ይድረስ አቢይ ይውረድ ለምትሉ ግራ የገባችሁም ሀቀኛ ዜጎች፣ሞርቱዎች  በያላችሁበት – ከአባዊርቱ

abiy 1እስቲ በዚህ መንደርደርያ ልጀምር!
ያልታደለች ሀገር፣ ያልታደለ ህዝብ ፣ ፈጣሪ አፈር በላሱበት አፈሩ አይቅለላቸውና እነዚህ ጅቦች አገሬን የሰው ምድረ በዳ አድርገው እንደጉም ቢተኑም፣ የነሱው ጀላባቴዎች ቁምስቅላችንን ማሳየታቸው ገና መጀመሩ ነው እኮ። ገና ምኑ ታይቶ? ከ 40 አመታት በላይ የኢትዮጽያዊነት ጠረኑ ጠፍቶ ገና አሁን እንደ ጥቅምት አበባ ማቆጥቆጥ ሲጀምር ነዘራችሁ አይደል? የት ነበራችሁ ከ ሶስት አመታት በፊት? እንዴት ይረሳል አቢይ አህመድ ባለፈው ፓርላማው ላይ ያጫወተን ጉዳይና ያሳለፈው መከራ? እስቲ ለሁላችንም ትምህርት ይሆነን ዘንድ አቶ ግርማ ከጠየቀው በመነሳት እንዲህ ልበል፣
1) አቶ ግርማ እንዳለው
እኔ እንደ አንድ ተራ ጦማሪ ለምንድን ነው ጠ/ሩ ቢለቅ ጥሩ ነው የምለው ? ለምንድን ነው የአብኑ አመራር ዶር ደሳለኝ ጫኔ ጋር የምስማማው ? ምክንያቶቼ እንሆ፡
አንደኛ ላለፉት ሁለት አመት ከ10 ወር (ሶስት አመት በሉት) አገሪቷን እየመራ ማመን በማይቻል መጠን፣ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት፣ እጅግ በጣም በርካታ ዘር ተኮር ጥቃቶች፣ ግጭቶች የዘር ማጥፋት ወንጀሎች እንዳይፈጸሙ መከላከል ባለመቻሉ ነው፡፡
መልስ
፩) ግሩም ነው. ሲጀመር ተራ ጦማሪ ብሎ የለም ባገር ጉዳይ ሁሉም ዋና ተጠሪ ነው። ሆኖም የአብኑን ጫኔ ዋቢ ማድረግህ በራሱ ብቃትህን ይመሰክራል። የአብኑ ጫኔ አቁዋቁዋሙን እያሳመረ በቃላት ዲሽቃ አቢይን  ከመጎሸም በዘለለ ባለፉት ሶስት አመታት የዘር ተኮር ፍጅት እንዲቆም ምን ያደረገው ኮንትሪቡሽን ነበር? ማን ይሙት አቢይ እንዲያ በካቴና የፊጥኝ ታስሮ ለኢትዮጽያ የዋለውን ውለታ ሲሶዋንስ ያደርጋት ነበር? ሲያዩት ያምር ሲይዙት ያደናግር እንዲሉ——
አቶ ግርማ
፣2) የመጀመሪያው ስድስት ወር ሕወሃቶች አላሰራ ብለውት ነበር እንበል፡፡በኋላ እነ ጌታቸው አሰፋ ወደ መቀሌ ተባረሩ፡፡ የኢህአዴግ እህት ድርጅቶችም ተዋሃድን ብለው ብልጽግና ፓርቲን ከመመስረታቸው በፊት፣ በኦህዴድ ውስጥ እነ ለማ መገርሳ አላሰራ ብለውት ነበር ብለን እንለፈው፡፡ (ያኔ እነ ጃዋርም ኦህዴድ ውስጥ ስለነበሩበት) ብልጽግና ከተመሰረተ በኋላ ግን ላለፉት አንድ አመት የፓርቲው፣ የመከላከያው፣ የፓርላማው፣ የበርካታ ክልሎች ድጋፍ ነበረው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ግን በብልጽግና ፓርቲ አመራር ነገሮች በጣም ተባባሱ፡፡ እኔ እንደው Prosperity Partyን GEP ( Genocide Enabler Party) ብዬ ሁሉ ስያሜ ሰጥቼዋለሁ፡፡
ስለዚህ በዚህ ሁኔታ ዶር አብይ በመሪነት ተቀምጦ ነገ ሌሎች መተከሎች፣ ነገ ሌሎች ጉሊሶዎች አይከሰቱም የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለዚህ ነው ታች ያሉትን ብቻ በማሰርና በመለዋወጥ ችግሩ አይፈታም ፣ ከላይ ከቁጮው ለውጥ መደረግ አለበት፣ በተለይም የፌዴራል መንግስቱ ከኦሮሞ ብልጽግናዎች ተጽኖ መላቀቅ አለበት የምለው፡፡
መልስ
፪) አጃኢባ ረቢ ነው! የመጀመርያው መንፈቅ  ይሁን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ እውን የወያኔ ሰንኮፍ ተነቅሎ አለቀና አቢይ ላይ እንዲህ አይነት “ቅባት” ለመለጠፍ የዳዳህ? ከአዴፓው ይሁን ኦዴፓው ከርሰምድር እውን ወያኔ ፀድቱዋል በሙሉ? ከቀበሌ እስከ ወረዳ ፣ ከባንክ እስከ ንግድ ተቁዋራጭ ፣ ከኮንስትራክሺን እስከ ኢንፍራስትራክቸር ምን ስር ነቀል ለውጥ መጣና ነውስ? የሰዎቹ የደናቁርት ጉልቶች ዛሬስ ቢሆን ተንሰራፍተው ኢኮኖሚውን ሆነ ፖለቲካውን ሳቦታጅ እያደረጉ የአቢይን ጅራት እየጎተቱ በአይናችን እያየን ልታሞኘን ትፈልጋለህን? እኔ አልሞኝም። የከዚህ ቀደሙም ይቆጨኛል። ገና ለገና ይሉኝታን ፈርቼ ዝም አልላችሁም።
አቶ ግርማ
3) ሁለተኛ ዶር አብህይ አህመድ “ትግሬ፣ ኦሮሞ አማራ መባባል ያተረፈልን ድህነትና እከክ ነው” ቢልም አገሪቷን ከዘር ፖለቲካ ለማውጣት ከንግግር ያለፈ መሰረታዊ የሆነ የፖሊሲ የሕግ ማሻሻያዎችን አላደረገም ብቻ ሳይሆን ለማድረገም ማሰቡን የሚያመለከት ምንም ነገር አላየሁም፡፡
ሲሳይ አጌና ተቀዳዶ መጣል ያለበት ያለው፣ ዶር ኅይሌ ላሬቦ ኮተት ያሉት ዘረኛ ሕግ መንግስት፣ ዘረኛ አወቃቀርን የመለወጥ ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ ነገር አላየሁም፡፡ እንደውም የርሱ ድርጅት ፣ የኦሮሞ ብልግጽግና ከፍተኛ አመራሮች በይፋ ነው አሁን ያለው ሕገ መንግስት ችግር የለበትም እያሉን ያሉት፡፡ ስለዚህ በዶር አብይ አመራር የሕወሃት ሕገ መንግስትና አወቃቀር ይቀጥላል የሚል እምነት ስላለኝ የርሱ መነሳት አስፈላጊ ነው ወደ ሚል ድምዳሜ ደርሻለሁ፡፡
መልስ
፫) ቀሽም ድምዳሜና አቢይ ያለበትን ፈተና በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ አባባል ይመስለኛል። ለመሆኑ ከንግግር ባለፈ ለውጥ ለማምጣት ማንን ይዞ ነው? ምንድን ነበር በተለይ ፊደል የቆጠረው ህብረተሰባችን የጠበቀው? ስንት እንደ አብይ የሚያስብ ዋላ ብልፅግና ውስጥ ይሁን ውጭ አይተሀል/ሰምተሀል? እኔማ ቁጥራቸው በየቀኑ እጅግ እየመነመነብኝ ተቸግሬ ሰው መጥራት ሁሉ አቁሜ፣ ግራ ተጋብቼ በሀዘን ከተሳታፊነት ሁሉ እራሴን ካራንቲን ካስገባሁ ሰነባበትኩ። አንድ ታዬ ደንደአ አለኝ የምለውም ሰውዬ ግልፍተኛ እየሆነብኝ ግራ አጋብቶኛል። ለመሆኑ አቢይን አውርደህ ማንን ልትሰቅልልኝ አስበሀል በኢትዮጽያ አምላክ? አንድ ሰሞን እባክህን አገርቤት ተመልሰህ አማክርልኝ ያልኩትን ሻለቃ ዳዊት አይነት መላ ያጣ ክስ አስመሰልክብኝ። ማን ይምጣላችሁ  በዚህ ፈተና ዘመን? ጫኔውን ብለህ ወገባችንን ቁረጠው ።የህውሀት ህገመንግስት በግለሰብ ፍላጎት የሚወሰን አይሆንም መቼስ በዴሞክራሲ ምርጫ ከሆነ። እዚህ ላይ ሳታውቀው ተንፍሰሀል። አቢይ የህውሀትን ህገመንግስት የሚያስቀጥለው ቅቡልነቱ ሳይታለም የተፈታ መሆኑን አምነሀል ማለት ነውና። ይህ በእንዲህ እያለ ያም ቢሆን መቼስ የመማክርት ሸንጎ ሳይመክርበት አቢይ ኢዲአሚን አይደለም ይህን የሚያደርገው። ስለሆነም ስሜታዊ ድምዳሜህን ዳግም ፈትሸው ወንድሜ። ሌላው ባትለውም ሌሎች እንደሚሉት በደቦ እናስተዳድር ጊዜያዊ ሸንጎ አቁዋቁመን ከሆነ ለቦዘኔ ፖለቲከኞች የስራ እድል መክፈቻ ካልሆነ በቀር ለኢትዮጵያ ምንም የሚፈይደው አይኖርም። ይህው ነው ሀቁ።
አቶ ግርማ
4) ሶስተኛ ዶር አብይ የተከበበው በነ ሺመልስ አብዲሳ ነው፡፡ የርሱ ሹመኞች እነ ፍቃዱ ጸጋ ናቸው፣ እነ እስክንድርን በውሸትና በፈጠራ ክስ የሚከሱ፡፡ እነ ታከለ ኡማ ናቸው ዘረኛና አፓርታይዳዊ አሰራርን ዘርግተው ፍቅር የነበረችዋን ሸገር የመቃቃር ከተማ ያደረጓት፡፡ እስቲ አስቡት ዶር አብይ አሁንም በነ ሺመለስ አብዲሳ ተከቦ፣ የርሱ አቃቤ ሕጎች እነ እስክንድር ነጋ በዉሸት ክስ እያሰቃዩና እያንገላቱ እንዴት ነው ላምነው የምችለው ?????
የዘር ፖለቲካ አራማጆችና ጎጠኞች ዶር አብይ መቀየር የለበትም ቢሉ የሚፈልጉትን ፖለቲካ ስለሆነ እያስቀጠለ ያለው ይገባኛል፡፡
ሌሎች ግን ኢትዮጵያ በልጆቿ ደም እንድትጨማለቅ ያደረገውን የዘር ፖለቲካ ለማስቀረት፣ ሕገ መንግስቱን ለማሻሻል፣ ሁሉም ኢትዮጵያዉያን ዘራቸውና ኃይማኖታቸው ሳይጠየቅ በሁሉም የአገሪቷ ግዛት በሰላም ለመኖር እንዲችሉ የሚያስችል፣ ዘር ላይ ያላተኮረ አወቃቀር እንዲኖር እና እውነተኛ ፍትህ በአገራችን እንዲሰፍን ለማድረግ ዶር አብይ አህመድ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ቁርጠኝነቱ እንዳለው የሚያሳይ፣ ትንሽ ፣ ከንግግር ያለፈ፣ ተግባራዊ ማረጋገጫ ከሰጣችሁኝ ፣ እመኑኝ ፣ እንኳን ዶር አብይ ከስልጣኑ ይልቀቅ ልል ወገቤን ታጥቄ ነበር የምደግፈው፡፡
ያኔም ለዶር አብይ ድጋፍ ስሰጥ በምክንያት ነበር፡፡ የሚናገራቸው መልካም ንግግሮቹ ተስፋ ስለሰጡኝ፡፡ አሁን ደግሞ ስቃወመው በምክንያት ነው፤ ንግግሮች ስለሰለቹኝና ከንግግሮቹ በተቃራኒው ተግባራዊ አመራሮቹ እያስከተለ ያለው ጥፋቶች መቆም አለባቸው ስለምል፡፡
አሁንም በድጋሜ እላለሁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቅ የለበትም የምትሉ አሳምኑ፡፡ በጭፍን ወያኔ የጁንታው ልጆች ማለት አያዋጣም፡፡ ጠ/ሩ ራሱ ከአስርተ አመታት ከሕወሃትች ጋ ሲሰራ እኛ ሕወሃትን ስንታገል ነበር፡፡ ይልቅ በመረጃ አሳምኑን፡፡ የምር ከላይ እንዳልኩት ካሳመናችሁኝ ሀሳቤን መለወጥ አይደለም እንደው ደጋፊ ነው የምሆነው፡፡
፬) መልስ
አቶ ግርማ እንደወገን ኢትዮጽያዊ (with respect) ዶር አቢይ  ጭፍን ድጋፍ ይሁን ጭፍን ቅዋሜ የሚፈልግ አይነት ሰው መስሎ አይታየኝም በዚች ሶስት አመታት እድሜ ሳውቀው። መላቅዱሱ የጠፋበት በተለይ የተማረው ክፍል ሲዝረከርክበት ልቡ እንደሚደማ ግን አስባለሁ። አንተ ብቻ አይደለህም ብዙዎች ከኔው ወዳጆች በዚህ ጉዳይ ተቃቅረናል። እንዴት ማየት ይሳናችሁዋል? አቢይ አይደለም በሺመልስ አብዲሣ በለውጡ ሀዋርያ ለማስ ተከቦ አልነበረም? በማ ይከበብ ታድያ? ለ 40አመታት በአገሬ ላይ የዘር ፖለቲካ ጢባጢቤ ሲጫወት ኖሮ ምሩቃኑ  ሁሉ ከአንድ ሰንበቴ ገንቦ ሲጠጡ የኖሩ ሆነው ፈጣሪ ይህን ድንቅ ልጅ ከመሀላቸው መንጥቆ መሀላችን ቢጥልልንና የኢትዮዮጵያዊነት ጠረን ከአስከሬን ቀዳዳ  መሀል መሽተት ሲጀምር ያቅበዘብዛችሁ ጀመር። ከዬት ይምጣ የመንግስትን እርከን የሚረግጥ ከመንግስት ውጭ? መሬት ላይ ባለው ህገመንግስት መሰረት እዛው ለ 40/አመታት ከሚርመጠመጡት ውስጥ አይደለም ወይ? እየተስተዋለ እንጅ ። በማንስ ማንዴት እንደምንስ ይህን ሀቅ መለወጥ ይችላል? አቢይ እኮ የዜናዊ ልጅ አይደለም የራሱን ፓርቲ እያማከረ የሚሰራ ቅንና ዴሞክራት ነው። እኔ አቢይን የማየው ብቻውን የተዛባውን ለማቅናት ደፋቀና የሚል ቆፍጣና ወታደር አድርጌ ነው። የገባው ሰው ነው። የሁሉንም ሴራ ያውቃል ታድያ። ብርታት የሚሰጠኝ ይህ ብሩህ አይምሮው ነው።
ማጠቃለያ!
በዛሬው ቀንም ሆነ ለሚቀጥሉት በትንሹ አራት አመታት ባለው የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አቢይን ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ብሎ ያመጣው ድንቅ መሪ ነው። ድንቅነቱም እንዲህ ነውና
ሀ) ትእግስቱና የኢትዮጵያዊያንን ጭንቅላት የመረዳት ክህሎቱ ። በትእግስቱ መስሎኝ የማይደረመሰው የፅልመትን ሰራዊት ድባቅ የመታው። ኩራት ለመከላከያ ስንል ዋናው ኤታማዦር አቢይ መሆኑን ልብ በሉልኝ።
ለ) በመተከልም ይሁን በማይካድራ በከሀዲዎች የታረዱትና የሚታረዱት ጫኔ በለው ብርሀኑ ነጋ፣ መረራ በለው በየነ ጴጥሮስ ማንም ይሁን ሊያስቆመው አይችልም ። ለምን የአርባ አመታት የስራ ፍሬ  ነውና የተቃመስነው። እንደውም አቢይ አባመላው ባይሆን የሩዋንዳውን እልቂት ላለመደገሙእሰጋለሁ። እስቲ ማን አሰበ ከባለ ማተቦቹ ትግራዋይ አርዮስ ይፈልቃል ብሎ? በፈጣሪ አምሳል የተፈጠረን የሰው ልጅ እንደበሬ የሚበልትና የሚያቅራራ?
እንደኔ ምኞት ቢሆን ኢትዮጵያዊ የሆነ በተለይም በዳያስፖራ ያለ የቻለ በእውቀትና ገንዘብ፣ ያልቻለ በፀሎትና ትእግስት ይህን ድንቅ ሰውዬ መርዳት አለበት። ዛሬን ላይ ሆኖ ፣ ያለፉትን ሶስት አመታት የቃኘና ይህ ድንቅ ሰው ያሳለፈውን ፈተና ለተረዳ አለማድነቅ ወይ ለየት ያለ የፅልመት አጀንዳ ማራገብ ነው (ሳርቅጠሉ የነሱው አንጋች ነውና) ወይም የነገርዬውን አስከፊነት ካለመረዳት ነው፣ ወይም ከፍ ያለ ለምን ይህ ሰው በአይምሮ በለጠን ምቀኝነት ነው። ሌላ ምንም ማለት አልችልም ። የዛሬ ሁለት አመት 42 ትውልደ ኢትዮጵያዊ ምሁራን የባልደራሱ እስክንድር መከራ በላ ተብሎ አቢይ ላይ የቀረበው ማመልከቻ ትዝ አለኝ። ሰውዬው ያኔ (በቅርቡ በፓርላማው እንዳሰማን) የነበረበትን ውጥረት ዛሬን ላይ ሆነው ሲረዱት ምን ይሉ ይሆን እላለሁ። ያኔም እንዳልኩት ዛሬም የምደግመው ይህ እንደሰም እራሱን እያቀለጠ የድርሻውን የሚወጣ ዜጋ ቢያንስ ለማብጠልጠል ሀቅን ባትፈሩ ፈጣሪን ፍሩ።  እንደኔ ምኞት ቢሆን የነ ጄ ብርሀኑ ጁላ፣ አበባውና ባጫ ለየት ያለ ከዶር አቢይ የተጣመረ ወታደራዊ አስተዳደር ለ አራት አመት አሻግሮን ከዛ በሁዋላ ምርጫ ቢሆን እንዴት ባማረ? እንደው የደርግ ናፋቂ ትላላችሁ ብዬ እንጅ ። ደርግንም አውሬ ያደረገው ምሁር ተብዬው ነው እንጅ ከአጥናፉና ተፈሪ በንቲ በላይ ቅን ኢትዮጵያውያን አልነበሩም በዚያን ወቅት። አሁንም ቢሆን provisional national military council አቁዋቁመው ተጠሪነቱን ለፕሬዘደንቱዋ በማድረግ አዲስ ውቅር ማድረግ ይቻላል። ከዛ አገር ወዳድ ምሁር ዳያስፖራ ቴክኖክራቶችን ይህ ካውንስል እየቀጠረ ምድረ ደናቁርት የውጭ ሚስዮናችንን ያዘምናል። ከዛ በአገር ውስጥም ከሁሉ ዘርፍ እያዳቀለ በብቃት አመራር ያጎለብታል። እንደው ሁሉ ምርጫ የሚለው ለራሱ ነው እንጅ ለኢትዮጵያ አዋጭ ይህ ነበር። ። ምን ያደርጋል። እያረርንም ቢሆን እናዳምጥ እንጅ ።
በመጨረሻም!!
 ይህን እድሜውን ይሁን ምን ይሆን የማላውቀውን እንደዋዛ ያያችሁት አቢይ ወያኔ የተጨማለቀበትን  መከላከያ ተብዬ የሰንበቴ ቤት  በ 2 አመታት እፍርሶ መልሶ በኢትዮጵያ መሰረት ላይ ያቆመ ታላቅ መሪ ነው:: የተፈራውን ተራራውን ያንቀጠቀጠውን ወያኔን በ3 ሳምንታት የቀበረ ጀግና የጦር መሪ ነው:: አንተ ባታደንቀው ታሪክ ያደንቀዋል:: ለመሆኑ እሱ ይነሳ ብለህ የፌስቡክ አርበኞችህን ስታሰልፍ ስንት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንደሚደግፉት አጣርተሀል?? አዳሜን የጨነቀው በመጪው ምርጫ የስራ እድል ማጣቱን እንጅ የዚች ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ግድ የሚለው በቁጥር ነው። በተለይ እድሜው ከ አርባ አመት መለስ ያለ “ምሁር” ተብዬ ሁላ። የአየር ባየር እውቀትና ዝርፍያ ብሎም ማላገጥን ይዞ እንደምንስ በደም ባጥንታችን ስላቆየናት ኢትዮጵያ ግድ ይለው ኖረዋል? ያሳዝናል። ባለፈው አቢይ ተቃዋሚ ተብዬን ሁሉ ሲጋብዝ የአልጋና የአስቤዛ ከደሀው ጉሮሮ በየአገሩ የቀፈለውን ሲያበላ ምድረ ተቃዋሚ ተብዬ የጨነቀው በምርጫው ማግስት ስለሚቀራመተው ስልጣን እንጅ ይህ ሰው በውስጥ ስለነበረበት መከራ የተረዳው አልነበረም። ዛሬም ብዙዎች አልተረዱም። ጭራሽ መተከል ደርሶ ሲመለስ “አማራን ለማስጠፋት በአይን ጠቅሶ ተመለሰ ” አይነት የወረደ አስተሳሰብ ፊደል ከቆጠረ መስማትና ማየት ያማል። ይህ ሰው ባለፈውም አምባቸውን ያስገደለ ተብሎ እንዳልታማ። የነበረበት የወያኔ የጭንቅ የቁም እስረኛ ሆኖ ሊያውም ። እንግዲህ ለናንተ ብሎ አይሰዋ ነገር ፈጣሪ ኢትዮጵያን ያስባታልና አስቸጋሪ ነው።  ሁሉ ወደቀልቡ ይመለስ ዘንድ ግን የዘወትር ፀሎቴ ነው።
የግርጌ ማስታወሻ!
ክቡር አቢይ አህመድ ሆነ ማንም ሰው አባዊርቱን አያስተዳድርም ከህሊናው በቀር።  ለዳረጎትም የማልመች ነኝና። ይህው ነው። የፈለጋችሁትን ለማለት ግን መብታችሁ ነው። አበቃሁ።

7 Comments

 1. እንግዲህ ይኅው ነው፤፤ ልብ ያለው ልብ ይበል! ስለ አቢይ ሚሊዮኖች – “silent majority” – የአባዊርቱን ሃሳብ ይጋራሉ፤፤ Nothing personal but Ethiopia must prevail!

  “አጃኢባ ረቢ…..” ይቺን ቃል እንደመርሳት ብዬ ነበር፤ በትዝታ ወደኋላ ወሰደችኝ፤፤

 2. ያስብኩትን በሙሉ በተባ ብዕርህ ገለፅህልኝ።ዘርህ ይለምልም አባዊርቱ፣ሌላ የምለው የለኝም። መሪ ይነሳ ቀላል ነው! ማን ይተካው ነው? ትልቁ ጥያቄ። አንድ ቀበሌ አስተዳድሮ የማያውቅ ሁላ ይወሽክታል።በርታ አቢቹ፣ አጠገብህ ያሉ አስዳቢዎችን እያፀዳህ ወደፊት ተራመድ፣ ልብህ ንፁህ ስለሆነ፣እግዚአብሄር ይርዳህ።

 3. I am very much pleased that I read my friend’s piece after so many times, after his “quarantine”, as he himself correctly said it. I was worrying as to how he was silent for so long. But now thanks God, I have got him. There are other writers also who disappeared, like Yigerem Alemu, who had been one of my favorites.
  Thanks Abbawirtu, and welcome back. I read your piece with enthusiasm, though my stand is a bit different from that of yours. I absolutely understand that we are brothers. This time will definitely pass; we were not here some 100 years back. We have the right to express our views in modesty irrespective of any difference we might have. But one thing we have to realize should be, let’s not generous in badmouthing and giving names and labeling. Otherwise, it is not abnormal even to love Satan, live alone one among humans. I don’t mean anyone mentioned in this piece is Satan by the way. And I wish God would visit Dr. Abiy soon and change his mindset so that ethnic politics gives way to humanity. I don’t fool myself, of course, Abiy is the best remedy for the solution of our problems. Actions speak more than words. Tantalizing speech has short span of life unless supported by equivalent mode of action.

 4. Thanks so much aba wirtu. We ethiopians are so cruel that we act against pm Abye Ahmed unfairly . Let almighty Allah support Dr. Abye and ethiopian people. I feel so sorryfor some people who hear people like Dawit w/Giorgis who work day and night for the interest of foreign countries. He was responsible for demise of ethiopian defence force during Derg time. He worked for foreign countries to enable tplf by taking over the power in ethiopia in 1991. Now he try to do the same job using some ethiopians. He is cruel!

 5. The only reason I demonize Derg is for murdering the ministers and high officials of Haile Selassie’s Government. Mind you, I am not condemning the military for taking over power from Haile Selassie because they innocently thought they can do better for Ethiopia. Other than that they did their best and achieved modest progress. They would have done better if it weren’t for Somali invasion and the secessionists EPLF and TPLF. Also EPRP and MEISON were big distactions. If it were not for all these fronts, the military dictatorship would have improved the living standards of our people. If Abiy is also given the chance, he would eventually bring peace to Ethiopia and raise the living standards of our citizens. Of course, he must be weaned from the likes of ethnicist Shimelis Abdissa. He must dissociate himself from ethnic interests and gravitate his party to Ethiopianism.

 6. አባ ዊርቱ ከዚህ መድረክ በመጥፋትህ እሆይ ብለን ነበር!የአብይ ደንገጡር ካድሬ ስለሆንክ ገና ለገና አብይ ይውረድ ሲባል እቅልህን የሳትህ ያህል ሆኖ ነው የትሰማኝ ::ምክንያቱም የተከበሩ አቶ ግርማ በምክንያታዊነት ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ ብለህ ስትሰጥ የስነፍ ተማሪ አራምባና ቆቦ ስትዳክር ለአንዱም ጥያቄ ሚዛናዊ መልስ ሳትሰጥ እንዲህ መባተለህ ወያኔ ከሲቪል ስርቪስ ኮሌጅ ምስለኔዎችን ሰነፎች ካድሬዎች አንዱ እንደሆንክ ተረዳሁ! ጥያቄውንና የሰጠኸውን መልስ ደግመህ ብታነበው ወይም አስተዋይ ስው ቢያነብልህ መልካም ነበር!እራስ መስክርም ሳትጠየቅ የአብይ ወፈር ያለ ዳረጎትና ወንበር ላይ ስላፈናጠጠህ ማስተዋሉ ቢርቅህ አይፈረድብህም!
  የእነ እስክንድር በእብይ ገና ከጅምሩ ጦር ያማዝዘናል ያለ ወቅት ነበር አብ ይን ሴረኛነት ኦነግነት የታወቀው!!አሁንም እነ እስክንድር በፈጠራ በአብይ ክስ ይንገላታሉ!አነ ዶር አምባቸው የሱ ስለባ ነሩ!
  ዛሬ ኢትዮጵያ በአለም ላይ ያልታየ ያልተስማ ዝርን የለየ ይአማራ ላይ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ከቶ ማስቆም አቅቶት ነው ብለህ ታስባለህ?አቃተው እንበል ለምን ስልጣን አይለቅም!ለምን?ኢትዮጵያ የመሪ ደሃ አይደለችም! እሱንም ያወቅነው ሃይለማርያም ስልጣኑን አቃተኝ ብሎ በመልቀቅ ነው!እሲት የሱማሌውን ክልል መሪ የተከብሩ ሙስጠፌን ተመክልክት ንፁህ ህሊና ካለህ?እጅግ ድንቅ መሪ ነው!ለምን እቶ ሙስጠፌ ለሀገር ስላም ሲባል ጠቅላይ ሚንስቴር ለን አይሆኑም!?የግድ ኦነግ መምራት አለበት?ኦነግና(አብይ) ወያኔ አይናቸው!አይበቃንም?ወደቴ እየሄድን ነው አባዊርቱ ?ወደ ገድል እገሪቱን ይዞ እይሄድ ነው!አብይ እጅግ መስሪ አስመሳይ ውሸታ ችሌታም የለውም!መትከል ላይ ስብሰባ መምራትና ችግር መፍታትም ችሎታም ፍላጎትም የለውም!
  አባዊርት ለአንተ ዳረጎትና ውንበር ሲባል አማር በገጀራ በአስቃቂ ሁኔታ መገል አለበት!ሁሉ ያልፋል አብይ ግን እራሱን ለትውልድ የዘለቀ የኦሮሙማ ሂትለር እየፈበረክ ይገኛል!በታደሉ አገራቸው ህዝባቸውን የሚወዱ ፈርያ እግዚአብሔር ያደረብቸው አስተዋይ መሪዋች ግን ስልጣናቸው አስቀድመው ሲለቁ የምናየው የምንሰማው?
  የአብይ ስልጣን መልቀቅ ወይም ፖርላማው መበተን ግድ ይላል!

 7. Abiy Ahmed made Ethiopia peaceful by eliminating the JUNTA . If we don’t want JUNTA to make a come back then we need to keep Abiy Ahmed in power , there is no other choice.

  VOTE FOR PROSPERITY!!
  SUPPORT PROSPERITY!!
  LEARN PROSPERITY!!
  PREACH/TEACH PROSPERITY!!
  DEFEND PROSPERITY!!
  BECOME PROSPEROUS!!
  SAY NO TO ANYTHING LESS THAN PROSPERITY!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.