ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ሦስት ሳተላይቶችን ታመጥቃለች

sateliteኢትዮጵያ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ለተለያየ አገልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን እንደምታመጥቅ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ እንደገለፁት፤ በቀጣዮቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ አግልግሎቶች የሚውሉ ሦስት ሳተላይቶችን ለማምጠቅ ታቅዷል።
በአሥር ዓመቱ ከሚመጥቁት ሳተላይቶች ውስጥ አንደኛው የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሲሆን፤ የተቀሩት ሁለቱ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ናቸው።
እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ የኮሚዩንኬሽን እና ብሮድካስት ሳተላይት የሚባለው በብሮድካስት ሚዲያዎች ለኢንተርኔት፣ ለስክልና ለኮሚዩንኬሽን አገልግሎት የሚውል ነው።
በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን እነዚህን አገልግሎቶች ከውጭ በመከራየት በሚሊዮን ዶላር የሚገመት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ታወጣለች።
ለአብነትም፣ ከብሮድካስቲንግ በዓመት እስከ አሥር ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ ለቴሌ ኮሚዩንኬሽን ደግሞ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ወጭ ይሆናል ።
ሳተላይት የመገንባት እቅዱን በተግባር በማረጋገጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ ታስቧል።
ኢፕድ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.