ትዝብት – የየኔታው ስዩም ተሾመ የአብይ አህመድን ኦሮሙማ ለማዳን ስለሚያደርገው ከንቱ ጥረት

ይድረስ ለአቶ ስዩም ተሾመ (የኔታ ቲዩብ)

ጉዳዩ ፡ አብይ አህመድን ለማዳን ኢትዮ360ን የማብጠልጠል ትዝብት
ታህሳስ 10 ቀን 2013 ዓ.ም.

syum Teshomeስዩሜ፦ ጎበዝ ሰው ነህ፡፡ ጉብዝና የሚመስልህ ስራህ ግን መጨረሻው ፍሬ ቢስ ሆኖ ይቀራል፡፡ አንድ ጊዜ አብይን የሚደግፍ ዝግጅት ይዘህ ብቅ ትላለህ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አብይን የሚቃወም የሚመስል ዝግጅት ይዘህ ብቅ ትላለህ፡፤ በዚህም አድራጎትህ ስዩሜ ደፋር ነው፡ ስዩሜ ጎበዝ ነው፡ ጥሩ መረጃ አፈንፋኝና አዋቂ ሰው ነው፡ ጎበዝ ተንታኝ ነው፡ አብይንና የአብይን ባለስልጣናት እንኳን ለመተቸትና ለማጋለጥ የማይፈራ ደፋር …ወዘተ ሰው ነው የሚያሰኙ ማንነቶችን ለመላበስ ረድቶሀል፡፡የምታደርገው ተንኮል የተሞላበት ረቂቅ ሴራ የሚደነቅልህ የሚመስልህ ብስለት በጎደላቸው ሰዎች ዘንድ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፤ ይህም የሚቆየው ነገሮች እያደር እስኪጠሩና እውነታው እስከሚደረስበት ድረስ ብቻ እንጅ ሀቅና እውነት ከአንተ ጋር ስላልሆኑ መጨረሻህ የአብይ አህመድ ተቀጣሪ መሆንህን ህዝቡ ሲረዳ ….(ምን) የነካው እንጨት እንደሚባለው ሆነህ ትቀራለህ፡፡ አብይን የማዳን ከንቱና አስመሳይ ጥረቶችህ በሂደት ፉርሽ ሲሆኑ የሚቀሩህ በትርፍራፊ ሳንቲም ስካር የሚንቀዠቀዠው ማንነትህና ጫትህ ብቻ ናቸው፡፡

አንተ አላማ የሌለው ሰው የሚያደርገው መገለባበጥ አይነተኛ ማሳያ ነህ፡፤ በአጭሩ ለአንተ የዛሬው መልእክቴ የሚከተለው ነው፡፤ ኤርምያስ ለገሰ ዋቅጅራ ወይንም አንተ እንደምትጠራው “የዋቅጅራ የልጅ ልጅ ኤርሚያስ” በፈለግህ መንገድ ጥላሸት ልትቀባው ብትሻና የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ልታቆራኘው ብትሞክር አቋሙን አታስቀይረውም፡፤ በእርግጥ እንደ አብይ ሁሉ ኤርምያስም ኢህአደግ ውስጥ ነበረ፡፡ይህንኑም በይፋ አሳውቆ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ አቋሙ ጸረ ወያኔና ጸረ ኦነግ ነው፡፤ በአቋሙ በዘር ላይ የተመሰረተ ፌደራሊዝምን ይቃወማል፡፡ በአቋሙ ኢትዮጵያዊነትን ለጥቅምም ሆነ ለዝና የሚያቀርብ ሰው አይደለም፡፡ የኦሮሙማው ቀንደኛ መሪ የሆነውን የአብይ አህመድን ዘረኝነቱንና አማራን የማጥፋት ስውር ዘመቻውን በገሀድ ይቃወማል፡፡አብይ በአዲስ አበባ ፖለቲካ ላይ የሚያደራውን የኦሮሞነት ድር በሚገባ ያወግዛል፡፡ ወያኔ በራያና ወልቃይት የአማራ እርስትና ጉልት ላይ ዘርግቶት የነበረውን በትግራይ ክልል ስር የማቆየት የፖለቲካ ድሪቶ በጽኑ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ አሁን ላይም አብይ አህመድና ኩባንያው (ብልጽግና ፓርቲ) በመሬት ላይ ያለውን እውነታ በመካድ (በአማራ ብልጽግና ውስጥ ያሉትን “የአማራ የእንግደ ልጅ ቡድን” በሴራ በመከፋፈል) የወልቃይትና የራያን ጉዳይ ሊፈቱበት ያቀዱትን የተንሸዋረረ ወራዳ የፖለቲካ ቁማር ይቃወማል፡፡በታሪክ ትግራይ በጎንደር በኩል ከተከዜ ወንዝ ተሻግሮ አያውቅም፡፤ስለዚህ ወያኔ በጉልበት ይዟቸው የነበሩት የወልቃይት፡ ጠገዴ፡ ጠለምትና ከፍታ ሁመራ መሬቶች አሁን በጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ስር እንዳሉ ሆነው በአማራው ክልል ስር መተዳደር አለባቸው፡፡ በወሎ በኩልም ወያኔ በጉልበት ይዟቸው የነበሩት የራያና አካባቢው ታሪካዊ የአማራ መሬቶች አሁን በጀግናው የአማራ ልዩ ሀይል ስር እንዳሉ በአማራ መስተዳድር ስር መሆን አለባቸው፡፡

ስዩሜ ሆይ:- እንደ ኤርምያስ ሁሉ አብይን በድፍረት የሚተቹ ሌሎች ሰወችንም ለማሸማቀቅ የምታደርገውን ከንቱ ድካም አብይን አይጠቅመውም አንተንም ያዋርደሀልና ተወው፡፤ ከሰሞኑም ወ/ሮ ሙፈርያትንም ጀምረሀታል፡፡ እንምከርህ፡፡ ሽራፊ የአብይ ሳንቲም ይቅርብህ፡፡ሰርተህ ብላ፡፡ በከንቱ የምትዋደቅለት አብይ የኢትዮጵያ ትክክለኛ መሪ ሳይሆን የቀረው በዘሩ ሳይሆን በራሱ ስብእና መሆን ስላልቻለ ብቻ ነው፡፤ ማንነቱም በተግባር ተፈትኖ ታይቷል፡፡ከቻልክ አንተም ይህንኑ ተረዳ፡፤ ካልቻልክም በውርደትህ ቀጥልበት፡፤ በእውነታው ላይ ግን የምታመጣው ምንም ለውጥ የለም፡፤ ከእውነት ርቀሀልና፡፡ እዚህ ላይ ስለጠ/ሚ/ሩ ችሎታ ማነስ ዘረኝነትና ብቁ የአገር መሪ መሆን አለመቻልን የሚያስገነዝቡ ሶስት ትንንሽ ማሳያዎችን ብቻ ላንሳ፡፡ ጠ/ሚ/ሩ አያሌ የዘር ማጥፋቶች በቀን በጸሀይ በስፋት ሲካሄዱ፡ ብዙ ባንኮች በቀን በጸሀይ በኦሮሙማዎች ሲዘረፉ፡ ከሰሜኑ ጦር የተወሰነው ክፍል ከትግራይ ክልል እንድንቀሳቀስ ጠ/ሚ/ሩ ራሳቸው የሰጡት ትእዛዝ በወያኔ እንዳይፈጸም ሲደረግ ጠ/ሚ/ሩ ያሉትም ነገር የወሰዱትም እርምጃ የለም፡፡ወያኔ መንገድ ዘጋ ጦሩም ተመልሶ ካምፕ እንዲገባ ታዘዘ፡፤ አለቀ፡፡ በቃ፡፡ ለዛሬዎቹ የአገሪቱ ሁሉ አቀፍ መመሳቀሎችና ውድቀቶች ሁሉ መነሻው ያ ውርደት ነው፡፡ ያ ክስተት የጠ/ሚ/ሩ ውድቀትን፡ ችሎታ ማነስንና መሪ መሆን አለመቻልን በገሀድ ያረጋገጠ ጉዳይ ሆኖ በታሪካችን ውስጥ በአስነዋሪነት ተመዝግቦ ይኖራል፡፡ ለአሁኑ የሰሜኑ ጦር በወያኔ መታረድና ጭፍጨፋ ዋናና በቂ ምክንያትም ሊሆን በቅቷል፡፡ይህም በጠ/ሚ/ሩ በአገር ላይ የተሰራ ወንጀል ነው፡፤ ህዝብን በኦሮሙማ ማደናበርና ስለእውነታው ዝም ማለት ወንጀልን ማዘግየት እንጅ ከወንጀሉ ነጻ መሆንን አያረጋግጥም፡፡ ስዩሜ ስለዚህስ የተቀበረ ሀቅ ምን ትል ይሆን??

በነገራችን ላይ ሀብታሙ አያሌውም ሆነ ዘመድኩን ብሩኬም ሆነ ሌሎች በዝነኛው ኢትዮ 360 ውስጥ የሚሰሩ አንተ በስም ያልጠቀስካቸው ባለሙያዎች ለእኛ ጀግኖቻችን ናቸው፡፡ አንተና መሰሎችህ ከኦሮሙማው መሪ ከአብይ አህመድ ተልእኮ ተቀብላችሁ ልታጠፉት የምትረባረቡበት ኢትዮ 360ም ሆነ ሌሎችም እንደ ዘሀበሻና እንደ አባይ ሜዲያ የመሳሰሉ ተቋማት አጀንዳቸውን ኢትዮጵያዊነት መርሀቸውን ሀቅ አድርገው የሚሰሩ ስለሆነ ለእኛ ለሚሊዮኖች ኢትዮጵያዊያን አለኝታወቻችን ናቸው፡፡ እንደ አንተ ወይንም እንደ ሲሳይ አጌና እና ሌሎች መሰሎቻችሁ ለአብይ አህመድ ፍርፋሪ የተሸጡ አይደሉም፡፡ ይህንኑም እውነታ የኦሮሙማው ቀንደኛ መሪ አብይ አህመድ ጭምር ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡

ከሰልምታ ጋር፡
ዘመድ ባይረሳው

3 Comments

  1. ጥሩ ትዝብት ነው። እኔም ልጽፍ ብዬ በይደር ያቆየሁት ጉዳይ ነበር። ልጁ ዘመድ አጥቶ እንጂ የአእምሮ ህክምና ዕርዳታ የሚያሥፈልገው ነው። እያበደ ነው። ምን ያህል እንደሚከፈለው መገመት ይቸግራል እንጂ በአቢይ የገንዘብና የሞራል ጉርሻ ሁለመናው ዞሯል። ብሎ ብሎ እነዘመዴን “የግብጽ ተላላኪዎች ናቸው” ሲለን ነው ዕብደቱን ያላንዳች መጠራጠር ያመንኩት። በል ካለኝ መጻፌ አይቀርም። ለዚህ ጸሐፊ ያለኝ አድናቆት ግን ከፍተኛ ነው።

    • አምባቸዉ ወገንህ እኮ ነዉ እንዴት ዝም ብለህ ታየዋለህ? ትኩስ የፈለቀ ጠበል ወስደህ 7 ጊዜ አስጠምቀዉ አብሮት የሚሰራዉንም ልጅ አሳቀቀዉ እኮ።

  2. ግሩም ድንቅ ምልከታ ነው ። ሰውየው እንዳበደ ውሻ መክለፍለፍ አብዝቷል ኤርሚያስ ለገሰ ለእንደሱ አይነቱ አድር ባይ የሚበገርና አንገት የሚደፋ አይደለምና ባይለፋ መልካም ነው ።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.