ኢትዮጵያ ኦሮሞን እድትመስል ወይንም ኦሮሙማ እውን እንዲሆን አማራና እሴቶቹ መጥፋት አለባቸውን ?

132418175 10223964126361762 6366457812133501636 nትህንግ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋት ማኒፌስቶ አዘጋጅታ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች 40 ዓመት ያለፋት ሲሆን ከ 1995 ዓም ጀምሮ የዓላማዋ ተጋሪ ከሆነው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ ራሱን ከሰየመው ጽንፈኛ ድርጅት ጋር በመሆን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ዘመቻውን ህገመንግሥታዊ እውቅና እንዲኖረው በማድረግ በየቦታው ክልል ብለው በሰየሙት የአማራውን ተወላጅ ፈጅተውታል ። አሁንም ለውጥ መጥቷል ብሎ ከአፍ ወደ እጅ የሆነውን ኑሮ በሰላም እመራለሁ ብሎ ላይ ታች የሚለውን መከረኛ አማራ አነተ ካልተወገድክ ፣ ቋንቋህና እምነትህ ካልጠፉ ኢትዮጵያ ኦሮሞን መምሰል ( ኦሮሙማን ) መተግበር አንችልም ከሚል እምነት ተረኞቹ ዳግማዊ ኢሃዴጎች መልከጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ ራሳቸውን ‘’ብልጽግና‘’ ብለው የሰየሙ ዘረኞች ህወሀት በ27 ዓመት ከፈጀው አማራ የላቀ ሶስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፈጅተውታል ።

ያልዘሩት አይበቅልም እንዲሉ የህወሃት ውላጅ የሆኑ የኦህደድ ( ‘’የኦሮሞ ብልጽግና’’ ) አመራሮች ፖለቲካ ማለት የማስተዳደር ጥበብ መሆኑ ቀርቶ ቁማር ፣ ማጭበርበርና መዋሸት እንደሆነ በገሀድ እየነገሩን እንደ ፈጣሪአቸው በቁማር የበሉ እየመሰላቸው እየተበሉ ፤ ያጭበረበሩ መስሏቸው እየተጭበረበሩ ፤ ሌላውን የዋሹ እየመሰላቸው ራሳቸውን እየዋሹ በተረኝነት የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዘውታል ።

ለውጡ እንደት እንደመጣና እነ ማን ህይወታቸውን ገብረው እንዳመጡት የማናውቅ ይመስል እንደ ዶክተር አብይና እንደ አቶ ለማ መገርሳ ያሉ ‘’ነፍሳችንን አስይዘን ያመጣነው ለውጥ ነው’’ ብለው አይናቸውን በጨው አጥበው ሲዋሹን እስኪ እንያቸው ብለን አልፈን ነበር ። እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ ኦቦ ለማ መገርሳ እንደ ጥዋት ጤዛ ውሎ ሳያድር ረገፉ ። ዶክተር አብይ እንደ አፋፍ ላይ ዛፍ ንፋስ ያለ እረፍት ሲያወዛውዛቸው ማየቱ የእለት ተእለት ተግባራችን ሆኗል ።

አማራውን ከኢትዮጵያ መድር በማጥፋት ኦሮሙማን ለመመስረት ያለ ስንቅ የዘመተ ማንኛውም ዘረኛ ቡድን ሊያውቀው የሚገባው ነገር አማራን ፣ አማርኛንና የኦርቶዶክ ተወህዶ እምነትን ማጥፋት ይቅርና ማዳከም እንኳን እንደማይችል ነው ።

ዶክተር አብይ እውነት ኢትዮጵያና ሕዝቧን ለመታደግ ቁርጥ አቋም ካላቸው የሚያሳዩትን ሁለት ፊት ትተው ማስኩን ( ጭንብሉን በማውለቅ ) የሚያምኑትን ለመተግበር ትክክለኛ ፍታቸውን ቢያሳዩ የሚደግፋቸው እስከ ግቡ ይከተላቸዋል ። በተለይም በአሮጌ አቁማዳ አዲስ ወይነ ጠጅ ጨምረው ሩቅ መጓዝ አይችሉም ። ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር በቀድሞው እርሶም በነበሩት አስተዳደር ወቅት እጃቸው በሌብነትና በሰው ደም የጨቀዩ ባለስልጣናት ይዘውና እርስ በርሳቸው ሲጠፋፉ የነበሩ የስልሳዎችን የሴራ ፖለቲክኞችን አማካሪ አድርገው አስቀምጠው ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ይኖሮታል ብሎ ማመን እስካሁን ከታዘብነው ተግባርዎ ጋር ተዳምሮ የማይታሰብ ነው ።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር የህዝብን አመኔት የሚያገኙት ለታመመቺው አገራችን ማስታገሻ ሳይሆን መፈወሻ መድኃኒት ሲሰጡ ነው ። ይሔውም የከፋፍለንን ሕገመንግሥት ለሕዝብ አቅርበው እንዲቀየር ማድረግና የሚያጨራርሰንን የጎሳ ፌደራሊዝም በጂኦግራፊያዊ የአስተዳደር ጠገግ እኔ አውቅልሀለሁ በሚሉ ያረጁ ጅቦች ፍላጎት ሳይሆን በሕዝብ ተሳትፎ እውን እንዲሆን ማድረግ እንጂ ሰላም እንደ ሰማይ የራቀውን ሕዝብ መዋሸትና ማደናገር መፍትሔ አይሆንም ።

ከድሉ ዘገዬ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.