ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ

Tedros bijgesneden 1ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው ከኢትዮጵያ መንግስት ተጻራሪ በመሆን እያደረጉት ያለው ተግባር ተገቢ እንዳልሆነ በሲውዝርላንድ ጄኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነበ ከበደ አስታወቁ።
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እያደረጉት ባለው እንቅስቃሴ የኢዮጵያ መንግስት ደስተኛ አይደለም ያሉት አምባሳደር ዘነበ፤ ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስት አቅራቢነትና ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ መሆናቸውን አስታውሰዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ድጋፍ ጭምር አሁን ላሉበት ከፍተኛ የስራ ሃለፊነት መብቃታቸውን ያስታወሱት አምባሳደሩ፤ በዚህ ከፍተኛ ቦታ ላይ ሆነው በእንደዚህ አይነት ወገንተኝነት የታየበት ተግባር ላይ መሰማራታቸው ደስተኞች አይደለንም ብለዋል።
ይህንን የዶ/ር ቴድሮስ ተግባር መንግስት አግባብ ባለው መልኩ የሚሄድበትና ምላሽ የሚሰጥበት ይሆናል” ሲሉም ነው አምባሳደሩ የገለጹት።
Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
ተጨማሪ ያንብቡ:  በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተጥሏል o በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው

1 Comment

  1. ከዝንብ ማር መጠበቅ አይሆንም ነገሩ፡፡ አብሮ ሲጨፈጭፍ እና ሲያስጨፈጭፍ ከነበረ ምን ይጠበቃል፡፡ አሁንም መንግስት መለሳለስ የለበትም፡፡ ከበቂ በላይ የወንጀል መረጃዎች በመኖራቸው ክሱን በቶሎ አፋጥኖ ፍርድ ቤቱ በዛው ቅርብ ሰለሆነ ወደ መቀመቅ ነው እንጂ፡፡

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.