ጠ/ሚኒስተራችን ‘ርሰዎ ብቻ የገባዎት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልገባው ነገር አለ ይሆን?

abiy 4በዚች አገር የሚካሄደው የዘር ማጥፋትና ሰቆቃ ሁሉ፤ የኋላ-የኋላ አላፊነቱ የ’ርስዎ መሆኑን እንኳን እያወኩ ፤ ” ኢትዮጵያ!.. ኢትዮጵያ! ” ስለሚሉ ልቤ ቅልጥ ይላል።

በትላንትናው ንግግረዎት ስለ “ሚዲያ” እና ስለ “ክልል” ሲናገሩ ሰማዎት። ……ታዲያ ከንግግረዎት ውስጥ ፤ ” …..ቤኒሻንጉል ክልል የአማራው፣ የኦሮሞው፣ ወዘተ– የሁሉም ማለት ነው። አማራ ክልል ሲባል፣ የአገው፣ የትግሬው፣ የኦሮሞው ፣ ወዘተ—የሁሉም ማለት ነው። የኦሮሞ ክልል ሲባልም እንዲሁ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ማለት ነው። …..” አሉ።

ይህን ሲሉ ፤ ‘ርሰዎ ብቻ የገባዎት የኢትዮጵያ ህዝብ ያልገባው ነገር አለ ወይም ‘ርሰዎ ብቻ የልገባዎት ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ የገባው ነገር አለ። በመጀመሪ ደረጃ ህገ-መንግስተዎ ክልልን በጎሳ ስም ሲሰይም ነገሩ ሁሉ ተበላሸ። በስሙ የተሰየመለት ጎሳ እሱ “ባለቤት” ነው ማለት ነው። ያስቡት እስቲ…. በአንድ ሰው መታወቂያ ላይ የጎሳው ስም መፃፍ ምን አመጣው?  የእኔ ቢጤ ጎሳ የሌለው ዜጋ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ “አየር ላይ ያለ ፊኛ ” እንዲሆን ተፈርዶበታል።

ይህ ብቻ አይደለም ህገ – መንግስተዎ ለዜጋ ወይም ለሰው ወይምለኢትዮጵያዊ እውቅና አይሰጥም ። እርሰዎ ከገጠር እንደመጡ ደጋግመው ነግረውናልና ” ክልል” ማለት ለከብቶች የግጦሽ ቦታ እንደሚከለል ያውቁታል። ቃላቱ ‘ራሱ ለእንሰሳ መንጋ እንጅ ለሰው ልጅ አይውልም ። ክቡርን የሰውን ልጅ እንደሰሳ መንጋ ተቆጥሮ ” የጎሳ ክልል” ተሰጠው።

ታዲያ አንድ ጎሳ በተለይም እርሰዎ የመጡበት “የኔ ክልል ነው።” እያለ ፣ ኢትዮጵያዊያንን በመጤነት ፈርጆ እያሳደደ እና እያረደ ይገኛል። ታዲያ እርሰዎ የሚናገሩት እና መሬት ላይ ያለው እውነታ የሰማይና የምድር ያክል የተራራቀ በመሆኑ ነው፤ “’ርሰዎ ብቻ የገባዎት የኢትዮጵያ ህዝብ ያልገባው ነገር አለ ይሆን?” ለማለት የተገደድኩት።

እውነታው

  • አሁን ያለውን ህገ-መንግስትና የጎሳ ክልል ይዘው ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሚሊዮን ግዜ ቢናገሩ፣ ትርጉም የለውም። እናም ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ በራሱ በኢትዮጵያዊያን ህገ መንግስት አስረቅቀው ያፀድቁ፤ “ውክልና የለኝም “ ለሚሉት፤ ኢህአዴግ ሲፈርስ፣ ውክልናዎም አብሮ ፈርሷል። እውነት እንነጋገር ከተባለ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ማንንም አልዎከለም። ጉልበታችሁ ነው የወከላችሁ። የኢትዮጵያ ህዝብ ያን ያህል መሰዋአትነት የከፈለው፤በአንድነትና በእኩልነት ኢትዮጵያን የሁላችን ለማድረግ ብሎ እንጅ ወያኔን አስወግዶ እናንተ ስርዓቱን ይዛችሁ እንድትቀጥሉ አልነበረም፤ እርሰዎም ወደ መመበረ ስልጣኑ ሲወጡ ህዝብ ከዳር እስከዳር የደገፈዎት “ኢትዮጵያዊነትን አነግሳለሁ፣ ጎሰኝነትን አጠፋለሁ!” ስላሉ እንጅ ሃይለማርያምን ስለተኩ አይደለም።
  • የኦዴፓ ብልፅግናዎች ብዙዎቹ ከኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ ኦነግ ናቸው፤ በቀጥታ ኦነግ ባይሆኑ እንኳን የኦነግን ተልዕኮ አስፈፃሚዎች ናቸው። ይህ ማለት ደግሞ ኢትዮጵያ ጠላት ናት። ግባቸው ” ታላቋ ኦሮሚያ” ነው። የራሰዎት ፓርቲ በህገ መንግሥቱና በጎሳ ክልል እንደማይደራደሩ ደጋግመው ነግረውናል።

በአሁኑ ሰዓት እንኳን “አዲስ አበባ የእኛ የግላችን ናት” በማለት ዲሞግራፊዋን በመቀየር፤ በእርሰዎ በተሾሙ ህገ ወጥ ከንቲባዎች የሚሰራውን ህዝብን- ከህዝብ የሚያጫርስ ተግባር በአይናችን እያየን ነው።

እንግዲህ ኦዲፓ ብልፅግና ከአቅመዎት በላይ ሆኖበዎት ከሆነ ፤ እውነታውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያድርጉ።ይፋ ካደረኩ ከስልጣን ይገለብጡኛል ብለው ፈርተው ከሆነ ደግሞ፣ አይፍሩ!

..የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎነዎት ነው። ዙር ዞሮ የመጨረሻ አሸናፊ ኢትዮጵያዊነት መሆኑንም ከ’ርስዎ የበለጠ የሚያውቀው የለም።

  • ኢትዮጵያዊነትን ከጎሳ ፓለቲካና ክልል ጋር አብሬ ይዥ እዘልቃለው ብለው አስበው ከሆነ “ውሃን እና ዘይትን ” ለመቀላቀል እየደከሙ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠላቶችም፣ ኢትዮጵያን “እናፈርስበታለን” ብለው የነደፋት አሁን ያለው ” በጎሳ” ከፋፍሎ እርስ-በ’ርስ ማባላት ነውና ፤ ‘ርሰዎ የሚወዷት ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ የለችም።

በርግጥ እርሰዎ እንደሚሉት ” ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚሉ፣ ቀድመው እነርሱ ይፈርሳሉ።”

———-//——-

ፊልጶስ / ታህሳስ/2013

E-mail: [email protected]

1 Comment

  1. ደጋግሜ እለዋለሁ!
    አቢይ የሌለውን ሥልጣን አትስጠው፤፡ አብይ ህገ መንግስት የመቀየርም ሆነ ክልል የማፍረስ ሥልጣን አለው ብለው የሚያስቡ ሰዎች ይገርሙኛል፤፤ አቢይ ቢችል እኮ እስካሁን ያደርገው ነበር፤፤ በቃ አይችልም! አይችልም! ይህንን መረዳት ምንድነው የሚከብደው? ጊዜ ተወስዶ በስምምነት ነው የሚሆነው፤፤ ልታደርጉ የምትችሉት፤ አቢይ ክልል ስለማያፈርስ ክልል የሚያፈርስ ፓርቲ እና መሪ በምርጫ ወደ ሥልጣን ማምጣት ነው፡፤ ኢዜማን ወይም ባልደራስን ተቀላቀል!
    እንግዲያው እውነቱን ንገረኝ ካልክ፤ አሁን የተያዘው በኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶች/ጸሃፊዎች ሁኔታ ወያኔ “አሃዳዊ መንግስት ሊያመጡባችሁ ነው” እያለች የሰበከችውን፤ “አሃ ዉነቷን ሳይሆን አይቀርም?’ ወደሚል ጥርጣሬ ወስዶታል፤፤ በትንሹ ማለት ነው፤፤ ወሬና ጽሁፋችሁ እርስ በርስ መሞካሸት ስለሆነ “ሌላው” ምን ያስባል? የሚለውን ትታችሁት ጭራሽ “የኢትዮጵያዊነት” ሰጭ እና ከልካይነት ስልጣናችሁን ልታድሱ ትፈልጋላችሁ፤፤ ወለ በሉ አቦ አይሰራም!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.