ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም – መስከረም አበራ

20201205 MAP501በመተከል ዛሬም ሌላ ማንነት ተኮር የሞት አዋጅ ታውጆ ከ96-106 የሚደርሱ ንፁሃን አማሮች/አገዎች አልቀዋል። ዛሬ ደሞ ቤት ማቃጠልን የጨመረ ማጥቃት ነው የተደረገው። መንግስት አለሁ በሚልበት ሃገር ነው ይህ የሚሆነው????
ይህ የሚፈፀመውም መንግስት ተሽሎክላኪ ታጣቂዎችን አድኖ መያዝ አቅቶት ሳይሆን ግድያውን ስለሚያቀናብር ወይም ስለሚያግዝ ነው።ወስፌ ሲለግም ቂቤ አይወጋም! መንግስትም ሲለግም የመንደር ሸማቂን አንድ ማለት አቃተኝ ሲል ያላዝናል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘር ማጥፋቱን የፀጥታ ችግር ሲሉ አላግጠውበት የተመለሱት፣ህዝብ አወያየሁ ብለው ግድያውን የሚያቀናብር የዞን አስተዳዳሪና የካድሬ ጥርቅም አነጋግረው የመጡት ለዚህ ነው።
አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ትግራይ ክልል ህግ ለማስከበር የገባው የአማራ ልዩ ሃይል ቤኒሻንጉል ክልል ልግባና ህግ ላስከብር ሲል የሚከለክለው ለምንድን ነው??????? ቤኒሻንጉል ለኦሮሚያ ስለሚዋሰን?!
ነገሩ ወዲህ ነው የአብይ አህመድ የጀኖሳይድ መንግስት የአማራ ልዩ ሃይል ወደ ቤኒሻንጉል መተከል እንዲገባ በይፋ የማይፈቅደው የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ቤኒሻንጉል ክልል ጥሶ ከገባ በህገ-ወጥነት በመክሰስ መከላከያ የአማራ ልዩ ሃይልን እንዲወጋ በማድረግ ቅዠት የሆነበትን የአማራ ልዩ ሃይል ለመምታት፣እግረ መንገዱንም የአማራ ልዩ ሃይል ወደ ቤኒሻንጉል እንዲገባ አደረጉ በማለት ብአዴን አልሆንልህ ያሉትን የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ለመክሰስ ብሎም ለማሰር ነው።
የአብይ የጀኖሳይድ መንግስት ይህን ሁሉ ሲያደርግ ጀኖሳይዱን ባለማስቆሙ የሚጠይቀው የለም -ተረኛው ህወሃት ነዋ!!!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ታየ፥ እባክህ አሁንም እንደ ሌላው ጊዜ ተነሣ | ጌታቸው ኃይሌ

2 Comments

 1. “አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ትግራይ ክልል ህግ ለማስከበር የገባው የአማራ ልዩ ሃይል ቤኒሻንጉል ክልል ልግባና ህግ ላስከብር ሲል የሚከለክለው ለምንድን ነው??????? ቤኒሻንጉል ለኦሮሚያ ስለሚዋሰን?!”
  ችግር አለ፤፡ በጣም ትልቅ እና አደገኛ ችግር! በአንቺ አባባል “የአማራ ልዩ ሃይል ቢገባ መፍትሄ ያገኛል ማለት ነው፤፡” እንደው ሌላው ይቅርና በምን እርግጠኛ ሆንሽ?

  “የአብይ የጀኖሳይድ መንግስት ………….!”
  በርግጥ በ”አብይ” እና በ”አቢይ መንግስት” መካከል ልዩነት አለ፤ አቢይን ለማለት ከሆነ አሉላ ሰሎሞንስ ከዚህ የበለጠ ምን ተናገረ?
  ብቻ ቲቸር መስከረም ነገረ ጽሁፍሽ ሁሉ “አወቅሽ አውቅሽ ሲሏት የቄሱን መጻፍ አጠበች” እንዳይሆን፤

 2. በሀገራችን የሚታየው ፓለቲካ ሳይሆን ሀገራችንን መበታተን ወይም በአንድቱተዋ ማስቀጠል ግብ ግብ ነው።
  በአለፉት 27 አመታት አፍራሽ ሀይሉ የአንበሳ ድርሻውን ይዞ በመቆየት አውራው ሀይል በቅቡበ እየተቀበረ ነው። ቅርጫፎቹ ተተኪ ለመሆን አለን አለን እይሉ ነው።
  ኢትዬጵያን ለማስቀጠል የሚውተረተረው ሀይል እየተሽኮረመሙ ነው። ከአማራ ውጪ የደቡብ፣ ሲዳማ፣ አፋር፤የሶማሌ፤ጋንቤላ ህዝቦች እርስ ብርስ ተቀራርቦ አፍራሾችን ሲጋፈጡ አይታይም። በፓርላማም አይስተዋልም። የሚቀጥለው ፈተና ከኦሮሞ አክራሪዎች እና እነሱ ከሚዘውሩት ሀይል ጋር ይሆናል በግልፅም እየታየ ነው።
  በዚህ ታሪካዊ ጊዜ ኢትዬጵያዊነቱን ያለ ጥርጥር ያስመሰከረው የመከላከያ ሀይላችን ነው፣ የዘር ፓትቲካ ያመጣዉን መራር ገፈትም ተግቶ አይቶታል።
  ስለዚህ በሀገራችን የፓለቲካ equation. ውስጥ በመግባት የዘር ፓለቲካ በህግ እንዲከለከል እና የዜግነት ፓለቲካ እንዲሰፍን የራሱን ተፅእና ማሳረፍ ይኖርበታል። አሀዳዊ እያሉ የሚያደነቁሩን ደናቁርት እንደሚሉት ሳይሆን ፣ የዜግነት ፓለቲካ ብሄረሰቦች በራሳቸው ቁንቁዋ የመማር፣ የመዳኘት፣የመተዳደር፣ባህላቸውን የማስፋት መብታቸውን ይስከብርላቸዋል። የሚያስቀረው በኢትዩጵያዊኖች መሀል አንደኛ እና ሁለተኛ ብሎ ዜጎችን ማበላለጥ ነው።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.