ኢትዮጵያዊነት ጥፋት ከሆነ፣ የአማራ ጥፋቱ ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው !!

አማራ! ዘመናትን የዋጀ የሃገር ምስረታ ታሪክ ያለው ታላቅ እና ኩሩ ህዝብ ፤ ዳር ድንበሩን ለማስከበር ገና ከጅምሩ የመሳሪያን ጥቅም ተርድቶ ነፍጥ ያነገበ፣ ነፍጠኛ የሚል የሃገር ኩራት ማዕረግን የተሸለመ ጀግና እና አይደፈሬ ኢትዮጵያዊ ነው። የዚህን ህዝብ ስሪተ-መዋቅር አያሌ የውጭ ጸሃፊዎች ባስደማሚ ብዕራቸው እውነቱን ሳይሸራረፉ ከትበውታል። የኢትዮጵያን ለዓያሌ የውጭ ሃያላን መንግስታት አልገዛም ባይነት ቁጥር አንድ ተጠያቂ አድርገው የሚከሱትም፡ የሚያሞካሹትም ይህንኑ ህዝብ ነው።
unnamed 13 925x1024 ኢትዮጵያዊነት ጥፋት ከሆነ፣ የአማራ ጥፋቱ ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው !!ይህ ክብር እና ሞገስ የሚገባው ሰፊ ኢትዮጵያዊ ላለፉት ዓርባ እና ሃምሳ አመታት ለፖለቲካ ፍጆታ እንዲውል ታቅዶ በረቀቀ ፋሽስታዊ የትህነግ የፖለቲካ ሰነድና ይሄን ተመርኩዞ በጸደቀ ‘’ሕገ- መንግስት ‘‘ እጅግ ዘግናኝ የሆነ የዘር ማጽዳት ጥቃት ሰለባ ሁኗል። ለማመን በሚከብድም ሁናቴ ሲሳደድ፣ ሲገደል፣ ሲጨፈጨፍ፣ ሲፈናቀል፣ ሲዋረድ እና ሲሰደብ ኖሯል። ሃገር እንደ ሃገር መሰረቷ ተናግቶ ወደለየለት የመፈራረስ አደጋ እንዳትገባ አማራው እንደ አማራ ያልከፈለው ተዘርዝሮ የማያልቅ መስዋትነት የለም። ለመስማት የሚከብድ፣ ለማየት የሚቀፍ፣ ለማመን የሚቸግር ወንጀሎች ተፈጽመውበት “ሃገር አንድ ሁና እንድትቀጥል” በሚል እሳቤ መከራን የቻለ ህዝብ በመላው ዓለም ቢፈለግ እንደ አማራው አለ ለማለት ይከብዳል።
የአማራው ጥፋቱ ኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ነው። ጽንፈኞች ባንድም በሌላም መንገድ እንድትፈራረስ ቀን ከሌት የሚተጉላትን ሃገር አማራው ከግባችን መሰናክል ሆኖናል ሲሉ ያልተፈጠረ፣ ያልነበረ፣ ያልተመዘገበ እና  እጅግ ከእውነት የራቀ የውሸት ትርክትን በ ‘’ሕገ- መንግስት’’ አስደግፈው መንበረ ስልጣኑን በመቆጣጠር የመከራውን ጎርፍ ከጀመሩ ዘመናት ተቆጠሩ። ለድፍን ሰላሳ አመታትም ይህን የውሸት ትርክት ትምህርታዊ ቅርጽ በማስያዘም ጭምር በአራቱም የሃገሪቱ ማእዘናት አዳረሱ።
እጅግ በጣም የሚያሳዝነው፤ በወቅቱ ይሄን ሰፊ ህዝብ እንወክላለን ያሉ ጉግ ማንጉጎች የአማራውን ጨቋኝነት በደስታ እና በፌሽታ ተቀብለው አጨብጭበው ማጽደቃቸው ነበር። እነሱ የሰሩት ግፍ እና በደል ይሄው እስካሁን ድረስ ለአማራው ዘርፈ-ብዙ እልቂት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል። ሃዘናችንን እጥፍ ድርብ የሚያደርገውም አሁንም ድረስ ያልነቁና ህመሙ እና ዋይታው የማይሰማቸው ሆነው መቀጠላቸው ነው። ፈጽሞ አማራው ከተሰራበት ስሪት ያልፈለቁ መሆናቸውንም በተከታታይ በድርጊታቸው “እያበሰሩን” ይገኛሉ።
መተከል የጎጃም/አማራ ርስት መሆኑን እንኳ ዘንግተው ተደጋጋሚ የሆነ የዘር ፍጅት ሲፈጸምበት ከውይይት የዘለለ ተጨባጭ መፍትሄ ማምጣት የተሳናቸው እጅግ ደካሞች መሆናቸውንም አሳይተውናል!
ለውጥ ላይ ነን ያለው የአብይ መንግስትም ችግኝ ከመትከል እና ከመፎከር የዘለለ አንዳችም ተጨባጭ ዘላቂ መፍትሄ ሲያመጣ አልታየም። ይባስ ብሎ ለአንድ ክልል ብለን ”ሕገ- መንግስት”  አንቀይርም የሚል ጥላቻ የተሞላበት ንግግር እስከማድረግ የደረሰበት ሁኔታን ታዝበናል።
በመተከል ውስጥ አብዛኛው ኗሪ/ተወላጅ አማራው እና አገው በሆነበትና መተከል ራሱ የቀድሞ የጎጃም ግዛት መሆኑ እየታወቀ ከአፓርታይድ አገዛዝ ባልተናነሰ መልኩ በክልሉ ‘’ሕገ-መንግስት’’ ላይ የሰፈረውን የባለቤትነት መብት እጅግ አድርገን የምንቃወመው እና የምንታገለው መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን!!
በተከታታይ በዚህ አለምአቀፍ ዘርን የማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ፣ ሆን ብለው በዝምታ የተመለከቱ እና ድርጊቱን ለማድበስበስ የሚሞክሩ የመንግስት አካላት እና ደጋፊዎቻቸው ከፍርድና ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ድርጅታችን ማስገንዘብ ይፈልጋል።
ድርጅታችን ጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር በተከታታይ በየቦታው በአማራው ላይ የሚደርሰውን በደል እጅግ አድርጎ ያወግዛል። ካሁን በኋላም ህዝቡ የሚጠብቀኝ/የሚደርስልኝ የመንግስት አካል አለ ብሎ መዘናጋቱን እንዲያቆምና አባቶቻችን እንዳስተማሩን ራሱን በአካባቢው በተመረጠ የጎበዝ ዓለቃ ስር በማደራጀት እንዲመክት ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ፈጠሪ በግፍ የተሰውትን ነፍስ በሰላም ያሳርፍልን! ለመላው ህዝባችንና ለቅርብ ቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ያድልልን!
ጎጃም ዓለምአቀፍ ትብብር
ዋሽንግተን ዲሲ፤ አሜሪካ
September 22, 2020

1 Comment

  1. ክብር ለመከላከያ ሰራዊት አንዱን ባንዳና ጁንታ ሲገላገል ወደ ሌላ ኦፕሬሽን ቤኒሻንጉል፣ ሱዳን፣ ወለጋ እንዲህ እንዲህ ብሎ ከጠራ በኃላ ኢትዮጵያ እንደአገር በሰላም የምትቀጥልበት ጊዜ በአምላክ ፈቃድ መምጣቱ አይቀሬ ነው፡፡ አለአግባብ በግፍ ለተገደሉት ምስኪን ህዝቦች ስትሉ ለምትሰው የሰራዊቱ አባላት ክብር ለናንተ ይገባል፡፡ ዘግይቶ ቢሆንም አሁን ቤኒሻንጉል፣ መተከል፣ ወለጋ ኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ያለ እርምጃ የህዝብን የሁል ጊዜ እሮሮ እና እንባ የሚመልስ ነው፡፡ አሁንም በሚደረገው ኦፒሬሽን የሰንሰለቱ እርዝራዞችን በደንብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከያሉበት ማደን ያስፈልጋል፡፡ ይህን ጊዜ ነው ደማቸው አለአግባብ ለፈሰሰው ካሳ የምትከፍሉት፡፡

    ጀግኖች የኢትዮጵያ ልጆች በርቱ በምታደርጉት ኦፕሬሽን ህዝብ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አምላክም ይረዳችኃል፡፡
    ምንም እንኩዋን የአገር ውስጥ ባንዳዎች እና የቅርብ ጎረቤት ጠላት አገሮች የፈለጉንት ቢመኙም በዚህ ትግላችሁ አገሪቷ ሰላም የምትሆንበት ቀን ሩቅ አይሆንም በውጤቱም የሁሉም ልጆች ሳይሣቀቁ የሚኖሩባት፣ አዛውንቶች ሰላም አግኝተው ምረቃት የሚሰጡበት ሌላውም በዘር፣ ሃይሞኖት፣ ብሔር እንዲሁም አድርባይነትን እና ወገናዊነትን ተላቆ ሰላማዊ አገር እንደሚፈጠር ምኞቱ ነው፡፡

    ክብር ለጀግናው ሰራዊት!!

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.