በመተማ በኩል የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባው የሱዳን ሰራዊት በአብዛኛው ጃንጃዊድ የሚባለው ጦር እንደሆነ ተነገረ

sudan
መሪያቸውም ሃማዲ ይባላል::
የጃንጂዊድ ጦር የዳርፉርን አማፅያን ለመውጋት ከሰላሳ አመታት በፊት በአልበሽር አማካይነት እንደተቋቋመ ይታወቃል:: ጃንጃዌድ: “በፈረሶች ጀርባ የሚቀመጡ ሰይጣኖች’ በመባልም ይታወቃሉ:: እጅግ አረመኔ የሆነ የጦር ቡድን ሲሆን በዳርፉር የዘር ማጥፋት ፈፅሟል በሚል አሜሪካን ጨምሮ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ በሽብር እና በጦር ወንጀለኝነት የሚከሱት ቡድን ነበር:: በክሱ አልበሽርን ጨምሮ የጦሩ መሪዎችም መካተታቸው ይታወሳል:: ሰሞኑን ግን የአሜሪካ መንግስት ሱዳንን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ በይፋ መሰረዟ ታውቋል::
– የጃንጃዊድ ቡድን በቅጥር ነፍሰ ገዳይነት እንደተሰማራም ይነገራል:: ሰራዊቱ በቅጥር ነፍሰ ገዳይነት ተዋውለው በሊብያ እና በየመን እንዲሁም በቻድ ይገኛሉ:: ሰራዊቱን የሚመራው ሐማዲ ከወቅቱ የሱዳን የሽግግር ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር የላላ ግንኙነት ስላላቸው: ለሲቪል አስተዳደሩ ታዛዥ እንዳልሆኑ ይነገራል:: ከግብፅ እና ከሳዑዲ አረብያ ጋርም ውል ሳይኖራቸው እንደማይቀርም ይገመታል::
– በኢትዮጵያ ላይ ወረራ የፈፀመው ይህ ቡድን ከሱዳን መንግስት ይልቅ የግብፅን እና የሌሎች አገሮችን ፍላጎት ለማስፈፀም እንደዘመተ መጠርጠር አይከብድም::
– አስገራሚው እና ለሰሚው ግራ የሆነው ጉዳይ: በዚህ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ቡድን አማካይነት በደረሰው እልቂት እና የፀጥታ መታወክ ሳቢያ ኢትዮጵያ ከ 2 ሺህ በላይ ሰራዊቷን የበሱዳን ዳርፉር- አልፋሽር በሚባለው አካባቢ ሰላም ለማስከበር አሰማርታ ባለችበት በዚህ ወቅት: የሱዳን የጃንጃዊድ ሚሊሻዎች እስከ 25 ኪሜ ወደ ድንበራችን ዘልቀው በመግባት ሉአላዊነታችንን መዳፈራቸው ነው:: ዘበነ ግርምቢጥ ይሉሃል ይህ ነው::
ሳሙኤል በላቸው

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.