ብልተዉ ምሳ የማይደግሙበት አገር ነች። ለማንኛዉም እዛ ሳንገባ አገር ችግር ላይ ነች እነ ሺመልስ አብዲሳ፤ታየ ደንዳ፤ሌንጮ ለታ/ባቲ፤አባዱላ ገመዳ በዚህ ዉስብስብ አለም መፍትሄ ሊሰጡ አይችሉም
  አጼ ሐይለ ስላሴ በምን አይነት የዲፕሎማሲ ጨዋታ እንግሊዝና በአሜሪካ አድርገዉ አንድነቷን ግዛቷን ነጻነቷን እንዳስጠበቁ ለርሶ መንገር ድፍረት ነዉ ሰዉ ካለበት ወደ ላይ ከፍ ይላል እንጂ እንዴተ ከ50 አመት በሁዋላ ወደ 500 አመት እንመለሳለን? ይህ ህገ መንግስት የረቀቀዉ በመለስ ዜናዊና ሌንጮ ለታ፤ዳዉድ ኢብሳ አረጋዊ በርሄ ነዉ እስቲ በአጼ ሐይለ ስላሴ ጊዜ የነበሩትን ባይነ ህሊናዎ ይመልከቱ በቂ መጽሀፍ ስላለ ለማስታወስም ይረዳል። አክሊሉ ሐ/ወልድ፤ከተማ ይፍሩ፤ይልማ ዴሬሳ፤አዲስ አለማየሁ…. እያለ ይቀጥላል ዛሬ እርግማን ሁኖብን ሰዉ ስንጠራ ታየ ደንዳ፤ሺመልስ አብዲሳ፤ሱሌማን ደደፎ፤ሺፈራዉ ሺጉጤ በየባንኩ በየመስሪያ ቤቱም እንደዚህ ያሉ ጉዶች ናቸዉ። እንግዲህ ይሄ ስርአት ደስ ካሎት መልካም ነዉ በርቱ በሏቸዉ።

  እስቲ አምባሳደሮቻችንን ተመልከቷቸዉ በነ ይልማ ደሬሳ አይን አቶ አዲስ አለማየሁ ጁኒየር ነበር የሚባሉት እንግዲህ አሁን በየአገሩ ያለዉን አምባሳደር ተመልከቱት ባይናደዱ አይቆጩም? ሺፈራዉ ሺጉጤ፤ሱሌማን ደደፎ፤ስየም መስፍን( አልፈልግም ብሎ ተመለሰ እንጂ እሱም አምባሳደር ነበር)። የአባይ ድርድር ጉዳይ መስመር ስቶ እርሶ በሚጠሏቸዉ በኢትዮ 360 ጩኸት ነዉ የተመለሰዉ ወደኢትዮጵያ። ለማንኛዉም ብዙ ግንዛቤ እንዳሎት ጥርጥር የለኝም ይሄ ኦሮሙማን የማንገስ አካሄድ ግን ጥፋት እንጂ ልማት አያመጣም። ከህወአት ጋር ነበረበረዉ ጦርነት ኦነጋዉያን እነ ሺመልስ፤ለማ መገርሳን፤ታየ ደንዳን፤ሌንጮ ለታ/ባቲ፤አባ ዱላን….. አይመለከታቸዉም ማለት ነዉ? የነሱ ጉዳይ ሰዉ ማረድና ኦሮሙማን ማስፋፋት ብቻ ነዉ ማለት ነዉ? 33 ዙር ሰልጥኖ ልምድ ለማግኘት እንኳን ወደዛ ተጉዞ አርበኞች እንዴት እንደሚዋጉ በርቀት አይከታተለም? 33 ዙር ስልጠናዉ ያለበትን ቦታ ያቆዩለትን ዜጎች ለማረድ ነዉ ማለት ነዉ ስልጠናዉ? ለማንኛዉም መልካም አመት በአል።
  አማራዉን ያዉቁታል ምንም እንኳን ጸረ ኢትዮጵያ ሀይሎች በገራ ቢነሱበትም አስተሳሰቡ እንደ ባህር የሰፋ ነዉ ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ጎንደርን ሲያስተዳድሩት በደስታ ነዉ ያስተናገዳቸዉ። አሰፋ ጫቦም አዉራጃ ገዥ ነበር ኢትዮጵያዊ እሰከ ሆኑ ድረስ ችግር የለበትም። አሁንም አንድነት ይሻላል የተያዘዉ የብልጣ ብልጥ ፖለቲካ አያዋጣም ግብጽ ጂቡቲን፤ኬንያን፤ሶማሊያን፤ሱዳንን ከባ ቁጭ ብላለች ኢሳይያስ የክፉ ጊዜ ወዳጆቼ ነዉ የሚላቸዉ አልሰሙ ከሆነ በዚህ ሁሉ እነ ሺመልስ አብዲሳና ታየ ደንዳ ካፍንጫቸዉ ባልራቀ እይታ ከስር አገሪቱን ይገዘግዛሉ። ስለ አብይ አማካሪዎች ብዙ ማለት ይቻል ነበር እስቲ ይቅር። ሀገር ችግር ላይ ነች በርቱ ሳይሆን ቆም ብላችሁ አስቡ በሏቸዉ።
  ሰላም ለርሶ ይሁን

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.