/

ልፃፍ ስለ ጎጃም

Metekeleእስኪ ፍቀዱልኝ ……… !!!
ልፃፍ ስለ ጎጃም _ ለትውልድ ሀገሬ ፣
ከ ማሆይ ገላነሽ _ ቅኔን ተበድሬ ፣
ዜማውን ተውሼ _ ከአድማሱ ጀምበሬ ፣
ከሐዲስ አለማየሁ _ ቃላትን ቆጥሬ ፣
ከጎጃም አርበኞች _ ጀግንነት ተምሬ ፣
አትነካኩኝ ልፃፍ _ በግጥም ዘርዝሬ ።

መሸንቲ ቢኮሎ _ ዱርቤቴ ይስማላ ፣
ዘንዘልማ አዴት _ መራዊ ሰከላ ፣
እጅግ ይጣፍጣል _ እሸቱ ሲበላ ።
ቲሊሊ ኮሶበር _ ቻግኒ እንጅባራ ፣
የሚገበይበት _ የፍቅር እንጀራ ።
ቢቡኝ ድጎ ፅዮን _ ቋሪት ደጋ ዳሞት፣
መለያቸው ድፍረት _ አርማቸው ጀግንነት ።
እነሴና እነብሴ _ ደጄንና አቸፈር ፣
ሸበልና ማርቆስ _ ዳንግላ ባህርዳር ፣
የማርና ቅቤ _ የማኛ ጤፍ ምድር ፣
እንዴት ብዬ ላውራው _ አያልቅም ቢነገር ።

Alem T.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.