የጎበዝ አለቃ ሥርዓት አሁኑኑ! – በላይነህ አባተ

በላይነህ አባተ ([email protected])

belay Zeleke in Gojjam

ሲፈጁት እንደኖሩት የአማራ ሕዝብ ሁሉ ስንቱን የሰሜን ጦር አባል በክህደት የፈጁት የድሮ ጌቶቻቸው ናዚዎች አብዮት አመዴንና በዙሪያው የኮለኮላቸውን ጓደኞቹን ጆሮዎቻቸው እንደተሰበሩ ጉልቻዎች ተወንበር ሊፈነግሏቸው ሲቃጡ ስልጣናቸውን ለማቆየት ሽቅብ ተመናገር አልፈው ሰራዊቱንና የአማራን ፋኖ ተጠቅመው እንደሚዳቋ ለማስደንበር ስለበቁ የአማራ ሕዝብ አሁንም መንግስት ያለው መስሎት ተዘናጋ፡፡

በውጪም ሆነ በውስጥ በሚጮሁ ሆዳም ምሁራን ካድሬዎቹ የተወናበደው አማራ እነዚህ የቀድሞው ናዚ አሽከሮች የሕዝብ እልቂትና መከራ የሚሰማቸው ቢሆን ኖሮ ቀደም ሲል የናዚውን ሥርዓት ከሃያ አምስት ዓመታት በላይ በካድሬነትና በሰላይነት እንደ እቃ እንደማያገለግሉ፤ አሁንም የአማራን እልቂት የማስቆም ፍላጎት ቢኖራቸው ሰራዊቱን ሰሜን ተማዝመት ጎን ለጎን ሀረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ከፋ፣ ወለጋ፣ ሻሸመኔ፤ ደራና መተከል መላክ ይገባቸው እንደነበር ቆም ብሎ ለማሰብ ዘገየ፡፡

በአማራ መቃበር አገር ለመመስረት የተነሱትን ኢትዮጵያውያን ናዚዎችን እንደ ቤት አሽከር ብቻ ሳይሆን እንደ እቃ ያገገለገሉትን አገልጋዮች እንደ አገር መሪዎች ቆጥሮ በሆዳም የምሁር ካድሬዎች እየተወናበደ ራሱን አደረጃችቶ ራሱን የመከላከል የተፈጥሮ መብቱን አማራ አሁንም ችላ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት ከአርባ ሁለት ዓመታት በፊት ወልቃይት የጀመረው የአማራ ዘር ፍጅት ዛሬም በመላ አገሪቱ ቀጠለ፡፡

ከሰባ አምስት ዓመታት በፊት አይሁዳንና ሌሎችን በመጨፍጨፍ ከሂትለር ጋር የተሳተፉ የናዚ ፓርቲ አባሎች እስከ አሁን እየታደኑ ለፍርድ እየቀረቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ [1-2] ለምሳሌ በአለፈው አመት የ95 ዓመት እድሜ ሽማግሌ ስሙን ለውጦ ከተደበቀበት ተይዞ በ21 ዓመቱ በፈጠመው ወንጅል ችሎት ቀርቧል፡፡ [3] የእኛውን አገር ሂትለር ያገለገሉት ወንጀለኞች ግን ዛሬም የአገር መሪዎች ተብለው ተዙፋን ተቸክለው ተሂትለሮች የተረፈውን የአማራ ሕዝብ ማስፈጀቱን ቀጥለዋል፡፡ በዘሩ መፈጀቱ እንዲቆም የአማራ ሕዝብ ተሂትለር ርዝራዦችና ተቀድሞ የቤተ አገልጋይ ባሪያዎቻቸው ተላቆ እንደ ጥንቱ በራሱ ጎብዝ አለቆች መመራት ይኖርበታል፡፡

ዓለም እንደሚያውቀው የጎብዝ አለቃ ሥርዓት መንግስት ባልነበረበት ወቅት የአገሪቱን ሰላም ብቻ ሳይሆን ወራሪዎቿን ድባቅ እየመታ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ሲያስከብር ኖሯል፡፡ የአምስቱን ዘመን ተጋድሎና የእነበላይ ዘለቀን የእነአበበ አረጋይን የጎብዝ አለቃ መሪነት ልብ ይሏል፡፡ በጥንቱ ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ተእየሩሳሌም እስከ ማደጋስካር ተዘርግቶ የነበረው በጎበዝ አለቃ የሥርዓት አደረጃጀት እንጅ  በመጤው የጥበቃ ጓድ፤ አውደልዳይ ፖሊስ  አለዚያም ጅላንፎው ሁሉ በሚለብደው የጀኔራልነት  ሥርዓት እንዳልሆነ ታሪክን መመርመር ይበጃል፡፡

የቱርክ፣ የግብጥን የጣሊያንንና የሌሎችንም ወራሪዎች ደንደስ ሲሰበር የኖረው በሰላም ጊዜ ገበሬ በጦር ወቅት ሰራዊት በሚሆኑት የጎበዝ አለቃዎች መሪነት መሆኑ መጤን ይገባዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰላምን፣ ሥርዓትን፣ እምነትንና የመንፈስ ልእልናን ሲያስጠብቁ የኖሩት ጎበዝ አለቃዎች መሆኑን ማወቅ ያሻል፡፡ የጎበዝ አለቃ ሥርዓት ጎበዝን እንደ ስንዴ እየዘራ አብቅሎ እንደሚያጎመራ ረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ኢትዮጵያ ቁልቁል መንሸራተት የጀመረችው የጎብዝ አለቅነት ሥርዓት መፍረስ ተጀመረበት ጊዜ መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡ ጎበዝ አለቃ እንደ ፖሊስና ካድሬ በነፍሰ-ገዳይዎች እንደ ቀንበር በሕዝብ የሚጫን ሳይሆን ከሕዝብ አብራክህ እንደ ሺል የሚወጣ የሥጋና የመንፈስ ልጅ መሆኑን ማወቅ ያሻል፡፡ የጎበዝ አለቃ በጀግነቱ፣ በምግባሩና በመንፈስ ልዕልናው በሕዝብ የሚመረጥ የአገር ደጀን መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ከውጪ ተስፋፊዎች ባሻገር የጎበዝ አለቃ ወንበዴ ገዥዎችን ልክ የሚያስገባ የማህበረሰብ ዋስትና መሆኑንም ማስተዋል ይገባል፡፡

የጎበዝ አለቃ የአካባቢውን ሰላምና ደህነንት በሚገባ የሚያስከበር የተዋጣለት መሪ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡ የጎበዝ አለቃ ዳር ድንበር ሲደፈር ፎክሮ የጠላትን ጉርንቦ የሚያንቅ የተቆጣ አንበሳና ነብር መሆኑን መገንዘብ ይገባል፡፡  ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንደ ጎባጣ ሞፈር አርቆ ልክ የሚያስገባ የእርሻና የጦር ገበሬ መሆኑን ማማን ያሻል፡፡ ጎበዝ አለቃ ባንዳን እንዴት እንደ ጎባጣ ሞፈር አርቆ እንደሚያስተካክል ለመረዳት ገድለ-በላይ ዘለቀና ገድለ-አበበ አረጋይን ለማንበብ ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል፡፡

ጎበዝ አለቃ በሱስ ተጠምዶ ለሂትለር ሰላዮች እስክስታ የማይመታ በአካልና በመንፈስ የጠና የህብረተሰብ አለኝታ መሆኑን ማጤን ይገባል፡፡ ጎበዝ አለቃ ለነጻነቱና ለፍትህ ሲል ለልጆቹም የማይሳሳ ባለማተብ ጀግና መሆኑን የጣልያንን የማታላያ ወጥመድ ሁሉ ሰባብሮ የሞሶሎኒን የጀርባ አጥንት እንደ ሸንበቆ ተቀለጠመው ተበላይ ዘለቀ መማር ይገባል፡፡ የጎበዝ አለቃ ሥርዓት ፍትህን ተጀግንነት፤ እምነትን ተሥራ የሚያዋህድ የተባረከ የኢትዮጵያ እሴት መሆኑን  መረዳት ይጠቅማል፡፡

ስለዚህ በአገር ውስጥ ሰላምን ለማስፈንም ሆነ ኢትዮጵያን ከታሪካዊ ጠላቶቿ ለመጠበቅ በሽለላ፣ በፉከራና በወኔ ጠንሳሽ ሰምና ወርቅ ቅኝቶች አለት ላይ የተመሰረተና በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታነፀ፣ ጀግና ሴቶችና ወንዶች የሚመሩት የአጎብዝ አለቃ ሥርዓትን አሁኑኑ መገንባት ያስፈልጋል፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

 

ዋቢ

  1. 10 Most Wanted Nazi War Criminals, History channel https://www.history.com/news/10-most-wanted-nazis
  2. The last Nazi hunters, https://www.theguardian.com/news/2017/aug/31/the-last-nazi-hunters
  3. Nazi war crimes suspect, 94, faces German youth court trial https://www.theguardian.com/world/2018/sep/21/nazi-war-crimes-suspect-faces-trial-german-youth-court

ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.