የቅጥር ማስታወቂያ በኢትዮጵያ አየር ኃይል መቀጠር ለምትፈልጉ:_

133867489 4129373887091579 7099241211211152073 n

ሀ/ አጠቃላይ የምልመላ መስፈርት

1) ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ
2) ከአሁን በፊት የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባል ያልነበሩ
3) በወንጀል ይሁን በፍትሕብሔር ተከሰው ክርክር የሌለባቸው
4) ኢትዮጵያዊ የሆኑ
5) ለአየር ኃይል አብራሪነት ቢያንስ ለ10 አመት፣ ለቴክኒሻንነት ቢያንስ ለ7 አመት ለመፈረም ፈቃደኛ የሆኑ
6) ትዳር ያልመሰረቱና ልጅ ያልወለዱ
7) የጤና ምርመራ የሚያልፉ
8) በአካባቢያቸው ሕብረተሰብ ተቀባይነት ያላቸውና ከአጉል ሱሶች የራቁ
9) በሚመለመሉበት ቦታ ቢያስ በ2 አመት በነዋሪነት የታወቁ
10) ከላይ ለተጠቀሱት መመዘኛዎች ከቀበሌ መስተዳድርና ከፖሊስ የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
ለ) ለአየር ኃይል ተመልማዮች አካላዊ ሁኔታ
1) ቁመት 1 ነጥብ 68 ሳ/ሜና ከዛ በላይ የሆኑ
2) ክብደት ከ55 እስከ 60 ኪ/ግ የሆኑ
3) እድሜ ከ18 እስከ 22 አመት የሆኑ
ለ) የትምህርት ሁኔታ
1) በ2009 ዓ/ም የ10 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሶስት የትምህርት አይነቶች ማለትም በእንግለዘኛ፣ በሂሳብና በፊዚክስ ውጤታቸው B እና ከዛ በላይ ውጤት ያላቸው
2) ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለሆኑ በ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ 300ና ከዛ በላይ ያመጡ
3) በዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ አጠቃላይ ውጤት 2 ነጥብ 6 ያላቸው
4)በአየር ኃይል አካዳሚ የሚሰጠውን Aptitude ፈተና ከ65 በላይ ማምጣት የሚችሉ
5) በአብራሪዎች ስልጠና የተዘጋጀ ቃለ መጠይቅ አጥጋቢ ውጤት ያመጡ
6) የ8ኛ እና 10 ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱበትን ሰርተፊኬት ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ
7) የትምህርት ውጤታቸውን በሀገር አቀፍ የፈተናዎች ድርጅት ለማረጋገጥ ፈቃደኛ የሆኑ
ሐ/ ለአውሮፕላን ጥገና ተመልማዮች
1) ቁመት ከ1 ነጥብ 65 ሴ/ሜ በላይ
2) ክብደት ከ50 እስከ 60 ኪ/ግ
3) ከ18 እስከ 22 አመት
መ) የትምህርት ሁኔታ
1) በ2010 እና በ2011 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ10 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው በእንግሊዘኛ፣ ሂሳብና ፊዚክስ ውጤታቸው C እና ከዛ በላይ የሆኑ፣ አጠቃላይ ውጤት 2 ነጥብ 4 እና ከዛ በላይ ያላቸው
2) በ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ፈተና ወስደው አጠቃላይ ውጤት 270ና ከዛ በላይ ያላቸው
3)በአየር ኃይል አካዳሚ የወታደራዊና አካል ብቃት ትምህርት ቤት የሚሰጠውን የሳይኮሜትሪክ ፈተና ማለፍ የሚችሉ
4) የ8፣10 እና 12 ብሔራዊ ፈተና ያለፉበትን ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፣ በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለማረጋገጥ ፈቃደኛ የሆኑ
የምዝገባ ቦታና ጊዜ:_
ለአዲስ አበባ:_ጦር ኃይሎች ፊት ለፊት ከሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ማደ/ማስ/ ቢሮ
አማራ ክልል:_ ባሕርዳር፣ ጎንደርና ደሴ
ለኦሮሚያ ክልል:_ ባሌ ሮቤ፣ ጅማ፣ ነቀምቴ፣ ደብረዘይት
የሌሎች ክልሎች:_በየ ክልሎቹ ዋና ከተሞች
የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 15/2013 እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም
ለበለጠ መረጃ 0114330636 መደወል ትችላላችሁ
(ሕገ መንግስቱን የሚቀበልና መሰል ሌሎች የተለመዱ ለተቀጣሪዎች አዲስ ያልሆኑ መመዘኛዎችም አሉበት)
132995347 4129374247091543 1112433273041065971 n

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.