በጀነራል ባጫና አበባው መልዕክቶች እስማማለሁ ሆኖም ወሮበሎች አገር መሪ ሆነው አይሆንም! – ሰርፀ ደስታ

abebaw and Bachaሰሞኑን የጀንራል ባጫና ጀነራል አበባውን የፌስቡክ ገጾች ተብለው የተከፈቱትን ስመለከት አገር እንመራለን ከሚሉት በብዙ እጥፍ አስተዋይና በእርግጥም ስለ አገር አሳቢና በትክክልም የኢትዮጵያ የሚባለውን የሠራዊት መንፈስ ያለው ከልብ አገር ከሚወድ የሚመነጩ መልዕክቶችን አንብበያለሁ፡፡

የአማራው ክልል ወደቤኒሻንጉል ገብቼ ሕግ እንዳስከብር ይፈቀድልኛ ያለውን ያልበሰለ ሀሳብ ቀደም ብዬ የማይሰራበትን ገልጬ ነበር፡፡ በሌላ ክልል የሆነን ጉዳይ የአማራ ክልል ሄዶ ሕግ የሚያስከብርበት አንዳችም ምክነያታዊ አሰራር የለም፡፡ ይሄን አይነት አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች አገር እንመራለን እያሉ ነው የችግሩ ሁሉ መነሻ፡፡  ይሄንኑ አይነት ምልከታ ከትናን በስተያ ጠ/ሚኒሰቴር የተባለው ሰው ችግሩን የሁለቱ ክልሎች በጋራ እንዲፈቱ እናደርጋለን ሲልም ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩ በክልሎች ድንበር የተፈጠረ ችግር ሳይሆን በቀጥታ በቤኒሻንጉልና ኦሮሚያ በሚባሉት ክልሎች እየሆኑ ያሉ አረመኔያዊ የዜጎችን እልቂት በክልሎች መካከል የተፈተረ ችግር አስመስሎ ማውራት አለመብሰልንና አገርና ሕዝብ እንዴት እንደሚመራ አለማወቅንም ያሳያል፡፡  የአማራ ክልል በክልሉ ስለሚሆን የሕዝብ ደህነት እንጂ ሌላ ክልል ሄጄ ሕግ አስከብራለሁ የሚለው አስተሳሰብ የመጣው የ30 ዓመት የወሮበሎች እሳቤ እንጂ በየትኛውም አግባብ ይሄ ልክ አልነበረም፡፡

እያንዳንዱ ክልል ነኝ የሚል በዛ ክልል ስለሚኖሩ ማንኛውም ዜጋ ይሁን ዛጋን እንኳን ባሆን ለነዋሪ ሰዎች ሁሉ ደህንነታቸውን መጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡ ይሄ አስተሳሰብ ከቶውንም የሌላቸው አረመኔና ወሮበሎች መሪ ነን በለው በተሰገሰጉባት አገር ግን ይሄ ሊሆን አይችልም፡፡ ሲጀምር የየክልሉ ሕግ ተብሎ የተቀመጠው ሰነድ በራሱ በወሮበሎች የተረቀቀ በመሆኑ ሕገ ወጥ ነው፡፡ የየክልሉ ሕገ መንግስት ሰነድ በግልጽ ዜጎችን የሚያገልና በዓለም ዓቅፍ ድንጋጌወች ለሰዎች ልጆች የተሰጡን መብቶች ሳይቅር የማይቀብል የወሮበሎች አስተሳሰብና ወሮበላነትን በአገርና ሕዝብ ላይ ለመከወን የተወጠነ ነው፡፡ ዋናው ተብዬው ሕገ-መንግስት የእነዚሁ የየክልሎች ሕገ መንግስት የሚባሉት ሰነዶች ዋና መነሻቸው ነው፡፡ የፌደራል ሥርዓት በሚል እያንዳንዱን ክልል በዘር የሸነሸነና ዛሬ ክልሎች በዜግነት ሳይሆን በማንነት መስፈርት ብቻ ነዋሪዎችን የሚፈቅዱ ናቸው፡፡ ይሄ ሁሉ ነውር በሕግ በተቀመጠባት አገር ነው ዛሬም ሕገመንግስቱ አይነካብንም የፌደራል ሥርዓቱም በመቃብራችን ላይ ካልሆነ የሚሉን፡፡ አዎ ከእንግዲህ በመቃብራቸው ላይ ለኢትዮጵያን ሕዝቧ ደህንነት ሲባል ሕጋዊ የሆነ ሕግ መቆምና በመቃብራን ላይ እያሉ የሚደነፉትን እንደወደዱት ወደመቃብራቸው መላክ ነው፡፡

ከዚህ በከፋ የክልል መሪዎችና ባለስልጣናት ዋና ሥራቸው ሴራና ሕዝብን ከሕዝብ ማባላትና ከሕዝብ ሰቆቃ በሚገኝ የንግድ ትርፍ እየደለቡ መሆናቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት ከሱማሌው ሙስጠፌ ውጭ እርግጥ ነው ከአፋርም አንዳችም ክፉ የሰማንው የለም፡፡ ሌሎቹ ግን እንዴት ነው የሚያስቡት፡፡ በተለይ በተለይ የኦሮሞ ባለስልጣናት ለ50ዓመት በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት ስሜት በተመረዘ እሳቤ በምን አግባብ ነው የሕዝብ አስተዳዳሪ የሚሆኑት፡፡ የኦሮሚያው ሽመልስ አብዲሳ የተበላ ወሮበላ በየቀኑ ሲደነፋ ሀይ የሚለው እንኳን የለም፡፡ የኦሮሞ ባለስልጣኖች ሁሉም ያው ናቸው፡፡ የክልሉ መሪ የተባለው ግን ከሁሉም የከፋ በዘረኝነት፣ጥላቻና የበታችነት ስሜት የተበላሸ ምንም እውቀትና ብስለት የሌለው በአጭሩ ከቀድሞው የሱማሌ ክልል መሪ ከነበረው አብዲ ኢሌ ጋር የሚመሳሰል ወሮበላ ነው፡፡

የኦሮሞ ባለስልጣናት ተባባሪዎች የሆኑት የቤኒሻንጉልና ሲዳማ  ወሮበላ ባለስልጣናት በኦሮሞ ባለስልጣናት እየተመሩ ሕዝብና እየጨፈጨፉ አገርን እያወደሙ እናያቸዋለን፡፡ ያ ለሌላ ሲሆን በመቃብራችን ላይ የሚባልለት የወሮበሎች ሕገ መንግስት የሚባለው ሲዳማን ክልል ለማድረግ ግን አይመለከተውም ተባለ፡፡በበታችነት፣ የእነዚህ ሶስት ክልል ባለስልጣናት በዋናው የኦሮሞ ባለስልጣናት እየተመሩ ተመሳሳይ የሆነ የዘረኝነት፣ ጥላቻና የበታችነት ስሜታቸውን ላስተዋለ ከየትኛውም የአገሪቱ ቦታዎች ሊታገዱ ይገባል፡፡ የሲዳማ ወሮበሎች የክልል ጥያቄን በማሳበብ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ከሲዳማ ውጭ የሆኑ ዜጎች ላይ ነበር የዘመቱት፡፡ ኦሮሞዎች ሥልጣን ሲይዙ ይሄን ላደረገ የወሮበላ ቡድን ክልል የሚል ሥልጣን ሰጠው፡፡ ያደረጉት ድርጊት ከሱማሌው አብዲ ኢሌ ተመሳሳይ ነበር፡፡ አሁን ሌለው አብዲ ኢሌ ቤኒሻንጉል ነው፡፡

በአጠቃላይ ከወያኔ ጋር የከረሙና በሪፎርም ሥም ዛሬም በአገሪቱ ላይ በሥልጣን ላይ ያሉ በሙሉ ተወግደው አዲስ ጤነኛ እምሮ ያለው ካልተተካ መቼም ቢሆን አገርም ሕዝብም ሠላም የሚሆንበት እድል ያለ አይመስለኝም፡፡ የዛሬው የሱማሌ ክልል ለዚህ አይነተኛ ምሳሌያችን፡፡ ያን የለየለት የወሮበሎች መበኝጫ የነበረን ክልል ዛሬ እነ ሙሰጠፌ እንዴት ከሕዝብ ፍቅር ጋር እየመሩት እንደሆነ እያየን ነው፡፡ በተቃራኒው በለውጥ ሽፋን በወያኔ ያደጉና እንዳለ እንደወረደ በወያኔ የአስተሳሰብ ባርነት የወደቁ ዛሬም ጭራሽ ትልልቁን ሥልጣን ይዘው ከአሳዳጊያቸው ወያኔ የተሻለ ነገር ማየት ዘበት ነው፡፡ ለዛም ነው ዛሬ ከወያኔ ወደ ኦፒዲ/ኦነግ የተቀየረው ሥርዓት ጭራሽ የስግብግብነቱ ብዛት ከዘረኝነት፣ ጥላቻውና የበታችነት ስሜቱ ጋር ተዳምሮ አሁን የምናየውን ሁሉ የምናየው፡፡ በሁለት ዓመት አዲስ አበባ የሆነውን ማየት በቂ ነው፡፡ በሁለት ዓመት 13ሚሊየን ካሬ ቦታ፣ በመቶ ሺ የሚቆጠር የሕዝብ ኮነደሚኒየም ሌላም ሌላም ዘርፎ አገር ላይ ዛሬም ሊቀጥል ያስባል፡፡ የግዜ ጉዳይ እንጂ ወያኔ የደረሳት እጣ በፍጥነት አፍንጫው ላይ እየመጣ ነው፡፡ እንደኖህ ዘምን ሰዎች አፍንጫው ላይ ያለውን የሕዝብ ትግስት ማለቅን ማሰብ ሳይሆን ድሮም ወሮበላ ሲሰገበገብ እንደሚሞት እንደወያኔ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡ ከወያኔ ተማሩ ብንልም የሚሰማ የለም፡፡ በምን አእምሮ ይማራል፡፡

ብዙ ጉድ አለ፡፡ በዋናው ፌደራል መሪ ነን የሚሉት ይገርመኛል፡፡ ጠ/ሚኒስቴሩን መናፈሻ ከመስራት የሚሰራውን ሥራ ስንል ጭራሽ የኢትዮጵያ ልክ እያለ የመናፈሻ ዶኪመንተሪ ሲሰራብን ነበር፡፡ ይሄ እውነት ቀልድ ነው፡፡ አሁንም በቤኒሻንጉል ሄዶ ያደረገው እንደ አገር መሪ ሳይሆን ያው የመናፈሻ መሪነት ነው፡፡ ለዛም ነው በሌላ ክልል የሆን ጉዳይ ክልሉን በቀጥታ በፌደራል መንግስት ጣልቃ ገብነት የዜጎች ደህንነት ማስከበር ሲገባው በሁለቱ ክልልሎች በመነጋገር ሲል ምንም የማይገናኝ ነገር ሲናገር የነበረው፡፡ የአማራ ክልል በቤኒሻንጉልና ኦሮሚያ ስለሚሀነው ጉዳይ ምን አገባው፡፡ እያንዳንዱ ክልል በአንድም ዜጋ ላይ ችግር ከተፈጠረ ሊጠየቅ ሲገባው አማራን ስገደሉ አማራ ክልል ጋር እንደራደር አይነት እጅግ አሳዛኝ የሆነ የወሮበሎች አስተሳሰብ ይስተዋላል፡፡ እያንዳንዱ ይክልል መሪ ከዛም በተዋረድ እስከቀበሌ ድረስ በአንድም በማንነቱ ምክነያት ለሚጎዳ ዜጋ ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ በአረመኔነቱ እንዲደራደር እድል ይሰጠዋል፡፡  እሺ እንበልና ቤኒሻንጉል ለአማራ ቅርብ ስለሆነ አማሮችን ለመታደግ የአማራ ክልል ገባ የሩራ ፈርዳዎቹን አማሮች ማን ይታደጋቸው፡፡

ለሁላችሁም አልለው፡፡ መጀመሪያ አገርና ሕዝብ እንዴት እንደሚመራ ሳይሆን እድሜ ልካችሁን በተንኮልና በሴራ በዌኔ አድጋችሁ እናንትን ማስተማር የሚቻል አይመስለኝም፡፡ መማር ብትችሉ ከጅምሩ ለውጥ የተባለ ጊዜ ሁሉንም ነገር በእርግጥም በመለወጥ ዛሬ አስተማማኝ የሆነ የሕዝብና አገር ደህንነትን ማስፈን በቻላችሁ፡፡ አሁንም እጠቅሰዋለሁ የሱማሌው ሙስጠፌና ባልደረቦቹ ያን ክልል ዛሬ ያደረሱበትን ላሰበ በእርግጠም ለካ መሪ ወሳኝ መሆኑ ያስተውላል፡፡ ደግሞ መቼም ተንኮልና ሴራ ስለሆን እድሜ ልካችሁን የጨረሳችሁት ወደሱማሌም ሄዳችሁ የሰፈነው ሰላም ለማወክ ሴራ ከመሸረብ  ወደ ኋላ እንደማትሉ እናስባለን፡፡ ምክነያቱም የዛ ክልል መሪዎች ሁላችሁንም እያሳጧችሁ ነውና፡፡ እንኳንስ እነ ሙስጠፉ ለዘመናት ሱማሌን እገነጥላለሁ እያለ የነበረው ኦብነግም ዛሬ ተለውጦ ማየት ችለናል፡፡ ለውጥ ይልሀል ይሄ ነው፡፡ የወያኔው ስሪት ኦነግ ግን ይሄው ዛሬም እዛው የ50 ዓመት ተከርቸሙ ነው፡፡

በመጨረሻ የጀነራል ባጫን ሐገራዊ ስሜት ያለውን መልዕክት አደንቃለሁ፡፡ አገር በወሮበሎችና በሕዝብ ደም በሚነግዱ አረመኔዎች እየተመራች ሠላም የለም፡፡ እኔ መከላከያውን አሁንም የኢትዮጵያ ነው የሚል እምነት የለኝም ጀነራል ባጫ በዚህ ላይ መረጃ እያዛባችሁ መከላከያችንን አታሳጡ ይሉናል፡፡ እኔ መከላከያው የኢትዮጵያን የኢትዮጵያውያን ብቻ እንዲሆን እፈልጋለሁ፡፡ ለዛ ደግሞ ሁለት ግዴታዎች አሉበት የአገር ሉዓላዊነት የኢትየጵያን መንግስት (ሕዝብን) መጠበቅ፡፡ መንግስት ማለት ፓርቲ አደለም፡፡ የኢትየጵያ መንግስት ሥሪት የሕዝብ ደህነትና ለዚሁ የሚሰሩ በተለይ ሶስት ወሳን ተቋማት ናቸው፡፡ ፍትህ፣ ደህንነትና ሕግ ማስከበር፣ እና መከላከያው፡፡ ሌላው የመንግስት መዋቅር በሙሉ ከፖለቲካ መዋቅሮች ሊጸዳ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ልዋእላዊነት የፖለቲከኞች መቆመሪያ ሳይሆን የኢትዮጵያን ደህነነት በሚስጠብቅ ገለልተኛ ተቋም ሊመራ ይገባል፡፡ ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና የሆነው ዲና ሙፍቲ የተባለ ግለሰብ ከግብጽ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ማረጋገጨ ማግኘት የሚችል ተቋም ያስፈልጋል፡፡ ማንም አገር ደህንነቱ በፓርቲ ወይም በባለስልጣን የተያዘ አደለም፡፡ የእስራኤል ደህንነት በሞሳድ እንጂ በእስራኤም ፖለቲከኞች  አደለም፣ የአሜሪካም በሲአኤ፣ የራሺያም እያለ ይሄዳል፡፡  የፖለቲካ ሥልጣን መንግስ አደለም፡፡ የፖለቲካ ሥልጣን የመንግስትን ሥራ እንዲያስኬድ ለተወሰነ ጊዜ ሕዝብ የሚመርጠው እንጂ፡፡  ከሁሉ በፊት አገርና ሕዝብን የሚወክል ሕግና ሥርዓት መበጀት አለበት፡፡ ዛሬ በወሮበሎቹ ወያኔና ኦነግ በተሰራ ወሮበላ ሥርዓት አገር እየተመራች ሠላምና ደህነነት ዘበት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ መከላከያው አሁንም የኢትዮጵያ ነኝ ካለ ከኢትዮጵያዋያን ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፣ የኢትዮጵያውያንን ደህንነት መጠበቅና ኢትዮጵያ ሥርዓትና ሕግ አግባብ የምትመራበት ሁኔታ ማገዝ አለበት፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! አሜን!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.