/

ሞረሽ ተጠራራ! – በላይነህ አባተ

Metekele

ተናዚ ተሂትለር ተጅብም የከፋ፣
ተገደል የሚጥል ተነነፍሱ ገላ፣
ሺልን ተሆድ አርዶ ጉበት የሚበላ፣
አውሬ ተዱር ወጥቷል ሞረሽ ተጠራራ!

ተራራ ላይ ወጥተህ መለከቱን ንፋ፣
አዋጅ ብለህ ንገር አገር ምድሩ ይስማ፣
የአበደ አውሬ እረብቷል አማራ እሚበላ!

ተሞያሌ ጎንደር ተሀረር ጋንቤላ፣
ተዳሞት ማጄቴ ተመራኛ ላስታ፣
ተራያ ወልቃይት ተመተከል ደራ፣
ተጭልጋ አላማጣ ተደባርቅ ሞጣ፣
ተጅሩ ብቸና ተናዝሬትም ጎባ!
ተዳባት አቸፈር ተምንጃር ወረታ፣
ተመንዝ ኮምቦልቻ ተቆቦም ዳንግላ፣
ተማርቆስ ባህርዳር ተደሴም ወልዲያ፣
ተአዲስ ዘመን ደጀን ተእንጦጦ አዲሳባ፣
ጨርቄን ማቄን ሳትል ሞረሽ ተጠራራ!

Maykadra 2 1

በምድር ታይቶ እማያውቅ ተጭራቅ የከፋ፣
የአማራ ደም ልሶ አርባ ዓመት ያልረካ፣
ሕፃናትን አርዶ ኩላሊት የበላ፣
አውሬ ጦቢያን ወሯል ሞረሽ ተጠራራ!

ተአሜሪካ ለንደን ተሜልቦርን ካናዳ፣
ተፈረንሳይ ጀርመን ተጣልያን ሩሲያ፣
ተፊላንድ ዴንማርክ ተስፔንም ሰርብያ፣
ተአምስተርዳም ኦስሎ ተስቶኮልም አፍሪካ፣
ዛሬ ነገ ሳትል ሞረሽ ተጠራራ!

የመጣብህ አውሬ ተዱሩ እንዲገባ፣
እንደ ድር አብረህ ዘራፍ በል አማራ፣
ልክ እንደ አያቶችህ ሁልህ ሁን አርበኛ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ህዳር ሰላሳ ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንተ ወንድሜ ነህ -  ዘምሳሌ

5 Comments

 1. ለ መብቱ የ አል ተዋደቀ አይኖረውም መብት፣
  ይቺን መመሪያችን ከ አል አደረግን አንተርፍም ከ ዕልቂት።
  ጠላቶቻችን አሰፍስፈዋል መሬታችንን ለ መቀራመት፣
  ተባብረው እኛን ከ ምድረገጽ በ ማጥፋት።
  ሳንዘናጋ እንነሳ ለ ህልውናችን፣
  አለበለዚያ ወዮልን፣ ወዮልን።

  • “ለመብቱ የአልተዋደቀ አይኖረውም መብት፣
   ይቺን መመሪያችን ከአልአደረግን አንተርፍም ከዕልቂት።
   ጠላቶቻችን አሰፍስፈዋል መሬታችንን ለመቀራመት፣
   ተባብረው እኛን ከምድረገጽ በማጥፋት።
   ሳንዘናጋ እንነሳ ለህልውናችን፣
   አለበለዚያ ወዮልን፣ ወዮልን።”

   ገና አሁን ችግርህን እየተገነዘብክ የመጣህ ትመስላለህ፣ Gratulation
   ‘የጥበብ መጀመርያ ራስን ማወቅ ነው’
   ወይንም ፈረንጆቹ እንዲሉት Selbsterkenntnis
   ጥላሁን ገሰሰም በ’Vulgarität መልኩ:
   “ራስን አውቆ መኖር ጥሩ ነው፣ ታላቅ ችሎታ ነው” ብሎት ነበር
   እንግዲህ አሁን የሚጎልህ፣ ሌሎቹም በየበኩላቸው እንዳንተው እንደሚሉና፣ መፍትሄው ከእነሱ ጋር በመግባባት እንደሚመጣ እንጂ እነሱን ዝቅ-ዝቅ በማድረግ እንደማይሆን ብቻ ነው! ይህ ከተሟላ ኢትዮጵያም ተረፈች ወዳነች ማለት ነው!

   • @ ዘረ-ያዕቆብ

    አማራ ማንንም ዝቅ-ዝቅ አድርጎ አያውቅም፤ የ ማንንም መሬት ቀምቶ አያውቅም። ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ህዝብ ነው። ለዚህም ነው ለ 30 ዓመታት ሲገደል በ አጻፋው መልሶ ማንንም ገድሎ የማያውቀው። አመጸኛ እና ህግ አክባሪ ባይሆን ኖሮ የማንም አናሳ ብሔረሰብ ሰለባ አይሆንም ነበር። አማራ ከ ማንም ባላነሰ እራሱን የሚያውቅ አዋቂ ህዝብ ነው።

    • አልሸሹም፣ ዞር አሉ ሆነ ነገሩ!
     እኔ የምናገረው ስለ ሃሳብ አቅራቢው ዘውዱ የነገሮች ግንዛቤና መግባባት ችሎታዎችንና (self consciousness) የሶሊዳሪቲ ችሎታዎችን ነበር እንጂ፣ በድምሩና በጅምላው ስለ አማራ አልነበረም::
     ወደ ጅምላነት ከተሸጋገርን ግን DC -‘አማራ’ Propagandist-och are responsible for many ማህለቅያ የለሽ Catastrophic in the Ethiopian ህብረተሰብ!
     ወይንስ ደግሞ በአብስሉትዝም ዘመነ መንግስት፣ L’État, c’est moi! እንደተባለው፣ ራስህንና አማራን በአንድ ፍንጃል ውስጥ ነው ደቁሰህ የምታስቀምጠው ልበል እንዴ? ይሄ ከሆነ ደግሞ የባሰው ካታስትሮፊው ሊሆን ነው!
     One step ወደፊት ተራምደን with sincerity ወደ ተሻለው አንድ እርምጃ ወደላይ ከፍ ብሎ መገኘቱ ያዋጣናል………..!

 2. “ለመብቱ የአልተዋደቀ አይኖረውም መብት፣
  ይቺን መመሪያችን ከአልአደረግን አንተርፍም ከዕልቂት።
  ጠላቶቻችን አሰፍስፈዋል መሬታችንን ለመቀራመት፣
  ተባብረው እኛን ከምድረገጽ በማጥፋት።
  ሳንዘናጋ እንነሳ ለህልውናችን፣
  አለበለዚያ ወዮልን፣ ወዮልን።”

  ገና አሁን ችግርህን እየተገነዘብክ የመጣህ ትመስላለህ፣ Gratulation
  ‘የጥበብ መጀመርያ ራስን ማወቅ ነው’
  ወይንም ፈረንጆቹ እንዲሉት Selbsterkenntnis
  ጥላሁን ገሰሰም በ’Vulgarität መልኩ:
  “ራስን አውቆ መኖር ጥሩ ነው፣ ታላቅ ችሎታ ነው” ብሎት ነበር
  እንግዲህ አሁን የሚጎልህ፣ ሌሎቹም በየበኩላቸው እንዳንተው እንደሚሉና፣ መፍትሄው ከእነሱ ጋር በመግባባት እንደሚመጣ እንጂ እነሱን ዝቅ-ዝቅ በማድረግ እንደማይሆን ብቻ ነው! ይህ ከተሟላ ኢትዮጵያም ተረፈች ወዳነች ማለት ነው!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.